Tuesday, December 15, 2015

ለጽንፈኞች ሲሰግዱ የነበሩ አንዳንድ ጸረ ወያኔ ሚዲያዎች ዛሬም በመስገድ ላይ ናቸው ጌታቸው ረዳ(editor Ethiopian Semay)ለጽንፈኞች ሲሰግዱ የነበሩ አንዳንድ ጸረ ወያኔ ሚዲያዎች
ዛሬም በመስገድ ላይ ናቸው
ጌታቸው ረዳ(editor Ethiopian Semay)
 አሜሪካ ኔቫዳ ክ/ሐገር ውስጥ ቬጋስ ከተማ የሚገኝ “ሕብር ራዲዬ” እያለ ራሱን የሚጠራ ሚዲያ፤ እንደተቀሩ የተቃዋሚ ሚዲያዎች ይህም “ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና ሉኣላዊ አንድነት በጎ የማይመኙ ለሕብተሰብ ሰላማዊ መረጋጋት እጅግ አደገኛ የሆኑ” ሰዎችን በመጋበዝ በሕብረተሰባችን ሕሊና ተቀባይነት እንዲኖራቸው፤ ሕብረተሰባችንን “ምከሩልን፤አስተምሩልን” በማለት በበጎ ዓይን እንዲመለከታቸውና የምናውቀው መርዛማ ዓላማቸውን ቀስ በቀስ በሕብረተሰቡ ሕሊና እንዲረጩ የአባሪ ተባባሪ ስራ በመስራት ላይ ነው።
 
ደጋግሜ እንደገለጽኩት ኤርትራኖችና ኦነግ/ጎች እንዲሁም የመሳሰሉ ጸረ ሰላም አሸባሪ ሃይሎች እንዲጎለብቱና ኢትዮጵያ አሁን ለደረሰችበት ውርደት አስተዋጽኦ ያደረጉ ክፍሎች፤ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፤ አውቀውም ሳያውቁም ቅስቀሳቸውን በማሰራጨትና በቀጥታም ከመስራቾቹም ግንኙነትና ንግግር በማድረግ “የሚመጣብንን አደጋ ባለማየት” አርቀው ማየት የተሳናቸው ኢትዮጵያዊያን ጭምር ‘ሚና’ እንደነበረበት “በጦርነትም ቦለቲካውም” ያደረጉት አፍራሽ ሚና ካሁን በፊት በርካታ ወገኖች የተቹበት ጉዳይ ነው።

ዛሬም እነሱን በመተካት ከነሱ በባሰ መልኩ *በይፋ* “በተቃዋሚነት የተሰለፉ ነፃ ሚዲያ ነን” ብለው ራሳቸውን የሚጠሩ የዜና ማሰራጫ “ሚዲያዎች” የተለያዩ የኢትዮጵያ ጠላቶችን ወደ ሚዲያቸው በመጋበዝ በጎ ስብዕና እየቀረጹ “ሕዝባችን በሚናገሩት ቅጥፈት እንዲሞኝ” ጎጂ የሆነ የጠላት ፕሮፓጋንዳ በማራገብ ስራ የተጠመዱበት ዓይነተኛ  ሙያቸው በተለይ ከቅንጅት ለሁለትና ሦስት መፈረካካስ ወዲህ የተያያዙት ስራ “ጸረ ኢትዮጵያ ክፍሎች” እና እንዲሁም “ዩዝ ፉል ኢደየትስ” በመባል ሲጠሩ የነበሩ፤ ወያኔ እንደ ‘አህያ’ ሲጭናቸውና ሲነዳቸው የነበሩ ግለሰቦችን በመቀባባትና በማመጎስ ስራ ላይ ተጠምደዋል። 

አብሮ በተመሳሳይ ደግሞ ኢትዮ-ሚዲያ የተባለው ድረገጽ “ኢትዮጵያንና አማራን ለማጥፋት የሚዝትና በርካታ አመራ ህጻናትና ሽማግሌዎችን በመጨፍጨፍ በዘር ማጽዳት ወንጀል የተካፈለ ከሻዕቢያ የማይተናነስ “ናዚያዊው ኦነግ” ኢትዮጵያዊ አርማና ኢትዮጵያዊ መንፈስ በታጀበ ሰላማዊ ሰልፍ ያካሄደ አስመስሎ ላዘጋጀው ቪዲዬ “ኢትዮጵያዊ ርዕስ” በመስጠት  ሕዝባችን ለማወናበድ የለጠፈው “ቪዲዮ” በርካታ ሰው ያስቀየመ መሆኑን በፌስ በኩል የሚተላለፉት ቅሬታዎች አንብባችል። ከዚህም አንዱ ታዋቂው “ተድላ አስፋው” ኢትዮ-ሚዲያን በመቃወም ለአዘጋጁ ‘ለአብርሃ በላይ’ የጻፈለትን የቅሬታ ደብዳቤ በኢ-መይላችሁ ደርሶአችሁል፤ ወይንም በሚዲያ ተለጥፎ አንባበችሁ ሊሆን ይችላል። እነዚህ እና የመሳሰሉ የተቃዋሚ ሚዲያዎች፤ እነ ተስፋዬ ግበረአብና እነ ጃዋር የመሳሰሉ “ይፋ የወጣላቸው” ጸረ ሰላም ግለሰቦችና ድርጅቶች ካሁን በፊት “ነፃ  ሚዲያ ነን” በሚሉ ሚዲያዎች ሰፊ ሽፋን አግኝተው እንደነበር ይታወሳል።

ዛሬም አብርሃ በላይ ፤ አቶ ተድላ አስፋው የጻፈለትን ቅሬታ ስታነቡ፤ ሚዲያዎቹ ካለፉት አስቀያሚ ፕሮፓጋንዳዎቻቸዉ ልምድ ወስደው ያንን ላለመድግም ከመጣር ይልቅ’ ዛሬም ያንኑ ጠላትን ከማመቻቻት ስራ እንዳልተቆጠቡ ከሚንጸባረቁ ውግዘቶች መረዳት ይቻላል። እነኚህ አብዛኛዎቹ የወያኔ ተቃወሚ ነን የሚሉ ሚዲያዎች፤ ለጸረ-አንድነት ሃይላት “የሚዲያ-ሽፋን” በመስጠት የኦሮሞ ሕዝብም ሆነ ሌላው ማሕበረሰብ በኦነግ ላይና በመሳሰሉ “ጸረ ሰላም ሓይላት” ላይ ሕዝባችን ጥልቀት ያለው ግንዛቤ እንዳይኖረው፤ ሌላ ቀርቶ፤ ጸረ ኦነግ የሆኑ በታላላቅ ጸሐፊዎች የተጻፉ ሰነዶችን እንኳ ለሕዘብ እንዳይነበቡ እያገዱ ለጠላት ግን ከፍተኛ አገልግሎት ሲሰጡ እንደነበሩ ብዙ ጊዜ ለአመታት የተቸነው ጉዳይ ነው። ዛሬም ያንኑ የለመዱበት “የሳብቨርሲቮቹ/አፍራሾቹ” መሳሪያ የመሆናቸውን ሁኔታ በመቀጠላቸው ስመለከት አጅግ ያሰዝናል። 

የእነዚህ “ነፃ ሚዲያዎች” ነን የሚሉ የብዙሃን መገናኛ አዘጋጆች አብዛኛዎቹ በዕድሚያቸው ወጣቶች ስለሆኑ ያገራቸው ሰቆቃና ውጣ ውረድ መከራ፤ እነሱ ከመወለዳቸው በፊትና እነሱ ታዳጊ ህጻናት በመነበሩበት ወቅት ስለነበር፤ የዛው ወቅት ተዋናዮች መሰሪነትና ብስለት በቅጡ አልተረዱትም። ያኔ የተሸረበብንን አደጋ አሁን ላለንብት መከራ የዳረገንን አንሶን፤ ዛሬ ደግሞ “ነፃ ጋዜጠኞች” በሚል ማታለያ ሚዲያ በመመስረት ደጋግመው እስኪሰለቸን ድረስ በዜና ማሰራጫ መድረኮቻቸው የሚጋብዙዋቸው ሰዎች ፍጹም የተዋጣላቸው ጸረ ሰላም እና ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑ ግለሰቦችን ነው።

መጋበዛቸው ላልቀረ፤ “የሚዲያ ሃላፊነታቸው” ለመወጣት ሲሉ፤ እነዚሀ ግለሰቦች የሰሩዋቸውን ወንጀሎች፤ የሰቡኩዋቸው አናካሽ ንግግሮቻቸው ወጥረው በመጠየቅ ሕዝብ እንዲያውቀው ከማድረግ ይልቅ፤ ሃላፊነታቸውን በመዘንጋት፤ ‘ያሰራጩት ጸረ ሰላምና የሽብር ቅስቀሳ ከምንም ሳይቆጥሩት’ ፤ የሰላምና የአንድነት ሰባኪዎች እያስመሰሉ በማቅረብ ፤ “ሕዝባችንን ምን ምክር ትምከረዋለህ?” እያሉ ሕዝባችን ከነዚህ ጸረ ሰላም ክፍሎች “መፍትሔ እንዲጠብቅ” እየነገሩት ነው። ይህ ከፍተኛ ክሕደትና “የጠላት መሳሪያ ሆኖ መገኘት የተለመደና አሳሳቢ ደረጃ እየሆነ በመሄዱ፤ አገር ወዳድ አርበኞች በቂ ትኩረት አንዲያደርጉና አፍራሽ ሚናቸው እስኪያቆሙ ድረስ ማውገዝ ይጠበቅብናል”። 

እነዚህ የጠላት መሳሪያ እየሆኑ ያሉት፤ ከነጃዋር እና ከመሳሰሉ ‘ተገንጣዮች’ ጋር የሚሽኮረመሙ “ነፃ ሚዲያዎች” በመሞዳሞዳቸው ምክንያት በነጃዋር የሚያገኙት መልስ ምስጋና ሳይሆን ዘለፋ ነው። እንዲህ ይላሉ፤

 “አበሾች ካለ እኛ በስተቀር ሕዝባቸውን የሚያስተምርላቸው የራሳቸው ምሁር ስለሌላቸው ሚዲያዎቻቸው ካለ እኛ አይሆንላቸውም”። “ብናስተምራቸውም ሕዝቡ የሚገባው አይደለም፤ ደደብ ነው።” ይልና ጃዋር፤ “ባስተማርኳቸው ቁጥር እንደውም ድድብናቸው እየባሳበቸው ሄዷል” እያሉ እነ ጃዋር ‘የልብ ልብ’ ተሰምቷቸው በይፋ ትምክሕታቸው ለኦሮሞ አድማጮቻቸው ሰብስበው በየአዳራሹ መሳለቂያና መሳቂያ አድርገውናል። 

ይህ ደግሞ ከነማስረጃ ነው የማቀርብላችሁ። እነ ሃብታሙ/ “ሕብር ራዲዮ” የመሳሰሉ ጋዜጠኞች ደግሞ እነ ጃዋርን በመጋበዝ ሕዝባችን ደደብ ስለሆነ፤ አስተምርልን እያሉ ለውርደት ዳርገውናል። ሕብር ራዲዮ እና የመሳሰሉ የጠላት ሟሟሺያዎች፤ ጃዋር “የአማራ ሚዲያ” በማለት ይጠራቸዋል።

ለማንኛውም ለሕዝብ ያለው ንቀት እንዴት እንደሚገልጸውና ስለ ራሱ ያለው የተሳሳተ ሙሶሎኒያዊ ባሕሪ (ባዶ እግራቸው የሚሄዱትን አቢሲኒያዎች ለማስልጠን ነው የተጠራሁት ብሎ ሙሶሎኒ እንዳለው ሁሉ) ጃዋርም እንዲህ ያለ ንግግር አይወጣውም ብላችሁ እየዋሸህ ነህ እንዳትሉኝ፤ ቪዲዮውን “The ugly truth about Jawar Mohammed” የሚለውን ቪዲዮ ለማስረጃ ጽሑፌን ስደመድም እለጥፍላችለሁ። ጃዋር መሐመድ ለኦሮሞ አድማጮቹ በኦሮሞኛ የተናገረውን ተተርጉሞ የተላለፈልን እንዲህ ይላል።

“ላለፉት 5 አመታት፤ኢትዮጵያ የምትባለዋን አገር ለኛም ለነሱም እንድትሆን ያላደረግሁት ሙከራ የለም። ሕዝቡ ግን የሚሰማ ሕዝብ አይደለም። በእውነት! ባስተማርኳቸው ቁጥር ይብስባቸዋል። (እዚህ ላይ አድማጮቹ ይስቃሉ)፤..እውነት እውነት! ነው የምላችሁ እየባሰባቸው ነው ያለው።”   
ሲል ሁሉም ሳቅ በሳቅ በመሆናቸው ደስታውን፤ትምክሕቱና ንቀቱ በፊቱ ላይ ልክ እንደ ‘በኒቶ ሙሶሊኒ’ ከውስጥ የገነፈለው የትምክሕተኛነት ስሜቱ ሲወጥረው በግልጽ ይነበባል።
ጃዋር መሐመድ አሜሪካ ‘ሳውዝ ዳኮታ’ ውስጥ በተዘጋጀለት “ኦሮሞ ፈረሰት” ዘመቻው ለማስፋፋት የስብሰባ አዳራሽ ተገኝቶ ያደረገው ደግሞ እንዲህ ይላል፡-

“በነሱ ሚዲያ ላይ ሄጄ የምቀርበው በሙያዬ ምክንያት ነው! I am an expert! ባለሙያ ነኝ! ዛሬም ይፈልጉኛል! ባይፈልጉኝ እንኳ እነሱ ናቸው የሚጐዱት! ለምን በነሱ ሚዲያ ላይ እንደምቀርብ ታውቃላችሁ? ጃዋር መሐመድ የተባለው የኦሮሞ ልጅ የሆነው፤ ኦሮሞ በልጦ ያወራል ተብሎ ሲሰማ፤ አገር ውስጥ ያለው የአሮሞ ልጅ ራስ/ሞራል ከፍ ይላል በሚል ነው!” 
(እዚህ ላይ ሞቅ ያለ ጭብጨባ ይሰማል)።

ቀጠል በማድረግም፤-

“አይታችሁ ከሆነ በአማራ ሚዲያ ላይ ከኦሮሞ ልጅ ጋር ተጨቃጭቄ አላውቅም፤Never! Never! ኔቨር! አማራ ሚዲያዎቹ ብዙ ጊዜ ይጋብዙኛል፤ነገር ግን ፈጽሞ ሄጄ አላውቅም።ምክንያቱም በሰው ቤት ውስጥ በሰው ቋንቋ፤ ከወንድም ጋር የምጨቃጨቅበት ምክንያት ስለሌለ ነው። (ጭብጨባ ይደመጣል) ከዚያ የበለጠ፤ ብዙ ጃዋሮች እንዲወጡና፤ በሰው ቤት የሚያወራ ብቻ፤በቤቱ እንደ ቤቱ፤……..”

 በማለት ፋሽስታዊ የሆኑ ባሕሪዎችን ለተከታዮቹ ሲሰብክ ታሪክ ዘግቦታል።

“ፉጎራ ኒውስ” እንዳለው “ይህች ዓለም ‘አንድ/1/’ ጃዋር እንዳይበቃት እንደገና ብዙ ጃዋሮች ታፍራልን?” ሲል እንዳንተው ዓይነት አደገኛ ፍጡር ከማራባት ይህች ዓለም ቢቀርባትስ፤ ምን በወጣት? ሲል “ፉገራ ኒውስ” የጃዋር መሐመድ ማንነት ግሩም በሆነ ቀልድ በተቀላቀለበት ቁም-ነገር “ለራስ ገናናነቱና ለፋሺስታዊ ጉራው” ተገቢውን መልስ ሰጥቶታል። 

አሳዛኙ ጉዳይ ግን፤ እንደ እነ ሓብታሙ የተባሉ የሕብር ራዲዮ አዘጋጆችና መሰሎቹ ይህንን እንደ ሙሰሎኒ በአጉል ስሜት እየተወጣጠረ በሕዝብ ፊት በካሜራ እየተቀረጸ “አጉል ጉራውን እየነዛ ራስን አጋንኖ ሲክብ፤ትንሽ ምንተ ሐፍርት የማይሰማው ወጣት” ወደ ኢትዮጵያዊያን ሚዲያ እየጋበዙ ሕዝባችንን ‘አስተምርልን’ እያሉ “ፖለቲካ ተንታኝ” የሚል ቅጽል ስያሜ በመስጠት ሕዝባችንን ለማስሰደብ ‘ሆን ብለው’ የሚጋብዙትን እንደ “ሕብር ራዲዮ” ያሉ ሚዲያዎች ሕዝባችን እንዲያወግዛቸው ጥሪ አቀርባለሁ።

ጃዋር በዚህ በራስ መወጣጠርና “አማራ ሚዲያ” ብሎ በሚጠራቸው በራዥ ሚዲያዎቻችን የሰነዘረው የራስ መነፋፋት ጉራ ሳይወሰን፤ እስላሞችና ክርስትያኖች በሐበሻ መስጊዶችና ቤተክርስትያኖች ከሐበሾች ጋር በመዋሃድ አብራችሁ እንዳትጸልዩ ሲል ሰብኳል። ኦሮሞ ለኦሮሞ መስጊድና ቤተክርስትያን ብቻ በመስራት ከሐበሻዎች ጋር አብሮ እንዳይጸሊ ከሓበሻ መራቅ አለበት በማለት እጅግ አደገኛ የሆነ የተነሳበት አክራሪ ዓላማውን ግልጽ በሆነ ንግግሩ ያረጋገጠልንን ደግሞ ይኼው፦

“ኦሮሞ ሕዝብ ስንል የኮሚኒቲ ብቻ ሳይሆን፤የኦሮሞ መስጊድ፤ የኦሮሞ ቤተክርስትያንና የኦሮሞ እድሮች መሰራት አለባቸው። ባለንብት ሐገር በተለይ፤ 5-10 ኦሮሞ ባለበት ቦታ፤ በሓበሻ ‘ቸርች’ ሄደን የምናስቀድስበት፤ በሐበሻ ‘መስጊድ’ ሄደን የምንሰግድበት ምክንያት የለም። ሁሉም ቦታ ይሄ አስፈላጊ እንደሆነ በጣም እወቁ! አወቁ!....”

(ጃዋር መሃመድ) ለኦሮሞ አድማጮቹ አሜሪካ አገር ውስጥ ከሰበካቸው ፋሺስታዊ ንገግሮቹ። ምንጭ (ፉገራ ኒውስ Fgugera News- Published on Mar 24, 2015

Fugera news (ፌገራ ኒውስ) መድረክ አቅራቢ በጃዋር ንግግር እጅግ በመሳቀቁ እንዲህ ይላል፡
“ውይ! ውይ! ጃዋር! ጃዋር! ይህንን ንግግረህስ አልሰማም።” በማለት ከላይ አንደምታዩት ‘ላለመስማት ጀሮውን ከከደነ በላ፤ ”በቋንቋና በጎሳ እዚህ ምድር ላይ መለያየታችን ሳይንሰን እንደገና ደግሞ በሰማይ ቤት በፈጣሪያችን ቤት እንድንለያይ ትፈልጋለህ? እግዚኦ መሐረነ!!!!!! ይኸንንስ ካንተ አልጠብቅም ነበረ። ሕዝቡን-ከፈጠሪ-ጋር-እያጣላ-ነው-መሰለኝ።”

ይልና፤ የፉገራ ኒውስ ዜና አቅራቢ የመጽሐፍ ቅዱስ እና የቅዱስ ቁርዓን ጥቅሶችን በመጥቀስ እንዲህ ይላል፡

*እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጣሪ* (ሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 17፡ 27) እያለ ክርስትያኑን ስያስተምራቸው፤
ቅዱስ ቁርአን ሙስሊሙን 

*እላንተ ሰዎች ሆይ እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ* (ሱለተ- አል ሑጁራት የቤት ክፍሎች ምዕራፍ 19፡43) ይላል።

ጃዋር በእንደዚህ ያለ ፋሺስታዊና መሰሪ ከፋፋይ ስብከት ኦሮሞዎቹን ሲያሳስት ቆይቶ፤ በሌላ መድረክ ደግሞ እንዲህ ሲል ይዋሻል፡

ከእነሱ በበለጠ … ( “ከእነሱ በበለጠ” እያለን ያለው እኛኑን ነው) ተከታተሉት ምን ይላል?
“ከእነሱ የበለጠ ስለ ሌላው ማሕበረሰብ ስለ ሃይማኖታዊ መቻቻል፤አብሮ መኖር ከነሱ በበለጠ ስሰራ እንደነበር፤ አሁንም እንደምሰራ የቃሉ። ያንን ለማክሸፍ “በወያኔ ፕሮፓጋንዳ ተደግፈው” እንደዚህ ያለ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲያደርጉ ነበር”
 
አሁንም የፉገራ ኒውስ መድረክ አዘጋጅ ‘ጃዋር የራሱን ንግግር ሽምጥጥ አድርጎ በመካድ የሚከታተለኝ ሰው የለም ብሎ ሕዝብን በመናቅ፤ 

ስለ ሃይማኖትና ማሕበራዊ አንድነት መቻቻል ከነሱ በበለጠ እንደምሰራ ሰለሚያውቁ ያንን ለማኮላሸት በወያኔ ፕሮፓጋንዳ ተደግፈው ስሜን ለማጥፋት በወያኔ ፕሮፓጋንዳ ተደግፈው ዘመቻ ከፈቱብኝ  ብሎ በመወሸቱ ‘የፉገራ ኒውስ’ አዘጋጅ እንዲህ ይላል፡

“what? ወያኔ! Really? Do you have to go there?” በማለት ደረቅ ዋሾነቱን አስገርሞት መዋሸት ላልቀረህ ሌላ የመዋሻ መንገድ እንዴት አጣህና ከፋፋይ መሆንክን የራስክን ንግግር እየመሰከረልህ እያወቅክ “በወያኔ ፕሮፓጋንዳ ተደግፈው” ወደ እሚለው አስገራሚ ምክንያት ለመስጠት አበቃህ ሲል ጠይቆታል።

ከክርስቶስ ልደት በፊት የጥንቷ ቻይና የንጉሱ “የፍትሕ አማካሪ የነበረው በወታደራዊ ጥበብ የተካነው “Sun Tzu” የተባለው “The Art of War” በሚባለው ገናና ምክሩ “ጣላትን ሳታውቅ እራስክን ብቻ ካወቅክ፤ በምታገኛቸው በእያንዳንዱ ድሎች ሁሉ፤ በዛው ልክ ሽንፈትክንም ትከናነባለህ” ይላል። እነዚህ ካፍንጫቸው ርቀት ማየት ያቃታቸው “የስነጽሑፍ፤ የቋንቋና የንግግር አሳማሪ” ጋዜጠኞች የተካኑበት ወይንም ያደጉበት ወይንም የናታቸው ቋንቋ በመሆኑ አማርኛውን በቀላሉ አሳምረው ስለሚጽፉና ስለሚናገሩት ፤ የጋዜጠኝነት ሙያ ትርጉሙ በቅጡ የሚያውቁት እየመሰላቸው፤ የጣለቶቻችንን ባሕሪና ማንነት ሳያጤኑ፤ ጠላትን ወደ ሚዲያዎቻቸው በመጋበዝ (ከጋበዟቸው ደግሞ ከመጋፈጥና ከማጋለጥ ይልቅ) ፤ ወይንም የነሱን ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት፤ ትግላችን ወደ ወያኔ እንዳናደርግ የተጣመመውን አካሄዳቸው ለማስተካከል ስንል ሕዝባችን እንዳያሳስቱብን በማሰብ ‘በነሱ ላይ’ ተጨማሪ ጉልበትና ጊዜ እንድናጠፋ ተገድደናል። ጣላቶቻችንም የዘረጉት ‘የሳብቨርሲቭ’ ዕቅድ አንዱ ትኩረታችንን በዚህ እንድንጠመድ ማድረጋቸው ቀዳሚ ትኩረታቸው ነው።

እንግዲህ ይህ ሁሉ ጉድ እያወቁ ‘ሕብር ራዲዮና መሰሎቹ” እንዲህ ዓይነት ዓይን ያወጡ ፍጡራን የግንዛቤ እጥረት ወዳለው ሰፊው ሕዝባችን “አማክርልን” እያሉ ጃዋርን እንደ ታላቅ ሰው አድርገው እየቀባቡ በማቅረብ፤ ሕዝባችን በዋሾች እንዲደናገር የአፍራሾች ሚና እየሰሩ ስለሆነ ሁሉም አገር ወዳድ ዜጋ እነዚህ ሚዲየዎች በማውገዝም ሆነ ደብዳቤ በመጻፍ፤ካልሆነም በጥንቃቄ እንዲከታተላቸው እጠይቃለሁ። 

ለምንድነው? ብለው የሚጠይቁ ሰዎች አሉ። “ተስፋዬ ገብረአብ” የተባለ የሻዐቢያ ሰላይና “ጃዋር መሐመድ” የተባለ እስላሙና ክርስትያኑን በማናከስ፤ እንዲሁም ኢትዮጵያ እንድትበጣበጥ በሕዝባችን ላይ እየዘረጋቸው ያለውን መሰሪ ተግባሮቹ “እንደጠላትነቱ” ማን መሆኑን በቅጡ ያልገባቸው ሰዎች፤ የጃዋር ማንነት ካለፈው ከጻፍኩት የቀጠለ ክፍል ሁለት ማቅረብ አስፈላጊ መሆኑን በቅርብ ያወያዩኝ አገር ወዳዶች ስለጠየቁኝ፤ አሁን ስለጃዋር በብዛት ሰምታችሁ የማታውቁዋቸው(ኦሮምኛ ቋንቋ እየተጠቀመ የተናገራቸው በመሆኑ) ለኦሮሞ ተከታዮቹ ያደረጋቸው ንግግሮቹን፤ ሕዝባቻን የማወቅ ግዴታና የማወቅ መብት ስላለው፤ ይህ ሰነድ በታሪክ እንዲመዘገብ ለረዱን አገር ወዳድ አርበኞች የሆኑ የ“ፉገራ ኒውስ/Fugera News” አዘጋጆችና/ Ethio Tube/ አዘጋጆች እጅግ፤በጣም እጅግ ከመጠን በላይ ከፍተኛ ምሳጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ።

ጃዋር መሐመድ ሕዝብ ለማሞኘት “ሁለት” መሰሪ ምላሶቹን ይጠቀማል። ኢትዮጵያዊያን ጋር ሲሆን፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ በማለት የሚደልልበት ንግግሩን ታደመጣላችሁ፤ ኦሮሞዎችንና ፤እስላሞችን ሲያነጋግር ደግሞ ኢትዮጵያዊያንን ያሞኘበትን አንደበቱ ተለውጦ ተቃራኒው ሲሰብካቸው ታደምጣላችሁ። ለማንኛውም፤ ቪዲዮውን ከመመልከታችሁ በፊት በታሪክ እንዲመዘገብ ለታሪክ መጽሐፍ ጸሐፊዎች እንዲያመቻቸው የጃዋር አደገኛ እና ፋሺስታዊ ንግግሩን ካለፈው ያቀረብኩት ጽንፈኛ ንግግሩን እጅግ ለየት ያለውን ንግግሩን በሚከተለው ቪዲዮ እንመለከታለን። 

ጃዋር ያደገው ራሱ እንደነገረን፤ “የኦነግ” ቅስቀሳ እየተመገበ ነው ያደገው።በዚህ ላይ አርሲ የተወለደ ይሁን እንጂ፤ ሕሊናውና ዝንባሌው ወደ ሶመሌው/ሐረር (ምሰራቅ) አካባቢ ያሉት ማሕበረሰቦችን ባሕል አጥብቆ እንደሚጋራ ካሁን በፊት በቃሉ ነግሮናል። ደጋግሞ እንደነገረን ኢትዮጵያ “የመቶ ምናምን አመት” (የራሱ ቃል ነው) እንዳላት ነግሮናል። ወያኔዎች ደግሞ ወደ 24 አመት ዕድሜ እንዳላት ነግረውናል። የሻዕቢያው መሪ ኢሳያስ ደግሞ ወደ 65 አመት እንዳላት ነግሮናል። ለማንኛውም የሰዎቹ ብስለት እንኳን የተወለዱባት የትልቋ ገናና አገር ዕድሜ በተገቢው ሊረዱት ቀርቶ፤ የወላጆቻቸው የትውልድ ሐረግ ማንነት በቅጡ የማያውቁ “ራሳቸውን በመካድ የሚመረቅኑ ፤ ራሳቸውን ያጡ”፤  የዚህ ዓለም ዳገት ለመውጣት ያልተዘጋጁ፤ ዳገቱ በተጠጋቸው ቁጥር የሚሸሹ፤ ዳገቱን ሳይወጡ እግርጌ ላይ ተጠግተው የቀሩ፤የሰነፉ ደካማ ፍጡራን ናቸው ።
The Ugly Truth about Jawar Mohammed
አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ getachre@aol.com )