Wednesday, January 4, 2023

የልደቱ አያሌው ከደደቢት ሚዲያ ቃለ መጠይቅ ንግግሮቹን ልበልታቸው ጌታቸው ረዳ ክፍል 1 Ethiopian Semay 1/4/2023

 

የልደቱ አያሌው ከደደቢት ሚዲያ ቃለ መጠይቅ ንግግሮቹን ልበልታቸው

ጌታቸው ረዳ

ክፍል 1

Ethiopian Semay

1/4/2023

በልደቱ ላይ እንደምታውቁኝ ብዙም አልጨከነኩም ነበር። ፖለቲከኞች ስጠምድ እጅግ አምርሬ በማስረጃ ነው ያላማቋረጥ ስተች የምታውቁኝ። ብርሃኑ ነጋን እና ኢሳት እኔ በግለሰብ ብቻ እንደ አንድ ድርጅት ሆኜ ፍርስርሳቸው እንዲወጡ ካደረጉት ቀዳሚ ሰው እኔ መኖርየን ብዙዎቻችሁ ስጽፋቸው ከነበሩት በርካታ ጽሑፎቼን ታስታውሳላችሁ።

በሌለቹ ላይ እንደምጨክነው ያልልጨከንኩበት ፖለቲካ ቢኖር ልደቱን ነው። ልደቱ አያሌው ወጣትና በጣም ትንታግ ተናጋሪ ፖለቲከኛ ሲሆን “አወዛጋቢ” የሚባል ቁንጮ ፖለቲከኛ ነው።ከተጻረርኩበት ይልቅ ላለመተቸት የተቆጠብኩባቸው ወቅቶች ያመዝናሉ። ድንገት እያሻሻለ ከመጣ የአገር መሪ እስከመሆን እንደሚደርስና አቅም እንዳለውም ሳልናገር ውስጣዊ አመኔታም አሳድርበት ነበር።

 በልደቱ ላይ ቅሬታየ የጀመርኩበት ወቅት አፓርታይዱ የባንቱስታን አስተዳዳሪው “ወያኔ” (ልደቱ ‘ቲ ፒ ኤል ኤፍ’ እንጂ ወያኔ ብየ አልጠራውም የሚለን የልደቱ አባባል በክፍል 2 እመለስበታለሁ) ወያኔ ስልጡን ነኝ ለማለት የዜጎች ተቆርቋሪ ነኝ የሚል ምሁርና ፖለቲከኛ ጥሪ አድርጎላቸው ሂልተን ሆቴል ሰላማዊ የውይይት/ዕርቅ/ባህሪ ማመቻቸት የሚል ተቃዋሚውን ለማደንዘዝ ጥሪ አድርጎ በነበረበት ወቅት ነበር ልደቱን ፖለቲካ ማየት የጀመርኩት።

እኛ እዚህ ውጭ አገር ሆነን (ኢ ኢ ዲ ኤን በተባለው የምሁራን የድረገጽ የኢመይል ልውውጥ በሚደረግበት መስመር ላይ) ልደቱን ከተቃወሙት አንዱ እኔ ነበርኩ (በወቅቱ ሌሎቹ ስር ነቀል የሆነ ሕዝባዊ አመጽ በማስነሳት ለውጥ ለማምጣት ካልታገልን ይህ የወያኔ ውይትና መሞዳመድ ፍሬ ከርስቺ ነው ሲሉ ከነበሩት አንዱ ነበርኩ። በወቅቱ አዲስ አባባ  ሂልተን ውስጥ ስብሰባውን እንካፈልም ሲሉ ልደቱ ግን እንካፈል እያለ ሲወተውት የነበረ ፖለቲከኛ ስለነበር አስታራቂው “ቄስ ልደቱ” ብየ ስጠራው ነበር)። ግምባር ቀደም ሆኖ ዕድሜ ልኩን የዘለቀበት ከአፓርታይዱ ወያኔ ጋር “ከወያኔ ጋር እንደማማጥ የፖለቲካ መስመሩ” ዛሬ ሳይሆን ያኔ ነበር በከፍተኛ ጩኸትና ክርክር የጀመረው። ልደቱ በወቅቱ የወያኔ እንደማመጥ ጥሪ” ተንኮል ያዘለ ርቀት የሌለው እንደሆነ እና  ብዙ አገር ወዳዶችን በጠራራ ፀሐይ ሲገድል፤ ከሥራ ሲያባርር፤ ሲያፈናቅል፤ የአገር ንብረት ወደ ትግራይ ሲጭን ፤ አማራን ለይቶ ሲያጠቃ፤ ለዕርቅ ወደ አዲስ አባባ የጠራቸው ተቃዋሚዎችን አስሮ ያሰቃይ እንደነበረ ፤ ጸረ አንድነት የሆነ ድርጅት መኖሩን የማያውቅበት ዕደል አልነበረም ማለት አይቻልም።

ከዚያም ወደ ቅንጅት መጥቶ “ሦስተኛ መንገድ” የሚል የጅሎች ፖለቲካ አማራጭ ውስጥ ገበቶ በBantusta ዎቹ  ፓርላማ ውስጥ ገብቶ ለውጥ አመጣላሁ ብሎ ከቅንጅት ቡድን አፈንግጦ ፍርክስክሱን አወጣው። 

“ፕሮፌሰር መስፍን ሕንድ አገር “የማጅራት ኦፔረሺን” ለማድረግ ስለምሄድ ድንገት ሞቼ ያልተናገርኩት ምስጢር ይዤ አንዳልሞት ይህንን ልበል አሉ። “የቅንጅት መሪዎች ልደቱና ኢንጂኔር ሃይሉ እርስ በርስ ለሥልጣን ሽምያ ገብተው በዲክታተርነት ባሕሪያቸው ቅንጅትን አወከው ያፈረሱት እነሱ ናቸው” ብለው ልደቱንም በቪ ኦ ኤ አማርኛ መድረክ መክሰሳቸውን ታስታውሳላችሁ።

ልደቱ ማህተም ስጥ አልሰጥም ክርክር ተገጥሞ ቅንጅት በውስጣዊና በውጫዊ ትርምስ ተፍረክርኮ ልደቱ ባንቱስታን አቀንቃኝ ፓርላማ ውስጥ ገብቶ ለውጥ አመጣለሁ ብሎ “ሦስተኛው መንገድ” በሚለው የፖለቲካ መስመር ውስጥ እየተቃኘ ፓርላማ ውስጥ ገባ። የደቡብ አፍሪካው “እሰቲቭ ቢኮ” ባንቱስታን አስተዳደር ተቀበለን ለውጥ እናመጣለን ያሉ ጥቁር አፍረቃ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ለይ ሁለት እይታ ነበረው። ሁለቱም የተቃዋሚዎቹ የባንቲስታን አስተዳዳር ተቀባዮች “ትብብርና ከነጮቹ ጋር መደማመጥ” በጣም አደገኛ መስመሮች ናቸው ይላቸዋል።

ልጥቀስ፡

<< With this background in mind it therefore became necessary for us black people to restate in very strong terms the case against the bantustan idea. There are two views regarding bantustans. The first one is that of total acceptance with the hope that any demands made by the blacks thorough peaceful negotiation will lead to granting further concession by the white power structure placement. The second is that as a strategy the Bantustan philosophy can be exploited towards attainment of our overall goals. Both views are dangerous short-sighted >> ይላል።

"… ስለዚህ እኛ ጥቁሮች በባንቱስታን አስተዳዳር ላይ ያለውን አቋማችን በመንኛውም መልኩ በጠነከረ መሰረት ላይ እንደገና የመቃወም አስፈላጊነቱነታችንን ማትኮር ያስፈልጋል። ባንቱስታን በተመለከት የተሰጡ ሁለት አመለካከቶች አሉ። የመጀመሪያው ዕይታ የባንቱስታን ራስ ገዝ አስተዳዳር  ሙሉ በሙሉ መቀበል ሰላመዊ የሰለጠነ የድርድር ቅብብሎሽ ሆኖ እንዲታይና ከዚያ ወዲያ የሚመጣ ድረድር በጥቁሮች ጥልቅ ሰላማዊ ድርድር የሚቀርብ ማንኛውም ጥያቄ በነጮች የስልጣን መዋቅር ላይ ተጨማሪ /የጥቁሮች ጥያቄ/ መልስ ላመስገኘት ስምምነት እንደሚያስገኝ አጋጣሚ ዕደል ነው ብሎ የሚያምን የተስፈኛ ዕይታ ሲሆን። ሁለተኛው እንደ ስትራቴጂ የባንቱስታን ፍልስፍና የሚከፍተውን ዕድል በመመዝመዝ ገርበብ ያለውን በር ተጠቅሞ አጠቃላይ ግቦቻችንን ለማሳካት ዕድል ይከፍታል የሚል ነው። ሁለቱም አመለካከቶች አደገኛ የሆኑ ሩቅ የማያይ ያስተሳሰብ ዕጥረት የጋረዳቸው አቋሞች ናቸው። ስለዚህም ይልና ቢኮ  << The bantustan theory was designed precisely to prevent us from getting what we want. After all as one writer once said, ‘there is no way of stopping fools from dedicating themselves to useless causes’>>

<< የባንቱስታን ቲዎሪ በትክክል የተነደፈው የምንፈልገውን እንዳናገኝ የተዋቀረ ተንኮለኛ አሰናካይ ጥበብ ነው።  ደግሞም አንድ ጸሐፊ በአንድ ወቅት እንደተናገረው ‘ሞኞች ራሳቸውን ለማይጠቅም ነገር መስዋዕት ከማድረግ የሚያግዳቸው ነገር የለም’>> እንዳለው እኛም መስመራቸውን ለማይረባ ስርዓት ተስፋ ከማድረግ እንዲቆጠቡ ከመምከር አልፈን የምንለው ነገር አይኖርም። ይላል ቢቶ። እኛም ልደቱን የመክረነው ወቅት በዚህ መንገድ ነበር።

ያ እንደዚያ ሆኖ ልደቱ ለወያኔ “ለስላሳ አንጀት” አለው እያሉ ብዙ ሰዎች ያሙታል። ለለ ለስላሳነቱም ምንጩ ለወያኔ ያደረ ሰላይ ስለነበረ ነው ይላሉ። ማስረጃ ሲባል ደግሞ ወያኔ ያስታጠቀው ሽጉጥ እንደነበር በቅርቡ የባንሱስታው አዲሱ “የተረኞች መሪ” አብይ አሕመድ በግፍ አስሮት በነበረበት ወቅት መኖርያ ቤቱ ሲፈተሽ የተገኘውን የመንግሥት ታርጋ ያለው ሽጉጥ ራሱም ወያኔ እንዳስታጠቀው በፍርድ ቤት የታመነበት ሲሆን፤ እንዴት ታጠቀው ለሚለው ጥያቄ ደግሞ መልሱ “የወያኔ ደህንነት ለሕይወትህ መከላከያ ብሎ እንዳስታጠቀውና እንደተቀበለው አምኗል”። ይህ የሁላችንም ድንጋጤ ያስከተለ ክስተት ስንሰማ እውነትም ልደቱ በዚህ ደረጃ ከወያኔ ትጥቅ ከተሰጠው፤ የልደቱን ነብስ  አስጊ ወያኔ ሳይሆን ተቃዋሚው ክፍል እንደነበር አስገራሚ ታሪክ ሀኖ አግኝቼዋለሁ።

ይህን ለማጠናከር ደግሞ የወያኔ የአገር ውስጥ ደህንነት ክፍል ባለሥልጣን የነበሩት አቶ አያሌው መንገሻ “የሚባሉ ይመስሉኛል” ልደቱ የደህንነት ሰራተኛ እንደነበር አጋልጠዋል። በዚህ የሚታሙ ተቃዋሚዎች ልደቱ አያሌው ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚ መስለው ሰርገው የገቡ ለምሳሌ  “ሕዝቡ ያልቅስ ኣያልቅስ እኛ ኢዜማዎች የሰብአዊ ድርጅት ተቋም አይደለንም” በሚል ንግግሩ የታወቀው  ልደቱ አያሌው ከፓርላማ ሲወጣ እርሱን የተካው ብቸኛ የፓርላማ “ተቃዋሚ” ተብየው “ግርማ ሰይፉ” ጋዜጠኛ ቴድሮስ ፀጋዬ-ርዕዮት- ጋር ቀርቦ “ሰሞኑን አፈሳዎችና ጋዜጠኞች እስር በመንግሥት እየተፈፀመ ነው፤የእናንተ ፓርቲ “ኢዜማ” ስለዚህ ጉዳይ ምን` ይላል?” ብሎ ሲጠይቀው “እኛ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ አይደለንም” ሲል የተናገረ ግርማ ሰይፉም እንደ ልደቱ የደህንነት ሰራተኛ እንደነበረና ብዙ ሃብት እንዳካበተ እኚሁ አቶ አያሌው መንገሻ ይገልጻሉ።

በተጨማሪም የአብይ አሕመድ ካድሬው “ሥዩም ተሾመ” እንዲህ ይላል “በልደቱ የስለላ ስራተኛነት ምክንያት በሰራው ስራና የተጠቀመበት መደናገርያ ፖለቲካ ክብደት 15 አመት በአፈና ኖረናል!” ሲል ልደቱ የወያኔ ሰላይ እንደነበረ ይከሳል። ስለዚህ የልደቱ በወያኔ ሽጉጥ የመታጠቁ እውነታ እና የደህንነቱ ባለስልጣን የነበሩ ሰውየ ልደቱ ሰላይ እንደነበር “በግል አውቃለሁ” ብለው ያሉት ንግግር ስናገናዝብ እውነታነቱ ያመዘነ ነው ብንል አልተሳሳትንም።

ለማንኛውም የሕብር ራዲዮ አዘጋጅ ሁለቱም ዛሬ ውጭ አገር ስላሉ (ልደቱና አቶ አያሌው መንገሻ) ጠርቶ ቢያነጋግራቸው እውነታው ማወቅ እንችል ነበር፤ በዚህ አጋጣሚ ጥቆማየን ለሕብር ራዲዮ አቀርባለሁ።

ከዚህ ሌላ ያስገረመኝ ነገር ልደቱ ለትምህርት ስልጠና ወይም ለሌላ ጉዳይ  ወደ እንግሊዝ አገር ሄዶ ነበርና መለስ ዜናዊ ሲሞት አገር ውስጥ አልነበረም። “ድሬ ሚዲያ” ሲባል በነበረ አንድ ሚዲያ የአፓርታይዱና ጸረ አማራው መለስ ዜናዊ ሲሞት ልደቱን ቃለ መጥይ ቀድርጎለት ነበር። “ክቡር” እያለ መለስ ዜናዊን የሚያከብረው የድሬ ጋዜጠኛ እንዲህ ይለዋል “በክቡር ጠ/ሚኒሰትር ሕልፈተ ሞት በግልህ የተሰማህ ስሜት ምንድነው?” ሲለው ልደቱ እንዲህ ይላል

“ ኢትዮጵያ  አንድ ሰው አጥታለች!!” “መጽሐፌን አይተህ ከሆነ ተቃዋሚዎች እሳቸውን ከሚያይበት ዓይን መቀየር እንዳለበት መለወጥ እንዳለበት (እኔ ከተቃዋሚው) ለየት ባለ ዓይን ነበር የማያቸው” “ያኔ ብዙ ሰዎች እንደዚያ ብየ በመጻፌ ብዙ ሰዎች ደስ ያላለቸው እንደነሩ አውቃለሁ።ዛሬ (እኔ ያልኩትን) የኢትዮጵያ ሕዝብ በዚያ መልኩ እያሳየ ይመሰልኛል። በመሞታቸው አዝኛለሁ፡ ለቤተሰቦቻቸው፤ ለኢትዮጵያ መንግሥትም ‘ለኢትዮጵያ ሕዝብም’ መጽናናት እመኛለሁ። የፖለቲካ ልዩነታችን እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ ወቅት የማይታጡ ምናልባትም ለወደፊቱ ለሃገሪቱ በጎ ተግባር ለማበርከት ዕድሉ ይኖራቸው ነበር ብየ አስባለሁ።እና “ኢትዮጵያ አንድ ሰው አጥታለች ብየ አምናለሁ!” ከፓርላማ ውጭ እኔና እሳቸው በጋለ ስሜት ስንከራከር እንደነበር እና ከዚያ መድረክ ውጭ በአካል ስታገኛቸው “ሰውነታቸውን/ (ሰብዕናቸውን) የምታየው ያኔ ነው”። እና ምናልባትም እሳቸውን የምናይበትን ዓይን ቀደም ብሎ ቢለወጥ ኖሮ የአገሪቱን ችግር ሳይሆን የመፍትሔ አካልም አድርገን አይተናቸው ቢሆን ኖሮ ‘ተገቢውን ዕውቅና እና ምስጋና’ ሰጥተናቸው ቢሆን ኖሮ ምናልባት አሁን ከሰሩት የተሻለ ይሰሩበት የነበረ ዕድል ይኖራቸው ነበር ብየ አምናለሁ።>> ይላል።

 አቶ ልደቱ እያለን ያለው ‘መለስ ዜናዊ’ በአካል ስታገኘው እጅግ ሰብአዊ ነው፤ ችግር አምጪ ሳይሆን መፍትሔ አመንጪ አድርጋችሁ ብታዩት ኖሮ ተገቢውን “ዕውቅና እና ምስጋና ስላልቸራችሁት” ዕንቅፋት ስለሆናችሁበት እንጂ ለኢትዮጵያ ከአፓርታይድ ባንቱስታ አስተዳዳር ውጭ የተሻለ መፍትሔ ያመጣ ነበር እያለ እኛን ለመለስ/ለወያኔ/ ኢትዮጵያዊ ተክለሰውነት ያለመኖርና ያለመሻሻል “ዕንቅፋት እየሆንበት” እንደሆነ እኛን አምርሮ ይወቅሳል። ወያኔነት ከዚህ ወዲያ ካለ ንገሩኝ ወደ ማለት የገፋኝ ይመስለኛል የልደቱ አስገራሚ ወቀሳ።

አሁን፤ አሁን ልደቱን ስመዝነው በልደቱ የነበረኝ እይታ የነበረኝ ግምት እየራቀ ከፖለቲካው እጅግ እየተገፈተረ እየመጣ ይመስለኛል በተለይ እርሱ ከተወለደበት አማራ ማሕበረሰብ።

በመቀጠል ልደቱ በዛው ቃለ መጠይቅ እንዲህ ይላል፡-

“ የዓላማቸው ጽናት ማንም ሰው ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባው አይደለም።ላመኑበት ዓላማ ሁለመናቸው የሚሰጡ ሰው ናቸው። ይህ የሚያስቀና ነው። በሌላ በኩል በልማቱ መስክ የሰርዋቸው ቀላል የሚባሉ አይደሉም።በአህጉራዊ መድረክ ኢትዮጵያ ተቀባይነት እንዲኖራት የበለጠ እንዲያድግ አድርገዋል። በሌላ በኩል ትንንሽ በሰብአዊነት በዲሞክራሲ ያለው ጉድለት እንደተጠበቀ ሆኖ እነዚህ በጎ ጉዳዮች ላይ የሰርዋቸው ጠቅመዋል ብየ ነው የማምነው።” ሲል ለ27 አመት የተካሄደው የድምበርና የባሕር መዝጋት ሴራ፤ የተካሄደው ከባድ መድልዎ፤ ዘረፋ፤ የዘር ጭፍጨፋና ድብደባ፤ ከባድ የሰብአዊ ጥሰቶችን “ትንንሽ ጉድለቶች” በሚል ቃል ይገልጻቸዋል። ትዝብቱ ለናንተ ልተው። ልደቱ መለስ ዜናዊን የሚያሞካሽበት ቃላት ያጥረዋል!

እንዲህም ይላል፤-

<< በነበሩኝ አጋጣሚዎች (የታዘብኳቸው)የአመራር ብቃታቸው ቀላል የማይባሉ ሰው እንደነበሩ፤ ፖለቲካ በደምብ የሚያውቁ ሰው እንደሆኑ አምናለሁ። (ጠቅላይ ምኒስትሩ- ፖለቲካውን) እኛ በምናምንበት እና በምናይበት መልኩ ሆደ ሰፊ ሆነው ሰፋ ያለ መግባባት ፈጥረው ሁሉም ፓርቲ በዚያው ጭምር ጉዳይ ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ሳይችሉ ቀርተዋል ብየ አምናለሁ።…. ሕዝቡ በዚህ ደረጃ ወጥቶ የፖለቲካ እምነታቸውን የሚደግፋቸውም የማይደግፋቸውም ሓዘኑን እየገለጸ ያለው ያለምክንያት አይደለም። ጥሩ ነገር የሰሩ ስለሆኑ ነው ብየ አምናለሁ። …ኢሕአዴግን የምናይበት ዓይን መቀየር አለበት።” እያለ በኢትዮጵያ ምድር ታይቶም ተሰምቶም የማናውቀው “አፓርታይድ” ሥርዓት ያሰፈነ ወያኔ/ኢሕዳግ በአፓርታይድነት ዓይን ማየት ትታችሁ የልደቱን ዓይነት “ሽጉጥ” ለመታጠቅ ኢሕዴግ የምታዩበትን ዓይን መለወጥ አለባችሁ እያለን ነው።

አከታትሎም “ኢሕአዴግን የምናይበት ዓይን መቀየር አለበት” ስላልን ብዙ ዋጋ ከፍለናል” ይላል ልደቱ። የቀጠለው ብዙ ያስከፈለው የልደቱ ፖለቲካ ኪሳራ ዛሬም ከአመት አመት እየባሰበት እንጂ እተሻለ እንዳልመጣ ብዙ አከራካሪ አቋሞቹን መጥቀስ ይቻላል። በቅርቡ እኛ አማራዎች እያለ ሲያጭበረብር የነበረ “ፈረንጅ” የሚመስል መልክ ያለው የወያኔ የትግራይ ሰው ልደቱን ጋብዞ “ወያኔ ጸረ አማራ ማኒፌስቶ ጽፎ ያውቃል ወይ?” ብሎ ሲጠይቀው ልደቱ “የሚባለው ማኒፌስቶ” አንብቤው አላውቅም አላየሁም ሲል ልደቱ ትንታግ ፖለቲከኛው ልደቱ የወያኔን ጸረ አማራ ማኒፌሰቶ አላየም ብሎ ማመን እጅግ ይከብዳል።  

ሰሞኑን አነጋጋሪ ከሆነው አንዱ በቅርቡ አውስትራሊያ የሚገኘው “ደደቢት ሚዲያ” ከተባለው አደገኛ የወያኔ ጸረ አማራ ክንፍና ትምክሕተኛ የትግሬ ፋሺሰዝም አቀንቃኝ “ቆዛሚ” ሚዲያ ሰሞኑን ልደቱን ጋብዞት ነበር፤ ልደቱ በዛው በሳላ የክርክር ችሎታው የደደቢት አዘጋጁ መሸከም የማይችለው የፖለቲካ ትምህርት ያስተማረው ቢሆንም በዛው ላይ ልደቱ የተነተናቸው አንዳንድ ነገሮች እርማት የሚያስፈልጋቸው ያለኳቸውን ንግግሮቹን በክፍል ሁለት አቀርባለሁ።

ሕዝብ እንዲወያይበት ጽሑፉን ተቀባበሉት።

ክፍል ሁለት ይቀጥላል…

ጌታቸው ረዳ  (Ethiopian Semay) 1/3/2020