Sunday, May 26, 2019

ነጭ ባንዲራ አውለብላቢዎች ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)


ነጭ ባንዲራ አውለብላቢዎች

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)
ራሱን በማቃጠል መስዋዕት በመሆን የቱኒዚያን አብዮት ያቀጣጠለው ቦአዚዝ
የኔ ሰው ገብሬ ራሱን በማቃጠል መስዋዕት በመሆን የኢትዮጵያን አብዮት ለማቀጣጠል መስዋዕት ቢሆንም ተቃወሚዎች የከዱት መስዋዕት ሆኖ ቀርቷል። ዛሬ የሚዘክረውም የለም።
የጣሊያኖችን ዘመን ትተን እኛ በነበርንበት ዘመን በእኛ አቆጣጠር በ60ዎቹ ከተማሪዎች አብዮት ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያችን በሶቭየት ሕብረት ኮሚኒስት፤በምዕራባውያን እና በዓረቦች ዓይን ውስጥ ከገባችበት ወቅት ጀምሮ እስካሁን ድረስ እየታየ ያለ ጥቃት የነዚህ አገሮች ምስጢራዊ እና የግሃድ የጥቃት ዘመቻ ዛሬም አላባራም

 ጃስሚን አብዮት Jasmine Revolution (የኑሮ ምስቅልቅል ያስከተለ ተከታታይ ሕዝባዊ አመጽ) ተብሎ የሚታወቀው “አገልግሎቱ የጨረሰ” ተብሎ በአሜሪካኖቹ የተወገደው አገልጋያቸው የነበረው የቱኒዚያ መሪው ቤን አሊን ያስወገደው አብዮትም ሆነ ብዙዎቹ ታዋቂ ዓረብ አገሮችን ፈራረሱ አገሮች” ያደረገው “አረብ ስፕሪንግ” በመባል የሚታወቀው ሱናሚው አብዮት የተቀነባበረው በአሜሪካውያኖች መሆኑን ታስታውሳላችሁ። ይህ ዘመቻ ግምባር ቀደም የተጫወተው ልክ እንደ አብይ አሕመድ ስልጣን በያዘ በጥቂት ወራት “የኖቬል የሰላም ሽላማት ተሸላሚ” ሆኖ የሰላም ሰው ለማስመሰል በሴራ እንዲሸለም የተደረገው  ወያኔዎችን “በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት” በማለት ሲያሞካሻቸው የነበረው በዓለም ውስጥ ሥርዓተ አልበኛነትና ስደተኛን በዕቅድ እንደ 'ሰደድ-እሳት' ያስፋፋ አደገኛው የዓለማችን ሰው “ባራክ ኦባማ” ነው።

በራሱ የአስተዳዳር መሪነት የተመሰረተው PSD-11 የተባለው የምስጢር ዘመቻ በተጠቀሱት አረባዊ እና እስላመዊ/አፍሪካዊ አገሮች ላይ ያጠነጠነ አገርን የማፍረስና መሪዎችን የመተካት ምስጢራዊ ዘመቻ መከናወኑ በተመራማሪዎች የተገኘ ሰነድ MANIFEST DESTINY - DEMOCRACY AS COGNITIVE DISSONANCE(F. WILLIAM ENGDAHL) ወዳጄ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ እንዳነብበው ከሰጠኝ መጽሐፍ ውስጥ ለማየት ችያለሁ 

ዘራፊዎቹ እና አገር አጥፊ ኮሎኒያሊስቶቹ የወያኔ መሪዎች ያገራችንን ነባራዊ እሴት ባሕል “ፍርስርሷን አውጥተው” ለዓለም ዘራፊዎች ሁሉ አጋልጠዋት የዘረፉት ገንዘብ ሁሉ ለማሸሽ እንዲመቻቸው ፊታቸው ወደ ቻይና ማዞር ከጀመሩበት ወቅት ጀምሮ ወደ ልጣን ያወጡዋቸውና በገንዘብ ሲደጉሙዋቸው የነበሩት አሜሪካኖች ነገረ ስራቸው ስላልተመቻቻው በምትካቸው ሌላ “አስበዝባዥ እና ታዛዥ” ቡድን መተካት ስለነበረባቸው የጃስሚን አብዮት Jasmine Revolution መሳይ ቀስ እያለ በኢትዮጵያ ሲቀጣጠል ቆይቶ እንደምታውቁት ያንን ‘ሕዝባዊ አመጽ’ በመጠቀም ሴረኛው እና ተንኮለኛው አብይ አሕመድ የተባለ “የኦሮሚያ እና የአፍሪካ ፕሮጀክት ንድፍ አቀንቃኝ ለበርካታ ወቅቶች” ውስጥ ለውስጥ ስልቱን በተጠና ዘዴ እየተሰራበት ቈይቶ በሚገርም ስልት ወደ ሥልጣን እንዲወጣ ተደርጓል።

ያማሞቶ የተባለው መሰሪ ጃፓናዊ አሜሪካዊ ዲፕሎማት “ፐራያ ስቴት” (ባይተዋርዋ አገር) ተብላ ለ27 አመት ተገልላ ሕዝብዋ ስታሰቃይ የኖረቺው የስቃይና የእሪታ ምድር ወደ ሆነቺው ወደ ኤርትራ በመጓዝ ኢትዮጵያ ውስጥ አብይ አሕመድ የተባለ ወታደራዊ ኮሎኔል ወደ አገር መሪነት እንደሚመጣ መወሰኑን የ ‘ሲ አይ ኤ’ ወዳጅ ለሆነው ለኢሳያስ አፈወርቂ አብስሮት ለሁለቱም ሕዝብ “ደንገተኛ” የሆነ የድምበር መከፈት እንደተከሰተ ሕዝብን 'በአፍዝዝ ወ አደንዝዝ' በስሜት አስክረው እምባ አራጭተው በማስጨፈር እንደገና በሕዝቡ ሕሊና በመጫወት ድምበሩን ላሁኑ እንዲዘጋ ተደርጓል።ኢትዮጵያ ወደቦቿን በባንዳ ልጆቿ ተባባሪነት የተፈጸመባት ሴራ ማጋገም አቅቷት ይኼው እስከዛሬ ድረስ አገራዊ መሪ እንዳይኖራት የመደረጉ ዋናው ሴራ እና ምልክቱ እንዲህ ያለ ቲያትር ማየት አንጀት ያሳምማል።

ይህ ምስጢራዊው PSD-11 ዘመቻ የሚካሄደው በብዙ ቅርንጫፍ ቢሆንም ዘመቻው ሲመራው የነበረው በኦባማ የአገራዊ ደህንነት ባልደረቦች እና በእነ ‘Dennis Ross, Samantha Power, Gayle Smith, Ben Rhodes, and Michael McFaul.” የተባሉ በበላይነት መዋቅሩን ይሚመራ ምስጢራዊ የዘመቻው መሪዎች ናቸው  እንደምታውቋት Gayle Smith ማለትGuerilla Mistress” በመባል የምትታወቅ  (“Guerilla Mistress To Obama Confidant; The Life And Crimes Of Gayle Smith (By Thomas C Mountain 01 December, 2010 Countercurrents.org የሚለው ጽሑፍ አንብቡ) በዚያ “Guerilla Mistress”  እየተባለች የምትታወቅዋ ይህች ሴት የወያኔው “ተወልደ ጃማይካ”  ውሽማ የነበረች ( በ1980 ዎቹ (በፈረንጅ ዘመን) በ ሲ አይ እና በመለስ ዜናዊ መካካል ምስጢራዊ ተልዕኮዎችን እንደ ድልድይ ሆና የሰራች እና ዛሬም አገራችን ውስጥ ሆና “ዩ ኤስ ኤይድ” በመባል የሚታወቀው በአሜሪካን ኤምባሲዎች ስር የተዋቀረ “የ ሲ አይ ኤ  “ሰብኣዊ ተራድኦ ድርጅት” (ለስለላ ስራ በሽፋን የተዋቀረ ድርጅት) በበላይነት ተጠሪ ሆና እየሰራች ያለች ከዚህ በታች ፎቶግራፍዋ የምታይዋት ሴት ነች።

 እንግዲህ እነዚህ ናቸው የአገራችንም ሆነ የዓረቡ ዓለም መፍረስ አቅደውታል የሚባሉት ሰዎች።

እነዚህ ሰዎች በሚመሩት ምስጢራዊ ዘመቻ ሩስያንም ሆነ ሌሎች አገሮችን ለማፍረስ በዋናነት የሚጠቀሙበት ስልት ኢላማ በሆኑት የአገር መሪዎች ላይ የመሪ ለውጥ ለማድረግ ሲፈልጉ በእዛው አገር ውስጥ “ሁማን ራይት፤ ዩ ኤስ ኤይድ…..መንግስታዊ ያልሆኑ በጎ አድራጊ ድርጅቶች፤ አይ ኤም ኤፍ (የገንዘብ አበዳሪ ድርጅቶች)…” የመሳሰሉትን በአገሪቱ ውስጥ እግር እንዲተክሉ ካደረጉ በላ የሚከሰቱ የሕዝቡ ተከታታይ ቅሬታዎች እንዲባባሱ በማድረግ ሚና ይሰጣቸዋል።  

ወደ ኋላ ስንመለስ ለምሳሌ የእንቅስቃሴው ተዋናይ የሆነ ‘በአረቡ አለም’ “እስላሚክ ብራዘር ሁድ” (ኣኽዋን) የተባለ “አይሁዶችን ለመምታት” ከናዚ ጋር ሲሰራ የነበረው፤ በኋላ ግብጽ ላይ እንደ አዲስ የተዋቀረው አኽዋን በዓረብ አገሮች እና እስላማዊ አገሮች ብጥብጥ ለማስነሳት ያለው ሚና አሜሪካኖች እንዴት እንደሚጠቀሙበት ከላይ የጠቀስኩት መጽሐፍ ማንበብ ይጠቅማል። የአኽዋን የሽብር ድርጅት መሪዎች ከዚህ ከተጠቀሰው የአሜሪካኖች የዘመቻ ዕቅድ በምስጢር በመገናኘት ከአሜሪካኖችየመሳሪያ እና ገንዘብ ዕርዳታ በማግኘት” በሕዝብ የሚሰሙ ስሞታዎች እና የሚታዩት ተቃውሞዎችን እንዲባባሱ በማድረግ እሳት ይለኩሳሉ። በአፍጋኒስታን፤ በኢራቅ፤ በቱኒዚያ፤ ግብጽ፤ሊቢያ፤በሶሪያ፤ሶማሊያ…በመሳሰሉ አገሮች “ኣኽዋን” አሜሪካኖች ከሚለግሱዋቸው ምስጢራዊ ድጋፍና ማበረታታት ተደግፎ አገር እንዲፈርስ መሪ እንዲለወጥ ያደርጋሉ።

ኢትዮጵያም ውስጥ የተደረገው ይህንኑ ነበር። ለበርካታ አመታት በባሌ፤በወሎ’ ባዲስ አበባ ፤በጅማ በበርካታ ኦሮሞ እና ምስራቃዊ ኢትዮጵያ “አኽዋኖች” ተስፋፍተው በርካታ ጥፋት አድርገዋል። ዛሬም ዘመናዊ ትምሕርት የቀሰሙ ወጣት “አኽዋኖቹ ለጊዜው አንገታቸውን አቀርቅረው ቢታዩም ቡዙዎቹ በተገንጣዮች በተለያዩ ድርጅታዊ መዋቅሮች እና ብዙዎቹም በፖለቲካ ተሰግስገው በምስጢራዊ ሽፋን “ፖለቲካል እስላም” በማካሄድ ላይ ናቸው።

ለምሳሌ ጃዋር የተባለ የሚናገውን ንግግር ሳያሸማቅቀው በግልጽ ማንነቱን ሳይደብቅ “የኦረሞ ፖለቲካ” ከፖለቲካል እስላም ጋር መያያዝ  እንዳለበት የሚሰብክ የቄሮ ኦሮሞ ዋና ተዋናይ “በሚደርሰበት አቤቱታም ሆነ ፔቲሽን/ ክስ” አሜሪካኖች ከአሜሪካን ያስወጡት ነበር። ሆኖም ያ ተቃውሞ ከአሜሪካኖች ፍላጎት ጋር ስለማይጣጣም ጉዳያቸው አይደለም። ብርሃኑ ነጋ አሜሪካዊ ዜጋ ሳይሆን መንግሥት በብረት ትጥቅ አስወግዳለሁ ብሎ አሜሪካ ውስጥ የሚዲያ ተቁዋም (ኢሳት)
መስርቶ እራሱም በፈለገበት ወቅት ያለ ምንም ስጋት የኤርትራን ፓስፖርት እና የአሜሪካ ፓስፖርት የመሳሰሉ እየተጠቀመ ሲዞር ምንም አልተነካም። ብርሃኑ ነጋና ብርቱካን ”የያስፖራ ማሕበረሰብ አንድነትን” ለማፍረስ ወደ አሜሪካ እንዲመጡ አሜሪካ ኤምባሲ ቪዛ ሲፈቅድላቸው ‘ሃይሉ ሻውል’ ወደ ካናዳም ሆነ በላም ወደ አሜሪካ እንዳይሄዱ ተከልክለው እንደነበር የሚታወስ ነው።

ለምን ቢባል እነዚህ ሁለቱ ሰዎች በአገራችን ላይ ወሳኝ ሚና እንዳላቸው አሜሪካኖች ያውቃሉ። በስልጣን ያስወጥዋቸው ስርዓቶች በማንኛውም ወቅት ከተሰጣቸው የታዛዥ አገልጋይነት ፈቀቅ ካሉ ፤ እነዚህን ግለሰበች በመጠቀም ተከታዮቻቸውን አመጽ እንዲያስነሱ በመገፋፋት ስርዓቱ እንዲለወጥ መሳሪያ አያደርጉዋቸውም ማለት አይቻልም።

ሁለት ክስተቶችን ልጥቀስ፤ ቱኒዚያ እና ኢትዮጵያ። ቦአዚዝ የተባለው ቱኒዚያዊ የሱቅ በደረቴ የቀን ሰርቶ አደር የሥራ ፈቃድ ማስረጃ ከሌለህ ጉቦ ስጠኝ ብላው ገንዘብ እንደሌለው ሲነግራት “ለመሸጥ ይዞት የነበረው ፍራፍሬ አትክልት በመድፋት ''ነገዱን እና የቤተሰቡ ማንነት አንስታ” መጥፎ ስም በመስደብ በጥፊ ስለመታቺውየደረሰበት ጥቃት አቤት ለማለት ወደ ባለስልጣኖች ቢሄድም እዛውም በባሰ መልኩ ስላመናጨቁት “ሕግ ባለመኖሩ በዚህ ብስጭትና ውርደት ከመኖር አገሬው አብዮት እንዲያስነሳ ማስታወሻ ጽፎ በመተው ቤንዚን እራሱ ላይ አርከፍክፎ ራሱን አቃጥሎ ገድሏል።” በዚህ የተነሳ ሲቀጣጠል የነበረው ተከታታይ የቱኒዚያ የሕዝብ ብሶት ለማቀጣጠያ መነሻ ሆኖ በመላ አገሪቱ አብየት ተነስቶ መሪው “ቤን አሊን” ተወገደ።

የቱኒዚያ አብዮት እንዲቀጣጠል ትልቅ ሃይል የሆነው የቦአዚዝ” ምክንያት ይሁን እንጂ ከበስተጀርባው ክርቢቱን ያቀጣጠለው በአሜሪካኖች (ናሺናል ኤንዳውመንት ፎር ዲሞክራሲ/National Endowment for Democracy) ተብሎ የሚጠራ የስለላ መዋቅር ድርጅት ‘የቱኒዚያ ወጣቶች ዲሞክራሲን ላማጎልበት’ በሚል ስም $131,000 ለዚህ Al-Jahedh Forum for Free Thought (AJFFT) የተባለ ‘አኽዋን’ ወጣቶች (አክራሪ ለሆነው ሙስሊም ብራዘር ሁድ) በመለገስ ነበር አመጹ ተቀጣጥሎ ቤኒ አሊ ከሥልጣን እንዲወገድ የተደረገው። ኔድ/ NED/ የተባለ ይህ የስለላ ድርጅት ለነሱ ብቻ ሳይሆን የጎዳና ነውጡን ለማፋፋም በእዛው በ2009 (በፈረንጅ ዘመን) (APES)፣ (CEMAREF)….” ለተባሉ ማሕበራትምህራን እና ለወጣቶች በሥልጣና ሽፋን ገንዘብ አፍስሷል። በዛውም ተሳክቶለታል።

በተመሳሳይ በደቡብ የአገራችን ክፍል አዋሮ በተባለ አውራጃ ዋካ በተባለ አካባቢ “የኔ ሰው ገብሬ” የተባለ መምህር “ፍትሕ እና አስተዳዳር” በኢትዮጵያ መበላሸቱን ያሰተዋለ ይህ አርበኛ ሕዝብን ያስነሳ ይሆናል በሚል እምነት ሕዳር 1/2004 ዓ.ም (በኛ ዘመን አቆጣጥር) እራሱን ቤንዚን አርከፍክፎ በማቃጠል እራሱን የሳዋ ይህ አርበኛ ሲሞት፡ ለሞቱ ሰበብ የሆነውን የዱርየዎቹ የወያኔ ስርዓት ለምን በጉዳዩ ማጣራት አላደረገም ብለው ፓርቲዎች መንግሥት እንዲያጣራ መግለጫ ከማውጣት ያለፈ ያሳዩት ሕዝባዊ ተቃውሞ አልነበረም። ሕዝቡም ከቤተሰቡም ሆነ ከሚያውቁት ባልደረቦቹ ጤነኛ እንደነበር እና በስርዓቱ እንዳልተደሰተ ሁሌም ይናገር እንደነበር በቂ መረጃ ቢዘረጋም ሕዝቡ እንደ ቱኒዚያው ቦኣዚዝ ሆ ብሎ የወያኔዎቹን ስርዓት ለመገርሰስ “አልተነሳም”። ምክንያቱም መለስ ዜናዊ የለየለት የአሜሪካ  ቅጥረኛ እና አገልጋያቸው ስለነበር ምስጢራዊው PSD-11 ዘመቻ መሪዎች ልክ ቱኒዚያ ውስጥ የተጠቀሙት የቡአዚዝ አይነት የጎዳና ነውጥ አቀጣጣዮች ኢትዮጵያ ውስጥም በገፍ ቢኖሩም በወቅቱ  ሊጠቀሙባቸው አልፈለጉም እና የየኔ ሰው ገብሬ’ ን መስዋእት ከንቱ ሆኖ እንዲቀር ሆኗል።

መለስ ዜናዊ ከሞተ በላ ግን በሚፈልጉት መንገድ እንደመለስ ዜናዊ  ዓይነት አፈ ጮሌ በየአፍሪካም ሆነ በየአለማቱ እየዞረ የሚያያጃጅል ምላጭ አፉ’ አገልጋይ ስላጡ፤ መለስ ዜናዊ ትቷቸው የሄደው የትግሬ “ጀዝባ” ጎሬላ መሪዎቹ ለዚያ ወንበር ስለማይመጥኑ ከመለስ ዜናዊ እጅግ የተለ የፖለቲከኞች እና የጤነኛ ምሁራን ሕሊናን የሚያደነዝዝ ‘በአፍዝዝ ወ አደንዝዝ’ ስልት የተካነ አብይ አሕመድ የተባለ አደገኛ የሕሊና ጠላፊ ወታደራዊ ኮለኔል እና የዶክተሬት ትምሕርት ያለው የስርዓቱ ኣባል የነበረ በነገዱ “ኦሮሞ” የሆነ አገልጋይ ስላገኙ ምርጭያቸው አደረጉት። ስለተሳካላቸውም ብዙ ሰው ያከበራቸው ዩኒቨረሲቲ ታዋቂ ምሁራን “እንደ አብይ የመሰለ ደፋር መሪ አላየሁም” እያሉ መሳቂያ ምሁራን ሆነው ሕሊናቸው ተጠልፎ ለማየት በቅተናል።

መለስ ዜናዊን የሚተካ ሰው በመገኘቱ ልክ እንደቱኒዚያው ጃስሚን አብዮት Jasmine Revolution (የኑሮ ምስቅልቅል እና ሰብአዊ ጥሰት ያስከተለ ተከታታይ ሕዝባዊ አመጽ) ስልት በመላ ኢትዮጵያ በመቀጣጠሉ የኦሮሞ እስላማዊ ሃይሎች፤ የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች እና ኦሮሞ ቄሮዎች ለዚህ ምቹ መሰሪያዎች ነበሩና አመጹ እንዲቀጣጠል እውን ተደረገ። ከመቀጣጠሉ በፊት በርካታ የተቃዋሚ መሪ ተብየዎች እና ጠባቡ እና አደገኛው ጸረ ኢትዮጵያ መረራ ጉዲና ለበርካታ ጊዜ በመመላለስ ስልጠና እንዲቀስም ተደርጓል። በእግረ መንገዱም ሚኔሶታ ድረስ እየሄደ ኦሮሞ ወጣቶች እና ተዋቂ ኦሮሞችን አንድነት አንዲፈጥሩ በማበረታታት “አገራችሁ ውስጥ ሪፑበሊክ ማቋቋም ባትችሉም ሙኔሶታ ውስጥ ‘ሪፑብሊክ’ መስርታችል…..” በማለት የወደፊቷን ኦሮሚያ ለሪፑብሊክ ምስረታ እንደምትሄድ ሲያስተምራቸው እንደነበረ ካንደበቱ የተናገረው ሰነድ አንድ ወዳጁ አስደምጦኛል።አብይ አሕመድ እና ጃዋር መሓመድም ምስጢራዊ በሆነ የኢመይል ግንኙነት ይጻጻፉ እንደነበር ጃዋር እራሱ ተናግሯል።

የእነ ቄሮ እና የነ ጃዋር እንቅስቃሴ ልክ እንደ ቱኒዚያው ሳይሆን በከፋ መልኩ “መረራ ጉዲና፤በቀለ ገርባ፤ዳውድ ኢብሳ፤ነጋሶ..” የመሳሰሉ የነገድ ፌደራሊዝም አስታክኮ ‘ኦረሚያ ሪፑብሊክን’ ሲሰብኩ ያንን ለማጠናከር “ዶ/ር እዝቄል ጋቢሳ የተባለ የፕሮተስታንት ፓስተር” የነበረ (ልጆቼን አማርኛ ባለማስተማሬ ኩራት ይሰማኛል ብሎ ያለ) ደግሞ በልዩ የስራ ምደባ ተሰማርቶ ከሜኔሶታ ወደ ኢትዮጵያ ሄዶ “የተወሰኑ የደቡብ” ነገዶችን በመሰብሰብ “እኛ ኦሮሞዎች እና እናንተ ‘ኩሽ’ የምንባል ዘሮች ነን። እኛ ኩሾች “ሰሜቲክ” ልሳን ከሚናገሩ ቋንቋ ተናጋሪዎች የተለየን ዝርያዎች ስለሆንን ልዩ ማሕበረሰብ መን ዓለም ስትፈጠር ወደ ነበርንበት ልዩ ዝርያነታችን ይዘን እንገንጠል እያለ በመቃዠት ሕዝብን እና ቤተሰብን የሚነጣጥል አደገኛ የዘር ፖለቲካ እንዲቀሰቅስ በቅጥረኛው አብይ አሕመድ ተፈቅዶለት የተጠቀሰው ሚስጢራዊው አገር የማፍረስ ዘመቻ አገራችን ውስጥ እየተጧጧፈ መሆኑ ለመረዳት አያዳግትም። በዚህ ዘመቻ መሳሪያ ሆነው የታጩ እና አገልጋዮች የሆኑ ነጭ ባንዴራ አውለብልበው እጃቸውን ለአገር አፍራሹ ቡድን አብይ አሕመድ በመስጠት አገር ውስጥ እንዲገቡ ተፈቅዶላቸው በተምበርካኪነት የዘመቻው አካል የሆኑት ነጭ ባንዴራ አብለውላቢዎቹም በማፍረስ ሂደት ላይ የሚኖራቸው ሚና በሚከተለው…. ክፍል ሁለት እንመለከታለን።….. ይቀጥላል………
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)