Saturday, April 10, 2021

ክፍል 2 የብርሃኑ ሱቆች

 

 

ክፍል 2

የብርሃኑ ሱቆች

ከጌታቸው ረዳ

(ኢትዮ ሰማይ)

4/10/2021



ከላይ በመጀመሪያ ረድፍ ያለው ፎቶግራፍ የሚታየው በጥቅምት ወር 2001 ዓ.ም በየወሩ የሚያሳትመው የግንቦት 7 የመፅሄታቸው ርዕሰ አንቀጽ እትም ላይ “ስልጣን እስካሁን አማራና ትግሬ እየተፈርረቁ ሲገዙ ኑረዋልና ወደሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ወደ ደቡብ እና ኦሮሞ መውረድ አለበት ሲል የጻፈው ነው።

እንዲህ ይላል፡

 

ኦባማ ተመረጠ ፤ ዓለም ተደሰተ። የኢትዮጵያ አምባገነን ግን ሃዘን ተቀምጧል።

 

በአገራችን ኢትዮጵያ ለአስርተ መቶዎቹ አመታት እየተፈራረቀ ሲገዛን የነበረው የአማራና የትግሬ ልሂቅ ቦታውን ለደቡብም ለኦሮሞም ለአኙዋኩም ለመልቀቅ ፈቃደኛ የማይሆንበት ምንም ምክንያት የለም…” የሚለው ር ዕሰ አንቀጹ ነው። ይህ የማቀርበው አንድ ጭጋግ ሕሊናው የጋረደው የግንቦት 7 ጀሌ ማስረጃው አሳያን ስላለኝ ይኼው አቅርቤአለሁ።

ግንቦት 7 የዛሬው ኢዜማ እያለ ያለው አማራው እስካሁን ስለገዛ አመራር መሆን አይችልም የሚል ሲሆን ከምንም በላይ ግን “አማራው ገዥ ነው/ነበር” በማለት ሌላው ሕዝብ በአማራው ላይ እንዲነሳበት የማድረግ ስልት የብርሃኑ ነጋ ተክለሰው ነው።

እንዲያውም አቶ አያሌው መንበሩ የተባሉ ጸሐፊ “እንዳውም ብርሃኑ ነጋ “ለአውሮፓ ሕብረት ፓርላማ አባላት’ ያቀረበው ጽሑፍ እስካሁን ኢትዮጵያን እየተፈራረቁ የሚመርዋት (በአሁኑ ወቅት ጭምር) ትግሬና አማራ ናቸው” ሲል አቅርቧል። ሲሉ ጽፈዋል። ብዙዎቻችሁ ታስታውሱ እንደሆነ በድረገጼ ላይም ሌሎቹ እንደ ሞረሽ ወገኔ የመሳሰሉ አማራ ድርጅቶችም ጭምር የተባበሩት መንግሥታት ስለ አንድ ጉዳይ አንስቶ በመግለጫው ብርሃኑ ነጋ የሚመራው የአማራ ድርጅት ግንቦ 7” በማለት እነ ብርሃኑ ነጋ ሲያምታቱ የተባበሩት መንግሥታትም ተቀብሎ ያንን የማምታታት ሴራ አናፍሶ ተቃውሞ ጽፈን ነበር።

ለመሆኑ ግንቦት 7 አመራር ውስጥ ስንት አማራዎች ነበሩ? ይህንን መረጃ ልስጣችሁ እና እኔን ከወቀሳ ነፃ አድርጉኝ፡

ይህ ጽሑፍ በፈረንጆች ዘመን በ2016 የጻፍኩት ትችት ነው። ታሪክ የዘገበው ለመፋቅ ቢሞከርም አይቻልም እና በኔ ዘገባ የተዘገበው የታሪክ ማሕደር ምን እንደተዘገበ እንመልከት። ወደ ርዕሳችን ከመግባታችን በፊት የግንቦት 7 የጎሳ ዘራቸው በዘሓበሻ ድረገጽ ከተለጠፈው ምንጭ ያገኘሁት እንዲህ ይነበባል።

WEDNESDAY, OCTOBER 3, 2018

 

ግንቦት 7 እና የኦነግ ግንኙነት በአማራ ላይ ሲያሴሩት የነበረው ሴራ እንደገና ላስታውሳችሁ! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)” በሚል ርዕስ ያቀረብኩት መረጃ እነሆ፡

 

1ኛ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ————ጉራጌ G7 Executive

2ኛ ዶ/ር ታደሰ ብሩ————-,ጉራጌ G7 Executive

3ኛ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ——–ከምባታ G7 Executive

4ኛ አቶ ንአምን ዘለቀ ———-ኤርትራና ኦሮሞ G7 Executive

5ኛ አቶ አበበ ቦጋለ————–ኦሮሞ G7 Executive

6ኛ አቶ ቸኮል ጌታሁን———–ጉራጌ G7 Higher leader Ship

7 ኛ አቶ አንድነት ሐይሉ ——–ጉራጌ G7 Council

8ኛ አቶ ሙሉነህ እዮኤል———ከንባታ G7 Council

9ኛ አቶ አበረ አዳሙ————-ኦሮሞ/ጎጃም/ G7 Council

10ኛ አቶአንዳርጋቸውጽጌ- ፀሃፊ = ኦሮሞ

 

እስኪ አሁን ደግሞ ኢዜማ ውስጥ የተካተቱት መሪዎች ማንነትና ውሸታቸውን ላስነብባችሁ!

ሌላው ግንቦት 7ን ተከትሎ የብርሃኑ ነጋ ጭራ ተከታይ የሆነው በማራኪዎቹ ሕሊና የተሰለበው የኢትዮጵያ ዜጎች ማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢ-ዜማ) አመራር አባል አንዳለም አራጌ በ21/05/2019 ሸገር ታይምስ ባልደረባ ከሆነቺው ‘መክሊት ኃብታሙ’ ያደረገውን ቃለመጠይቅ። ቀንጭቤ

ከሰጠው ቃለ ምልልስ አንዱን ልጥቀስ፡

 

21/05/2019 ሸገር ታይምስ ባልደረባ መክሊት ኃብታሙ በአዲሱ ፖርቲና በአመሰራረቱ  እንዲሁም በፖርቲው ራዕይና ግብ ፤ ከመመስረቱ በፊት ስለ ተከናውኑ ተግባራት ፤ በአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ፤ በ2012 ዓ.ም ይካሄዳል ስለሚባለው አገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ፣ በአዲስ አበባ ጉዳይና በተያያዥ ጉዳዩች ዙሪያ ከአንዱአለም አራጌ ጋር ተከታታዩን ሰፋ ያለ ቆይታ አድርጋለች፡፡

ጋዜጠኛዋ እንዲህ ስትል ትጠይቀዋለች

 

“ጥያቄ” ፤_--- 

 

 በርካቶች አሁን በየቦታው ያለውን ግጭት፣ግድያ እና መፈናቀል ከለውጡ ድክመት ጋር ያይዙታል፡፡ አንተ በዚህ ላይ ምን ትላለህ? ይህ ሁሉ የሚከሰተው ስር ነቀል ለውጥ ባለመምጣቱ ነው ?

 

መልስ-

 

አንድአለም አራጌ፡ እንዲህ ይላል፦

 

ሞት እና መፈናቀሉን ያመጣው ኢህአዴግ ነው ወይ? እኔ እጠራጠራለሁ፡፡አሁን ኢህአዴግ ከስሩ ባለመነቀሉ እንግልቱ መፈናቀሉ እና ግድያው በዶ/ር አብይ መሰሪነት ነው ብሎ የሚያምን ካለ እኔ በበኩሌ አይመስለኝም፡፡

 ይሄ ነገር እየተከሰተ ያለው በተለያየ አካባቢ ነው፡፡ አንደኛ የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት ታፍኖ እና ተጨቁኖ ነው የኖረው፡፡ ስለዚህ እንደሚመስለኝ የችግሩ መንስኤ ያገኘነውን ነፃነት በግባቡ ያለመጠቀም ነው፡፡ ለምሳሌ አንቺ አንድ አካባቢ ሄደሽ በቀናት ውስጥ የሆነ ነገር ተናግረሽ 40 እና 50 ሺህ ሰው ማሳለፍ የምትችይበት ሁኔታ ተፈጥሯል ፣ ነፃነት አለ መሰለፍ ይቻላል መናገር ይቻላል፡፡ ነገር ግን ያንን ነፃነት ለበጐ ነገር ሰዎች እየተጠቀሙበት አይደለም፡፡ ይሄ ነፃነትን በግባቡ ማስተዳደር አለመቻል ነው፡፡ ኢህአዴግ ከስሩ ቢነቀል ምን ትርፍ እናገኝ ነበር እኔ አላውቅም።”

አንዷለም ስለ ዶር ብርሀኑ ነጋና ስለ አማራ ብሄርተኛ..! እንዲህ ይላል፡

 

"የአማራ ብሄርተኞች ብርሃኑ ነጋን ነጥለው የሚዘምቱበት የብሄር አጥራቸውን እንዳያፈርስባቸው ሰግተው ነው። ሌላ የተለዬ በብርሃኑ ነጋ ላይ በማስረጃ የሚያቀርቡት ወንጀል የለም" (አንዱአለም አራጌ የኢዜማ ምክትል መሪ)።

ሥልጠን ከትግሬው እና አማራ ወደ ደቡብ እና ኦሮሞ ጋምቤላ መዛወር አለበት ብሎ ፖለቲካን በብሔር አጥር የሚሸነሽን ጎጠኛው ብርሃኑ ነጋ አንድአለም አራጌ ስለ ብርሃኑ ምንም እውቀት አንደሌለው ማሳያ ነው።

 

ቀጥሎ የዛሬው ኢዜማ አለቅላቂው የሺዋስ አሰፋን እንመልከት።

 

“መዲዮከር” ብለው የሚጠሩት እንግሊዞች ቃል “ሄዶ የማይጎዳ መጥቶም የማይረባው” የሺዋስ አሰፋ የተባለው ሌላው በእስቶክሆልም ሲንድሮም ተጠቂ የሆነ ፖለቲከኛ “አዲስ አበባን አስመልክቶ “ኦሮሚያና አዲስ አበባ በአንድ ቦታ መገኘታቸው ዕድል ነው እንጂ መጥፎ አይደለም” ሲል አክራሪ ሃይሎች የሚጠይቁት ያለው የባለቤትነት ጥያቄ ከማብራራት ይልቅ ርዕሱን ለማለሳለስ የሚሞክር ሌላው የብርሃኑ ነጋ አድናቂ ነው።

ያውም በሚገርም ሁኔታ የኢትዮጵያ ዜጎች ማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢ-ዜማ) ሊቀመንበር ሆኖ በተመረጠበት ወቅት የህወሓት ጁንታ በብሔር ስም ብዙ ሽፍጥና ተንኮል ሰርቷል" እያለ የሚቀባጥረው ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከተባለው የዜና ማዕከል ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ እንዲህ ሲል ኢትዮጵያን ልክ እንደወያኔ ሸንሽኗታል፡

እንዲህ ይላል።

 

"ኢትዮጵያ ውስጥ “ብሄር ብሄረሰቦች” የተፈጠሩት ቡድኑ ከመፈጠሩ ከሚሊዮን ዓመት በፊት ነው፤ ጁንታው ግን የብሄር ብሄረሰቦች ፈጣሪ መስሎ ታይቷል፤ ህዝቦቹ የነበሩና የሚኖሩ ናቸው፤" ከዚህ አባባል ምን እንደምትታዘቡ ፍረዱ። የሺዋስ በነገዱ ከአማራ እንደተወለደ ይነገርለታል። የብሔር ትርጉም ሐገር/መሬት/ ማለት ነው ብለው የግዕዝ አዋቂዎች የተረጉሙታል። የሺዋስ ግን ወያኔ የተጠቀመበትን “ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች” እያለ ወጣቱን ሲሰብክ ማድመጥ ያሳምማል።

አስደንጋጩ አባባሉ ደግሞ ይህንን አንብቡ በዚሁ በገለጽኩት የዜና ማሰራጫ ቃለመጠይቁ ነው እንዲህ የሚለውን ላስነብባችሁ፡

 "መንግስት በአሁኑ እርምጃ ዋነኞቹን ጥጋበኞች ልክ ስላስገባና ስላስተማረ ከዛ በኋላ ያለው መለስተኛ ጥጋበኞች ስርዓት ወይም አደብ ይገዛሉ ብዬ አምናለሁ፤" የሺዋስ አሰፋ Published on December 31, 2020 (ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

ልድገምላችሁ? ይሰማል አደል? ልድገመው ;……..

 

"መንግስት በአሁኑ እርምጃ ዋነኞቹን ጥጋበኞች ልክ ስላስገባና ስላስተማረ ከዛ በኋላ ያለው መለስተኛ ጥጋበኞች ስርዓት ወይም አደብ ይገዛሉ ብዬ አምናለሁ፤" የሺዋስ አሰፋ።

ይህንን ስትሰሙ እንዴት አያሳምምም? ያሳምማል እንጂ!

 

አህን ደግሞ ግርማ ሰይፉ የተባለው ድሮ በወያኔ ፓርላማ ተመርጦ የነበረ የፓርላማ አባል የዛሬ ኢዜማ አመራር አባል ምንነትን እንመልከት፡

ስለ መለስ ዜናዊ እንዲህ ይላል፦

 

“መለስ ዜናዊ ሞቷል፤ የሞተን ሰው የሰራውን ሓጢያት እያነሳን ማውራት እናቁም” እያለ ሲቦተልክ የነበረ እና በቅርቡም የእስክንድር ነጋን ሕዝባዊ ጥያቄ “የማየው በጎሪጥ ነው” ብሎ ያለን እና እንዲሁም ትግሬዎች የበላይነት ከተንጸባረቀበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 12 አብራሪዎች እና 4 ቴክኒሻኖች (ብዙዎቹ አማራዎች) ሲባረሩ ወጣት ግርማ ሰይፉ በሚያስደነግጥ አነጋገር “ካፕቴን አበርሃም ጥበቡ” የተባለ በነገዴ/በዘሬ ምክንያት ብዙ ግፍ ደርሶብኛል ብሎ“ፓይለት ሆኖ ባርያ ከመሆን አርሶ አደር ሆኖ በነፃነት መኖር” መሆን ይሻልል ብሎ አብራሪነቱን ትቶ ወደ አራሽ ገበሬነት የተለወጠው ግፍ የደረሰበት ዜጋችንን

“በማንነቴ ከሥራ ተባረርኩ ለሚል የነገድ ተጠቂ ኢትዮጵያዊው አማራው ፓይለት

 

"ዛሬ ጆሮ የለንም፣ ለምን ያኔ አላልክም? ብለን እንጠይቃለን። ፈርቼ፣ የት፣ ምናም ከሆነ መልሱ ፈሪ ከዚህም በላይ ይጠብቀዋል። ለፓይለትነት ከመውረድ በላይ የት እንዳያውርዱት ነው የሚፈራው። የት ሆኖ ልጅ ለማሳደግ ብለዋል ዶር ሀይሉ አርሃያ። ጎበዝ በብሄር ማንነት ተባረርኩ የፓይለቱን ከተቀበልኩ፣ የልደቱንም መቀበል ግድ ይለኛል። መውረድ አቃተኝ አልሞክረውም። "በመንጋ መንጫጫት እውነት አይፈጥርም። ፓይለቱ ወንድማችን በግብርናው ዘርፍ ምን አሰመዘገበ? ለአካባቢው አርሶ አደሮች ሞዴል ነበር? ወይስ ያው እንደ አነርሱ አራሽ ሆነ?" (አቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ)”

ሲል አማራ ስለሆኑ ስለ ተባረሩ አያሌ ፓይለቶች ግርማ ሰይፉ የተባለው የዛሬ ኢዜማ የያኔው የወያኔ ቱልቱላ በፓይለቶች ላይ ሲሳለቅ ነበር።

 

ሌላውን ልጨምርላችሁና ላብቃ ስለ መለስ ዜናዊ ሞት እና መለስ ከሞቶ በሗላ ወንጀሉን ስለሚያጋልጡ ዜጎች በመቃወም እንዲህ ይላል።

 

(1)አቶ ግርማ ሰይፉ የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሰብሳቢ እና የምክር ቤት አባል እንዲህ ብለዋል። የሰውየው አጀማማር “ያበሻ ሲንድሮም” ብየ የምጠራው “እንደ ሰው” የሚለው አጀማመር ነው እሳቸውም እንደ ብርቱካን እና የመሳሰሉት “እንደሰው” እያሉ ለሐዘናቸው የመሸፈኛ ጥበብ የሚጠቀሙት። ሂትለርም ፤ሙሶሎኒም “ሰው ነበር” ግን እንደሰው እናልቅስላቸው?”

“እንደሰው የጠቅላይ ሚኒስትሩ መሞት ያሳዝነኛል።ካሁን በሗላ ስለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ ነበር፤ እንዲህ ነበር ብሎ “ማውራት” ተገቢ አይደለም። ከዚህ በፊት የምናወራው ወሬ “እንዲህ ናቸው እንዲህ ናቸው” ብለን የምናወራው ወሬ ይማራሉ ብለን መልዕክት የምናስተላልፋቸው ነገሮች ነበሩ ፤ አሁን ግን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገር ካሁን በሗላ በታሪክ እሳቢ የሚያገኝ ስለሆነ (መውቀሳችን “ወሬያችን” ማቆም) እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን ለ21 ዓመት ያገለገሉ ስለሆነ ማረፋቸው ያሳዝናል።”

ይህ አባባል አልገረማችሁም? “ለ21 ዓመት ለኢትዮጵያ የለፉ፤የጣሩ፤ ያገለገሉ መሪያችን ስለነበሩ ማረፋቸው በጣም ያሳዝናል”? ሲል ያለቅሳል።

 

ምን እሱ ብቻ  

 

“ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ ነበሩ፤እንዲህ በደል ነበራቸው ሕዝቡን እንዲህ አደርገውት ነበር፤ የምንለው ወሬ ካሁን በሗላ ማቆም አለብን “ሲል የነበረ ማፈሪያ ሰው ነው። ዛሬም የኢዜማ አመራር አባል ሆኖ ቴድሮስ ፀጋየ (ርዕዮት ሚዲያ) የሚከተለው ጥያቄ አቀረበለት እንዲህ ሲል፡

“ሰሞኑን አፈሳዎች እና የጋዜጠኞች እስር በመንግሥት እየተፈጸመ ነው፤ የናንተ ፓርቲ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላል?”

 

ግርማ ሰይፉ መልስ፡

 

እኛ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ አይደለንም”

 

ሲል ዜጎችን መብት እወክላለሁ ብሎ የተደራጀ ድርጅት አመራር አባል ዜጎችና ጋዜጠኞች በመንግሥት ሲታፈሱ “እኛ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች አይደለንም” ብሎ ስለ ሰው መብት ግድ የማይሰጣቸው የሰው አረመኔዎች ግንቦት 7 ብለውም ይጥሩት ኢዜማ ሁሉም የዋሾችና የአረመኔዎች ስብስብ ድርጅት ነው የምለው ለዚህ ነው።

እኔ ጨርሻለሁ “ሸር” በማድረግ ሕዝቡን የማሳወቅ የናንተው ፈንታ ነው።

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)