Saturday, April 2, 2022

የትግራይ ፋሺሰት ተዋጊዎች የተማረኩ የኢትዮጵያ ሴት ጦር ሙርኮኞች ላይ ፤በግበረስጋ sexual harassment ሲዘባበቱባቸው የሚያሳይ የቪዲዮ ማስረጃ እነሆ! መጀመሪያ ትርጉሙን አንብቡ! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 4/2/22

 

የትግራይ ፋሺሰት ተዋጊዎች የተማረኩ የኢትዮጵያ ሴት ጦር ሙርኮኞች ላይ ፤በግበረስጋ sexual harassment ሲዘባበቱባቸው የሚያሳይ የቪዲዮ ማስረጃ እነሆ! መጀመሪያ ትርጉሙን አንብቡ!

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay)

4/2/22

በዚህ ቪዲዮ አንዳንድ የብልግና ቃል ታሪክ እንዲዘግበው በማለት ትግርኛ ለማታውቁ ወንድሞችና እህቶች “እየተሳቀቅኩም” ቢሆን በግሃድ ቃሉን ተርጉሜዋለህ፡ ይቅርታ አድርጉልኝ።

 በቪዲዮው ላይ ከፊት ለፊት ኩርትም ብላ የተቀመጠቺው ወጣት ሴት ወታደር አንዳንዴም የባለጌዎቹ ምላስ መዘባበት ሲበዛባት ሲያስጨንቃት ግምባርዋን በጉልበትዋ ላይ ደፍታ ብሰጭትዋን እና ቁጣዋን ለማፈን ስትሞከር ይታያል።

በሌላኛዋ ሙርከኛ ሴት ወታደርም “አንቺ ቆንጆ በእውነት አንቺ መልክሽ እንደ ስመሽ ነው ያምራል”,፣ ካለ በሗላ በትግርኛ የብልግና ቃል “ተጎራሞ” (ተበዲታዎች) ካለ በሗላ “አንቺ’ማ ወደ መቀሌ ትሄጂያለሽ” ሲላት አንዱ ቀጠል አድርጎ “ከስዋ በሗላ የተቀመጠቺውም ታምራለች” ሲለው ገና “አልቀመሱም” በነጻ ነው ያው መቀሌ እንወስዳቸዋለን…. እያለ  ያሾፋል።

 አንዷንም “አንቺ ትግሬ ትመስሊያለሽ?” ትግሬ እውነተኛ ነው። አንተ አንድም ጥይት አልተኮስክም? ምስኪን ትመስላላችሁ እንዲህ ስትታዩ! ውሸታሞች “ተገድደናል” እያሉ እያታለሉ ውሸታሞች ፤እያታለልዋችሁ ነው።”  ሲል እየጠየቀ ያፈጥበታል “ውሸታም!” እያለ ይሰድበዋል።

አንዱ በመጠጥ የተሸነፈ ይመስላል  በዓረብኛ “መርሓባ” ይላል  ተጎራሞ (ተበጂዎች) አንቺ እማ መቀሌ አብረሺኝ ትሄጃለሽ… ይላል” አንዱ ዓይን ዓይንዋን እያየህ “ሞባይል ስልክህ እንዳትጥል፤ ይችን የመሰልሽ ቆንጆ” ይለዋል። መልኩ ምን ይመስላል? አቤት አፉ ምን ያክላል!? በስመአብ! ሲል በሰው መልክ ሲያላግጥ ይደመጣል። አዛዦቹ ግን ዐድዋ/አክሱም ወይንም ሽሬ አራጃ  ልሳን ያለቸው ይደመጣሉ።

በዘለፋውና በብልግናው የሚዘላብዱ እንደርታዎች ናቸው። “አብይ ነው እንዲህ የዳረጋችሁ? አፈር አስበላችሁ! “ያ የገንፎ ዘር!!” ይላል። አንድዋንም “ሲሰተር ምነው? ምነው? ሳቅ በይ እንጂ… ያገር ሽማግሌ ነበርሽ እንዴ?” እያለ እየሳቀ ያሾፍባታል። “እርስዋን አንሳት! አንሳት! ያቺ ቆንጆ ነች ወደ መቀሌ እንወስዳታለን” ይላል። አሳዛኝ ሆኖ ያገኘሁት እንደርታዎች ከዘረኛነት ትንሽ የተሻሉ ነበሩ ከሚባሉ የትግራይ አውራጃዎች “አንደርታዎች” ነበሩ ዛሬ እነሱ ብሰው ማየት ያሳዝናል። ብዙዎቹ በቪዲዮው ላይ የምታደምጥዋቸው ይህንን ዘለፋ የካሄዱት የወረበላው ተዋጊ ሃይል “የእንደርታ ልሳን ተናጋሪዎች ናቸው።

እንዲህ ያሉ እጅግ አደገኛ “ቦኮሃራም” አይነቶች የትግሬ “ታሊባን ተዋጊዎች” የሙርከኛ መብት በመጣስ በሕግ መጠየቅ አለባቸው።

ካሁን በፊት ታስታውሱ እንደሆነ ሙርከኞችን ሰብስበው “ወላጆቻችን ተማርከዋል እኛም ተማርከናል!!” በሉ እያሉ ሙርከኞችን ሲያስጭንቁዋቸው በቪዲዮ የለጠፍኩትን ታስታውሳላችሁ ። ዛሬ ደግሞ በግሃድ ሴቶችን እንዲህ ሲያሾፉ መስማት “ሴቶች መብት ተጣሰ” የምትሉ “የዲያስፖራ የትግራይ ሴቶች ማሕበር” ይህንን ስታደምጡ ከዓለም ፊት መሸሸግ ይኖርባችል። 

እባካችሁ  ላልደረሰቀወ አዳርሱት!

 Tigrayan Fighters sexually harassing Ethiopian women army captives violating war rules

https://youtu.be/YgnQ0ylfm_Y