Monday, August 9, 2010

“እሰከ መገንጠል” ሞግዚት ላጣች አገር የተመረጠ የመግደያ መርዝ!”

“እሰከ መገንጠል” ሞግዚት ላጣች አገር የተመረጠ የመግደያ መርዝ!” ጌታቸው ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com getachre@aol.com “ይድረስ ለጎጠኛው መምህር” እና ሓይካማ (ትግርኛ) መጽሐፍቶቼን ለመግዛት እስካሁን ድረስ ዕድል ያላገኛችሁ ካላችሁ በሚከተለው ስልክ ቁጥር ብትደውሉ ማግኘት ትችላላችሁ። (408) 561 4836

ይህ ጽሑፍ ከ 1አመት በፊት ጽፌው የነበረ ሲሆን፤ ዛሬ በድጋሚ እንድለጥፍ ያስገደደኝ ሁኔታ “ተስፋየ ሃቢሶ”-የተባለ የወያኔ ባለሥልጣን የነበረ ዛሬ በጥሮታ የተገለለ፤ ግን አገልግሎቱ ዛሬም ለቀጣሪዎቹ ለወያኔዎች በማገልገል The Significance of Ethnic Identification: Clarifying the Essentials and Dispelling the Illusions (By Tesfaye Habisso) በሚል ርዕስ ጽፎ www.Ethioforum.orgwww.Aigaforum.comበተባሉ ድረገጾች በመለጠፍ ቀጣሪዎቹ “ብሔር/ብሔረሰብ/ሕዝቦች” እስከመገንጠል የሚለው የፋሽስቶች መርዘኛ ፖለቲካዊ ተልዕኮ መመከቱ አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘሁት አንባቢዎች በኛ በኢትኦጵያዊነት ሃይሎች ላይ የሚቀርብ ንባብ/ምጉት ቀርቦ እንድታነቡት ይኼዉ አንዳንድ ነጥቦች ተጨምረውበት በድጋሚ ለጥፌዋለሁ። ኢትዮጵያዊነትን እናጎለምሳለን የምትሉ ድረገጽ ባለቤቶች ሁሉ ልኬላችሗለሁ ለጥፉት። የድርጅት መሪዎቻችን ተወቅሰዋልና ሕዝቡ ከመማንበብ እናግደዋለን የምትሉ ከሆነም ጌታቸው ረዳ ሳይሆን የሚጎዳው ያገራችሁ ታሪክ እና ህልውናዋ ነው። ክፍል 1 ትንታኔየ በአንድ ድረ-ገጽ “በማሕደር.ዳት ካም” ብቻ ሲለጠፍ “በአሲምባ እና በደብተራዉ” ድረ-ገጽ ግን የላኩሁላቸዉ መሆነኔን ቢታወቅም “አልወደዱትምና” አንባቢ “ግንዛቤዉ” እንዲያሳርፍበት “አገዱት”። ለምን ለሕዝብ እናዳለቀረቡት ደፍሬ ባልጠይቃቸውም፤የቁርጥ ቀን ወንድሞቼ ናቸውና ቅር አላለኝም። ደግነቱ የራሴው የኢንተርኔት ሰሌዳ መኖሬን በበቂ አንባቢ መነበቡ ከተዘገቡት የእንግዶች ቁጥር ማወቅ ችያለሁና ክፍል ሁለት የመጨረሻው ትንታኔየ ዛሬ ይቀርብና ወደ ሌላ ርዕስ እንሸጋገራለን። ፋሺስቶች እና ስታሊኒሰቶች አስካሉ ድረስ ዛሬም ኢትዮጵያን በጣረሞት አፋፍ ላይ ሰቅዞ የያዛት ብሔር/ብሐረስብ እስከመገንጠል የሚባለው መርዛቸው ዛሬም በምዕራባዊያን ተደግፎ (ራሳቸዉ ሊያውሉት የማይፈቅዱትን) በሲ.አይ.ኤ እና በአረብ አሸከሮች የሚወዛወዙ እነ “እንቶኔ” እስካሉ ድረስ ወያኔ ሥልጣን ከሰረቀበት ከ18 ዓመት ጀምሮ የኢትዮጵያን ገበሬ ያገዳደለ ይኼው የጎሳ/ብሔር አቀንቃኝ ኤሊቶችና የ “ሲ አይ ኤ” (የነ ኸርመን ኮሆን) የተቀመመ መርዝ ለወደፊቱም የዋሁን ተጠቂው ገበሬውን ከመፈታተን ስለማይቦዝን ከሁሉም በፊት በቅድሚያ የሚቀርብ የፖለቲካ አጀንዳ ነውና ይህንኑ አስመልከቶ እንወያያለን። በዚህ ክርክር ሁሌም እያንዳንዳችን ራሳችንን ማዘጋጀት ይጠበቅብናል። በኢትዮጵያ ታሪክም ሆነ በአፍሪቃ የማይታወቀው እንግዳ የማርክሲሲቶች የብሔሮች፤ብሔረሰቦች፤ሕዘቦች… መብት “አስከ መገንጠል” ፍልስፍና በኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ እና ግስጋሴ ማርክሲስቶቹ ቀዳሚ መመሪያ አድርገዉ ተግባራዊ ለማድረግ ብዙ ትግል እና ትምርት ሰጥተዋል። በዚህ በኩል በግምባር የሚጠቀሱ በለስ ቀንቷቸዉ ወደ ስልጣን የመጡት እነ ወያኔ እና ለአንድ ዓመት ከምናምን ወራትም ቢሆን አብሮት ስልጣን ላይ ወጥቶ ከፍተኛ ብሔራዊ ጉዳት ያደረሰዉ የሌንጮ ለታ “ሃይማኖት” የነበረዉ “ኦነግ” የተባለው ወንጀለኛ የፓለቲካ ድርጅት አማርኛን በላቲንና በዓረብኛ ቋንቋ ተክተው የብሔሮች መብት አስከ መገንጠል በሕገመንግሥት አጽድቀዉ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ከህዝቡ መንፈስ እንዲገፈፍ ከፈተኛ ጉዳትና ሚና ተጫዉተዋል። (በነገራችን ላይ ሌንጮ የኮሎኒው ጥያቄ ያፍላ ወጣትነት የማርክሲስቶች ንቃተ ሕሊና ቅስቀሳ ስለነበር ዛሬ አርጅቼ ልብ ገዝቻለሁና የኮሎኒው ጥያቄ ጥየዋለሁ በማለት በወዳጆቹ በእነ ብርሃኑ ነጋ እና በአንዳርጋቸዉ ራዲዮን (የግንቦት 7 ራዲዮን) በሰጠው ቃለ መጠይቅ ማረጋገጡ አንድ በጎ እርምጃ ነው። አዘጋጁ አፍላ የራዲዮን አዘጋጅ (ቃለ መጠይቁን ያዘጋጀው ወጣት ይመስለኛል(?)) በመሆኑ የሌንጮንና የኦነግ ታሪክ ካለማወቅ ይመስለኛል “እንደ እርስዎ ያሉት የፖለቲካ ስብዕና የተላበሱ…” የማለቱን ሞኝነቱን መዝግቡልኝና…

ብሔር/ብሔረስብ አስከ-መገንጠል የሚለዉ የስታሊኒስቶች መመሪያ “ኦሪት” ለሆነችዉ አገር የውጭ ጠላቶች -እና የቆየ የሙሶሊኒ ከፋፋይ መምሪያ ተግባራዊ ለማድረግ የተወሰነው ካሁን በፊት በጦር ሞክረዋት አልሳካ ያላቸውን መርዛማው የመገነጣጠል ሴራቸው ዛሬ ያላንዳች የውጭ አስፈራሪነት በልጆቿ እጅ መርዙን ተግታ/ጠጥታ እንድትሞት ተደርጎ፤ ሞቷ ጊዜ ፈጅቶ ቀስ በቀስ እየኮሰመነች ብሔራዊ ሃይሏ እየተዳከመ ሕዝቦቿ እርስ በርስ በስድብ እየተቦጫጨቁ ጥላቻዉ ተስፋፍቶ መጨረሻ ግብአተ መሬቷ ከጊዜዉ እና ከመንፈስ መዳከም ጋር እንደሚከናወን እየተፈጸሙ ያሉ ሂደቶች እና ሁኔታዎች እያመላከቱን ነው።

ኤሊቶች/ምሁራን ነን የሚሉ ድርጅት ፈጥረው ይኼነን መርዝ በማቃመም ወደ ሕዝቡ በማጋባት በሴራው ምክንያት እርስ በርስ ከመጠላላት አልፎ ያንድ ሀገር ልጆች በሕዝብ ስም በፓለቲካ እና በሃይሞኖት ስም እየተነሱ ሽበር እና ግድያ በመፈጸም ሰውን ከነ ሕይወቱ ወደ ገደል ገፍትሮ መግደል እና ህጻናት በትምርት ገበታ ላይ እንዳሉ እሳት ለኩሶ መፍጀት፤ ዕዉራን አረጋዊያን ብልታቸው በሰላ ተቆርጦ በሙት/ሬሳ አፍ ላይ ማጉረስ፤ እናቶች በቢላዋ ጡታቸውን መቁረጥ፤እመጫት ህጻንዋን ታቅፋ ከሞት ለማምለጥ ስትሸሽ በጥይት እንደ ዥግራ እያባረሩ መግደል፤ወዘተ፡ በኢትዮጵያ ምድር የታየበት ዋናው የጭካኔው መነሾው ከሰው ልጆች ጭካኔ ጋር የተያያዘ ባሕሪያዊ ምንጭ ቢሆንም አንዳንድ ጭካኔዎች ካለመማር ተጨምሮበት ለጭካኔው ተጨማሪ ነዳጅ የሚሰጡ አፍራሽ የሆኑ ቅስቀሳዎች ያላስፈላጊ መተላለቅ ሊያስከትል እንደቻለ ከላይ የጠቀስኩዋቸው በምደሪቷ የተፈጸሙ ክስተቶች የተጠቀሰው የግራኛው ፍልስፍና ምንጮች ሰበብ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ለተከሰቱት በጥላቻ የመተላለቅ እና የመጠላላት ምንጮች ሁሌም ገዢ መደቦች እና የሥልጣን ጥመኞች በሚከተሏቸዉ መርሆዎች የሚከሰቱ ናቸው።

በሙሶሎኒያውያን ወያኔዎች እና “በግራ አወንዛፊዎቹ”/ክንፎች የፍልስፍና መመሪያ ተመርተው የአገሪቱን ሕዝቦች በጎሳ/ብሔር ካፋፍለዉ የአንድነት አርማ የሆነውን የኢትዮጵያ ገበሬ ለማናቆር ወያኔዎች ወደ ሥልጣን እንደመጡ ተግባራዊ ለማድረግ ቅድሚያ የተጣደፉበት አጀንዳ አገሪቷን በብሔሮች (አገሮች) እና በብሔረሰቦች ቀጥሎም በነሱ (በወያኔዎቹ በነ ተስፋየ ሃቢሶ) አጠራር “ሕዝቦች” የሚሏቸውም ጎሳዎች ሁሉ ተደራጅተው አስከ መገንጠል ድረስ የሚለውን መብታቸው አንደሆነ ነበር የሰበኩት።

ለዚህ ሥራ አስፈጻሚ እንዲሆኑ ለሰበካው ከተመዘዙት የወያኔ የፍልስፍና ካድሬዎች ዉስጥ ወያኔን በአምበሳደርነት ያገለገለዉ በጸረ-አማራ ፕሮፖጋንዳዉ “እኝኝ” የሚል ግለሰብ ዛሬ በጥሮታ ተገልሎ በመደበኛ አምደኛነት በወያኔዉ ሰሌዳ በዓይጋ-ፎረም ላይ (ዛሬ ደግሞ ኢትዮ-ፎረም ዳት ኦርግ ) ዘወትር ስለ አማራው ሕብረተሰብ ጨቋኝነት በተለይም የአማራው ሕዝብ ወንድም ከሆኑት ከተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች ከደቡብ ኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ጋር የነበረዉ ግኑኝነት የሻከረ እንደነበረ አድርጎ የሕሊና ደንቆሮች የሆኑ አንዳንድ የጥላቻ ቅኔኛዎችና ገጣሚዎች የገጠሙትና ያሰላሰሉትን የመሸታ ቤት “ጸረ-አማራ” ምሳሌና ግጥም ለቃቅሞ ከገዢነቱና ከጨቋኝነቱ (ነፍጠኛነቱ/ወራሪነቱ) የተነሳ በአማራው ሕብረተሰብ ላይ ጥላቻ እንደነበረ አስመስሎ ለጠወለገው ለወያኔ ፖለቲካ ጉሮሮ ውሃ ሲያጠጣ የሚነበበው አቶ ተስፋየ ሃቢሶ፦በሽግግሩ ወቅት ወሎ ክፍለ ሃገር ድረስ ሄዶ ገበሬዎችን ለመመረዝ ቅስቀሳ ሲያደርግ፤ ገበሬዎቹ የተናገሩትን በገዛ ብዕሩ ያሰፈረው ልጥቀስ እና የወሎ ገበሬዎች በሚከተለው አንደበታቸው ምዕዳናቸውና ተቃውሟቸው (ረዚዚስታንስ) ለወያኔ ቢያሰሙም እነ ወያኔ እና እነ ኦነጎች ለሕዝብ ከበሬታ የላቸውምና ዋጋ አልሰጡትም ነበር።ታሪክ ነውና ፤ታሪክ የዘገበውን ልጥቀስ። (እኛ በሽግግሩ ወቅት የብሔር ጥያቄዎችን በተመለከተ በየክልላችን ስንዘዋወር ነበርን። የምናስተምረዉን ትምህርት የሚያዳምጠዉ ሕዝብ ትምህርታችን አልጣመዉም ነበርና አንድ አባት ገበሬ ተቃዉሞአቸዉን በሎሆሳስ ሲገልጡ "ይሄ በብሔር በጎሳ መደራጀት የምትሉት ነገር በተለይም ገበሬዉን አላስደሰተዉም። ልጆቻችን/ ይልቁንስ እኛ ታሪክ እንንገራችሁ። የምታስተምሩትን ነገር ከታሪክ ብቻ ሳይሆን ከተፈጥሮ ጋር አገናዘባችሁ ብታዩት ጥሩ ነዉ። የዱባ ተክል አንድ ቦታ ነዉ የሚበቅለዉ። የሚያብበዉ እና የሚያፈራዉ ግን ተንሰራፍቶ ሄዶ ሌላ ቦታ ለይ ነዉ። ያንን ዱባ ወደ ሗላ ወደ በቀለበት ብትመልሱት ይበሰብሳል። ይሞታል። የኢትዮጵያም ሕዝብ ታሪክ ይኸዉ ነዉ። በመቶ ዓመት ታሪክ ዉስጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ አማራዉ ፤ትግሬዉ፤ከንባታዉ ፤ጉራጌዉና፤ወላይታዉ በአሁኑ ጊዜ የሚገኘዉ በመላ ሀገሪቱ ተንሰራፍቶ ነዉ። እስቲ የኛ ሕዝብ ያለበትን ተመልከቱ። ያንን በሀገሪቱ የሞላዉን ሕዝብ በቋንቋና በጎሳ ክልል ብቻ ታጥረህ ተቀመጥ የሚል ትምህርት ብታስተምሩ ሕይወታችን (በዚሁ ጉዳይ ላይ ሲናገሩ) የጥፋት ዘመን መሆኑን ብቻ ነዉ የምታስረዱን" አሉ። ሌላዉ አባት "ብሔረተኝነትና ሐይማኖት በጥንቃቄ ካልተያዘ አደጋ አለዉ። ብሔረተኝነትና አረቄ አንድ ናቸዉ። እና ድሮ አጋሰስ ለመሸጥ ስንፈልግ አጋሰሱን አረቄ እንግተዋለን። ፈረሱ ወዲያዉኑ ጊዜያዊ ጉልበት ያገኝና ጮሌ ሰንጋ ፈረንስ መስሎ አርፍ ይላል። እናም ጥሩ የደረስ ዕቃ ጭነን ወደ ገበያ ወስደን እንሸጠዋለን፡ ፈረስ አረቄዉ ከላዩ ላይ ተንኖ ሲያልቅ ግን ወደ ጌኞነቱ ይመለሳል። ስለዚህ እናነተ አሁን የምታስተምሩን ነገር ከሕዝቡ ጥቅም አንጻር የሚያዋጣ ስላይደለ ይህን መሰሉን ትምህርት ከእኛ ብታርቁልን እንመርጣለን" ብለዋል። ሲል ሕዘቡ በቋንቋ፤በጎሳመደራጀቱ አደገኛነቱ ገና ከጥንቱ ከጥዋቱ ያስጠነቀቃቸዉ ቢሆነም አገሪቷ ሞግዚት ያጣች አገር ነበረችና እንዲገድሉዋት ከጠላቶቿ ከነ ሞሶሎኒ የተሰጣቸዉን መርዝ ያግቷት ጀመር። ሁሉ ሆኖም ወያኔ እና የጎሳ አቀንቃኞች ምኑ ያክል ቢጥሩም ዉጭ ሲጓዙ ማን ብሎ እንደሚጠራቸዉ ካደሬዎቻቸዉ ሳይቀሩ እንዲህ ሲሉ ይመሰክራሉ፦በአሁን ጊዜ ወዴትም አገር ብንሄድ "አንተ ኢትዮጵያዊ ነህ?” ይላሉ እንጂ እንተአማራ፤አሮሞ አንተ ወላይታ ወይም ትግሬ ብሎም የሚጠራን የለም።…….” (ተስፋየ ሓቢሶ) የአፍሪካ ሰላምና የግጭት ማነጅመንት ጥናት መዕከል ሰኔ 30 ቀን 1993 . በኢትዮጵያ ሕዝቦች የመወራረስ ታሪክ ላይ ዉይይት ተካሂዶ በነበረበት ወቅት ከተገኘዉ ሰነድ። ለመሆኑ ይሄ ብሔር ብሔረስብ የሚባል ቃል ማርክሲሲቶቹ እና ወያኔዎች እንደሚተረጉሙት ያገራችን የቋንቋ ጠበብት የሚተረጉሙት እንደነሱ ነዉ? አስፈላጊ ሆኖ አግንቸዋለሁና አንድ ነገር ሲተረጎም የቃሉ ትርጉም ምን ማለት እንደሆነ ከአገሬዉ ቋንቋ ጋር ካልሄደ የተሳሳተ የዉጭ ትርጉም ተይዞ ለጥፋት ስለሚዉል የቃላቱ አተረጓጎም ትከክለኛነቱ እና ስሕተቱን ለማወቅ ይረዳን ዘንዳ በአገር ወዳድ እና በአንድነት ሃይሎች የተወገዘዉ ጎሰኝነትን ከትዉልድ ትዉልድ አስተላልፎ ለማለፍ ከከጀለዉ ከእዉቁ ከጎሰኛዉ የወያኔዉ ምክትል ያዲስ አበባ ከንቲባ፤እናየወያኔዉ ያማርኛ ፕሮፖጋንዳ ክፍልየሚባለዉ የኢሕአዴን/“ብአዴንታጋይ የነበረዉየአማራዉ ሕዝብ ከየት ወዴትመጽሐፍ ደራሲእንዳርጋቸዉ ጽጌበጻፈዉ ጸረ አማራ እና ጸረ-ኢትዮጵያዊነት መጽሐፉ ለመተቸት በሞረሽ ቅጽ 2 ቁጥር 2 (1986) የቋንቋ እና የተለያዩ ዘመናዊ እና ጥንታዊ ትምርቶች ጠቢብ የሆኑት ክቡር ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሃይሌ ቋንቋ እና ብሔርን በሚመለከት አንዳረጋቸዉም ሆነ ወያኔዎች በተሳሳተ መንገድ እንዴት እንደሚተረጉሙት እና ራሳቸዉን አሳስተዉ አዲሱን ትዉልድ እንዴት እንዳሳሳቱት የአመራዉ ሕዝብ ከየት ወዴትደራሲ የለበሰዉን አደናጋሪ የዉሸት ልብስ ፕሮፌሰሩ ሲያጋልጡት እንመልከት።

(ብሔር የመታወቂያ ባንዴራ) በሚል ንኡስ ርዕስ እንዲህ ይላሉ። ደራሲዉ የተቃዋሚዉን አፍ ለማስያዝ የሞከረዉ ገጽ 7-8 ላይ ባሰፈራቸዉ ከዚህ በታች ባሉት ቃላት ነዉ፦

በኢትዮጵያ ውስጥ ከሰባ የሚበልጡ ብሄር ብሄረሰቦች መኖራቸው ተቀብለዉ ነገር ግን ብሄረተኝነት ጥያቄ ሲመልሱ በኢትዮጵያ ሚገኘው ብሄረተኝነት አንድ ኢትዮጵያዊ ብሄረተኝነት ብቻ ነው የሚሉ አልታጡም። እንዲህ የሚሉ ሃይሎች ሊመልሱት የማይችሉት ጥያቄ አለ። ብሄረተኝነቱ ኢትዮጵያዊ ከሆነ ምን ዓይነት ቋንቋ ባህል ታሪክ ወግ፤ወዘተ፡ በአጭሩ ይዘቱ ምን ይሆናል የሚለውን ነው።” ክቡር ዶክተር ጌታቸው ሃይሌ ለዚሁ ሲመልሱ ብዕራቸዉን በማንሳት እንዲህ ሲሉ የለበሰውን አደናጋሪ ካባ በመግፈፍ እርቃኑን አስቀሩተውታል።

{ በደራሲዉ አስተሳሰብ የብሔር ማወቂያ (ባንዴራው) ቋንቋዉ ነው።በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ቋንቋዎች ስላሉ ብሔረሰቦችም ቁጥራቸው በዚያው ልክ ሊሆን ነው-- ከዚያም ላይበልጥ ከዚያም ላያንስ። በኢትዮጵያ ዉስጥ አንድ ቋንቋ ብቻ ቢኖር ኖሮ ቢሔርተኝነታችን ኢትዮጵያዊ ብቻ ይሆን ነበረ ሊል ነዉ። በብሔረተኝነት የሚጫረሱ ሶማሌዎች የሚናገሩት አንድ ቋንቋ እንደሆነ ደራሲዉ ያውቅ ይመስለኛል። ሰው ጎሳቸውን (ብሔራቸዉ) አንድ ያደርግባቸዋል እንጂ እነሱ ቢጠይቋቸው ሱማሌነታቸው ቢያምኑም ጎሳችን አንድ ነው አይሉም። ተጠራቅማችሁ አንድ ብሔር፤ አንድ ሕዝብ፤አንድ አገር፤አንድ መንግሥት ሁኑ ብላ ያስቸገረቻቸው እንደ አቶ አንዳርጋቸው የምታስብ እንግሊዝ ናት። ዩጎዝላቪያ ውስጥ በብሔረተኝነት የሚተላለቁት ሰርቦች፤ክሮዋቶች ቦዝኒያዉያን በቋንቋ አንድ ናቸዉ። ግን አንድ ጎሳ (አንድ ብሔር) ነን አላሉም። የብሔረተኝነት ምንጩ ቋንቋ ብቻ ቢሆን አይሪሾች ግማሾቹ ከ እንግላንድ ጋር መሆኑንን ሲመርጡ ሌሎቹ መለይትን አይመርጡም ነበረ። አሜሪካና ካናዳ ሁለት አገር ሁለት መንግሥት ባልሆኑም ነበር።ጌርማኒያንና ነምሳ ሁለት አገር፤ሁለት መንግሥት ባለሆኑም ነበር። የአሜሪካን ዩሁዲዎች ቋንቋቸው እንደሌላው የአሜሪካ ሕዝብ እንግሊዝኛ ነው። የኦሮሞ ጎሳዎችን ጨፍልቆ አንድ ጎሳ (ወይም ብሔር) የሚያደርጋቸው ሃይል አስካልመጣ ድረስ ቋንቋቸዉ አንድ ስለሆነ ብቻ አንድ ጎሳ (ወይም ብሔር) ናቸው ማለት የሌለውን አለ ብሎ መናገር ነው። ጎንደሬውንና ጎጃሜን የሚናገረዉ ቋንቋ አንድ ስለሆነ አንድ ጎሳ (ወይም ብሔር) ማድረግ ከነሱ የተለየ ቋንቋ የሚናገረውን ትግሬውን በቋንቋዉ ከጎንደሬው ይለያል ማለትን ያስከትላል። የእንግዲሁን አናዉቅም አንጂ አስከ ዛሬ እንዲህ አልነበረም።”

አንዳረጋቸዉ ጽጌ (በመጽሓፉ በገጽ 12 ላይ) እና የዛዉ ፍልስፍና ደቀመዛሙርቱም ጭምር እንደሚሉት “በኢትዮጵያ ብሄረተኝነትም ይኖራል። የብሄረተኝነት መፈጠር የራሱ መሠረት ስላለው ብቻ እንጂ በጉትጎታና በቅስቀሳ የመጣ አይደለም።” በማለት ጭልጥ ያለ ዉሸቱን አዲሱን ትውልድ መርዙን ሊግቱት ሞክረዋል። ሃቁ ግን እሱ አይደለም:: ክቡር ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ እንዲህ ይላሉ፦

{ እውነታቸው ግን በጉትጎታና በቅስቀሳ የመጣብን እዳ ነው። የደራሲውን አስተያየት የሚቀበል በኢትዮጵያ የብሔረተኝነት ታሪክ የማያዉቅ ሰው ነው።ታሪኩን የሚያውቅ (እንዲያውም ራሷን ይቺን ቁንጽል መጽሐፍ በጥሞና የሚያነባት) በኢትዮጵያ ብሔረተኝነት የተፈጠረው በሻዕቢያ አምላክነት እንደሆነ አይሰወረውም።አፈጣጠሩም ብዙዎች ደጋግመው እንደጻፉትና እንደተናገሩት “ኤርትራን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል የሚቻለው የኢትዮጵያን ሕዝብ በብሔረተኝነት በማተራመስ ነው” በሚል ፍልስፍና ነው። ሻዕቢያ ሐሳቡን ያገኘው ከቅን ገዢዎች ነው። ቅኝ ገዢዎች ኢትዮጵያን ለመግዛት አለዚያም ለማዳከም የሚቻለው በሃገሩ ላይ ብሔረተኝነትን እሳት በማቀጣጠል ብቻ ነው። ብለው በጊዜውም ተጠቅመውበታል። ዛሬ ኤርትራ ራሷን የምትችል ሀገር ብትሆንልን በ ሃገራችን የጎሰኝነት ጉዳይ ጋብ ይልልን ነበር።ኤርትራ ረሷን አስካልቻለች (ግን የምትችል አይመስልም፡ ሐረግ ሬሳይቱ ያለዋርካው ድጋፍ ራሷን ችላ አልቆመችም፡) ወይም የኢትዮጵያ ሕዝብ በዲሞክራሲ አስካልተዳደረ ድረስ ሻዕቢያና ወያኔ ቅድሚያ ሚሰጡት ሃገሪቱን ለማዳበር ሳይሆን ጎሰኝነትን ለማፋፋም ነው። ከሁሉ አስቀድመን መገንዘብ ያለብን ብሔረተኝነት ከውጭ የመጣ ሓሳብ እንጂ እኛ ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ የምንወግነው ለሀገራችንና ለሃይማኖታችን ነው። ብሔረተኝነት አለ ቢባል ሃይማኖታዊ ግፋ ቢል ጎጣዊ ነው። ካዲሲቱ ኢትዮጵያ ይጠበቅ የነበረው ሃይማኖትን የግል ብቻ አድርገን ወገናችንን በሀገር ላይ ብቻ ነበር። ….አሁን ግን “ጎሳ የጋራ፤ሃይማኖት የሚያጣላ፤ሀገር የግል” የሚል ፈሊጥ ሊያመጡብን ነዉ።}

ከላይ እንደተመለከትነው ባጭሩ እና በማያሻማ ተብራርቷል። በመጨረሻ ምሁሩ ሲያብራሩ ለመሆኑ ይህ ዛሬ ብሔር እየተባለ የሚጠቀስ የዘመኑ ቃል ባገሪቷ ቋንቋ አጠቃቀም ብሔር ስንል ትርጉሙ ምን ማለት ነው? አሁንም ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ፦

“ብሔር/ብሔረስብ የሚባለዉ ቃል በዛሬ ትረጉሙ በቋንቋችን አልነበረም። የተፈጠረው አሁን በኛ ዘመን ነው። የፈጠሩትም የኢትዮጵያ አንድነት ጠላቶች ናቸው። እዚሁ ሀገራችን ውስጥ የበቀለ ቢሆን ኖሮ ሀገራችን ውስጥ እንደበቀለው እንደማንናቸውም ነገር ሁሉ ስም ይዞ እናገኘው ነበር፦…” ይሉ እና አስቀድሜ የጠቀስኩት “የአማራው ሕዝብ ከየት ወዴት” መጽሐፍ ደራሲ “አንዳርጋቸው ጽጌ” እና የዛሬዎቹ ፋሺስቶች ስለብሔር ያላቸዉ የተሳሳተ ትርጉም ዶክተር ጌታቸው ሃይሌ ስሕተቱ የት እንደሆነ ይጠቁሙናል:_ ደራሲው “ብሄር ሲባል ከቀጥታ ትርጉሙም ከስሜቱም ተነስተን በምዕራፍ 1 ከቀረበው ሀተታ ጋር አገናዝበን ስናየው ኦሮሞ ትግሬ አፋር ቢል ትክክልም ተገቢም ይመስላል” ይላል። ተሳስቷል፤ትክክልም ተገቢም አይመስልም፤አይደለምም። “ብሔር” የግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “ሀገር” ማለት ነው። ቃሉ ምድርን እንጂ ሕዝብን አያመለክትም። እንዲህ ከሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ብሔሩን ሲጠይቁት፤ አትዮጵያ፤ ቡልጋ፤ጎንደር ኤሉባቡር፤መንደፈራ ቢል ምኑ ነው “ግር የሚያሰኘ ው”? (ገጽ 14 )? ወደድንም ጠላንም ለዚህ ስንጠቀምባቸ የነበሩ ቃላት “ዘር”፤”ነገድ”፤”ጎሳ”፤”ቤት”፤”ወረ” (ለምሳሌ ወረ ቃሉ ወረ ኢሉ ወዘተ) ናቸ ው።)

ተስፋየ ሃቢሶ ሲያሞኛችሁ ሲፈልግ ካለቆቹ ከፈረንጆቹ ተበደረው ጥቅስ እየጠቀሰ እንዲህ ይላል፡ “The conflicts that have occupied most men over the past two or three decades and which have led to the most horrendous outpouring of blood have had precious little to do with ideological divisions… In a world of the jet engine, nuclear energy, the computer, and the regionalized organizations, the principal conflicts are not ideological but tribal [ethnic]. Those differences among men which were supposed to be swept away by science and technology and political revolution are as destructive as ever.” [Said & Lerche, 1995:247].” እጅግ የመገረመኝ ነገር እነኚህ የተስፋየ ሃቢሶ ሊቀ ሊቃውንቶች እንዲህ ብሎዋልና እመኑኝ ይለናል ተስፋየ ሃቢሶ። በመሠረቱ እንኚህ ሊቃዉንት ናቸው ብሎ በጥቅስ ያቀረበልን ደናቁርት ዓለሙን ተረድተው ራሳቸው ተቀጣሪ ናቸው ወይንም ዓለመን አልተረዷትም። ምክንያቴን ላስረዳ።

ዓለምን እያቦጫጨቃት ያለው “ርዕዮተ ዓለም” የሚባል ሳይሆን “ርዕዮቱን” የሚገፉት ከበስተጀርባ ያሉት “ከበርቴዎች” መሆናቸው ለምን ሊደብቁት ፈለጉ? በማር የተጠቀለለውን የጎሳ ፖለቲካ እንዲቀጣጠል ጀማሪዎቹ እነማን ነበሩ ብሎ ተስፋየ ታሪክ መመርመር አለበት። ጣሊያን ሲመጣ በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ ሲያስተዳድርበት የነበረው አስተዳደር እና የመልክኣ ምድር ካርታ ባላገሮቹ/ገበሬዎቹ (አማራዎቹ? ጉራጌዎቹ ኦሮሞዎቹ እስላሞቹ..? ነበር ካርታውን የፈለሰፉት?ወይስ ጣሊያኖቹ የቅኝ ገዢዎቹ ነበሩ ፖሊሲውንና ካርታውን የፈጠሩት? በነዚህ ደናቁርት አመለካከት ዓለምን እያባላት ያለው የTribal ግጭት እንጂ ከበርቴው/ቅኝ ግዛት አስፋፊዎቹ/ኮርፖሬሺኖቹ/ስነዲኬቶቹ ከበስተጀርባ ሆነው የሚያነዱት እሳት አይደለም በማለት ጭልጥ ወዳለዉ ድንቁርና ሲገቡ ተስፋየ ሃቢሶ እና ተከታዮቹ ደናቁርትም አብረው በድንቁርናው ዓለም ተጉዘው እናንተን ለማሞኘት የፈረንጅ ደንቆሮ የጻፈዉን ጥቅስ እየጠቀሱ እንድታምንዋቸው ሲዳዳቸው አያነበባችሁ ነው። ዓለምን ያፋጀው የጎሳ /ትራይባል ፖለቲካው ሳይሆን ከየጎሳው የጎሳ እሳት አቀጣጣይ እየመረጡ ፈረንጆች የተከሉልንን ባንዳዎቻቸውና የነሱ አገልጋዮቻቸዉ በላጋሩን ቅየቀሰቀሱ እንዲተላለቅ እያደረጉ ያሉ “ዓለምን በማፍያ መልክ የተቆጣጠሩ ከበርቴ ሃያላን ባዕዳኖች” መሆናቸውን ኢትዮጵያውያን መገንዘብ አለባችሁ። እነ ተስፋየ ሃቢሶ እና ወያኔዎች/ተገንጣዮች የሚነግዱት ንግድ የጎሳ (ትራይባል) ንግድ በመሆኑ ንገዳቸው እንደቀዘቅዝ አይፈልጉም። ንግዳቸው ከቀዘቀዘ በሥልጣን የሚኖሩበት ዕድሜ ያጥራልና ነው! ስለሆነም ነዉ Tribalism አይከስምም እያሉ የሚሰብከዋችሁ።

በቃ ማለት፤ “በቃ!” ነው። ዘረኞች ይብቃችሁ። ተግማማችሁ! በቃ ማለት አዲሱ ትግላችን መሆኑን እወቁት! በዚህ አጋጣሚ የአንድነት ሃይሎች መልዕክታቸው እንዳያሰተጋቡ የኢንተርኔት መድረክ እየነፈጉ/እያፈኑ (በድርጅት ፍቅር ታውረው) ለጠባቦች/ለፋሺስቶ ርዕዮትና ለምንደኞች የሚፈቅዱትና እያገለገሉዋቸው ያሉት ግለሰዎች በታሪክ-ማሕደራችሁ በልቦናችሁ መዝግቡዋቸው።ገዢዎቹ ብቻ ሳይሆኑ ጠላቶች ባንዳዎች እና አገልጋዮች ቀዳሚዎቹ ናቸው። ኢትዮጵያን አምላክ ይጠብቅ።

ይድረስ ለጎጠኛው መምህር (አማርኛ) እና ሓይካማ (ትግርኛ) መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836

P.O.Box 2219

San Jose, CA 95109