Saturday, May 29, 2021

የደደቡ ፕረዚዳንት ማዕቀብ፤ ተቃዋሚዎች እና እንዲሁም የትግራይ ተዋጊ ሃይሎች የእርስ በርስ የመታኮስ አይቀሬ እጣ ፈንታ ትንበያ ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ (Ethio Semay) 5/29/2021

 

የደደቡ ፕረዚዳንት ማዕቀብ፤ ተቃዋሚዎች እና እንዲሁም የትግራይ ተዋጊ ሃይሎች የእርስ በርስ የመታኮስ አይቀሬ እጣ ፈንታ ትንበያ

ጌታቸው ረዳ

ኢትዮ ሰማይ (Ethio Semay)

5/29/2021



የሚታው ፎቶግራፍ የወያኔ ኮማንዶ አሰልጣኝ ሲሆን ከጀርባው የሚነበበው ጽሑፍ

 “በሰማይ ማርያም ጽዮን፡

በክልል ደብረጽዮን” ይላል።

 

ተከታታዮቼ እንደምን ሰነበታችሁ? ለትንሽ ወቅት ጠፍቼ ነበር፤ ሰላም እንደቆያችሁኝ ተስፋ አለኝ። በፌስቡክ መሰንጀር በኩል ሰላም ለማለት የጻፋችሁልኝ ወገኖች መልስ ባለመስጠቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ።

ለዛሬ የምትወያዩባቸው ሦስት ርዕሶችን ይዤ መጥቻለሁ።

1ኛ) የደደቡ ፕረዚዳንት ማዕቀብ

2ኛ) የትግራይ ወያኔ መንግሥት ለመጣል ሲታገሉ የነበሩ ተቃዋሚዎች

3ኛ) ወያኔ ከተወገደ በሗላ ኦሮሙማውን ሥርዓት ለመጣል እየታገሉ ያሉት ተቃዋሚዎች

4ኛ) በረሃ የወጣው የትግራይ መከላከያ ሃይል ተብሎ የሚጠራው የግንጣላ ዘመቻ ተዋጊው ሃይል እርስ በርስ የመታኮስና የመለያየት ትንቢታዊ እውነታ እንመለከታለን።

 

በመጀመሪያው በደደቡ ፕረዚዳንት ማዕቀብ፤ ልጀምር።

 

ድረገጾችን ስጎበኝ ዜናው ሁሉ አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ስለመጣል ጉዳይ በሰፊው ተዘግቧል። የአሜሪካ ማዕቀብ የመጣል ፍላጎት ስለ ሰው ህይወትና ሰላም አሳስቧት ሳይሆን አምጣ የወለደቻቸው ልጆቿ ወያኔዎች ጥጋብ አላስችል በሏቸው ባመጡት ባሕሪ ከሥልጣን በመወገዳቸው ኩፍኛ አዝና ተቆጥታለች። ስለሆነም ልጆችዋን ወደ ነበሩበት ለማስቀመጥና ከሌላኛው ቅጥረኛ ልጃቸው ለማስታረቅ በየትኛውም አገሮች የምትጠቀምበትን ማዕቀብ የተባለው ብዙ ሕይወት በረሃብና በምጣኔ ሃብት የምታሳልቅበት ስልትዋን ለመጠቀም ወስናለች።

 

አሜሪካ በታሪኳ ልክ እንደ ጀርመን ናዚ “ኣዲሱ የዓለም ስርዓት” ተብሎ የሚታወቀው አገሮችን የመዋጥና የመቆጣጠር በልዕለ ሃያልነት አባዜዋ የምትታወቅ የብዙ ሺዎች የዓርብ እና የቬትናም ሕዝቦች በመርዝና እሳት የሚተፉ አውሮፕላኖችን አሰማርታ በመጨፍጨፍ የታወቀች ወንጀለኛ አገር ነች። ለዚህ ወንጀልዋ የሚቀጣትም ሆነ ማዕቀብ የሚጥልባት አገርም ሆነ ፍርድቤት እስከዛሬ አልተገኝም። በታሪኳ አንድ ጊዜ የሳወዲ አረቢያ መንግሥት በፍልስጢየም ጉዳይ የነዳጅ ማዕቀብ አድርጋባት ምጣኔ ሃብትዋ ተቃውሶ የምትይዘው የምትጨብጠው አጥታ ነበር። በዚህ ጉዳይም ዓለም በሙሉ በነዳጅ እጦት ተናግቶ እንደነበር ይታወሳል። ከዚያ ወዲህ ጨክኖ ይህችን ወንጀለኛ አገር ማዕቀብ የጣለባት አገር ከቶ የለም።

 

አሜሪካን በማዕብ መቅጣትና ማንበርከክ የሚቻል ዕድል የሚኖሮው አፍሪቃኖች ባንድ ድምጽ አሜሪካን ላይ ማዕቀብ ቢጥሉ ትቀዝን ነበር (ለቃላቴ ይቀርታ) ። ሆኖም እርሷን የሚያገለግሉ ጀሌዎች ስላልዋት አይሞከርም። ሙሉን ተውት እና የምስራቅ ቀንድ አፍሪካ አገሮች ብቻ ማዕቀብ ቢጥሉ ሱሪዋን ትፈታ ነበር። ሆኖም በተለይ ጁቡቲ የመሰለች “የመላ አፍሪካን አገሮች የምታስደፍር” ክብረ-ቢስ ወራዳ አገር ይዞ አሜሪካ ላይ ማዕቀብ ማድረግ አይቻልም።

 

የ27 (21?) የሶቭየት ሪፑብሊክ እስቴቶች ከፈረሱ ወዲህ አሜሪካ ከአውሮጳዎች ጋር በመናበብ የልብ ልብ አግኝታ እነ ሀርመን ኮሀንን የመሰሉ አደገኛ አይሁድ አሜሪካኖችን በመክ ‘በወያኔ ቅጥረኞችዋ’ ተባባሪነት “በእጅ አዙር” ስልት በመጠቀም ኢትዮጵያ የአሜሪካና የእንግሊዝ የቅኝ አዙር ግዛት ሆና ቆይታለች። ይህ ቁጥጥር ዛሬም በፋሺስቱ ኦሮሙማ መሪው አብይ አሕመድም ጊዜ በትግራይ ውስጥ ጦርነት እስከተከተጀመረበት በፊት የተለወጠ ነገር አልነበረም። ዛሬ ምን ተገኘና ነው ማዕቀብ ለመጣል የወሰነቺው ለሚለው መልሱ ከላይ የጠቀስኩት ነው።

 

የአሜሪካ ባለሥልጣኖች መቸውንም ቢሆን ኢትዮጵያን በበጎ መልክ ተመልከተዋት አያውቁም። ብዙ ሰዎች የ100 አመት ወዳጅነት አለን ወዘተ እያሉ ሲያወሩ እመለከታለሁ። ሃቁ ግን ያ አይደለም።የአሜሪካ ቱባ ቱባ ባለሥልጣኖች ኢትዮጵያን እንዴት ይመለከትዋት እንደነበር ከነ ኒክሰን እና ከነ ሄንሪ ክሲንጀር ብንጀምር ስዕሉ ግልጽ ነው።

 

 ዛሬ በዘውግ የተከፋፈለችው ኢትዮጵያ በጣሊያን ፋሺሰቶች የተጀመረው ፖሊሲ አሜሪካ እንዴት እውን እንዳደረገቺው በቀርብ ገዝቼ ባነበብኩት ኢትዮጵያ ወዳጅ የሆኑት የፕሮፌሰር “ትዮዶር ቬስታል” “The Lion of Judah in the New World” (Author Theodore M Vestal) በጻፉት መጽሐፋቸው እንዲህ ይላሉ።

“The decline in the fortune of the Horn nations might have been foreseen by Henry Kissinger, who in 1972 as head of the National Security Council, known under his direction as the “committee in charge of running the world.” Wrote a confidential report on the future of Ethiopia. He purportedly recommended that U.S. policy should be to keep that nation in perennial internal conflict, using such vulnerabilities as ethnic, religious, and other divisions to destabilize the country. Kissinger’s recommendation appears to have been followed success fully, for not only Ethiopia but the Horn of Africa have been in turmoil ever since.” (The Lion of Judah in the New World - Author Theodore M Vestal page 188)

በተቀራራቢነት ስተረጉመው እንዲህ ይላል፡

“የምስራቅ አፍሪቃ ቀንድ አገሮች ሀብት ‘የማሽቆልቆል ምክንያት’ ሄንሪ ኪሲንጀር በ 1972 በአሜሪካ የብሄራዊ ደህንነት ም/ቤት ሓላፊ ሆነው በመሪነቱ ስር “ዓለምን በበላይነት የሚያስተዳድር ኮሚሽነር” በመባል የሚታወቀው ሓለፊነት ሲመራ በነበረበት ወቅት እንደሆነ ሲገመት ስለ ኢትዮጵያ ሁኔታ ሚስጥራዊ ዘገባ በጻፈው ሰነድ ውስጥ እንዲህ ይላል፡፡

“አገሪቱን ለማተራመስ እንደ ጎሳ ፣ ሃይማኖታዊ እና ሌሎች ክፍፍሎች ያሉ ተጋላጭነቶችን በመጠቀም ሕዝብዋ በየዓመታቱ ውስጣዊ ግጭት ውስጥ እንድትቆይ ማድረግ የአሜሪካ ፖሊሲ መሆን አለበት፡፡” በማለት ኪሲንጀር የሰነዘረው ምክር ተሳክቶለት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በመሆኑ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ከዚያ ዘመን ጀምሮ የምስራቅ አፍሪቃ አገሮች የብጥብጥ ቀጣና ሆኗል። (የይሁዳ አንበሳ በአዲሱ ዓለም - ደራሲ ቴዎዶር ኤም ቬስቴል ገጽ 188) ሲሉ ሰነዱን ይፋ አድረገውታል።

 

ስለሆነም ዛሬ “ደደቡና ሕሊና ቢሱ ፕረዚዳንት ባይደን” የግብጹ ሑስኒ ሙባረክ ከሥልጣን ለማውረድ ታሕሪር እስኩየር በሕዝብ ድምጽ ሲቀወጥ ባይደን “ሙባረክ አምባ ገነን አይደለም” ሲል በጆሮየ ሰምቼው ከዘያ ቀን ጀምሮ የባይደን ጭንቅላት ያወቅኩበት አጋጣሚ አንዱ ነበር።  ደደቡ ፕረዚዳንት ስለ ትግራይም ሆነ ጠቅላላ ስለ ኢትዮጵያ ታሪካዊና ፖለቲካዊ እውቀት የለውም። ደደቡ ፕረዚዳንት የመለስ ዜናዊ ወዳጅ በነበረቺው በ“ሱዛን ራይስ” እና በመሳሰሉ ጸረ አፍሪካ ግለሰቦች የሚዘወር እንደሆነ ግልጽ ነው”።

 

ደደቡ ፕረዚዳንት ኢትዮጵያን አስመልክቶ በማያገባው ገብቶ ከዘላበዳቸው “ከሦስቱ ነጥቦቹ ” ውስጥ አንዱ “የአማራ ሃይል ከትግራይ ይውጣ” የሚለው ነው።፡ይህ አባባል ምን ማለት እንደሆነ ከጣሊያን ጀምሮ ጥርስ ውስጥ የገባው ከዚያም በሻዕቢያ ከዚያም በወያኔ ከዚያም በኦሮሙማ ከዚያም ዛሬ በአሜሪካ ዒላማ ውስጥ የመግባቱ ምስጢር ከላይ የጠቀስኩትን የኪሲንጀር ፖሊሲ ህያው ቀጣይነቱን አማላካች ነው።

 

ደደቡ ፕረዚዳንት እና አማካሪዎቹ የጂኦ ፖለቲካ ዓላማዎቻቸውን ለማሳካት ምን ያህል ስኬታማ ናቸው የሚለው ለወደፊቱ የሚታይ ሲሆን፤ “ህጻንነቱን ያልጨረሰው” አብይ አሕመድ “በአገር ፍቅር የተቃጠለው የዙምባቤው ሮበርት ሙጋቤ” ስላልሆነ ሥልጣኑን ለመቆጣጠር ሲል ውሎ አድሮ ሸብረክ ማለቱ የማይቀር ነው።

 

 ማዕቀቡ ከፍተኛ የሰብአዊ ሰበቦች ቢያመጣም ለድሃው ማዕቀቡ ተደረገ አልተረደረገ አንዴ የፈራረሰ አገር (ፈይልድ ስቴት) ስለሆነ ውጤቱ ከድጡ ወደ ማጡ እንጂ ከምቾት ወደ ርሃብ አይሆንም።

 

የጊዜ ጉዳይ ቢሆንም ማዕቀቡ በአሜሪካ የባይደን ፖሊሲ አውጭዎችና አስፈጻሚዎች ላይ ከፍተኛ ዕዳንም ጭምር ያስከትልባቸዋል። ይህ ማለት በርካታው ኢትዮጵያዊ ባይደንን እና ኮንግረሶችን በመቃወም በምርጫ ወቅት የሚያስከፍላቸው ዕዳ ይኖራል። መዘንጋት የሌለበት ግን ደደቡ ፕረዚዳንት ሱዳኖችና ግብፆች ኢትዮጵያን እንዲወሩ ከገፋፋ “ጥቁር አሜሪካኖች” በባይደን አስተዳዳር ኩፍኛ ተቃውሞ ማስነሳታቸው አይቀርም። ያም ሆነ ይህ ማዕቀቡ ይሰራል አይሰራም ቆይተን የምናየው ይሆናል።

 

2ኛ) የትግራይ ወያኔ መንግሥት ለመጣል ሲታገሉ የነበሩ ተቃዋሚዎች!!

 

ፅሑፌን ስትከታሉ የነበራችሁ ወገኖቼ እንደምታስታውሱት በወቅቱ ወያኔን ለመጣል ስንታገል ብዙዎቹ ተቃዋሚዎች የትግል ስልታቸውም ሆነ የሚታገሉለት ራዕይ ፈጽሞ የተበላሸ ስለነበር፤ በሕብ ዘንድ አቃፊነት አግኝተው የነበሩ የሚዲያ ባለቤቶችም ሆኑ የፖለቲካ መሪዎች እያደሩ ከአክራሪ እስላም ፖለቲካ አራማጅ ፖለቲከኞች ፤ ከገንጣይ ቡድኖች እና ከፀረ አማራ ሃይሎች ጋር እየተገናኙ “በእፍ እፍ ፍቅር” አብደው “ስለ ኢትዮጵያ የቆሙ ሃይሎች ናቸው፤ እንግዲህ ግንጠላ ትተዋል” ወዘተ … እያሉ፤ “ተው” አይሆንም ስንላቸው ለነበርን ሰዎች ክፉኛ እየሰደቡና እያንኳሰሱን የትግሉን ዓላማ እንዲኮላሽ በማድረግ ሕዝቡን በሁለት ጎራ ከፍለው በማበጣበጥና በማደባደብ (አሁንም ሰበቡ አለ) ገንጣዮችና አክራሪ ሃይሎች ጉዞው ክፍት ሆኖላቸው “በመጨረሻ ወያኔ ከተወገደ በሗላ” ደብቀውት የነበረውን ቆዳቸው በግሃድ ወጥቶ ዛሬ ኢትዮጵያ ምን እያደረጓት እንደሆነ የምታውቁት ጉዳይ ነው።

 

በወቅቱ ይህንን እውነታ ስለታየኝ ወያኔ ከተወገደ በሗላ ጸባችን ያኔ ተቃወሚ ነን ከሚሉት ጋር ነው ብየ እንደነበረው ሁሉ ዛሬ እውን ሆኖ እነ ብርሃኑ ነጋ ፤ “አቃጣሪው” አንዳለም አራጌ እና እልፍ ተቃዋሚ ነን ባዮች አማራን በመዝለፍና ምን ታመጡ ብሎ አማራውን “መጤ” በማለት የኢንተርሃሙዌውን ቡድን ፕሮፐጋንዲሰት ሆኖው “የዱርውን መንግሥት” መሳሪያ ሆነው፤ እነሆ ዛሬ ልክ እንደተነበይኩት በተቃራኒ ቆመው ከኢትዮጵያዊው ሃይል እና ከአማራ ታጋይ ሃይሎች በሚዲያ ይጠዛጠዛሉ።

 

3) ወያኔ ከተወገደ በሗላ ኦሮሙማውን ሥርዓት ለመጣል እየታገሉ ያሉት ተቃዋሚዎች!!

 

ዛሬ የምር የሚናገሩ ጥቂቶች የሆኑም ሆኑ መስመራቸው ግልጽ ያላደረጉ አገር ውስጥም ሆኑ ውጭ አገር ብዙዎቹ ተቃወሚዎች በሙሉ በሚባል ደረጃ የሚናገሩት ንግግር ስታደምጡ “ወያኔንም ጭምር ወደ ምርጫ አስገብቶ ወደ ፖለቲካው ዓለም በማስገባት ሰላም ማምጣት የሚሉ አሉ”። ይህም በዕርቅና በምናምን የሚል ስልታቸው ነው። ይህ መስመር ደግሞ የወያኔና የኦነግ ፖለቲካዊ ባሕሪ (ተፈጥሮ) ካለመረዳት የመነጨ እንዝህላልነት ነው።

ኦነጉን ወደ ጎን እንተውና አሜሪካ እየጨሁለት ያለውን ሱዳኖችና ግብፆች እያንቋለጡለት የሚኘውን በሽሽት ላይ ያለው የወያኔ ተዋጊ ሃይል እና መሪዎች ዓላማ ምን ነው? የሚለውን መመለስ አለብን። ዓላማቸው ዛሬ ሳይሆን ገና ጫካ እያሉ ግልጽ አድረገውልናል። እኛ ትግሬዎች ኢትዮጵያን ዝነተ ዓለም ካልገዛናት “አፍርሰናት” ትግራይ ሪፑብሊክ አንመሰርታን ብለው በሰላማዊ ሰልፍም ሆነ በራድዮ በቴ/ቪዥን በጽሑፍ ግልጽ አድረገዋል። ተቃዋሚው ግን ከወያኔ ጋር ፍቅር ይዞት ሙጭጭ ብሎ “በዕርቅ” ይመለሰል እያሉ አንጀቴ እስኪያመኝ ድረስ ያስቁኛል።

ወያኔ ሁለት አማራጮች ነግሮናል። (1) ወያኔ ያዋቀረው በዘር የተለያየን ነን በማለት በቋንቋና በዘር ያዋቀረው “አፓርታይዳዊው” አስተዳዳር ቀጥሎ ትግራይ በወያኔዎች እንድትዳዳር እና አማራ ከርስቱ ከመሬቱ ተነቅሎ ወጥቶ በወራሪው ወያኔ  በኩል መሬቱን ለትግሬዎች እንዲያስረክብ ። ይህ ካልሆነ “መገንጠል”! (2) ያ ክልሆነ ግን ኤርትራ “ሃገረ ኤርትራ እንደተባለቺው’ ትግራይም “ሃገረ ትግራይ” ተብላ ጠላታችን ከሆነቺው ኢትዮጵያ መለየት”! የሚል ነው።

ይህ የማታገያ መስመራቸው ተቃዋሚዎች “የወያኔ ፋሺስታዊ ባሕሪ” ማወቅ አቅቷቸው “በሰላም በድርድር ዕርቅ” ምናምን የሚሰራ እየመሰላቸው በሕልመ አለም ሲቃዡ በየሚዲያው አደምጣለሁ። ይህ የወያኔ አቋማቸው የማይለወጥ ነው። ወያኔ ፋሺስት ነው።ፋሺስቶች በድርድር አያምኑም። በድርድር የሚያምን ቢሆን ኖሮ አብይ አሕመድ ወያኔዎች የዘረፉትን ንብረት በያዛችሁት ይጽደቅላችሁ ብሎ እነ ስዩምን በውጭ ጉዳይ ምኒሰትርንት እነ ..እነ በረከትን ወዘተ….. ሲለምናቸው “አፍንጫህን” ብለውት ነው ይህ ሁሉ ጦርነትና እልቂት ያመጡት። ከሪያ ኢብራሂምን አታዩም?! ከምን ወደ ምን ተለውጣ ከምቾት ወደ ቃሊቲ ትገባ አንዴት እንደመረጠች። ደቡብ ሱዳን የነበሩት የተባበሩት የሰላም አስከባሪ ሃሎች የነበሩት ትግሬዎች ወዴት አንደተቀላቀሉ እናስታውሳለን አደል?

የነገድ ፖለቲካ እጅግ አደኛ የፋሺስቶች ልዩ ባሕሪ የሆነ ድርድርን እንደ ሽንፈት ስለሚያየው ውይት ዕርቅ እይቀበልም። ስዚህ እነዚህ የዛሬ ቃዋሚዎችም ነገ ፋሺሰቱ አብይ ሲወገድ ወያኔን ወደ ዕር አምጥው ኦነግንም ወደ ዕርቅ አምጥተው የቤንሻንጉል የሰው በሊታው ታጣቂም ወደ ዕርቅ አምጥተው “ወንጀላቸውን በይቅርታ ተወስኖ፤ “የቋንቋና የነገድ ፖለቲካ አስተዳደር በከፊልም ቢሆን መቀበላቸው አይቀሬ ነው። በተለይ አብይ አሀመድ በዚህ ላይ ልዩ ተጫዋች ስለሚሆ ወንጀለኞች ዓለማቸውን ያያሉ። በዚህ አገሪቱ አዙሪቷ ይቀጥላል””


 4ኛ) በረሃ የወጣው የትግራይ መከላከያ ሃይል ተብሎ የሚጠራው የግንጣላ ዘመቻ ተዋጊው ሃይል የእርስ በርስ የመታኮስና የመለያየት ትንቢታዊ እውነታ በሚቀጥለው ክፍል በሰፊው እንመለከታለን።……..ተቀባበሉት (ሼር አድርጉት) ……………..ይቀጥላል