Sunday, July 16, 2023

የትግራይ ካህናት፤መለስ ዜናዊና እየሱስ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/16/23

 

የትግራይ ካህናት፤መለስ ዜናዊና እየሱስ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 7/16/23


የትግሬ ካህናት ስለ ሰብአዊነትና ስለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሕግጋት ስለማክበርና ስለ ይቅርታ ዝበዝንኬ ጥያቄ ውስጥ ገብተው ለመመጻደቅ እያደረጉት ያለው አስገራሚ ጎጠኛ ባሕርያቸው ከዲያብሎሳዊ ማርክሳዊ የጀርባ ታሪካቸው ስንፈትሽ ከናዚ ቀሳወስቶች ባሕርይ አይለዩም።

ጀርመን በናዚ ዘመን ስድስት ሚሊዮን አይሁዶች... ሞተዋል። በትግራይም እንዲሁ ቀሳውስቶቹ እራሳቸው ብረት ታጥቀው እየተኮሱ የተካፈሉበት የትግራይ እና የደርግ ዘመን (ኢትዮጵያ) ጦርነት ከአንድ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ሞቶ ተፈናቅሎ ስቃዩን ያየ ኢትዮጵያዊ በጥናት ቢደረግ ከምንገምተው በላይ ግፍ ተፈጽሞበታል፡ ይህ “የትግሬ ሥርወ መንግሥት”  መንግሥትነትን ከተቆጣጠረ በላ እነሱ ባመኑት ጥናት ብቻ እንኳ ቢሰላ 2.5 ሚሊዮን   አማራ ጠፍቷል)።

የትግራይ ቀሳውስት በዚህ ጦርነትም ሆነ በበ17 አመቱ የትግል ዘመናቸው የአዶልፍ ሂትለር 'ሦስተኛ ራይክ' ጭራቅነት በመቅዳት በአማራው ላይ ግፍ የፈጸመው የወያኔ “ፋሺሰት ፓርቲ” በመከተልና በማምለክ እንዲሁም ጥብቅና በመቆም ያንጸባረቁት ከሃይማኖት መርሆ ያፈነገጠ ጥላቻ በኢትዮጵያ የታሪክ ገጾች ውስጥ አስከፊ ምዕራፍ አስመዝግቧል።

“አይደንቲቲ ጂልትድ” የሚለው መጽሐፍ የጻፈው አክሱማዊው “የበርክሊ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ዶ/ር ዓለምሰገድ ዓበይ” የነገረን ማየት ጠቃሚ ነው።

የክርስትና ማእከል ነች የተባለላት የአክሱም ቀሳውስትና ባላባቶች መካካል ጥቂቶቹ ለናሙና ከመረጣቸው የታወቁት አክሱማዊው ሃለቃ ሶቛር ስለ አማራ ተጠይቀው የሰጡት መልስ “አማራ ሰው አይደለም፤አማራ ሓኪም ከሚያክመኝ ነጭ ወይንም ዓረብ ወይንም ሌላ ዘር እንዲያክመኝ እመርጣለሁ፡ አማራን አላምነውም ፤አክማሃለሁ ብሎ ሊገለኝ ይችላል።” ያሉትን ስትመለከቱ የትግራይ ካሕናት የፋሺሰቶች ፖለቲካ መሳሪያ እንደሆኑ ከመጽሐፉ ያሳየናል። የወያኔ ቄሱ ሰረቀብርሃን የተባለው ስለ አማራ ምን እንዳለ በሰፊው ስትመረምሩት፡የሚከተለው ጥያቄ ያስጭራል።

የትግራይ ካሕናት፤ በትግራይ ውስጥም ሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያመልኩት የፖለቲካ ድርጅታቸው ሲያደርሰው የነበረው አንድን ዘር ያነጣጠረና በርካታ ብሔራዊ ወንጀሎችና ሲፈጸም የትግራይ ካሕናትን ይህንን በሚመለከት አንድ ጥያቄ ጠይቁዋቸው ብትባሉ የትግራይ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ የት ነበረች? የሚል ትጠይቁ ነበር የ እገምታለሁ።

በወያኔው ፉህረር ሰይጣናዊ ስብከት ተታለው በመላው ትግራይ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች የወያኔ መለያ የሆነው ስዋስቲካዊው “ቀይና ቢጫ ባንዴራ” በመቅደስ ውስጥ ካለው የክርስቲያን መስቀል ጎን ለጎን ትልቅ ቦታ እንዲሰጠው አድርገዋል። የስዋስቲካው መሪም በክርስቶስ ምትክ መስቀሉ መሃል ላይ እንዲተካ አድርገዋል።

የእግዚአብሔርን የንጽህና ጥሪ ያስረሳቸው የትግራይ ትምክሕታዊ ብሔረተኝነት የትግራይ ቀሳወስቶች በሕዝብ ላይ ግፍ ሲፈጸም ካለ የራሳቸው ወገን ለማንም አልጮሁም ነበር። ይህ ታሪካቸው የቆየ ነው። በጥዋቱ ሲጀመር ወያኔ የገደላቸውና የሰወራቸው (መጽሐፌ ላይ የዘገብኩትን የትግራይ ቀሳወስተና ድያቆናት የሰቆቃ ማሕደር አንብቡ) ከጥቂቶች ድያቆናትና ቀሳውስት በስተቀር፣ የትግራይ ቤተ ክርስቲያን ካሕናት ልክ አዶልፍ ሂትለር ለአይሁድ የመወገጃ  “የመጨረሻውን መፍትሔ The Final Solution የተባለው ዘግናኝ ዘመቻ ሲተገብር ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ብለው የጠየቁ ጀርመን ቀሳውስት እንዳልነበሩ ሁሉ የትግራይ ካሕናትና ምእመናን በአማራና ኦርቶዶክስ ላይ የተወሰደው “አከርካሪያቸውን የመስበር”  የመጨረሻው መፍትሔ (The Final Solution”) ተባባሪዎች ወይንም ዝምታን የመረጡ ነበሩ።

በትግራይ ካሕናት ዛሬ ደርሰው ሃይማኖት አክባሪ ሆነው የመመጻደቃቸው ባሕሪ ሳደምጣቸው በአርምሞ ከመደመምየ በላይ የድፍረታቸው መጠን ለመግለጽ ቃል ስፈልግ እኳትታለሁ። በክርስቶስ መስቀል ላይ የክርስቶስን ሥልጣንና አምልኮት የተሰጠው “ሉሲፈሩ መለስ ዜናዊ” ምስሉን ለጥፈው ስንመለከት የቤተ ክርስቲያንን ፈጠሪነትና አምላከዊነትን ያጎናጸፉት የትግራይ ካሕናት ስለ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሕግ መጣስና ስለ ሌሎች ካሕናት ስነምገባር ለመናገር የሞራል በቃት የላቸውም (አብሮ ግን የማልመረው ዋናው ሲኖዶስም ጭምር ማለት ነው። ሁለቱ ሟቹ አባ ጳውሎስም ሆኑ የንግሥና እና የክሕነት ዘውድ ከጫነው ከነብሰ ገዳዩ ከወያኔ መሪው ከደብረጽዮን ጋር መተሻሸት ሲያበዙ የነበሩት አሁን ያሉት አባ ማትያስም ጭምር ከሓላፊነት ወቀሳ አያመልጡም)።

ትግራይ ውስጥ የምናየው ሃይማኖት እና ምህላ ወያኔዊ (ሪቮሊሺናሪ) ሕሊና ተሸክሞ ነጠላ ደርቦ ቤተክርስትያን መሳለምና ምህላ መማለድ የበቃ ምእመን አያደርግም። የምእመኑ የሃይማኖት ግራ መጋባትና የወኔ መሪዎችን በክርስቶስ መስቀል ላይ መለጠፍ የሚያሳየን ምልክት ቤተክርስትያንዋ በፖለቲካ ተጠምቃ በባዕድ አምልኮ በመውደቅ አደጋ ላይ መሆንዋን ማሳያ ነው። ለዚህ ውድቀት የትግራይ ካሕናት ተጠያቂዎች ናቸው።

በትግራይ የተዋህዶ እምነት ቤተ ክርስቲያን ትኩረቷን በፖለቲካ ድርጅት እየተመራች መስቀሎችዋንና ጽላቱን የፖለቲካ ባንዴራ አልብሰው የመቀጠሉ ሁኔታ ሳስበው ለተመራማሪዎች አስቸጋሪ ክልል እንደሆነ እገምታለሁ። የትግራይ ካሕናት እንዲህ ያለ የሃይማኖት መጣረስ ሲገቡ በሰው ሰቆቃ ውስጥ-የእግዚአብሔር ሚና (ቁጣ ያስከተለው ብል ይሻላል) ምን ያህል እንደሆነ አልተረዱትም።  

ትግራይ “ክልል” ውስጥ በክርስቶስ ምስል “የሰይጣን መለኪያ” የሆነውን “መለስ ዜናዊን” መተካት ሕዝቡ ለነዚህ ካሕናት መገዛቱ እስከመቸ እንደሚቀጥል ለመገመት አዳጋች ሆኖ አይቼዋለሁ። እዚህ ላይ ከባድ ሚና የሚጫወቱት የትግራይ ካሕናትና የትግራይ ምሁራን በጋራ የፈጠሩት “ክልላዊ ሃይማኖት” ክልሉን (ሕዝቡን) ወደ ባሰ ማጥ እንደሚገፈትሩት አርግጣኛ ሆኖ መናገር ይቻላል።  

ኢትዮጵያን ለማዳከም እስከ አጽናፍ የተጓዘው መለስ ዜናዊ የትግራይ ሕዝብና ካሕናት በዚህ “ሉሲፈር” ላይ ያላቸው አምልኮአዊ ታማኝነት፣ በናዚያዊው ሂትለር መነሳት እና መምጣት መካከል ያለው ንፅፅር ስንመለከ <<የክርስቶስ ተቃዋሚ አገዛዝ>> በትግራይ መነሳትና አሁንም የመቀጠሉ ርዝማኔ ስናነጻጽረው የጀርመኖቹ አጭር ዘመን ነው።

የትግራይ ካሕናት መለስ ዜናዊን ብክርስቶስ መስቀል ሰቅለው ወጣት ትግሬዎች እንዲሳለሙትና በሕሊናቸው ተቀርጾ አዲሱን ክርስቶስ እንዲያመልኩ በማድረጋቸው ቤተክርስቲያኒቱ ሂትለርን ወደ ክርስቶስነት ከለወጡት ከጀርመን ካሕናት ቀጥለው በታሪካችን የመጀመሪያ የክርስቶስ ጥሪና ሕግጋትን <<ካለ እኔ ሌላ አምላክ አታምልከ>> የሚለውን ወፍራም ደወል የረሱ በታሪክ የትግራይ ካሕናት ናቸው።

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)