Tuesday, August 3, 2021

የባህርዳሩ ጸረ ትግሬ ዘመቻ ዛሬም እንደቀጠለ ነው ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ ዋና አዘጋጅ 8/3/2021 ፈረንጅ አቆጣጠር

 

የባህርዳሩ ጸረ ትግሬ ዘመቻ ዛሬም እንደቀጠለ ነው  

ጌታቸው ረዳ

ኢትዮ ሰማይ ዋና አዘጋጅ

8/3/2021 ፈረንጅ አቆጣጠር

አንባቢዎቼ እንደምን ሰነበታችሁ፤



በውስጥ አገርም በውጭ አገርም ሆናችሁ በምንም ከማንም ፖለቲካ ቡድን ያልወገነው የወንድሜን መታሰር ያሳሰባችሁና ለማስፈታት የጣራችሁ ወገኖቼ ሁሉ እያመሰገንኩዋችሁ፤ በሌላ በኩል ግን “ትግሬ በመሆናችሁ በምናችሁ እንመናችሁ?” “ስለዚህም መጥፋት አለባችሁ” ብላችሁ የወያኔ ጀሌዎች ከነበሩት ከነተመስገን ጥሩነህ እና ከነደመቀ መኮንን ዓሊ ሥርዓት አብራችሁ የኛን መጥፋት ስትጽፉልኝ ለነበራችሁ “የጎስታፖ” ተከታዮች ምኞታችሁ ሰምሯል ደስ ይበላችሁ።

ዛሬም ወንድሜ ያለምንም ወንጀል እና የክስ ዝርዝ “አቃቤ ሕጉ” ወንድሜን አስሮ ከሥራው አፈናቅሎ ፍርድቤት ስያንገላታው ከርሞ ምንም ማስረጃ ማቅረብ ስላቃተው እንደገና “ዳኛውን” ያለምንም ማሳመኛ ክስ ለአንድ ወር ቀጠሮ በመጠየቅ “ፌደራል አጣሪዎች ከአዲስ አባባ መጥተው እስኪያጣሩ ደረስ” ጭለማ እስር ውስጥ ይቆዩ በማለት ንጸሁን ወንድሜን በማሰቃየቱን ቀጥለውበታል።

ሥርዓቱ የስም ለውጥ እንጂ ወያኔ አዋቅሮ የፍትሕ እና የዜጎች መብት ምን እንደሆነ የማያውቁ  ብዙ ግብዞችን  አሰቀምጦት እንደተወው ነው አሁንም ዜጎች በማሰቃየት ላይ እየቀጠለበት ያለው።

“አብይ አሕመድ ጸረ አማራ እንጂ ጸረ ትግሬ አይደለም” ብየ በዚህ ፌስ ቡክ ስከራከርለት መቆየቴ ስሕተተኛ እንደሆንኩ አሁን አብይ ጽረ ትግሬ መሆኑንም ጭምር በተግባር አረጋግጦልኛል።

ፋሺሰቱ መሪያችሁ አብይ አሕመድ “ሳናጣራ አናስርም” ሲል የነበረው ዛሬ ንጹሃን ትግሬዎችን አስሮ ቤተሰብ ፍርድቤት እንዳይገቡ በማገድ፤ ይባስ ብሎ ታሳሪውን በቂ ጊዜና  የማነጋገሪያ ጊዜ ሰጥቶ ቤተሰቡን እንዳያነጋግሩት በሩቅ እንዲነጋገሩ በማድረግ ይኼው የጀርመን የዘር ጽዳት ሥራ ባሕርዳር ከተማ ውስጥ ተከስቶ እንደገና አንድ ወር ቀጠሮ በመስጠት ንጸሁን ወንድሜን እያንገላታው ይገኛል።

አሳዛኙ ነገር አሰሪዎቹ በአማራ ክልል የደህንነትና የአስተዳደር ባለሥልጣናት በኩል ያለምንም ወንጀል ትግሬዎች ዘመቻ እንደተከፈተባቸው እርሱም መታሰሩን እያወቁ በሦስት ቀን ወደ ሥራ ካልመጣህ በፈቃድህ እንደለቀቅክ እናስታውቃለን በማለት “ማስተወቅያ” ለጥፈውበታል። የደመቀ መኮንን ሥርዓት እያደረገ ያለው አስሮ እንደገና የወደፊት ህይወታቸው አንዲበላሽ እያደረገ ነው።

እንግዲህ በዚህ ግፍ የተማረሩ ትግሬዎች ህይወታቸው ተመሰቃቀሎ ሥራ አጥተው በብስጭት ወደ ወያኔ ጦር ተቀላቅለው “ኢትዮጵያን” ብያውኩ ተጠያቂው እራሱ የአብይ አሕመድ እና የደመቀ መኮንን ሥርኣት መሆኑን አንባቢዎች ግንዛቤው ውስጥ አስገቡልኝ። ወያኔዎች እያጠናከረ ያለው እራሳቸው አብይ እና ደመቀ መኮንን ናቸው።

አማራም ሆነ ኦሮሞ ወይንም ትግሬ ያለ ምንም ወንጀል ሳይፈጽም ታስሮ ነጻ ከወጣም ቢሆን “ሥራው ተነጥቆ ሲቆየው” ሰርቶ ቤተሰቡን ማስተዳዳር ካልቻለ ወደ ጫካ ገብቶ ሥርዓቱ ቢፋለም እንዴት ሊፈረድበት ይችላል? ኢትዮጵያ ልምድ ያለው አስተዋይ እና ሁነኛ መሪ አጥታለች ሰል የነበረውም ከዚህ በመነሳት ነው።

 በዚህ ሁኔታ እኔ የብዙ አመት ጠንካራ መንፈስ ባይኖረኝ ኖሮ “ከዛሬ ጀምሮ ኢትዮጵያ አንሆንም “ትግራይ ታሸንፋለች” ብለው የትግራይ ሪፑብሊክ ምስረታና ኢትዮጰያን ወደ ማወክ” ወደ ወያኔ ከተቀላቀሉት ከእነ “አብርሃ በላይ” ጋር እቀላቀል ነበር። ሆኖም የኔ አስተዋይነትና ልበ ሰፊነት ባይጨመርበት ኖሮ ስለ አማራ  የዘር ማጽዳት ሲኮንን የነበረው ይህ ከፊታችሁ ያለው አንድ ብርቱ ትግሬ ዛሬውኑ ኢትዮጵያ አንድ ታጋይዋ ከጎንዋ ታጣው ነበር። ሆኖም እንዲህ ያለ የዘር ፖለቲካ የሚከተል መንግሥት የሚፈጽመው ባሕሪ መሆኑን ስለማወቅና የጀርምን ናዚ ባሕሪዎችንም መጠነኛ መጻህፍቶችን ስላነበብኩ አቋሜን አይፈታተነውም።

የሚገርመው ደግሞ “አብይ አሕመድ” ለማስመሰል ትግሬዎች ለመደለል በትግርኛ መልእክት እያስተላለፈ “በጎንግን”  ንጹሃን ትግሬዎችን እስር ቤት እየከተተ ትግሬዎች በማስቆጣት ወያኔዎች ተጨማሪ ድጋፍ እንዲያገኙ እያደረገ ነው። እንዲህ ያለው ሥራ በማድረግም ይመስላል ከትግራይ ሕዝብ ሸሽቶ ወደ አማራ ድምበር በመጠጋት ወያኔዎችን የልብ ልብ ስጠቶአቸው እያየን ያለነው።

ለማንኛውም አዲስ አባባ ያላችሁ መሪዎችም ሆናችሁ እባሕርዳር ከታማ ያላችሁ የመንግሥት ጠበቃዎችና የደህንነት እና እስተዳዳር ባለሥልጣናት የፖሊስ ሹማምንት ከ3 አመት በፊት የነበረው ከወያኔ አወዳደቅ የቅርብ ትዝታ እንዴት መማር እንደልቻላችሁ የሚገርም ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ስለዚህም ወንደሜን በደምብ ስለማውቀው ያለምንም ወንጀል አስራችሁ ከማንገላታት ወንድሜን ለቀቅ አድርጉት።

ለማንኛውም “የፌደራል አጣሪ” መጣ አልመጣ  ንጹሃንን በማንገላታት እና ከሥራቸው እንዲባረሩ ምክንያት መሆን የእናንተም ሥልጣን ዝነተ ዕለት ሥልጣን ላይ ስለማትኖሩ፤  ለናንተ ለወደፊት ዕድላችሁም ሆነ ለኢትዮጵያ ጎጂ እንጂ ጠቃሚ እንዳልሆነ ምክሬን ላስተላልፍላችሁ እሻለሁ።

በመጨረሻም  ይህንን የጎስታፖ ጀርምን ናዚዎች የዘር ማጽዳት አሰራር ፖሊሲ እንዲቆም ዜጎች ሁሉ እንድታወግዙት እጠይቃለሁ። በተለይ የዘር ማጽዳት የተፈጸማባችህ የ30 አመት አማራ ወንድሞች እና እህቶች ይህንን ስራ አስቀያሚ መሆኑን ይጠፋችሗል ብየ አልገምትም። ስለዚህም የዘር ማጽዳት ኢትዮጵያ ውስጥ ላንዴና ለመጨረሻ እንዲቆም ይህ ሥርዓት መቃወም የግድ ነው። በተለይ ፌስ ቡክ ላይ ሆናችሁ “የተጠቃንበት ሰብአዊ በመሆናችን ስለሆነ ከመጠቃት ነጻ ለመውጣት አንደወያኔቹ የእንሰሳ ባሕሪ እንከተል” ብላችሁ ወጣቱን አማራ እንሰሳ እንዲሆን ግድያ ውስጥ እንዲሰማራ የምትቀሰቅሱ ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋችሗል።

ከወንድሜና ከቤተሰቦቼ ጎን ለቆማችሁ በውጭም በውስጥ አገርም ያላችሁ ወንድሞች እና እህቶች ሁሉ ምስጋናየ የላቀ ነው።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ