Friday, December 23, 2022

ኡር-ፋሺዝም የወያኔ ታጋዮች እውነተኛ መገለጫ!! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 12/23/2022


ኡር-ፋሺዝም  የወያኔ ታጋዮች እውነተኛ መገለጫ

ጌታቸው ረዳ 

Ethiopian Semay 

12/23/2022



የኡር ፋሺዝም (Ur Fascism) ባሕሪ ምንነት የነገረን  ተመራማሪው 7 የውጭ አገር ቋንቋዎች አጣርቶ መጻፍና ማንበብ ችሎታ ያለው ጣሊያናዊው “ኡምቤርቶ ኤኮ” ነው። በትርጉም ካልተሳሳትኩ “ኡር ፋሺዝም” ዘላለማዊ ሺዝም ማለት ይመስለኛል አንግሊዞች cult of tradition የሚሉት።

ኡር-ፋሺዝም ምንም ብንሰለጥንም አገዛዞች የተለያዩ ልዩነቶች ቢኖራቸውም የኡር ፋሺዝም ባሕሪ ዛሬም በተለያዩ ተዋጊ ቢድኖችና መንግሥታት ተኮልኩሎም ሆኖ በይፋ የሚታይ “ዛሬም”  የሚገኝ “ልዩ” የሆነ ፋሺስታዊ ባሕሪ ነው። ዳሰስ ብታደርጉት ታገኙታላችሁ ይላል ተመራማሪው “ኡሜርቶ  ኤኮ”

ኡምቤርቶ ኤኮ በመጽሐፉ መግቢያ እንዲህ ይላል። በ1942 በአሥር ዓመት ዕደሜየ “ለሙሶሎኒ ክብር እና ለኢጣሊያ ዘላለማዊ እጣ ፈንታ እንሙት?” በሚለው የጥያቄ ርዕስ ላይ በኢጣሊያ ወጣት ፋሺስቶች መካካል በተደረገው የንግግር ውድድር “ብልህ ልጅ” ነበርኩና ባደረግኩት ንግግር አዎንታዊ አድናቆት በማግኘቴ  የብልህ ተናጋሪ ወጣት ሽልማት ተቀዳጀሁ። ይላል።

ኡምቤርቶ ኤኮ  << ህይወት>>  ለኡር-ፋሺዝም <<የህይወት ትግል የለም>> ይልቁንም  << ህይወት ለትግል ነው የምትኖረው>> ይላል።

 ስለዚህ  ይልና  

<< ህይወት ዘላቂ ጦርነት ስለሆነ በጸጋ ይቀበለዋል። ይህ ግን የአርማጌዶን ስብስቦችን ያመጣል ጠላቶች መሸነፍ ስላለባቸው የመጨረሻው ጦርነት ሊኖር ይገባል ስለሚል፤ በዛው ቦግ እልም እያለ ያልተቋረጠ የጸብና የጦርነት ጫሪነት እንቅስቃሴው ሂደት ዓለምን መቆጣጠር ወርቃማ ሰላምን ማምጣት ይቻላል የሚል ባህሪ አለው>> ይላል። ነገር ግን እንዲህ ያለው ሁሉንም ተቆጣጥሮ ሰላም የሚያመጣ ተስፈኝነት የተሳካለት ፋሽስት መሪ የለም>>

በማለት የኡር ፋሺዝም ባሕሪ ርቀት ይገልጽና መጽሐፉን ሳነበው፤ ከጠቀሳቸው የኡር ፋሺዝም 14 ባሕሪያቶች ውስጥ ቀልቤን የሳበው ከርዕሴ መግቢያ የለጠፍኩት በመጀመሪያው የ17 አመት የወያኔ የጫካ ጦርነት ዘመን “አማረ ታረቀ” የተባለ የወያኔ ታጋይ በውግያው ውስጥ ቀኝ እግሩ በከባድ የጥይት አሎሎ ተመትቶ ተቆርጦ በመውደቁ የተቆረጠው እግሩ አንስቶ ወደ ሰማይ በመቀሰር የሞት ብስራቱን በጸጋ በመቀበል ወዲያውኑ ህይወቱ አልፏል።    

እንዲህ ያለ ሞት ኡምቤርቶ ኤኮ አንዲህ ሲል ይገልጸዋል።

<< … በእንደዚህ ዓይነት አመለካከት ሁሉም ሰው ጀግና ለመሆን ይማራል በእያንዳንዱ አፈ ታሪክ ውስጥ ጀግና ልዩ ፍጡር ነው ነገር ግን በኡር-ፋሺስት ርዕዮተ ዓለም ውስጥ ጀግንነትብርቅ” አይደለም የተለመደ ነው ይህ የጀግንነት አምልኮከሞት አምልኮ” ጋር በጥብቅየተያያዘ” ነው። የፈላንግስቶች መሪ መፈክርቪቫ ሙርቴ” ("ሞት ለዘላለም ይኑር!") ይላሉ። ይህ የሞት አምልኮ ባሕሪ በአጋጣሚ አይደለም ፋሺስትባልሆኑ” ማህበረሰቦች ውስጥ ምእመናንሞት ደስ የማይል” አንደሆነ ይነገራቸዋል። አማኞች ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ደስታ ላይ ለመድረስአሳማሚው መንገድ” እንደሆነ ይነገራቸዋል። በአንፃሩ የኡር-ፋሽስት ጀግናየጀግንነት ሞትን” ይመኛል፣ ለጀግንነቱሞት”ምርጥ ሽልማት ተብሎ ይታወጃል። የኡር-ፋሽስት ጀግናለመሞት ትዕግስት የለውም””። ትዕግስት በማጣቱምሌሎች ሰዎችን” ወደሞት” ይልካል። >>

 

በማለት የ ኡር ፋሺሰቶች “ ቪቫ ላ ሙርቴ” - "ሞት ለዘላለም ይኑር!" እያሉ የሞት ቅድስና በመስበክ በጦርነት ወቅት እኔ ልሙት እኔ ልሙት እየተሽቀዳደሙ ወደ ጦርነት እሳት በመግባት ይሰዋሉ። ይህ የኡር ፋሺዝም ከ14 ቱ ባሕርያቶች አንዱ ሞትን በቅድስና እንዴት እንደሚያመልኩት ስንመለከት የወያኔ እና የሻዕቢያ ተዋጊዎች ባሕር የኡር ፋሺዝም ባሕሪ እንደተላበሱ ከሚዘግብዋቸው የታሪክ ማሕደሮቻቸው ለማወቅ ችለናል።

 የኡር ፋሺስት ተከታዮች ሞትን ስለማይፈሩ የሰው ልጆች የሞት ምንጭ በመሆን በራሳቸው ሞትን በቅድስና ስለሚቀበሉ በጦርነት ወቅት አስቸጋሪ (ጠንካራ ተዋጊዎች) ሆነው ይታያሉ። ጠንካራ ተዋጊነታቸው ምንጩ “ለመሞት ትዕግስት የላቸውም”።  ሌሎች ሰዎችን በመረሸንም ሆነ ወደ ሞት ለመላክ ግድ የሌላቸው ገራፊዎችና ጨካኞች ናቸው።  በሁለመናዊ መልካቸው ከኡር ፋሺዝም ገንዳ የተቀዱት የኦነጉ የአብይ አሕመድ “ኦሮሙማ” እና የመለስ ዜናዊ  “ህወሓት” ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ሱታፌ መታገድ አለባቸው እያልን የምንወተውተው ለዚህ ነው።

ሰላም ሰንብቱ

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay