Friday, October 16, 2009

በብሔር ብሔረሰብ እና ሕዝቦች ሽንሸና ለሰከሩ የኮሚኒስት ዛሮች

በብሔር ብሔረሰብ እና ሕዝቦች ሽንሸና ለሰከሩ የኮሚኒስት ዛሮች

በብሔር ብሔረሰብ እና ሕዝቦች ሽንሸና ለሰከሩ የኮሚኒስት ዛሮች ከሰላሳ አመታት በላይ እስካሁን ድረስ ኢትዬጵያን እያሰቃያት የሚገኘዉ የፖለቲካ ዉዥምብር “የኮሚኒስቶች” የፖለቲካ ፖሊሲ መሆኑን ለዛች ሃገር ሕዝብ እቆረቆራለሁ የሚል ሁሉ መገንዘብ አለበት እላለሁ፣፣ በኢትዬጵያ ለ18 ኣመት የታየዉ የጎሳ ጽዳት እና የግድያ ወንጀሎች እና የታዩት አስነዋሪ ሁኔታዎች ፣ ዋና ተጠያቂዎች ቁጥራቸዉ በጣም የበዛ ኮሚኒስታዊ እምነት በሚከተሉ በጣም (ኤክስትሪም) ፋሽስታዊ እርምጃዎችን በመከተል ያንድ ሃገርን ሕዝብ በኮሚኒስታዊ አሰራር፣ባሕርይ እና እምነት እንዲበከል የሚያደርጉ ቡድኖች እንደ ኦነግ፤ወያነ ትግራይ፤የ ኤርትራዉ ሕዝባዊ ግምባር/ሻዕብያ፤ የኦጋዴን ነጻ አዉጪ ቡድን እና የሲዳማ እንዲሁም ባኦሮሞ እንቅስቃሴ ስም የታቀፉ የ እስልምና አክራሪ ሃይሎች ወዘተ መጥቀስ ዋናዎቹ ተጠቃሾች ናቸዉ ፣፣ በፕሮግራማቸዉ እንደ መመርያቸዉ በይፋ የነደፉ አወራ ተዋናዮቹ ለምሳሌ ኦነግ እና ወያኔ የተባሉት ለዉጭ ሃገር ጠላቶች ያደሩ ሁለቱ ኮሚኒስት ቅጥረኞች ለብዙ ዓመታት እና አሁንም የሚከተሉት ዕምነት “ፋሽስታዊ የኮሚኒሰት” የፖለቲካ አሰራር በመሆኑ፣ የደቡብ አፍሪካ እና የጥንቷን ሮዴሺያ ዘረኞች እና ወራሪዎች የነኛን አካባቢ ዜጎች በቀለም እንደሸነሸንዋቸዉ ሁሉ እንኚህ የኢትዬጵያ ኮሚኒስት ፋሺስቶች ደግሞ ዛሬ ኢትዬጵያን የሚሸነሽንዋት በቋንቋየዜጎች ማንንት መለያ በማድረግ እንዲስተዳደር አዉጀዋል፣፣ ወያኔ እና ኦነግ የተባሉ ቡድኖች በዉጭ ሃይላት ተደግፈዉ ያለ ሕዝብ ሱታፌ የመንግስት ስልጣን በጠመንጃ አስፈራርተዉ በተቆጣጠሩበት ጊዜ ጀምሮ በረሃ ዉስጥ የነደፉት የራሳቸዉ ሕገመንግስታዊ ንድፍ እዉን በማድረግ፤ ከቋንቋ አልፈዉ ሃገሪቱ በዉስጥዋ ብዙ ሃገሮች እና ከሃገር ያነሱ ሃገሮች ከዚያም ወረድ ብሎ “ሕዝቦች” የሚሉዋቸዉ ከሁሉም በታች ያነሱ “ሕዝቦች” የሚሉት ግራ ያጋባ ትንታኔ በመሸንሸን ሃገሪቱን ለግጭት ዳርገዋታል፣፣ ሃገሪቷን በፋሽስቶቹ እምነት ሃገሪቷን “ቋንቋን መሠረት ሲያደርጉ እያንዳንዱ በተለምዶ “ከሰባ በላይ”-የተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች አሉ የምንላቸዉን ኢትዬያዉን ዜጎች “የየጎሳቸዉ ልጆች” በማስመሰል በዉሸት እና በግምት ቋንቋን እንደ የማንነት አመላካች ምርኩዝ በማድረግ በሚጠቀሙባቸዉ የቋንቋ ልሳኖች የዜጎችን ህዳጣን ማንነት ደም እና አጥንት(ትዉልድ) ተጨባጭ አመላካች ማስረጃ በማድረግ የሃገሪቱ ሕዝቦች ማሕበራዊ እና ሰባዊ ግንኙነት በሚጠቀሙባቸዉ የመገናኛ ቋንቋዎች እንደ ዋነኛ የማንነት መገለጫ አድርገዉ እንደ የስጋ ቅርጫት ሲሸነሽንዋቸዉ እናያለን፣፣ ይህ ደግሞ የሕዝብ አንድነት ከማደፍረስ አኳያ አደገኛ ከመሆኑ አልፎ እያንዳንዳችን ማንነት በመንግስት እና በፖለቲካ ቡድኖች ጫና ከሰባዊ እና ማሕበራዊ መብት እይታ ግምታዊ ቦነ ማለትም ቋንቋን ተንተርሶ ማንነትን ለመግለጽ የሚደረገዉ አጉል ሽንሸና “ከተራዉ ሕዝብ ቤተሰብ እስከ ከቤተመንግሥት የጎሳዎችና የነገዶች ግንኙነት የድብልቅ ዉጤቶች የመሆናቸንን” የሚጻረር ነዉ፣፣ የፖለቲካ ወረበላዎቹ በትምክህት እና ማን አለኝነት ማንነታችንን በእነዚህ ቡድኖች እጅ ቁጥጥር በመግባት እኛነታችንን ሊነግሩን መሞከራቸዉ ታላቅ ወንጀል ስለሆነ እንኚህ ቡድኖች በሚሰነዝሩት አደገኛ ስታሊኒስታዊ ትንተና ሁሉም “ነኛ” ዜጋ መቃወም ይኖርበታል፤፤ ቋንቋ ከአህጉሮች ያካባቢ መለያ ያገለግል እንደሆን እንጂ ያም ቢሆንም ከየትኛዉ ዘር እንደመጣን አይለይም፣፣በዙህ ተንተርሶ፣ ፕሮፌሰር ሃይሌ የሚሉን ጠቃሚ ትምህርት እንደሚከተለዉ ይገልጹታል፤፤ በርግጠኝነት “የምንጠቀምባቸዉ ቋንቋዎች የአያቶቻችን ልጆች መሆናችን በማያጠራጥር ግምት የምንድርስበት ያህል የቅድመ አያቶቻችን ቋንቋ ግን ምን እንደነበረ አዉቃለሁ የሚል ሰዉ የለም/አንደረስበትም (ጌታቸዉ ሃይሌ- የአባ ባሕሪይ ድረሰቶች (ከዜናሁ ለጋላ የአማርኛትርጉም) ገጽ 166)፣፣ ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሃይሌ ከላይ በጠቀስኩት መጽሃፋቸዉ ቋንቋን ተገን እያደረጉ መንግስታዊ እና ፖለቲካዊ ስራ ለመስራት ሕዘብን በሚናገረዉ ልሳን ተመርኩዘዉ የእገሌ ጎሳ ነህ እያሉ የመታወቂያ ወረቀት የሚያዘጋጁ ዘረኝነትን ሚያራምዱ የፖለቲካ ቡድኖች አና በስልጣን ያሉት ግለሰቦችን ስህተታቸዉ ምን ላይ እንደሆነ ሲገልጹ እንደሚከተለዉ ያብራራሉ፣- “በደም የዛሬዎቹ ኢትዬጵያዉያን ከተራዉ ሕዝብ ቤት እስከ ቤተመንግሥት የጎሳዎችና ነገዶች ግንኙነት ዉጤት መሆናቸዉንን የሚያሳየዉ ያያቶቻችን የጋብቻቸዉ ታሪክ ያልተጻፈዉ በ ኢትዬጵያዉያን መካከል ጋብቻ ጉድ ወይም ብርቅ ስላይደለ ነዉ፣፣ የአጼ ምኒሊክ ልጅ ወይዘሮ ሸዋረገድ የራስ ጎበና ልጅ የአቶ ወዳጆ ባለቤት እንደነበሩ የተጻፈዉ የገዢዎች ታሪክ ስለሆነ ነዉ፣፣ እንጂ አጼ ምኒልክ አማራ(!) ራስ ገበና ዳጨ ኦሮሞ ስለሆኑ ያንን ታሪክ ለመመዝገብ አይደለም፣፣ ክቡር ልጅ ሚካኤል እምሩ ራስ ጎበና ዳጨ አያታቸዉ መሆናቸዉን የነገሩን አንድነት ጋዜጣ ስለጤቃቸዉ ነዉ፣፣ ያዉም ቢሆን ዘራቸዉን ለመቁጠር ሳይሆን ቤተሰባቸዉ ለኢትዬጵያ መንግሥት ትንሳኤ ስላደረገዉ አስተዋጽኦ ታሪክ ሲያስተምሩን ነዉ፣፣ በባህልም ረገድ ኦሮሞዎች ኢትዬጵያ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ በነሱና በወረሩት ሕዘብ መካከል ከፍተኛ መደባለቅ ነበረ፣፣ ለምሳሌ ክረስትያኖች ስማቸዉን “ዘጶ”፣ “ዐስቦ”፣ “ዐምዶ”፣ “መንገዶ”፣ “ተዝካሮ”፣ ”ዘሦ”፣ ወዘተ እያሉ በሳብዕ ሲያሳጥሩ እናያለን፣፣ የሆነዉ ኦሮሞዎች “ጢኖ”፣ “ጥሒቶ”፣”ሓለብዶ”፣ “በርባዶ”፣ወዘተ እያሉ ስም የሚያወጡበትን ዘዴ በመዉሰድና የራሳቸዉ በማድረግ ነበር፣፣ በአማርኛ ላይ የሚታየዉን የባህላቸዉን ጉልህ ተጽእኖ ትተን ግዕዝን ብንመረምረዉ የኦሮሞ ባህል ተጠቃሚ ሆኗል፣፣ ይህ የሆነዉ ኦሮሞዎች የግዕዝ ዓለም ጎረቤቶች ስለሆኑ ሳይሆን፣ እንደ ኦሮሞዎቹ እንደ አዛዥ ጢኖ እና የጎጃምን ታሪክ እንደጻፉልን እንደሰዓሊዉ እንደ አለቃ ተክለ የግዕዙ ሥነነ ጽሑፍ ባለቤት ስለሆኑ ነዉ፣፣ የሃገሪቱ ባህል በአዲስ ደም እንደፋፋ ግልጽ ነዉ፣፣ አባ ባሕሪይም ቢሆኑ ይኽንን ያህል ዝረዝር የጻፉት ስለባለቤት እንጂ ስለጎረቤት ወይም “እጋላ አገር” ሄደዉ ያገኙ=ትን “የመስክ ጥናት” አይደለም፣፣ የጎሳዉ ልጆች አስመሰለን ታሪካዊ አጋጣሚና በቦታዉ መወሰን ምክንአት ግማሾቻችን ያንዱን ነገድ ቋንቋ ስለምንነጋገር ነዉ፣፣ ለምሳሌ ደምብያን (ጎንደርን) እና ጎጃምን የወሰዱ ኦሮሞዎች ልጆች ቋንቋ አማርኛ ሆኗል፣ አማራ መስለዋል፣፣ የ አርሲ ሕዝብ ከግማሽ በላይ የሐዲያ ትዉልድ ሆኖ ሳለ ቋንቋዉ ኦሮሞ ሆኛል፣ ኦሮሞ መስሏል፣፣ ይህ መስሎ መገኘት ለጠላት መግቢያ ትልቁ ቀዳዳ እነሆ ሊያተራምሰን ይመላለስበታል፣፣ የምንነጋገረዉን ቋንቋ ተከትለን ኢትዬጵያ ዉስጥ ከተፈጸሙት ታሪካዊ ድርጊቶች እንዱን ክፍል የዚህ ቋንቋ ተናጋሪ እንዱን የዚያ ቋንቋ ተናጋሪ ታሪክ እናድርግ ብንል እዉነት አትፈቅደልንመ፣፣ የአያቶቻችን ልጆች መሆናችንን በማያጠራጥር ግምት የምንደርስበት ያህል የቅድመ አያቶቻችን ልጆች ቋንቋ ምን እንደነበረ አንደርስበትም፣፣ ዛሬ የትኛዉንም ቋንቋ ወርሰን ብንገኝ ሁላችንም፣በዚያን ዘመን አነጋገር የጋሎችና የሲዳሞቹ ወይንም በዛሬዉ ፣ የኦሮሞዎቹና የአማሮቹ ልጆች ነን፣፣ በምንናገረዉ ቋንቋ እየተመራን ከጥንት ዘራችን ልንደርስ የማንችልበት ምክንያት ቋንቋዎቹን ጥምዝምዙ የታሪክ መንገድ ስላሳወራቸዉ ነዉ፣ ዕዉር ደግሞ መምራት አይችልም፣ ቋንቋዎችን ታሪክ አካፋይ ብናደርጋቸዉ ሲደናበሩ ለነሱ (ለቋንቋዎቹ) እንደሚመች አድርገዉ ፣ግማሾቻችንን ከእናታችን ግማሾቻችንን ከአባቶቻችን ዘርና ታሪክ ይለያዩናል፣፣ በ16ኛዉ ምእተ አለም ኢትዬጵያን የወረሩ ኦሮሞዎችና ሊከለክሏቸዉ የሞከሩ የቀድሞዎቹ ነባሮች ሁሉም ከሞላ ጎደል እኩል አያቶቻችን ሆነዋል፣ እኛም እንደዚያዉ ከሞላ ጎደል እኩል ልጆቻቸዉ ነን፣፣ የምንነጋገርበት ቋንቋ ማስረጃ አድርገን ከተፈጸመዉ ረጂም ታሪክ ዉስጥ ኦሮሞዎቹ የፈጸሙትን ዛሬ ኦሮምኛ ለሚናገሩ ሌላዉን ለሌሎች ማካፈሉን የምንገፋበት ከሆን መጀመሪያ ታሪኩን ከ አያቶቻችን ነጥቀን ለወረስናቸዉ ቋንቋዎች መስጠት ይኖርብናል፣፣ ይህ ደግሞ “ባለታሪኩ የኢትዬጵያ ቋንቋዎች እንጂ የኢትዬጵያ ሕዝብ አይደለም፣ እኛ ታሪክ የለንም፣፣” እርግጥ ኦሮምኛ የሚናገሩ ኦሮሞ የሚባሉ ኢትዬጵያዉያንና ሌላ ቋንቋ የሚናገሩ የግል መጠሪያ ያላቸዉ ሌሎች ኢትዬጵያዉያን አሉ፣ እነዚህ ሰዎች ታሪክ አንድ የኢትጵያ ሕዝብ ያደረጋቸዉን ረስተዉ ልዩነታቸዉን ለማጠናከር ከፈለጉ ከ አሁን ይጀምሩት እንጂ ወደ ታሪክ አይሂዱ፣ ታሪኩ ያሳቅቃቸዋል፣ ፍላጎታቸዉንም ዉድቅ ያደርገዋል፣፣” ጌታቸዉ ሃይሌ - የአባ ባሕሪይ ድርሰቶች ገጽ166-168)/-/ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/