Sunday, February 28, 2010

የልደቱ አያሌዉ ወያኔነት ለሚጠራጠሩ ማስረጃዉ እነሆ

የልደቱ አያሌዉ ወያኔነት ለሚጠራጠሩ ማስረጃዉ እነሆ

ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com

“የንግግር ችሎታ” ማለት “ዝግ ብሎ ቁም ነገሮችን በቀላሉ አስተባብሮ ማስረዳት” ይሁን ወይም “ቁም ነገር የለሽ ማራኪ ቃላቶችን ብቻ አቀነባብሮ እያቀላጠፉ መለፍለፍ”፡ብቻ ከሁለቱም አንዱ ምረጡ እና የንግግር ተሰጥኦ አለዉ ለሚባለልለት የኢደፓዉ ለልደቱ አያሌዉ መገለጫ ስጡት። ስለ ልደቱ ብዙ ብዙ ተብሎለታል፤አሰልቺ ይሆንብኛልና አልደግመዉም።ዛሬ ስለ ልደቱ ልጽፍ የተነሳሁበት ዋነኛዉ መነሻየ፤ ባለፈዉ ሳምንት የኢደፓ ድረገጽ ስጎበኝ ልዩ ዐቃቤ ሕግ የመጨረሻ ሪፖርቱን ሲያቀርብ ኢዴፓ “የነጭ ሽብርን” ጉዳይ አነሳ” (Tuesday, 09 February 2010 15:07) የሚል ዜና ባነበብኩ ጊዜ፤ የደርግ ባለስልጣኖችን “በቀየይ-ሽብር” የከሰሰዉ የወያኔ ልዩ ፍርድቤት “የዘር ማጥፋት ወንጀል” ፈጽመዋል ብሎ ክስ የመሰረተባቸዉ ሰዎች እንዴት እና በምን ሁኔታ የፍርዱን ሁኔታ እንዳከናወነዉ ሁላችንም የምናዉቀዉ ያሻንጉሊት ፍርድ ቤት እንደነበር ብናዉቅም፤ አንዳንዱ ለዓመታት አስሮ ያለ ምንም ጥያቄ የፈታቸዉ ሰዎች እንዳሉ እና ለዛም ይቅርታና ካሳ ሳይከፈላቸዉ ሕይቀታቸዉ አበላሽቶባቸዉ ለስቃይ እንደዳረጋቸዉ የሚታወቅ ነዉ።

ታዲያ እንዲህ ዓይነት ፍርደገምድል በታየበት የወያነ ትግራይ ታጋዬች የቂም መወጣጫ እና መለማመጃ እንዲሆን የቆመ የፍርድ ተቋም እንዴት ሲኮን ነዉ ምራቁን ያልዋጠ ኢደፓ የተባለዉ ቡድን “በጫካ ሕግ” የሚፈርዱ እንደ እነ “መድሕን” (ከሦስቱ ዳኞች አንዱ) የመሳሰሉ የህወሓት ማአካላዊ አባላት የሚካሄድ አሻንጉሊት ፍርድ ቤት የመዘገባቸዉ የክስ አመሰራረቶች ሂደትና ዉሳኔ ፍትህን ተከትሎ እንደተከናወነ በማስመሰል ለኢትዬጵያ ሕዝብ ለማደናገር የሞከረዉ? በጣም የሚገርመዉ ነገር ፣ የህንን አስመልክቶ በኢደፓ ስም በልደቱ አያሌዉ የተደመጠዉ አቤቱታ - “የተወሰኑ ቁጥር ያላቸዉ (አሻንጉሊቱ ፍርድቤት የሰጠዉ ቁጥር በመመርኮዝ) ታሳሪዎች ጠቅሶ ያለምንም ጥያቄ ለአመታት ታስረዉ በነፃ የተሰናበቱ እንዳሉ ፍርድ ቤቱ ያመነበትን ዘገባ እንደማስረጃ ይጠቅስና ፤ እንዲያ ያለ ፍትሕ የጎደለዉ የፍርድ ክንዋኔ ተገቢ እንዳልሆነ እና ፍረድቤቱ ተገቢዉን የቤት ሥራ ባለመስራቱ ከወቀሰ በሗላ፤ ፍርድቤቱን በወቀሰበት አንደበቱ (ገና ምራቁ ሳይደርቅ) ወዲያዉኑ በዛዉ ዓይነት የተበላሸዉ የፍርድ ሂደት “የነጭ ሽብር ወንጀለኞች” ብሎ ለሚከሳቸዉ ኢሕአፓዎችን “ለፍረድ እንዲቀርቡ ለምን አላደረጋችሁም?” በማለት አቤቱታዉና እና ወቀሳዉ አቅርቧል። እስኪ ለማንኛዉም ልደቱ ለጌቶቹ ያቀረበዉ አቤቱታ ላስነብባችሁ እና እዉነታዉ ራሳችሁ ድረሱበት። በ እግረመንገዳችን ግን በዛዉ አሻንጉሊት የፍርድ ሰገነት ላይ የተቀመጡት እነ መድሕን በየትኛዉ ሞራላቸዉ ሌላዉን መፍርድ እንደሚችሉ “ኢደፓ” ቢያብራራልን መልካም ነበር።

ልጥቀስ

የአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘውዳዊ አገዛዝ ከተገረሰሰ በኋላ እስከ ግንቦት 20 ቀን 1983 . ድረስ ኢትዮጵያን ሲያስተዳድር የነበረው የደርግ ወታደራዊ ሥርዓት ባለስልጣናት የፈጸሟቸውንየቀይ ሽብርወንጀሎች እንዲያጣራና ለፍርድ እንዲያቀርብ ኃላፊነት ተሰጥቶት 1984 . በኢህአዴግ የሽግግር መንግስት ዘመን ተቋቁሞ የነበረው የልዩ ዐቃቤ ሕግ /ቤት ሥራውን አጠናቆ የመጨረሻ ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረቡን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመለከተ። ጽሕፈት ቤቱ ለፓርላማ ባቀረበው ሪፖርቱ፤ 5119 የደርግ ባለስልጣናት መከሰሳቸውን፣ ከእነዚህ ውስጥ 3583 ጥፋተኛ ተብለው በሞት በዕድሜ ልክና በተለያዩ ዓመታት የእስራት ቅጣት የተጣለባቸው መሆኑን፣ 656 ሰዎች ታስረው ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ በነፃ መሰናበታቸውን፣ በክሱም ሂደት 8047 የሰውና 15214 ገጽ ያለው የሰነድ ማስረጃ መቅረቡን ወዘተ. አብራቷል። የደርግ ባለስልጣናቱ የፈጸሙት ወንጀልየዘር ማጥፋት” (Genocide) መሆኑ በፍርድ ቤት መረጋገጡን የልዩ ዐቃቤ ሕግ /ቤት ባቀረበው ሪፖርቱ ገልፆ፤ ጥፋተኛ ተብለው በተለያዩ ዓመታት ቅጣት ከተፈረደባቸው ውስጥ ሰማንያ በመቶ (80%) የሚሆኑት ቅጣታቸውን አጠናቀው ወደ ህብረተሰቡ ተቀላቅለው በሰላም በመኖር ላይ መሆናቸውን ገልጿል። የኢህአፓ አባል የነበሩትና በደርግ ስርዓት ከፍተኛ ግፍ እንደተፈጸመባቸው የሚነገርላቸው የልዩ ዐቃቤ ሕግ /ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ግርማ ዋቅጅራ፣ ሪፖርቱን ካቀረቡ በኋላ በምክር ቤቱ መቀመጫ ያላቸው ፓርቲዎች አባላት አስተያየትና ጥያቄ አቅርበዋል። በዚሁ መሰረት በኢዴፓ በኩል፤ “… በሪፖርቱ ላይ 656 ያህል ሰዎች በቀይ ሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ለአስርና ከዚያም በላይ ዓመታት ታስረው በነፃ መለቀቃቸው ተገልጿል። እነዚህ ሰዎች ለበርካታ ዓመታት መታሰራቸው አግባብ ነው ወይ? …ያለ ጥፋታቸው ለታሰሩበት የሚካሱት በምንድን ነው?... በሪፖርቱ ላይበቀይ ሽብርወንጀለኞች ላይ መጣራት ተደርጎ በፍ/ቤት መቀጣታቸው ተገልጿል። በወቅቱ ግንየነጭ ሽብርአራማጆች እንደነበሩም ይታወቃል።የነጭ ሽብርጥፋተኞችንስ ጉዳይ ለምን አላጣራችሁም? ይህስ በታሪክ ሚዛን ሲሰፈር ትልቅ የፍትህ መጓደል አይሆንም ወይ?... በሪፖርቱ ላይ /ቤቱ ባለፉት ዓመታት ያከናወናቸውን ተግባራትና የደረሰበትን ድምዳሜ የያዘ መጽሐፍ ተዘጋጅቶ ማተሚያ ቤት እንደገባ ተገልጿል። እርስዎ ደግሞየቀይ ሽብርተጎጂ መሆንዎ ብቻ ሳይሆን ይህንን ሪፖርት ሲያቀርቡም ሆነ መልስ ሲሰጡ እጅግ ስሜታዊ ሆነው ታይተዋል። ታዲያ ይህ ስሜታዊነትዎ በስራዎ ሂደትም ሆነ ተዘጋጀ በተባለው መጽሐፍ ውስጥ ስላለመንጸባረቁ ምን ማረጋገጫ አለ?...” የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበው እንደነበር ከስፍራው የደረሰን መረጃ ጨምሮ ገልጿል።” ይላል- የኢዴፓዉ ዘጋቢ።

አይገርማችሁም? በሪፖርቱ ላይ 656 ያህል ሰዎች በቀይ ሽብር ወንጀል ተጠርጣረው ለአስርና ከዚያም በላይ ዓመታት ታስረው በነፃ መለቀቃቸው ተገልጿል። እነዚህ ሰዎች ለበርካታ ዓመታት መታሰራቸው አግባብ ነው ወይ? ብሎ ኢደፓ/ልደቱ አግባብ ነዉ ወይ ብሎ ሲጠይቅ - 10 ዓመት ያህል ያለምንም ወንጀል የታሰሩ ሰዎች በነፃ ስታሰናብቱ ከመነሻዉ ስታስሯቸዉ በቂ መረጃ ሳትይዙ ማሰራችሁ ፍትሕ ኣበላሽታችሗልና እና ቅጣታችሁ እንድትቀበሉ፤ከሥራም ትታገዱ ዘንድ ለዚህ የፓርላማ ጉባኤ እጠይቃለሁ አላለም። እሱ ያለዉ ምንድ ነዉ? ቅሬታዉ በቀጥታ ስተረጉመዉ፤ “ባዛዉ በለመዳችሁት ፍርደ ገምድል አሰራራችሁ ኢሕአፓንም ከየትም አፈላልጋችሁ 10 ዓመት ቃሊቲ አሰቃይታችሁ፤ቤተሰቦቻቸዉን በትናችሁ፤ለችግር ለልመና አጋልጣችሁ፤ልጆቻቸዉ ለስደት ለበሽታ ለድንቁርና እንዲጋለጡ እንድታደርጉ መች ዘንድ “ለምን የነጭ ሽብር” ተዋናያኑን ኢሕአፓንም እንደሌሎቹ አላሰቃያችሁትም ነበር?’ ብሎ ያለ ሓፍረት በድፍረት ሕዝብ ፊት “ልክ እንደ 656ቶቹ ሰለባዎች፤ በነጭ ሽብር ተካፍላችሗል ብሎ ሺዎቹን ሰብስቦ ለዓስር ዓመት አስሮ በነፃ እንዲያሰናብታቸዉ ኢህአፓም የወያኔ ሰለባ እንዲሆን በወያኔ የዲሞክራሲ ዘመን ተወለድኩ የሚለን ልደቱ አያሌዉ በወያኔ ታጋዬች የሚካሄድ ችሎት ፍትሃዊነቱን በተዛዋዋሪ እና በቀጥታ ገልጿል።

ይህ በታሪክ ሚዛን ሲታይ የፍትሕ መጓደል አይሆንም ወይ? ብሎ እንደገና ዘገባ አቅራቢዉን ይጠይቃል። የፍትሕ መጓደል ነዉ ብሎ እንኳ አላስቀመጠዉም “የፍትሕ መጓደል አይሆንም ወይ?” ብሎ ነዉ ጌቶቹን የጠየቀዉ።በደርግ ዘመነ መንግሥት ዜጎች ያለ ፍትሕ እያሰረ ለዓመታት በማጎርያ እሰር ቤቶች አሽጎ ግማሹ እስር ቤት እንዲሞቱ ግማሹም ተንከራትተዉ በነፃ እንዲለቀቁ አድርጓል ብሎ ደርግን ከስሶ በፍትሕ እፈርዳለሁ ብሎ የተመፃደቀዉ የወያኔ ልዩ ፍርድ ሰጪ አካል በተመሳሳይ/አንዳንዱም ቂም ለመወጣት በከፋ መልኩ፤ንጹሃን ዜጎችን ለቅሞ እየሰበሰበ ፍትሕን ቸል ብሎ ፍትሕ እንዲጓደል ያደረገዉ አካል “ያለፍርድ ቤት መብታቸዉ እንደተነጠቁት ዜጎች ሁሉ፤- ለምን ኢሕአፓንም አታሰቃዩትም ነበር” ሲል “ለዲሞክራሲ እና ለፍትሕ ቆሜአለሁ፤ ከ 70ዎቹ ግራ ዘመም ሃይሎች የመጠቅኩኝ ነኝ” የሚለን ልደቱ “ምጥቀቱ፤ዕዉቀቱ” “ገለልተኛነቱ” ‘ተቃዋሚነቱ’ የቱ ላይ ነዉ?

በጣም የሚገርመዉ ደግሞ ሪፖርት አቅራቢዉ “ግርማ ዋቅጅራን” የአዲስ ትዉልድ አርአያ ጋሻ ነኝ የሚለዉ ተመጻዳቂዉ ልደቱ እንዲህ ይላል። በሪፖርቱ ላይ /ቤቱ ባለፉት ዓመታት ያከናወናቸውን ተግባራትና የደረሰበትን ድምዳሜ የያዘ መጽሐፍ ተዘጋጅቶ ማተሚያ ቤት እንደገባ ተገልጿል። እርስዎ ደግሞየቀይ ሽብርተጎጂ መሆንዎ ብቻ ሳይሆን ይህንን ሪፖርት ሲያቀርቡም ሆነ መልስ ሲሰጡ እጅግ ስሜታዊ ሆነው ታይተዋል። ታዲያ ይህ ስሜታዊነትዎ በስራዎ ሂደትም ሆነ ተዘጋጀ በተባለው መጽሐፍ ውስጥ ስላለመንጸባረቁ ምን ማረጋገጫ አለ?...”

በቂም በቀል በቁጭት ስሜታቸዉ መቆጣጠር ያቃተቸዉ የፍርድ አካላት በታጠረ የፍረድ ተቋም ዉስጥ ኢሕአፓን ለምን አልቀጣችሁም ካለ እሱ እራሱ እንኳ በስሜት የሚከንፉ የፍትሕ አባልት መሆናቸዉ ካመነ፤ ለመን ኢሕአፓን በነዚህ ስሜታቸዉን መቆንጠጥ ባልቻሉ የፍርድ አካላት ስላለፈዉ ትግላቸዉ ተከስሰዉ በወያነ ትግራይ ኢሰባዊ ፍርድ ቤቶች እንዲጋፈጡ አንደፈለገ አልገባኝም ብሎ ማብራርያ መጠየቅ አያስፈልግም። ልደቱ ከ70ዎቹ እና ከግራ ዘመም ወይንም መሬት ላራሹ ብሎ ለጮኸዉ የዛኔዉኑ የዓለም አቀፍ ወጣት ታጋይ ቡድን “ኩፉኛ ስለሚጠላዉ” እና ከያ ትዉልድ አስተሳሰብ እኔ የተለየሁ ነኝ (በወያኔ ዲሞክራሲ የተወለድኩ ነኝ)፤እንደ እኔ ያለዉ ወጣት ታይቶም ተሰምቶም የለም፤ በማንዴላነት ቅጽል ስም የታወቅኩ እፁብ ድንቅ ወጣት ነኝ ከሚለዉ ጉረኛ ባሕሪዉ ክፍተት ለማግኘት እና “ልዩ ወጣትነቱን- አንደ ኤርትራኖቹ በተሳሰተ የራስ ምስል የማን አክሎኝ ስካር” የመወጠሩ ምልክት ነዉ የሚል ድምዳሜ ያደርሰናል።

ይህ ባይሆን ኖሮ፤ ወያነ ትግራይ ያቋቋማቸዉ እነ ሽዋ ሮቢት የስቃይ እስር ቤቶች ገብቶ በአካል ታስሮ የነበረዉ ልደቱ “ወያኔ ፍዳየን አሳይቶ ሊገለኝ ነዉ፤ በቁም ተከብቤ አለሁ፤ መዉጣት መግባት፣መመገብ መንቀሳቀስ፤ከጽ/ቤቴ መዉጣት አልቻልኩም፡ መተንፈስ መናገር አልቻልኩም ፤የስልክ መስመሬ ተጠልፋል….” በማለት “ይድረስ ለኢትዬጵያ ሕዝብ’ እያለ በራሪ ወረቀቶችን እንዳልበተነ ሁሉ፤ስለ የወያኔ የፍትሕ ተቋማት እንዳላማረረ ሁሉ፤- ዛሬ ፓርላማ ዉስጥ ገብቶ “ኢሕአፓዎች- (ነገም ደግሞ ወያኔን እነ ሃይሉ ሻዉልን አጉረልኝ ሊለዉ ነዉ) ኢፍትሓዊ በሆነዉ “የጉሬላዎች/ የጫካ ፍርድቤት” ዉስጥ ጎትታችሁ ለምን ለስቃይ አትዳርጛቸዉም ባላለ ነበር።ይህ ወጣት ባንድ በኩል ፍትሕ የጎደለዉ ችሎት አካሂዳችሓል እያለ ሲሟገት፤በሌላ በኩል ደግሞ ለሱ ግልፅ በሆነ ለኛ ግልፅ ባልሆነ ምክንያት የወያኔ ተቃወሚዎች የሆኑትን ኢሕአፓዎችን ለቅማችሁ ለምን የሞት ፍርድ አልፈረዳችሁባቸዉም ይላል። ለነገሩ ጎረምሳዉ የጉርምስናዉ እድሜዉ ከፖለቲካዉ ጋር ልቡ አፍኖት አላሳይ ብሎት እንደሆን እንጂ “ደርጎች ከመለቀማቸዉ በፊት ወያኔ እያፈነ የገደላቸዉ እና የሰወራቸዉ እነ ጋይም የተባሉ እነ ጸጋየ ደብተራዉ እና ወዘተ የኢሕአፓ ታጋዬች እንደ ደርጎቹም ሆነ እንደ የወያኔዎቹ እና የበረከት ስሞን አሻንጉሊት “የብእዴን ጀኔራሎች” የሚባሉት እንኳ ለይስሙላ ፍርድ ቤት ቀርበዉ ፊታቸዉን በቴሌቪዥን መስኮት ለሕዝብ እንዲታዩ አድርጎ አልገደላቸዉም። ታዲያ ከዚህ የበለጠ ስቃይ እና ኢፍትሓዊ አሰራር ምን እንዲፈጸም ፈልጎ ነበር ፓርላማ ዉስጥ ኢሕአፓዎች በወያኔ ፍርደገምድል አልተሰቃዩምና ይጨመርላቸዉ “አልረካሁም!” የሚለዉ?

አስኪ የጦብያዉ አቶ ጸጋየ ገ/መድህን አርአያን አገላለጽ ልዋስ እና ሕዝባዊ አመጽና ጠንካራ ተቃዉሞ እንዳይኖር ወያኔዎች “እንደ ልብ እንዲባልጉ” እና እያሰሩም እየገደሉም እንዳሻቸዉ እንዲቦርቁ እያደረገዉ ያለዉ ማን ነዉ? ሕዝብ እየተረገጠ እና እየተንገላታ ስቃዩ አንሶታልና ፍርደ ገምድል ፍረድቤት ድረስ እየተጎተተ ካለዉ ስቃይና ሃዝን ይጨመርለት ማለት ምን ማለት አምባገነኖችን ማወደስ እና ዕድሜ እንዲቀጥሉ መደገፍ ካልሆነ ምን ሊባል ይችላል? ሕዝብ በደል እና ኢፍትሃዊ የሆኑ ፍርድቤቶች ሰባዊ መብቶችን ተጋፍተዋል እየተባለ (ራሱም እያመነበት) ባለበት ወቅት ኢሕአፓን እጠላለሁ እና ፍትሕ እየረገጣችሁም ቢሆን ቆልፉባቸዉ ማለት ቂም በቀልተኛነት ወይስ ሞኝነት፤ወይስ ወያኔነት ወይስ ወያኔን በቅጡ አለማወቅ? ከተቃዋሚዉ ጋርም ልዩነት አለን የሚለን ልደቱ ያነጣጠረዉ በወያኔ የፍትሕ ተቋማት ላይ ሳይሆን በተቃወሚዉ ላይ መሆኑን ከዚህ አሳፋሪ እሮሮዉ በላይ ሌላ መረጃ ምን አለ? አንድ ዘመኑ ወጣት ካለፈዉ ዘመን ወጣት የተሻልኩኝ ነኝ ካለ፤ግራ ዘመሙ ወጣት አልወድደዉምና ኢሕአፓዎች ለምን በፍርድ ገምድል አልተቀፈደዱም ብሎ በሕዝብ በይፋ እሮሮዉ ሲያሰማ ፤ ወያኔ በሕዝብ መብት እንዲማግጥ እየሆነ ያለዉ እንደዚህ አይነቱ ዉዥምብራም ወጣቶች በዘዴ እየተፈለፈሉ የትግሉን አቅጣጫ እንዲያደናግሩ በመቀረጻቸዉ ነዉ ብል ስህተት ሊሆን ነዉ? ኢደፓ የዘመናችን “የወጣቶች ስብስብ” ድርጅት ስለ ወያኔ መቃወም ስብከቱ አንኳን ወያኔን “ማቁሰሉን ቀርቶ የሚመታም” (የጸጋየን ቃላት አሁንም ልበደር) አይደለም:: በዚህ መንገድ በነዚህ ዓይነቶቹ ወጠቶች እጅ የምትንተራስ አገር ወጣቶች ወዴት እያመራች ነዉ?።

ከዚህ በታች በሚቀጥለዉ በጸጋየ ገብረመድህን አርአያ ብዕር ልሰናበታችሁ።

“የታጋይነትና የተጋዳይነት ወኔን እየተሰለበና የፖለቲካ ጃንደራባ እየሆነ የመጣዉን ሁሉ “እግዚሔር በጥበቡ፡ይመልሰዉ” እያሉ የሚቀበሉ ወገኖቻቸዉ ሲጨፈጨፉ በድጋፍ ሰልፍ አገር የሚያተረማምሱ፣ በአገራቸዉ ላይ ማናቸዉም ደባ ተፈጽሞ እልል ዪሉና ከባለቤቶቹ ተጠቃሚዎች የበለጠ የሚያሽቃብጡ ሰዎች ለባርነት እና ለተዋራጅነት ትከሻቸዉን ያዘጋጁ መሆናቸዉ ግልጽ ነዉ። አልሰማን ያለ ጀሮ በጥይት መክፈት እንደሚጋባ ለማስተማር አልፈልግም። ለእኔ ትግል ማለት ተኩስ ማለት ብቻ አይደለም። ወደ ተኩሱ የሚያመሩ ጥቃቶች ይሰላሰሉ ነዉ የምለዉ። ዛሬም ነገም ወደፊትም” አመሰግናለሁ - ጌታቸዉ ረዳ 2002 ኢትዬ አቆጣጠር www.Ethiopiansemay.blogspot.com