Monday, December 19, 2011

አክራሪ እስልምና እና የሚዲያዎች አዘጋገብ ባሕሪ በኢትዮጵያ





 

አክራሪ እስልምና እና የሚዲያዎች አዘጋገብ ባሕሪ በኢትዮጵያ
ታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)

ትጉ እንጂ ስለ ስማችሁ መጥፋት አታስቡ! (የሳምንቱ የዚህ ዝግጅት ጥቅስ)

የአገራችን ሚዲያዎችም ነገሩ በውል ሳያጤኑና በበቂ ሳይረዱ በአክራሪ እስልምናው ወጥመድ ውስጥ ተዘፈቁ።በዚህም ለእነርሱ መብት የሚታገሉ ወይም ክብር የሚሰጡ መሆናቸውን ለመግለጽ ሲጣደፉ በሌሎቹ ፕሮፓጋንዳ ውስጥ ወድቀው የግፍ ተባባሪዎች ሆኑ’   ከዚህ ዓምድ የቀረበው ትችት የተቀነጨበ።

በዚህ ዓምድ የሚቀርበው ትችት ሰሞኑን አክራሪ እስላሞች በኢትዮጵያ ውስጥ ያደረሱት በኦርቶዶክስ እና በጠቅላላ በክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ የደረሰ እና ለበርካታ ዓመታት የደረሰው ጥቃት አብዛኛዎቹ ሚዲያዎች ለብዙ ዓመታት አውቀውም ሳያውቁም ለአክራሪው እስላም ትንኰሳ የዜና እና የፖለቲካ ሽፋን በመስጠት ያበረከቱት ድርሻ እንመለከታለን።
ጽሑፉ  ተገኘው ምሬታቸው ከገለጹ አንድ ድያቆን ሲሆኑ - ድረ ገጼ ፒዲኤፍ መቀበል ስለማይችል በዎርድ ፎርማት እራሴው እንደገና በመጻፍ አቅርቤዋለሁ። ትችቱን  ለላኩልኝ ከልብ አመሰግናለሁ።
በትችቱ ላይ አንዳንድ ነገሮች እርምት አድረጌአለሁ/ወይንም ላለማስረዘም ብዙ ሐተታ የያዙ ገጾችን ዘልያለሁ።  የትችቱ ዘገባ “ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉ” /ማቴ.፳፮፶፪/ የሚል ነው።
(“ወነገረኒ ዓዲ በእንተ ምጽአተ እስላም ወይበለነ ናሁ ይበጽሕ ጊዜሁ ከመ ኵሉ ዘይትቀትለክሙ ኢመስሎ ከመ ዘመሥዋዕረ ያበውእ ለእግዚአብሔር፣” (“ዳግመኛም ስለ እስልምና መምጣት ነግሮናል፣ እናንተን የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንዳቀረበ የሚመሰልበት ጊዜ ይደርሳል፣ ብሎናልና።”) አንቀጸ አሚን
የህን የወንጌል ቃል ጠቅሰው ስለ እስላም እንደተነገረ ያስረዱት አባ እንባቆም መጀመሪያ በእስላም ሃይማኖት የነበሩ ሰው ናቸው። አባ ዕንባቆም በትውልድ የመናዊ ሲሆኑ ቁርዓንን ሲመረምሩ የተነገረውን ይዘው አብዝተው በመጸለይና እውነቱን ግለጽልኝ በማለት ሱባ ሲገቡ ጌታችን እውነቱን ገልጾላቸው ወደ ክርስትና የተመለሱ ሰው ናቸው። አባ ዕንባቆም ወደ ክርስትና ሲመለሱ እንደተለመደው ሁሉ አክራሪ እስላሞች ሊገድሏቸው ተነሡ።
በእሳቸው ክርስትያን መሆን ምክንያትም ብዙ አብያተ ክርስትያናትን ያቃጠሉ ፤ክርስትያኖችንም ያሳድዱ ጀመር። አባ ዕንባቆምም ከአክራሪዎቹ እየሸሹ ነገር ግን ከዚያው ከቁርዓን እየጠቀሱ ክርከራቸውን በጽሑፍ ይልኩላቸው ጀመር። በዚህ ወቅት እርሳቸውን አሳድዶ ለመያዝ የተላከ አንድ የአክራሪ እስላም የጦር እዝማች እስኪ የምትለውን በደንብ አስረዳኝ፤ ከዚህ በላ እኔ ቤተ ክርስቲያንም አላቃጥልም፤ ክርስትያኖችንም አልገድልም፤ ሲላቸው ለእርሱ አንድ መጽሐፍ አዘጋጅተው ላኩለት፤ “አንቀጸ አሚን”ን።
ከዚህ መጽሐፍ በመጥቀስ የምንነሣው ክርስትና እንኳንስ የኖሩበትን የተለወጡትንም ሰይፍ ከማንሣትና በሰይፍ ከማጥቃት ኅሊና መልሶ እንዴት ሰላማዊ እንደሚደረግ ለማሳየት ነው። ራሳቸው አባ ዕንባቆምም ወደ ክርስትና ከተመለሱ በላ ሲጽፉለት “ኦ እማም እምይእዜሰ እወስአከ በቃለ ትሕትና በከመ አዘዘኒ መጽሐፈ እምነትየ፦(ኢማም ሆይ ከእንግዲህስ በላ የምመልስልህ የሃይማኖቴ መጽሐፍ እንዳዘዘኝ በቃለ ትሕትና ነው’) ይላሉ።
በዚሁ መሠረት ክርስትና ቀማኛውን መጽዋች፤ዓማፂውን አገልጋይ፤ዘማውን ድንግል ያደርገ፤…የትሕትና እና የፍቅር ሃይማኖት ነው። አባ ዕንባቆም ከሀገራቸው ከየመን ሸሽተው ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በተለያዩ ገዳማት ተዟዙረው የቤተ ክርስትያኒቱን ትምህርት ልቅም አድርገው የተማሩ እና በምንኩስና የኖሩ በመጨረሻም ለደብረ ሊባኖስ ገዳም አበምኔትነት/እጨጌነት/ የተመረጡ የበቁ ሰው ነበሩ። እስካሁንም የሚታወቁት እጨጌ ዕንባቆም በመባል ነው።
 ኢጨጌው ታሪክ ለመግቢያነት ቀንጨብ አድርገን ያየነው ክርስትና መርሑና አስተምህሮው ምን እንደሆነ በተግባር ከለወጣቸው ሰዎች ለማሳየት ብቻ አይደለም። ይልቁንም በየዘመኑ የነበሩ አባቶቻችን በየዘመናቸው ከአክራሪ እስላሞች የደረሰባቸውን የግፍና መከራ በመጠቆም ወደ ዘመናችን የአክራሪዎች ትንኰሳ ለመግባት ነው።
የአክራሪ እስላሞች ትንኰሳ በዘመናችን
በዚህ ጽሑፍ ትንኮሳውን በሦስት ደረጃ ከፍለን እንመከተዋለን።
ደረጃ አንድ
በኢትዮጵያ የአክራሪ እስልምናው የ፲፱፻፹ዎቹ እንቅስቃሴ ፖለቲካዊ ጥላውን የዘረጋ፤ ስውር ነበር ማለት ይቻላል። “ቀደም ባሉት ዘመናት የነበሩት የኢትዮጵያ ነገሥታት የእስልምና ሃይማኖትን ጨቁናዋል”፤ “እስላሞች የሚገባቸውን ቦታ አላገኙም”፤…የመሳሰሉትን ደጋግመው በማሰማት ለእስላሞች መብት የቆመ ይመስል ነበር። ይሁን እንጂ ዓላማውና እንቅስቃሴው እንደሚያሰማው ድምፅ ቦታዬን ላግኝ ብቻ  አልነበረም። ይህን ለማየት ባሳለፍናቸው ዘመናት የፈጸማቸውን ድርጊቶች መቃኘት ያስፈልጋል።
ብዙዎቻችን ባልተረዳንበት ጊዜ አክራሪዎች በኦሮሚያ እና በደቡብ ባሉ አንዳንድ አካባቢዎች ክርስቲያኖቹን ለይተው “ነፍጠኞች” በማለት ነገራቸውን መደባዊ ፖለቲካ በማስመሰል ብዙ በደል አድርሰዋል።በተለይ በጅማ እና  በኢሊባቡር አካባቢ ክረስትያን ሆኖ መገኘት “ነፍጠኛ” ለመባል ቀዳሚ ምስክር የሆነ እስኪመስል ድረስ ፍጹም ድሆች እንኳ ሳይቀሩ በክርስትናቸው ብቻ ተገፍተው ነበር። አክራሪዎች ይህ የማስመሰል ሒደታቸው እንዳልተነቃበት ሲያስተውሉ ነበር አካባቢውን ሙሉ በሙሉ የእስላማዊ ነፃ አካባቢውን ሙሉ በሙሉ የ እስላማዊ ነፃ መሬት ብቻ ለማድረግ በነበራቸው ጽኑ ፍላጐት ሰይፋቸውን ይዘው የወጡት።
በሓረር ገለምሶ፤ በአርሲ የተለያዩ ቦታዎች ያየነው የ፲፱፻፹ዎቹ (የ1980ዎቹ) አሰቃቂ ግፍ ፖለቲካዊ ርእዮተ ዓለምን ተገን ያደረገ የአክራሪዎቹ ዘመቻ መሆኑን አሁን መገንዘብ ይቻላል። የአክራሪ እስልምናው አራማጆች ይህም ተገልጦ ሳይነገርባቸው ሲቀር እንደገና ቀስ እያሉ ወደ ባሱ የድፍረት ሥራዎች ተሸጋገሩ። በተለያዩ ቦታዎች አብያተ ክርሲያናትን ማቃጠል፤ካህናትን ማሠርና መደብደብ፤አልፎ አልፎም በስውር መግደል፤ክረስቲያን ሴቶችን አስገድዶ መድፈር፤ካህናትን ሻሽ እንዳይጠመጥሙ የክርስትና ምልክት እናዳይዙ መከልከል ዋና ዋናዎቹ መገለጫዎቻቸው እየሆኑ መጡ። እነዚህ ዘገምተኛ ጥቃቶች ሲያደርጉ የተለየ ትኩረት አልተደረገም። መንግሥትም ምንም ትኩረት ወይንም እርምጃ አላደረገበትም።
ደረጃ ሁለት
አክራሪ እስልምናው ቀደም ብለን የገለጽነውን ሁሉ እያደረገ ዝም  በተባለ ጊዜ ወደ ሁለተኛ ትንኰሳ ተሸጋገረ።ሁለተኛው ደረጃ “እዚያ ማዶ ጠብ አድርሰኝ” ዓይነት መርሕን ይዞ የተነሣ ነበር። የሕዝቡ በውል ያለመረዳት ያስተዋለው የአክራሪ እስልምና እንቅስቃሴ ምክንያት እየፈጠረ ግጭት ማስነሳቱን ጀመረ። እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ከዩኒቨርሲቲ የተባረረው የሐዋሳውን የተማሪው ለዚህ አብነት መጥቀስ ይቻላል።
በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ ከነበሩት አንዱን ባለ ዕድል ከላው በመከተል ቁርዓን ቀድዶ ለመጸዳጃነት ተጠቅሟል የሚል ዓመጽ አቀጣጠሉ። ይህን የአክራሪዎች ወጥመድ በጊዜው ማንም አልተገነዘበም ነበር።በቤቱ ወይንም በዶርሙ ምንም ዓይነት ዓረባዊ ጽሑፍ የማግኘት ዕድል የሌለውን አንድ ክርስቲያን መጸዳጃ ቤት ገብተው ሲጠቀምበት ያላዩትን፤በርግጥ የተባለው የተቀደደ የቁርዓን ብጣሽ ሲጠቀምበት ያላዩትን በእርግጥ የተባለው የተቀደደ የቁርዓን ብጣሽ ለዚያ አገልግሎት ውሎ ከሆነ እንኳ ከእርሱ በፊት የተጠቀሙ ሰዎች ይሁን የእርሱ ሳይጣራ ግፊቱን አጧጧፉት።
ከውስጥና ከውጭ በሚዲያ ለማስተጋባት ተዘጋጅቶ የነበረው የአክራሪ እስልምና ሠራዊት ሁሉ “አሁንም እስላም ይገፋል/ተበድሏል” እያለ ይጮኽ ጀመረ። የአገራችን ሚዲያዎችም ነገሩ በውል ሳያጤኑና በበቂ ሳይረዱ በአክራሪ እስልምናው ወጥመድ ውስጥ ተዘፈቁ።በዚህም ለእነርሱ መብት የሚታገሉ ወይም ክብር የሚሰጡ መሆናቸውን ለመግለጽ ሲጣደፉ በሌሎቹ ፕሮፓጋንዳ ውስጥ ወድቀው የግፍ ተባባሪዎች ሆኑ።
ከላይ የጠቀስኩት ምሳሌ እውነቱን ለመናገር ሰውየው መጠቀሙን ቀርቶ ከሳሾቹ አክራሪዎቹ ወረቀቱን ከመጸዳጃ ቤት ማምጣታቸውን ለማረጋገጥ እንኳ የጣረ አልነበረም። ጤናማ ኣእምሮ ላለው ሰው መጸዳጃ ቤት ውስጥ ብዙ ሺሕ ተማሪዎች ባሉበት ዩቢቨርሲቲ ውስጥ ቀርቶ በሌላም ቦታ ቢሆን ላይንሳዊ በሆነ  መንገድ የአሻራና ሌሎች ምርመራዎች እስካልተካሔዱ ድረስ ማን ምን እንደተጠቀመ ማወቅ አይቻልም። የተከሰሰው ሰው እንደወጣ ስለገባን ነው ቢሉ እንኳ ከእርሱ በፊት ያ ወረቀት ጥቅም ላይ ላለመዋሉ ማረጋገጫ የስፈልጋል። ነገር ግን ሁኔታው ሆነ ተብሎ የተቀነባበረ ስለነበረ በየቦታው አንድ ጊዜ አክራሪው ሁሉ ጮኸ። በዚህ ሚዲያዎችም ሰለባቸው ውስጥ ጣሉት። በእርግጥ ሚዲያው በእነሱ ሰለባ የወደቀው በዚህ ብቻ አልነበረም።
ሁለት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ሕዘብ ይኖርባታል በተባለችው አዲስ አበባ ፲፭ በመቶው ፬፻፭  ሺሕ ብቻ የሚሆኑትን ግማሽ ሚሊዮን እንኳን የማይሆኑትን የእስልምና አማኞች ወገኖቻችን አንድ ጊዜ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ በማለት በአራት እያባዛ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከሁለት ሚሊዮን በላይ በማለት በአምስት እያባዛ ሲናገር እናዳምጣለን። ሚዲያውም ያንኑ በማስተጋባት ዘው ብሎ በመግባት በዚህ ጉዳይ እዚህ ለመዘርዘር የማያስፈልግ ብዙ ትዝብት ላይ የ የሚጥሉ ነገሮችን አሳይቶናል።
የሐዋሳውን ተማሪ ጉዳይ እና የቁጥራቸውን ጉዳይ እንደ ምሳሌ አነሳነው እንጂ አክራሪዎቹ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ያስነሧቸው ነውጦችና በአስተዳደርም ላይ የፈጠሯቸው ጫናዎች እጅግ ብዙዎች ናቸው። ሚዲያው ለዚህ ብዙ መጥፎ አስተዋጽኦ አድርጓል። በዚህ ጩሆታቸው እየተገፋፉ ያለ አግባብ ቦታ የሰጡ፤የክርስቲያኖቹን ያሠሩ ያፈናቀሉ ብዙ የመንግሥት እስፈጻሚዎችም ነበሩ። ደመራ ሲደመር ወይንም የጥምቀት በዓል ሲከናወን ድንጋይ በመወርወር፤ሆ በማለት ጩኸት ሲያስነሳ፤ሚዲያው ተቀብሎ ወጣቱ አመጽ አስነሳ እያሉ የአክራሪ ሴራ መሆናቸወን ሳያጣሩ ወደ ፖለቲካ ይዘት በመለወጥ ይዘግባሉ። እረ ስንቱ።
ሦስተኛው ደረጃ፤-
አክራሪዎቹ ትንኮሳቸው ግቡን እየመታ ዕቅዳቸው እያሳካ ሲመጣ ደረጃ በደረጃ ቀጠሉበት እንጂ አላቆሙም። በዚህ ጽሑፍ በሦስተኛ ደረጃ ያስቀመጥነው ትንኰሳቸው ገን እጅግ አብዝቶ መረን የለቀቀና የክርስቲያኑንም ትዕግስት በከፍተኛ ደረጃ እየተፈታተነ ያለ ነው።ለዚህ ማሳያ የሚሆን የቅርብ ጊዜ ትንኮሳዎች ጥቂቶቹን እናቅርብ። ይኸኛውን በደንብ ለመረዳት እንዲቻል በአምስት ከፍለን እንመለከተዋለን።
. የመስጊድ መሥሪያ ቦታዎች፦
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እጅግ ባልተለመደና በሚገርም ሁኔታ የአክራሪዎች ጤናማ ያልሆነ የመስጊድ ግንባታ እንቅስቃሴ ይታያል።”ጤናማ ያልሆነ” የምንለውም ቦታው አምልኮን ለመፈጸም ከመጠቀም ባለፈ ሁኔታ ነገር መፈለግ ስለሚታይበት ነው።ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አክራሪዎች ለመስጊድ መሥሪያነት የሚጠይቋቸው ቦታዎች ሆነ ብለው ክርስቲያኑን የሚያነሳሣሱ እየሆኑ ነው። አንደኛ የመስቀል ደመራ ቦታዎችን የጥምቀት ባሕር ቦታዎችን፤ከዚያም አልፎ ቤተክርስቲያን ተጠግተው ወይም በዋናው መግቢያ ፊት ለመሥራት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ። በደሴ ሀገረ ስብከት ፊት ለፊት ለመሥራት የጠየቁት፤ በጎን ዳር በኣታ ለማርያም  ቤተ ክርስትያን ጥምቀተ ባሕር ፊት ለፊት እየሰሩት ያለው በአፋር ዱብቲ በተ ክርስትያኒቱ ፊት ለፊት ለመሥራት የሚደረውን ጥረት እንደ ምሳሌ ለመጥቀስ ይቻላል።
በአዲስ አበባ የአየር ጤና ኪዳነ ምሕረት ጥምቀተ ባሕርን ክፍሎ ወስዶ የተሠራ ወይንም መስጊድ እና ያደረሰውን ግጭት እዚህ ላይ ይታወሳል።
ለትንኮሳ ሳሆን ብሎ የሚደረግ መሆኑን የምናውቀው ደግሞ አንዳንዶቹን ለመኖሪያ ወይም ለንግድ ቤትነት ከተቀበሉና ቤቱንም ከሠሩ በላ ቀስ ብለው የመስጊድ ምልክት የሆነውን  ሾጣጣ ነገር ምልክት ያወጣሉ የጨረቃውንም ምልክት ይሰቅላሉ። ይህን ካደረጉ በላ ቦታውን ለጠየቃችሀት አገልግሎት አውሉ ተብለው ሲጠየቁ በተለመደ የነቅተህ ጠብቅ እና የተባብሮ መጮኽ ዘዴ “እስልምና ተደፈረ…” በማለት ባንድ ጊዜ ይጮኻሉ። ሚዲያወም አብሮ ይጨፍራል፤ ጩኸታቸወን በገነነ መልኩ ያስተጋባዋል።
በመንግሥት በኩል ያሉ ለዘብተኞችና ይህን ይህን ዘዴ ያላወቁ አስፈጻሚዎችም ጩኾታቸውን በመፍራት ይረዷቸዋል። የህንን በምሳሌ ጠቀስናቸው እንጂ ባለፉት ሃያ ዓመታት የተፈጸሙ ትምኮሳዎች  እና የአስፈጻሚዎቻቸው ትብብር በርካታዎች ናቸው።
ሰላማዊ የእስልምና ተከታይ ወንድሞቻችንማ እስካሁን ድረስ መስጊድ ሲሠሩ ኖሮዋል። አገራቸው ነውና ለወደፊትም ይሠራሉ። ይሁን እንጂ “እስላም ተበደለ” የማስደንገጫ እና የማስፈራሪያ ደወል እየደወሉ ጩኾታቸውንም እንደ ገደል ማሚቶ የሚያስተጋቡላቸው ሚዲያዎች እና በዓለም ዓቀፍ ትስስራቸው (ፍንዳሜንታል ኔት ዎርክ)ስልት ሰለባ እየሆኑ ያልተገባ ሥራ መሥራት ግን ሊገታ ይገባል። የአንዱ ውድመት ላንዱ መሆኑን አና ሀገሪቱም የጋራችን መሆኗን መዘንጋት አይገባም።”)
 ከኢትዮጵያ ሰማይ አዘጋጅ፡ መደምደሚያ
ያገራችን ሚዲያዎች ብዙ ችግሮች እንዳላቸው አሌ ቢሉም ታሪክ የሚዘግበው ስለሆነ ብዙ ጉድለት እንዳላቸው አያጠያይቅም። የወቅቱ ስስነት በመመልከት ጊዜያዊ የፖለቲካ ጠቀሜታ ለማግኘት ከመጣር ይልቅ ለብዙ ዓመታት አክራሪ እስላም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ሥሩ የተንሰራፋ መሆኑን እና የተዘረጋው ሥርም ወደ አጋራችን በፍጥነት እየገባ መሆኑን በመዘንጋት አሸውርረው ወደ ሚያመለከቱት የጣት ቅሰራ ወደ አንድ ወገን ብቻ ሳይሆን ሃይማኖትን የፖለቲካ መጠቀሚያቸው በሚያደርጉት ግራ እና ቀኙ ሁለቱንም (መንግሥትም አክራሪው ሃይልም) በሃላፊነት መጠየቅ ይጠበቅባቸዋል።  
ሰፍቶ እና ተንሰራፍቶ የምናየው አገር በቀል ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ችግር መሆኑን ሚዲያዎች መርሳት የለባቸውም። እንደዚህ አድጎ እና አፍርቶ፤ ሰፍቶ ተንሠራፍቶ የምናየውን ነገር ሰላማዊ መፍትሔ ለማምጣት ምን ብናደርግ ይሻላል በሚለው በንነጋገር ነው የሚሻለው እንጂ ጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እና የማይገባ ድጋፍ ለማግኘት በኢትዮጵያ ውስጥ ከበባውን እያጠናከረ እና እያነጣጠረ የመጣው አክራሪ እስልምና እንዳለ እና እንቁላሉ አገር ውስጥ እየጣለ እና እየፈለፈለ እንዳለ እየታወቀ “እስላም ተበደለ”በሚል ሃይማኖትን ተገን አድርገው የጠነሰሱት ፖለቲካ በማፋጠን ሰላማዊ ሰዎች እየታረዱ፤ቤተርስትያናት፤ገዳማት እየተቃጠሉ ፤ አረጋውያን እና ህጻናት እያለቀሱ፤ሚዲያዎች አንዱን ወገን ብቻ በማሳጠት ግቡን የሳተ ሽፍንፍን ጨዋታ እራሰቸው ከመዘፈቅ መራቅ ይጠበቅባቸዋል። እንዲህ ያለው ጥቃት እና እንቅስቃሴ አንድ ሥርዓት ከተወገደ በላም ቢሆን የሚቀጥል እንጂ አሁን ተሸፋፍኖ በሁለተኛ ደረጃ የሚታየው ጠላት የተዳፈነው እሳት ነውና የሁለቱንም ተጠያቂ ሽብርተኞች ማለትም የወያኔው ሥርዓትና ሃይማኖትን ተገን በማድረግ ወንጀል፤ብጥብጥ እና ሁከት ለመፍጠር ገዳማትና ቀሳወስት የሚያቃጥሉ  አክራሪ የፖለቲካ ድርጅቶች ተጠያቂዎች እና አደገኞችም ስለሆኑ በግልጽ ሕዝቡ እንዲያውቅ እና ነቅቶ አንዲመራመር እና እንዲጠብቅ ራሱንም ከጥቃት እንዲከላከል ፤እስላሙና ክርስትያኑ ሕብረተሰብ ባንድነት የጋራ ጠላተቹን ነጥሎ ኣንዲያወቅ እንዲያመቸው ይረዳው ዘንድ ሚዲያው  በመንግሥት ብቻ ሳይሆን በፖለቲካ ድርጅት የተሰገሰጉ፤በውጭ አክራሪዎችም ጭምር የሚነዱ አክራሪ ድርጅቶችንም ማጋለጥ ይጠበቅባቸዋል። በየፓልቶኩ የሚነዙት የጥላቻ፤ የጎሳ እና አክራሪ የሃይማኖት ሰበካዎች ሚዲያዎች እየተከታተሉ ለሕዝብ በማስታወቅ ማጋለጥ አለባቸው እላለሁ። እኛ ሰዎች እውነትን ማጠፍ ይቻለን ይሆናል  መስበር ግን አይቻለንም! አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) getachre@aol.com



.