Saturday, October 8, 2016

ሃይሉ ሻውል አስራትን የትካ አምበሳ! ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ (Editor Ethio Semay)ሃይሉ ሻውል አስራትን የትካ አምበሳ!

ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ (Editor Ethio Semay)
የኢትዮጵያ ሰማይ በኢንጅኔር ሃይሉ ሻውል ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘኑን ይገልጻል። ፈጣሪ ለቤተሰብና ለወዳጆቻቸው ምጽናናትን እንዲሰጥ ጸሎቱን ያቀርባል። ከኦሮሞና ከአማራ ቤተሰብ የተገኘው ሃይሉ ሻውል አስራት ወልደየስን የተካ ባለ ግርማ አምበሳ ነበር። ወያኔ፤ተገንጣይና ጠባብ ቡድኖች የሃይሉ ሻውልን ርቱእ አንደባት እና የፖለቲካ ክርክር እጅግ ያርበደበዳቸው እንደነበር በዩቱብ፤ በጽሑፍና በቴ/ቪዥን እንዲሁም በራዲዮ ቃለ መጠይቆች የሰፈሩ ማሕደሮች ህያው ምስክሮች ናቸው።እንደሚታወሰው ‘በፋሺስቱ የትግራይ ወያኔ ቡድን’ መሰሪ ዐቅድ ታላላቅ ያገሪቱ ባሕርዛፎች እንዲቆረጡ መጋዝ ከተሳለላቸው መካካል አንዱ ሃይሉ ሻውል ነበሩ። “በፋሺስታዊ ጣሊያናዊ” ባሕሪ የሚመራው “ወያነ ትግራይ” ወደ መሃል ኢትዮጵያ ሲገባ፤ ሰንደቃላምን፤አማራን እና ተዋህዶ ክርስትናን ለማጥፋት በነዚህ እስቶች ላይ ጥላቻ ያሳደሩ አክራሪ ሃይላትን በማሰባሰብ ከፍተኛ የሆነ ዘለፋና የነገድ ጽዳት ወንል ሲፈጽም፤ ፕሮፌሰር አስራት እና ሃይሉ ሻውል ግምባር ቀደም የወያኔ ኢላማ ከነበሩት መካካል ነበሩ። ሃይሉ ሻውል ኢትዮጵያዊንትን ለማቆየት ሲታገሉ፤ከተለያዩ ሃይላት ጸያፍ ዘለፋና ዛቻ እንዲሁም የስም ማጥፋት ደርሶባቸዋል።በሃይሉ ሻውል ላይ ፋሺስቱ ወያኔ ብቻ ሳይሆን የተረባረበው፤ በጸረ ወያኔ ፖለቲካ  የቆሙ ተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎች (እንደ ብርሃኑ ነጋ ዓይነቱ ሻዕቢያዊ እና ኦነጋዊ ‘ጊላ’ )፤ ጋዜጠኞች እና ግለሰቦች ያልወረወሩት አስጸያፊ ድንጋይ አልነበርም። በጣም ዘግናኝና ፈታኝ በሆነ መድረክ ትግሉን ወደ ፊት ለማራመድ ሃይሉ ሻውል የከፈሉት መራራ ትግል አጅግ ብዙ ነበር።በፋሺስቱ ወያኔ የታገደው ኢትዮጵያ ሕጋዊ ሰንደቃላማችን ተቃዋሚዎች ለማውለብለብ ሲፈሩና የተለያዩ ቀለሞች የያዙ ትርጉማቸው የማይታወቅ ‘መሃረሞችን’ ሲያውለበልቡ፤ ‘ሰማያዊ ቀለም ቀብቶ ሰይጣናዊ ኮከብ በመለጠፍ ወያኔ ያጨማለቀው ባንዴራ አላውለበልብም’ ብለው ማሕበራቸውና ደጋፊዎቻቸው በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ሁሉ ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጡ ሕጋዊውን ሰንደቃላማ ይዘው አንዲወጡ ያደረጉና የታገሉ ብቸኛ ፖለቲከኛ ሰው ሃይሉ ሻውል ነበሩ።የአማራ ማሕበረሰብ በዘረኞችና በነብሰገዳዮች ወንጀል ሲፈጸምበት፤ከሚኖርበት ምድር እና ከአገሩ እንደ ባዕድ እየተገፈተረ ሲባረርና ሲገደል’ የአማራው ማሕበረሰብ ብሶት ያስተጋባ ብቸኛ ፖለቲከኛ እና የቁርጥ ቀን ልጅ ሃይሉ ሻውል ነበር! ሃይሉ ሻውል በዚህ ማሕበረሰብ የተደበቀው ወንጀል ለማጋለጥ በጣረ ቁጥር፤ በተቃዋሚ እና በወያኔ ቡችሎች እና ፖለቲከኞች ብዙ ዘለፋ እና ስም ማጥፋት ቢደርስባቸውም፤ ከቶ ከታገሉለት አላማ ፍንክች ሊያደርጋቸው አልቻለም ነበር።በኦክራሪ ኦሮሞ ብሔረተኛነት ያበዱ እስላማዊ እና ፖለቲካዊ ነብሰገዳይ እና ሽብርተኛ ተገንጣዮች በቢላዋ አማራዎች የገላቸው ሥጋ እየተቆረጠ የገዛ ሥጋቸው እንዲበሉ ሲደረግ፤ ሃይሉ ሻውል “የኢትዮጵያ ሕዝብ እና የተቀዋሚ የዜና ማዕከሎች ዝምታ የመረጡበት ምክንያት ምን ይሆን? ይጥፋ ተብሎ ተበይኖበት ከሆነም፤ አማራውን ከምድረገጽ ማጥፋት አይቻልም!!” ሲሉ መጠየቃቸው እናስታውሳለን። ይህ ወንጀል ሲፈጸም የተቃዋሚ የዜና ማዕከሎች ግን “ጋዜጠኖች ታሰሩ…” እያሉ ምድር ሲያቀልጡ ሰላመዊ ሰልፍ ሲያደርጉ፤ ሚዲያዎች በጋዜጠኞች መታሰር ብሶት ሲያጣብቡት፤ “የአማራው ዕልቂት” ግን ሰምተው እንዳልሰሙ በመሆን፤ የወንጀሉ ተባባሪዎች ሆነው መቆየታቸው ስጽፋቸውና ስናገራቸው ከነበሩ ቃለ መጠይቆቹ አንባቢዎቼ የምታስታውሱት ነው።የሃይሉ ሻውል ገድል ሲወሳ የአማራ ብሶትም አብሮ የሚወሳ ነው። በዚህ አጋጣሚ ከላይ የጠቀስኩት በፋሺስቱ ወያኔ አይዞህ ባይነት፤ በኦነግ (OLF) እና በጃራ የሚመራው እስላማዊ ኦሮሞ ነጻ አውጪ ድርጊት ፈጻሚነት በርዋንዳ እልቂት ያልታየ በኢትዮጵያ ምድር በአማራው ማሕበረሰብ ላይ የተፈጸመው አረሜናዊ ወንጀል መፈጸሙን ያልሰማችሁ ሰዎች እንዳትኖሩ ማስረጃ ማቅረብ ስላለብኝ፤ ከዚህ ቀጥሎ ያለውን በሞረሽ ወገኔ የተደገፈ፤ በጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው የተዘገበ “የጥፋት ዘመን ከ1983 እስከ 2007 ዓ.ም በዐማራ ሕዝብ ላይ የተፈጸመ ዘር ማጽዳት” በገጽ 56 እንዲህ ተዘግቧል፡-እታፈራው ደጀኔ ይምትባል በእህል የምትተዳዳር አማራ በገዳዮቿ እጅ ትገባለች። መጀመሪያም ቢሆን የገዳዮቿን ዓይን የገዛቺው፤ ያላት ንብረትና ሃብት እንደሆነ መረጃውን የሰጡ ሰዎች ይናገራሉ፡ ከዚያም እነዚህ ሰው በላዎች የጭካኔ ስልት ተለማመዱባት።


በመጀመሪያ አሰሯት።ከዚያ ልብሷን አስወልቀው አካላቶቿን አንድ ባንድ መምተር (መቆራረጥ) ጀመሩ።ጡትዋን ቆርጠው እንደትበላው ሰጧት። ከመቀመጫዋም ላይ ሥጋ አንስተው እንዲሁ ራሷ በራሷ እንድትበላ ጋበዟት። ብልቷንም እንደዚሁ ቆራረጡት። በሰው ልጅ መጨረሻ የሚባለውን ስቃይ አሰቃይተው ቆራርጠው ገደሏት።” (ገጽ 56በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አክራሪ እስላማዊ ቡድኖች እና ኦነግ ዐማሮችን በጉድጓድ ወስጥ አንገታቸው ብቻ እስኪቀር ድረስ ከቀበሯቸው በላ በድንጋይ ደብድበው ገድለዋል። ይህ በእርግጥ በሐረርጌ ብቻ ሳይሆን በአርሲም ተፈጽሟል።) (ገጽ 56)እንዲህ ያለ ግፍ በአማራው ላይ የተቀባበረ ወንጀል ሲፈጸም ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ጥቂት ከሚበሉት ሰዎች ይህንን ወንጀል ለዓለም ማሕበረሰብ ጋሃድ እንዲሆን ከታገሉት መካከል ኢንጅኔር ሃይሉ ነበሩ። ሃይሉ ሻውል አማራን ከሚኖርበት አገሩ እንደ ባዕድ ሲባረር እና ወንጀል ሲፈጸምበት በመጮሃቸው ምክንያት፤እንደ አንድ የፖለቲካ መሪ ከፋሺስቱ ወያኔ ጋር ሲደራደሩ፤ ከመለስ ዜናዊ ጋር ሲጨባበጡ በመሰሪ ቡድኖች እና የሚዲያ ሰዎች “አጅግ በሚያስገርም አስጸያፊ የፎቶግራፍ ቁመና በማጣመም” ለወያኔ አጎነበሰ ፤ ብለው ስማቸውን እያጠፉ ፖለቲካ ሲሰሩ እና ከዚያም ኣልፎ “ሃይሉን በወያኔነትም” ሳይቀር የከሰሱ የሚዲያ ሰዎች እና ፖለቲከኞች አይተናል።በራዦቹ በዚህ አላቆሙም። ቅንጅት ያፈረሱ እነ ብርሃኑ ነጋ እነ አንዳርጋቸወ ጽጌ እነ ብርቱካን መዲቅሳ፤ በእነ ታማኝ በየነ፤በእነ ንአምን ዘለቀ፤ በእነ አበበ በለው፤በእነ አል ማርያም እና በእነ ኤልያስ ክፍሌ አጨብጫቢነትና አራጋቢነት የሃይሉን ሻውል ተክለ ሰውነት ለማንኳሰስ ያልደረገ ክፉ ሴራ አልነበረም። በመጨረሻ ሁሉም ቅንጅትን አፍርሰው አማራን በመጨፍጨፍ ወንጀል ወደ እሚከሰሱት ወደ ሻዕቢያ እና ወደ ኦነግ ጉያ ሲወሸቁና የትግል ግምባር ሲመሰርቱ፡ ሃይሉ ሻውል ወያኔ ባባበሰባቸው የስኳር በሽታ እየተሰቃዩ፤ አገሬ ኢትዮጵያ ሞት ወይንም ድል ብለው የፖለቲካታ ታጋዮችን በሃሳብ እየረዱ ከአገር ሳይወጡ እስከ ሕልፈተ ሞታቸው ድረስ የተቻላቸውን ያህል ፋሺስቱ ወያኔ እና የተለያዩ አክራሪ ብሔረተኞችን ታግለዋል። የኢትዮጵያ ሰማይ አስራትን የተካ አንበሳው ሃይሉ ሻውል ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማው ጥልቅ ሃዘን ይገልጻል። ትግሉ ይቀጥላል!

ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ (Editor Ethio Semay) getachre@aol.com