Saturday, October 16, 2010

ሠላማዊ ትግል ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲ መፍትሔ ይሆናልን ?

ይድረስ ለጎጠኛው መምህር(አማርኛ) $25.00 እና ሓይካማ (ትግርኛ) $15.00 መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛችሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836 (Getachew Reda P.O.Box 2219 San Jose, CA 95109) getachre@aol.com http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/ ሠላማዊ ትግል ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲ መፍትሔ ይሆናልን ? ከጀሚላ አብዱልቃድር (By Jemila AbdelKader) አህጉራችን አፍሪካ ህዝቦቿ በወታደራዊና በአምባገነንነት ራስ ወዳድድነት በተጠናወታቸው ለዜጎቻቸው ግድ በሌላቸው መሪዎቿ የፍጥኝ ታስራ የዜጎች ነፃነትና የፍትህ ያለህ እሮሮ ታፍኖ ሠሚ ያጣች አህጉር መሆኗ ከአለም ህይታ ያልራቀ እውነታ ነው ፡፡ በአምባገነንነት፤በወታደራዊ የአገዛዝ ስርአት ተንተርሰው የህዝባቸውን የዲሞክራሲ የመምረጥ ፤በነፃነት የመናገር መብትን በእስራትና፤ በግድያ ገድበው ለአመታትና ለአስርተ አመታት የስልጣን ጥማቸውን በማርካት በህዝብ ሀብትና ንብረት የግል ፍላጎታቸውን የሚያራምዱ ፤ የህዝባቸውን ርሀብ ፤ ሰቃይ ፤ መከራ ለማየት ፍጹም አይና ቸው የታወሩ መሪዎች የሚሳለቁባት አህጉራችን ዛሬም ሁነኛና ለህዝቦች ተቆርቋሪ እና አሳቢና ሰብአዊነት የተሞላበትን አስተዳደራዊ ስርዓት ታልማለች፡፡ግን ችግሮቿ ተፈተው ዜጎቿ ንፁህ የዲሞክራሲ ጭላንጭል እርከን ላይ ለመድረስ ገና ብዙ ዓመታት ያስፈልጋታል፡፡ እንዲያው ለመንደርደርያ ያህል ሃሳቤን አህጉራዊ አደረግኩት እንጂ ዋናው የነጥቤ መነሻ ሀገራዊነትን የተላባሰ ነው ፡፡ ህዝቦች አፈና፤ኢሰብሃዊነት፤አምባገነናዊ ስርዓት የተላበሰን አስተዳደር በመቃወምና ለነፃነታቸው ትግልን እንደ አማራጭነት ይወስዱታል፡፡ በዚህ ትግልም ሀብት፤ንብረታቸውን፤ቤተሰቦቻቸውን ጥለው ይሰደዳሉ ፡፡ ከፊሉም ለነፃነቱ ይታሰራል ፤ ይገረፋል ፤ ከዚያም አልፎ ህይወትን አሳልፎ እስከሚሰጥ ትግል ይዋደቃል፡፡ ትግልን ሠዎች በተለያየ አገላለጽ ቢገልጹትም እንኳን ከነዚህ ውስጥ በዋነኛነት የሚጠቀሱት የሠላማዊ ትግል እና የትጥቅ ትግል ለፅሑፌ እንደ ሃሳባዊ ትንታኔ ለመግለፅ እወዳለው፡፡ ባገራችን ኢትዩጵያ አገሪቱን አስተዳድራለው የሚለው የኢህአዴግና የህወሐት ጥምራዊ አስተዳደር በህዝብ ላይ የሚያደርሱት እስራት፤ግድያና፤አፈናና ኢሰብሃዊነትን አስተዳደር በመቃወም በአገር ውስጥ በተለያየ ስምና በተለያየ ጊዜ በተቃዋሚነት ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱና የሠላማዊ ትግልን እንደ መፈክር ያነገቡ የፖለቲካ ድርጅቶች ላገራቸውና ለህዝባቸው ከቃላት ግርግር ያለፈ የተሳከለት ዓላማ ላይ ሳይደርሱ የኢህአዴግና የህወሐት ካድሬዎች በሸረቡላቸው የጥቅም አሊያም የውድቀት መረብ ተጠልፈው የቆሙለትን ዓላማ ዘንግተው ሲፍረከረኩ ማየት ለህዝባችን የተለመደ ትዕይንት ነው፡፡ አንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች ደግሞ ግራ ገብቶአቸው ጭቁኑን ህዝብ ግራ የሚያጋቡ ናቸው፡፡ዓላማቸውንና አካሄዳቸውን በግልፅ የተገነዘቡትም አይመስሉም፡፡ ሀገራዊነት ከመሆን ይልቅ በሔርተኝነትን ተነተርሶ በባህል፤ በሃይማኖት፤ በጋብቻ ለረጅም አመታት የተሳሰረውን አገራዊ የአንድነትና አብሮ የመኖር እሴታችንን በብሔርተኝነት ለመበታተን የሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያዊነት ስሜት የማይሠማቸው እጅግ አሳፋሪ መርህን ነድፈው የሚንቀሳቀሱ በህዝብ ደም የሚሳለቁና የፖለቲካ ድርጅቶች እንዳሉ ማንኛውም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የሚጋራው ሃሳብ ነው፡፡ ሠላማዊ ትግል ለኢህአዴግና ለህወሐት አምባነናዊ መሪዎች ከቃላት የዘለለ ትርጉም አይኖረውም ፡፡ ምክንያቱም ኢህአዴግ ራሱ መቼ በሠላማዊ ትግል ስልጣን ላይ ወጣና፡፡ያልተራመደበትን መንገድ መቀበልም ግራ ይገባዋል፡፡ሠላማዊን ትግል ባደጉ በአውሮፓ እና እንደ አሜሪካ ባሉ አገሮች የተለመደ ቢሆንም ወደ አገራችን ስንመጣ ከስክሪን ያላለፈ የፊልም ትዕይንት አድርገን ልንረዳ ይገባናል፡፡ዲሞክራሲ በገሃድ የሚለፈፍበትና በስውር የዜጐች አፈና፤እስራት፤ግድያ በሠፈነባት አገራችን ህገ-መንግስታዊ ህጐች ከወረቀት የዘለሉ ያልሆኑባት ፤ ከህግ ይልቅ የስልጣን የበላይነት ገዝፎ በሚታይባት አገራችን ሠላማዊ ትግል መፍትሔና ውጤት ያመጣል የሚለውን አስተሳሰባችንን ለነፃነት ለዲሞክራሲ የሚደረገውን ትግል ወደ የሚያዘናጋ እንጂ ወደ ፊት እንደማያራምደን ልንገነዘበው ይገባል፡፡