Saturday, May 2, 2020

ኦሮሞዎቹ ያበረከቱልን አዲሱ ሂትለር በኢትዮጵያ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay


ኦሮሞዎቹ ያበረከቱልን አዲሱ ሂትለር በኢትዮጵያ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay
የትግራይ ወያኔ ቡድን ገበያ ቀንቶት ከትግራይ ክ/ሃገር ከደደቢት በረሃ ገስግሶ ወደ መሃል አገር አዲስ አበባ በመግባት ከ1981 ዓ.ም ጀምሮ በረሃ ውስጥ ሲመራበት የነበረውን  “የብሔረተኛ-ፋሺዝም” መመሪያውን እውን በማድረግ ለ17 አመት ትግራይን ቀጥቅጦ፤ ለ26 አመት ደግሞ ኢትዮጵያን ቀጥቅጥ አድርጎ ገርፎ፤ የነበረውን ሁሉ እንዳልነበረ አድርጎ አሁን ላለንበት ውርደትና ሓዘን ዳርጎናል።

በዚህኛው ብሔረተኛ ቡድን ትምህርት ሰልጥኖ በስለላ ሥራ ተመድቦ ሕዝባችንን ከትግሬ ብሔረተኛ ፋሺስታዊ ቡድን ጋር  ወግኖ የወያኔ “ኩሊ” በመሆን ሕዝባችን  ለእስርና ለድብደባ ሲዳርግ ቆይቶ ከሁለት አመት በፊት ኦሮሞዎች ያበረከቱልንን ሥልጣን ዙፋን ላይ የወጣው ኮለኔል አብይ አሕመድ፤ የትግሬዎቹ ፋሺስት መሪ የነበረው የሟቹ የመለስ ዜናዊ  ባህሪና የአመራር ስልት በማስቀጠል ሕዝባችንን ባሰማራቸው ፖሊሶቹ በኩል “ሆን ብሎ” የሚቃወሙትን ተቃዋሚ መሪዎችን እና ግለሰቦችን እንዲሁም ሰላማዊ ዜጎችን ለዳግም ድብደባ፤እስር ዳርጎ ወጣቶቻችንን ወደ ከፋ ህይወት በመዳረግ ፍትሕ አልባነትን አስፍኗል።

 ምንም እንኳን ይህ ኮለኔል ዕልል ብሎ የተቀበለውን ሕዝብ ያስጨፈጨፈ፤ የካደ፤ በጣም ነውረኛ፤ ተንኮለኛ እና የከፋ ፋሺሰት መሆኑን ለሁለት አመት ሙሉ  ያስፀማቸው ወንጀሎችን በሚመለከት “የጣት ቅሰራ እና ጩኸት”  ለዓለም ሕብረተሰብ ያመላከቱ ተቆርቋሪ ዜጎች ቢኖሩም፤ ኮለኔሉ ወደ ሥልጣን ከመጣ ወዲህ በፖሊስ ሥራ ሰልጥነው ወደ ሥራ የመደባቸው አገልጋዮቹ ከእነዛኛዎቹ የ26 አመት የትግሬ  “ጎስታፖ” ፖሊሶች በከፋ መልኩ በእንሰሳነት ባሕሪ እየተመሩ ጭካኔ የተሞላበት የመብት ረገጣ እየፈፀሙ ነው።

የሚገርመው ነገር፤ የኮለኔሉ ደጋፊዎች የሕግ የበላይነትን በሚጥስ መልኩ የተለያዩ እጅግ ለጀሮ የሚቀፉ ድርጊቶች መፈጸማቸው እያዩም ቢሆን ስሜት አልባ ሆነዋል።

‘ኩሊ’ የምትለዋ የወዳጄ አምሳሉ ገብረኪዳን ቃል ልጠቀም እና ፤ ይህ የወያኔ “ኩሊ”  አምባገነን ነው ወይስ አይደለም” የሚል ክርክር ሳይሆን (የዚህ ኮለኔል አመጣጥ ወደ መጀመሪያው ታሪክ ላስታውሳችሁ እና) “አብይ አሕመድ ባይመረጥ ኖሮ ሁሉም ኦሮሞ በየቤቱ ጩቤ አዘጋጅቶ ሊወዳቅ ተዘጋጅቶ ነበር፤ አሁን ግን አብይን ወደ ሥልጣን ስለመጣ “ኡፎይ” ብለናል” ብለው የኦሮሞው አባገዳ መሪ “አቦ በየነ ሰንበቶ” የሚመራው የኦሮሞ ሽማግሌዎች ቡድን “ይግደላችሁ፤ያሰቃያችሁ” ብለው መርቀው የሰጡንን “የጂማው ኮለኔል” የዓድዋውን ተጋዳላይ መለስ ዜናዊ የተካ “አዲሱ አዶልፍ ሂትለር ነው”።

ይህንን ለማረጋገጥ የኮለኔሉ ፖሊሶች ምን ሥራ ላይ እንደተሰማሩ በሁለት አመት ውስጥ የፈጸምዋቸው ግፎችና የኩሊው ንግግሮቹ በየሚዲያው የተለጠፉትን የተለያዩ ‘ስዕለ-ድምጾችን’ አይታችሁ ፍረዱ።

የአሁኑን እና ያለፉትን የፖለቲካ ገጽታዎች ያለአንዳች ብልጭልጭ ማየት ለሚችሉ ሰዎች ፣ የማስጠንቀቂያ ምልክቶቹ ግልጽ ናቸው። የዜጎች መብት ለማፈን መለስ ዜናዊ መስርቶት የነበረው የስለላ መ/ቤት በሃላፊነት ተሰማርቶ “ያገለገለውን የወያኔን መንግስት ከሰብአዊ መብት አፈና ጋር ያደረበት ፍቅር ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የተዋሃደው የአፈና ባህል ዛሬ ሊለቀው አልቻለም ፡፡
በእርግጥ አብይ አሕመድ የትግሬዎቹና የኤርትራ ናዚያዊያን ስርዓት በጣም አድናቆትና አክብሮት ስላለው (መቀሌና አስመራ ሄዶ የተናገራቸውን ንግግሮቹን አድምጡ) ሥልጣኑን ከተቆጣጠረ በኋላም ቢሆን የወያኔ ግልገል ፋሺስት ፖሊሶችን፤ የፍርድቤት ባለሥልጣኖችን፤ሚኒስትሮችን፤ አምባሳደሮችን፤ ሲቪልና የደህንነት ሠራተኞችን በድብቅና በግልጽ እንዲያገለግሉት በማድረግ በዙርያው አስሰልፎ የነበረውን  “ፋሺስታዊ ፕሮቶኮሎቹን” እንደመመሪያው አስቀጠሎአቸዋል።

በዚህ መልክ መጠነኛ የሚያጃጅሉ ‘የገጽታ ቅባት’ በማድረግ የተረከበውን ሕግ እና ስርዓት ያለዉን አስተሳሰብ ተቀብሎ ፣ የከፉ የመብት ረገጣዎች ተግባራዊ አደረገ።

አንድ የታሪክ ምሁር እንደገለጹት ፣ “ሂትለር ተሸንፎ የጀርመን ጎስታፖና የናዚ ኤስ ኤስ የፖሊስ አባላት ወደ አሜሪካ እንዲገቡ ከተደረገ በሗላ ከ5 ዓመታት በኋላ የናዚ ፖሊሶች የ “ኤፍ. ቢ. አይ” ነት የምስክር ወረቀት ማረጋገጫ አግኝተዋል” አንዳሉት ሁሉ በአብይ አሕመድ መንግሥት ሥር ያሉት የፍትህ መዋቅሮች እና ፖሊሶችም ለ26 አመት ሕዝብን በጥይት ሲደበድቡና ዜጎችን ሲያስለቅሱ የነበሩ “አረሜ ፖሊሶች” በከፋ መልኩ ጭካኔአቸውን ያለምንም ተጠያቂነት መብት ተሰጥቶአቸዋል።

አሁንም ሥርዐቱ ውስጥ ያሉት እነዚህ የፍትህ አካላት ብዙዎቹ የአማራን ማሕበረሰብ ሲጨፈጭፉ የነበሩ ቢሆኑም፤ ከሥርዓቱ ‘የእልቂት ማሽን’  ጋር ያላቸው ትስስር እንደማናውቃቸው ለማድረግ አዳዲስ ካባዎችን በመደረብ በብዙ ስልት ማንነታቸውን ለመደበቅና ለመቅረጽ ተሞክረዋል (አብይ አሕመድ የስለላ/የጠለፋ/ ሓለፊ ሆኖ ሲሰራበት በነበረበት ወቅት የተለቀቁ የተክለ ሰውነት ቀረጻ በሚዲያ የተለቀቁትን የማታለያ ቪዲዮዎችን አትርሱ)፡፡

 በሚገርም እና የማታውቁት ሁኔታ አንድ ነገር ልንገራችሁ። በግልጽ የታወቁ የትግራይ ወያኔ ወንጀለኛችም አደጋ እንዳይደርስባቸው በሚል ስጋት ወደ መቀሌ ተግዘዋል።ይህ አብይ አሕመድን ጨምሮ በምክክር የተደረገ ስልት እንደሆነ አስምሩበት።

አብይ አሕመድ እንደልቡ ወደ መቀሌም ሆነ ወደ አክሱም ሁለቴና ሦስቴ ለመግባትና ለመውጣት ፈቃድ የሰጡት በወያኔዎች ፈቃድ መሆኑን እወቁ። ያ ባይሆን ኖሮ፤ አብይ ወደ መቀሌ የላካቸው ኮማንዶዎች አየር ማረፊያ እንደደረሱ አስረው እንደለቀቁዋቸው ሁሉ አብይን ቀፍድደው ማረፊያ ቤታቸው ያጉሩት ነበር። ስለዚህ መጀመሪያውኑ የሁለቱ የጋርዮሽ ስምምነት ሕዝቡ እስኪረጋጋ ድረስ ወደ መቀሌ ገለል እንዲሉ ባይስማሙ ኖሮ ወያኔዎች አብይን ወደ ትግራይ እንዲገባ አይፈቅዱለትም ነበር።አንዳንድ የዋሆች ወያኔዎች ወያኔ አቅም የላቸውም፤ተሸሽገዋል እያሉ የሚያወሩት ወሬ አንደኛውም የፖለቲካውን ሴራ አያውቁትም፤ወይንም አንዳንዴ በስሜት እንደምለው የወያኔ ጀሌዎችን ቅስም ለመስበር የምንለው አባባል ካልሆነ እውነታው ከላይ የጠቀስኩት ነው።

አንባቢዎቼ ማወቅ ያለባችሁ አብይ የሥልጣን ጥመኛ ስለሆነ “ሥልጣኔን አትንኩብኝ እኔም አልነካችሁም” በሚል ምስጢራዊ የጋራ ስምምነት ነው እነሱም ሆነ እርሱ በሰላም እየኖሩ ያሉት። የፋሺሰት ወያኔ ባህሪ የማያውቅ ሰው ብቻ ነው ወያኔ በሰላም ሥልጣን ይለቃል የሚል። ወያኔዎች ዛሬም የሥልጠን ተጋሪ ናቸው። የወያኔ ወኪሎቹ ዛሬም አብረው ከተቃዋሚዎች ጋር ሆነው እየተጋበዙ እንደማንኛቸውም ፓርቲ ውይይት እያደረጉ ነው። አባሎቹ በሚኒሰትር ደረጃና በወታደራዊ  ሹመት ውስጥ አሉ።

ለዚህም ነው አብይ አሕመድ ዛሬም በወየኔዎች መጽሐፍ እየተመራ ናዚያዊ ፖሊሶቹን በማሰማራት ዜጎችን በመደብደብ በመግደል እና በማሰር የናዚ ህዳሴ እያበሰረ ነው።
አንድ የቀርብ ምሳሌ ልስጣችሁ  - ፍርድቤት ያልቀረበ ወንጀል ያልፈጸመ፤ በወንጀል ያልተከሰሰና  ያልተፈረደበትን እስክንድር ነጋን አብይ አሕመድ ቤታቸውን የፈረሰባቸውን ዜጎች ለምን ቃለ መጠይቅ አደረግክላቸው ብለው የአብይ አሕመድ ፖሊሶች (ኩሊዎች) አንድ ቀን አስረውት ከለቀቁት በሗላ፤ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የግል ሞባይል ቴሌፎኑን በእግዝቢት አስቀርተው “የግል ምስጢሮችን በመበርብር ላይ ናቸው። እንደሰማችሁት እስክንደር ነጋም ስልኬን መልሱልኝ ብሎ ለዓለም እሪ እያለ ነው።የሰብኣዊ መብት ጠበቆችም ሁኔታውን ኮንነውታል።

የናዚ ጎስታፖዎች የጀርመን ዜጎችን የስልክ እና የግል ደብዳቤዎቻቸውን መፈተሽና መሰለል መብት እንደነበራቸው ሁሉ፤ የአብይ አሕመድ የፍትሕ አካላት እና ፖሊሶች የሰላማዊ ሰው የግል ሞበይል ቴሎፎንም ሆነ ኢመይልና የደብዳቤ ማሕደሮችን የመፈተሽ የመንጠቅ እና የመሰባበር መብት አላቸው።ለዚህም ነው “ኦሮሞዎች ያበረከቱልን አዲሱ ሂትለር በኢትዮጵያ” እናቶችና አረጋውያን በመራራ ዕንባ እያስለቀሰ ነው የምንለው።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (የኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)