Tuesday, November 5, 2019

ስሜተኛው የፌስ ቡክ አገር ወዳድ ወዴት እያመራ ነው? የሳውዲ ጩኸት አልሰማ ያለው ኢትዮጵያዊ! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay) 11/5/2019


ስሜተኛው የፌስ ቡክ አገር ወዳድ ወዴት እያመራ ነው?
የሳውዲ ጩኸት አልሰማ ያለው ኢትዮጵያዊ!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay) 11/5/2019
Ethiopia: አሳዛኝ ዜና - የሞ- ፍርድ ተፈረደባቸው ያሳዝናል

የዲያሰፖራው የፌስ ቡክ አገር ወዳድ የወላጆቹን የ27 አመት አመለ ዳተኝነት አልላቀቅ ብሎታል። 27 አመት ለወገን ድረስ ተብሎ ሲጠየቅ ጀሮ ዳባ ብሎ፤ ግማሹም ለጠላት ሲያድር፤ግማሹም ሲያሾፍብን ከርሞ ዛሬ “አገር ከተዋረደ በሗላ መጮህ ጀመረ”። እንዲያም ሆኖ ከዳተኛነቱ አልተላቀቀም።

ትናንት ስለለጠፍኩት ኢትዮጵያውያን በሳውዲ የድረሱልን ጥሪ ኢያለቀሱ በቪዲዮ የተለቀቀው መልእክታቸው ለሞት ቅጣት እየተጠባበቁ ስለመሆናቸው፤ እንድረስላቸው ብየ ስለለጠፍኩት አስቸኳይ ጥሪ አጥጋቢ ምላሽ ስላለገኘ ይህንን በሚመለከት አንድ ነገር ለማለት እነሆ ዛሬም መጥቻለሁ።

ብዙዎቻችሁ ኢትዮጵያውያኖች የምላስ አገር ወዳዶች ናችሁ። በመከራ ወቅት ድረሱ ሲባሉ አይደርሱም። መስፈን ፈይሳ የለተባለው “የአብይ አሕመድ ደጋፊ” ከባለቤቱ ጋር ተጣልቶ የገንዘብ ዕርዳታ አድርጉለት ተብሎ በብዙሺ ብር ዕርዳታ ተደረገለት።

ትናነት በፌስ ቡኬ ላይ ሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ያለ ወንጀላቸው ተወንጀለው ያለጠበቃ ፍርድ ቤት ቀርበው ሁሉም አንገታቸው እየተቀሉ እንዲሞቱ ተፈርዶባቸው፤ እባካችሁ ድረሱልን ስላሉን እኔም ለኢትዮጵያውያን እንዲደርሱለት ብየ የሳውዲ ኤምባሲ አዲስ አባባ እና ሳውዲ ዓረቢያ ያለው የኛው ኤምባሲ ተብየው ስልክ እንዲደውሉ ወይንም እንዲጽፉ ለጥፌላቸው፤ “መልዕክቱን የተጋራው (ሼር ያደረገው) አንድ ሰው ብቻ ነው፤፡ አሳዛኙና ጉረኛው የፌስ ቡክ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ዛሬም እንደ 27 ቱ አመት አንጀቴን እያቃጠለው ይኼው ዛሬም ቀጥሏል።

አበሻ ስሜተኛ ፤ጉረኛ ቢባል ያንሰዋል! 27 አመት የድረሱልን ጩኸት እንዳይበቃ ፤ዛሬም በድጋሚ “እባካችሁ የሰው ህይወት ከሞት እናድን ” እያልን መኳተታችን እጅግ ያሳዝናል! ሰውን ከሞት ለማዳን “ሼር” ለማድረግ ዳተኛ የሆነ የፌስ ቡክ ስሜተኛ ምን ቢደረግ ይሻላል? ማፈሪያ ሁላ!! በውርደት መኖር የሚመቸው ማሕበረሰብ ከእንሳሰ ሕሊና አይሻልም። ለሞት የተዳረጋችሁ የኢትዮጵያ አምላክ ይድረስላችሁ ከማለት ምን እላለሁ። ለዳተኞች ግን አምላክ በበሽታም፤ በድንገትም፤ በችግርም ድረሱልን እንዳያስብላችሁ እጸልይላችሗለሁ።
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)