ሁሌ ይሁን፤አልፎ-አልፎ-ብቻ፤-የታሪክ ፍጻሜ - የሚባል ነገር አላቸዉ ጸሐፍት ሲጽፉ። ዓለም ሸጋ-ሸጋዉን በልታ በራሷ ላይ ዘመቻ ከፍታ መጨረሻ ራሷን ስታጠፋ የሚታየዉ የመጨረሻዉ ትዕይንተ-ሕወት መሰለኝ ይሄ የታሪክ ፍጻሜ የሚሉት ጸሐፍቱ።
ደርሰንበታል-እኮ!አልደረስንበትም አትበሉ። ላንዶቻችን እኮ አርማጌዶን ነዉ። ከሀገር የሚያስኮበልል ጠላት በተቀመጠበት ምድር መኖር ሌላ “እንግላቴራ” (የእንግሊዝ ቋነቋ) ፍጠሩና ስሙን ስጡት እንጂ “ከአርማጌዶንነት አያልፍም።እኛ ትግሬዎች “ምጽኣተ-ዓለም” የምንለዉ እኮ ነዉ አርማጌዶኑ። ወይ እሩብን መንግድ ላይ አልያም ግማሹ ላይ የደረስን መሰለኝ። ሃማ ቱማ “ቃለ አጋኖ” የሚለዉ ዓይነት ባትሉኝ ሙሁራን ወደ “ጉቶነት” ሲለወጡ ወደ አርማጌዶን/ወደ ምጽኣተ-ዓለሙ የሚወስደዉ መንገድ ግማሽ መንገድ ጠረጋ እየተጠረገ መሆኑን እመኑኝ።
ብርቱ ሥራ ጠምዶኝ ነበር። ቪኦኤን ካዳማጥኩ ቆይቻለሁ። አረፍኩና ዳሰስኩት።ስለ ማዕቀብ መጠናከር በኢትዮጵያ ወቅታዊነት ይናገራል። ያዉም የማከብረዉ፤ዉዱ የቁርጥ ቀን ሰዉ፤ የምርጫዉ ስንሻዉ የዛ ምኡዝ ቃና፤ የኢትዮአዊነት ድምፅ! ደስ አለኝ!
የቪኦኤዉ አዲሱ እና ወንድሜ አቶ ምርጫዉ በቃለ ምልልስ ይወያያሉ። ምርጫዉ ከእንጀራ መግዛት አስከ የወያኔ ምግብ ቤቶችና ትልልቁ የወያኔ የንግድ አዉታሮች ላይ ማዕቀብ ማድረጉ ካሁኑ መጀመሩ ወቅታዊ ፤ሞራላዊ እና ሕጋዊ መሆኑን ያብራራል። ስለ ጤፍ ጉዳይ ብንመለከትም “ወያኔ በኮንተይነር እየጫነ “ኦሃዮ ሰቴት” በሳምንት ሁለት ጊዜ እያራገፈ ያከፋፍላል። ህዝቡ ተርቦ እያለ፤ ጤፍ እየጫነ ወደ እዚህ መላኩ በሰብአዊነትም በሞራልም ያስወቅሳል። ተከራካሪየ ካነሱት ዘንዳ ላይቀር አየር መንገዱንም በሚመለከት፡ በኢትዮያ አየር መንገድም ይሁን በማንናወቸዉም ማዕቀብ እንዲደረግ እንፈልጋለን፡ አስከ ዛሬ ድረስ ማዕቀብ በማድረግ አገዛዙን አልታገልነዉም። ሕበረተሰቡን ማለማመድ አለብን።ሕዝቡ ነገሩን አዉቆት፤ገብቶት፤ ለምን እንደሚያደርግ አዉቆት፡ከትንሹ ወደ ከፍተኛዉ የአገዛዙ ተቁዋሞች መሸጋገር አለብን። ደረጃ በደረጃ እየገለጽነዉ ነዉ እንጂ ብሎም ህዝቡ አስኪለማመደዉ ብለን እንጂ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ በፈቀደዉ መንገድ አገዛዙ ላይ ማኢቀብ አርጎ አገዛዙን ብያዳክምልን ደስታችን ነዉ”። ይላል ምርጫዉ።
“አየር መንገዱ ላይ ማዕቀብ መጣል አገሪቱን ለማንኮታኮት ነዉ። አየር መንገዱ ቢወደቅ ተመልሶ እሱን መሳይ ለማግኘት የሚወስደዉ አመታት አና ጉዳት ኢሕዴግ ከሚወድቀዉ በላይ ጉዳት ይደርሳል። ማእቀብ በወያኔ ላይ አይሰራም እና ወያኔን ተንከባክባችሁ ኑሩ የሚል ተማጓችም የደመጣል።
ተናጋሪዉ ምርጫዉ ስንሻዉንም በፊደላዊ ትዕቢት ሲጎንጥ -የአስተሳሰብ ጥረት ይጎድለዋል። ሲሉ ራሱን ባለ ጥራት አድረጎ ይመጻደቃል። "…ቃላት መደርደር ይቻላል።የኢትዮጵያ ሕዝብ እያለቀ ነዉ! ሰዉ እየሞተ ነዉ! ሰዉ እየተቀበረ ነዉ! የኢሕአዴግ መንግሥት እየገዛዉ ነዉ! እየጨፈጨፈ ነዉ!.. የሚሉት ስሜታዊ ቃላቶች መደርደር ይቻላል። ነገር ግን እኔ የምለዉ ነገር አይገባቸሁም። "input out put የሚባል ፈረንጂኛዉ የማይገባችሁ “ፋራዎች” ትግሉ ዉስጥ አትታገሉ። የኔ ልምራችሁ። እኔዉ ዶክተሩ! ይላል።
'አቶ ምርጫዉ ኢክኖሚከስ ትምርት እንዳላቸዉ አላቅም። (አዲሱ ጣለቃ ገብቶ- ለተራዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነዉ እየተናገርን ያለነዉ እና ለተራዉ ሕዝብ ልናስረዳዉ ያስፈልጋል። በዚህ ብንነጋገር”? 'እሺ.. እሺ…የምቀንኝነት እና የድህነት ፊሎሶፊ ነዉ ወይስ ፑር ፊሎሶፊ ነዉ? ወይስ ፊሎሶፊ ኦፍ ፖቭርቴ? ነዉ የሚናገሩት?። ድሃዉ ገበሬዉ ስሜቱ እየቀሰቀሱት ነዉ። አንዲንገነፍል! አንተ ድሃ ነህ ይሄዉ ..ይሄዉ ኢሕአዴግ ስልክህ እየተጠቀመብህ ነዉ ….እያሉ።…’ “ ማእቀቡ በአየር መንገዱን በሚመለከት፤ የሰዉ ሃይል ትሬይኒግ ለማድረግ አገሪቱን ያለ አየር መንገድ ሊያሳጣት ነዉ። በተለይ የካርዱን ስልክ ይሁን የእንጀራዉ ማእቀብ ማድረግ የኔን መብት መጋፋጥ ነዉ።የፈለገዉ ሰዉ ሄዶ መብላት ይችላል። ይህ ለወያኔ “ኤ ድሮፕ ኦፍ ዋተር ኢን ዘ ኦሽን” ነዉ።ለመሆኑ የሄ ጥሪ የሚያደርገዉ ማን ነዉ? ይህ ማዕቀብ መሣርያነቱ “ታንክ ነዉ? ጩቤ ነዉ? ምንድ ነዉ የሚያደርገዉ? ስለዚህ ለኔ ስሜት አይሰጥም። ማዕቀብ አይሰራም፡ ጊዜዉ አይደልም። ወያኔንን መተንኮሻም አይደልም። ገፍቶ መጣያም አይደለም። የፕርንሲፕል እጦት ነዉ!>> ብሎ ሲጨርስ
ፈረንጁ “ፓራፍሬዝ” እንደሚሉት ነገር ላጠቃልለዉና...
ጉቶዉ ጉቶ ብቻ መሰላችሁ? ያዉም “ዶክተር!”፡ ብቻ መሰላችሁ ከታራ ሕዝብ መነጋገር የሚጠየፍ ዓባይ ወንዝ ተሸክሞ አዙሮ አዙሮ ከሕዝብ አስርቆ ዕሩቅ የወረወረዉ “ጎቶ”።ያዉም መለስ ዜናዊ እና ካሱ ኢላላ ለካቢነት አጩኝ የሚለን ደ/ር ጎቶ!
“አየር መንገድ ሰርቼ ነበር” ይልና ደርግን ወቅሶ ወያኔን ሲሸልም ይደመጣል።አላወቀዉ-እንዶህ-እንጂ መዝገቡ የሚለዉ ሌላ እሱ የሚያወራዉ ሌላ።
አስኪ- “የምሁራን መራቆት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ በጦቢያ ላይ ከዓስር ዓመት በፊት በ1991 የቀረበዉ አቶ ወልዱ ሃይሉ የተባሉ ጸሃፊ ስለ አየር መንገዱ ያሉትን በጥቂቱ ልግለጽ።
<የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጎሳ ፖለቲካን በመቃወም በገዛ ፈቃዳቸዉ ሥራቸዉን የለቀቁ ከ5 በላይ የሚሆኑ አብራሪዎችም ነበሩ። <<አምባገነን እና ጭራቅ> እተባለ በወያኔ በሚወገዝዉ በደርግ ሥርዓት እንኳን የአገራቸዉ አንድነት ጥያቄ ዉስጥ በለመግባቱ፤ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ባላቸዉ ፍቅር፤ በዝቅተኛ ደሞዝ አየር መንገዱን ያገለግሉ እንደነበር ይታወሳል። በአሁኑ ጊዜ የሌላ አገር አይሮፕላን ያበራሉ።
ጉቶዉ ይህነን ታሪክ ያዉቀዉ ይሆን? የዉሸት ቃላት እየደረደራችሁ “ወያኔ ሕዝብ ጨረሰ ፤ሰዉ አለቀ እያላችሁ በስሜት በምቀኝነት ገበሬዉን ትቀሰቅሱታላችሁ የሚለን ይህ “ጉቶ” “የጎሳ ፖለቲካ አላሰራም አለን ብለዉ ያነን በመቃወም ከ 5በላይ የንግድ ኢይሮፕላን አብራሪዎች አገሪቱን ለቀዉ ለባዕድ ተቀጥረዉ ሲሰሩ አየር መንገዱ አልተጎዳም ሊለን ሊሆን? የነዚህ አገር ጥሎ መሰደድሳ የኛ የስሜት የዉሸት ቅስቀሳ ይሆን?
The worlds 20 worst living dictators ተብሎ በዓለም ምድር ዉስጥ ከተመዘገቡት ጭራቆች ባንዳዉ “መለስ ዜናዊን” በጦርነትም አትዋጉት፡ በኢኮኖሚ ማዕቀብም መታገል ሕዝብን ማደህየት አገር ማራቆት ነዉ ብሎ ሲከራከር፡ “ጉቶዉ” በሰማዩ-ዓለም ዉስጥ እየኖረ ወይንስ የሀገሩን ሁኔታ አያቅም?
አየር መንገዱን በማዕቀብ ማንኮታኮት በሰዉ ሃይል ሥልጠና ምክንያት ወደ ሗላ ልንሄድ ነዉ ይቅርብን እያለ ሊሰብክ ይሞክራል። አስተማሪዎቹ ያላስተማሩት አሱ ያልገባዉ የማያዉቀዉ አነድ ነገር አለ። አገር እየለቀቀ የሄደዉ በጣም አንቱ ሚባሉ ወደ አምስት ሺህ ሳይነቲስቶችና ሃኪሞች ጠበብቶች ኢትዮያን ለቀዉ ባእድ አገር እያገለገሉ መሆናቸዉን አያወቅም!? እነኚህስ በእኛዉ ማዕቀብ ወይስ ጉቶዉ እንደሚለን ቃላት ደርድረን ከሀገር አንዲወጡ ያደረግናቸዉ ናቸዉ?
እስኪ ልጨምር 'ስደተኝነት በፓለቲካ ወይም ባኮኖሚ ችግር ምክንያት ሀገር ለቆ መዉጠት ብቻ አይደለም። መዉጫዉ በር እየተዘጋበት እንጂ ቢወጡ የሚሄዱበትን አቅጣጫ ባለማወቅ እንጂ በመንፈሳቸዉ የሸፈቱ የሞራል ስደተኞችና የሕሊና ድርቅ ያጠቃቸዉ ኢትዮጵያዉያን ቁጥር ከ50ሚሊዮን በላይ ነዉ።>> ጦቢያ፤ቅጽ 5፤ቁትር 8/1990)'
በሚል ርዕስ አዲስ ትርቢዩን ጋዜጣ በአምዱ ላይ ቀረበ ያሉትንም ልጥቀስ። << የተሻለ ዕዉቀትና ብሩሕ አእምሮ ያላቸዉ ሰዎች አገራቸዉን ጥለዉ ወደ ዉጭ አገር ከተሰደዱ እንዴት ነዉ የአገር መሪዎችን ማግኘት የሚቻለዉ?>>
“በጉቶዉ” ጭንቅላት አገሪቱ እየተራቀተች ያለችዉ ጤፍን ወደ ኦሃዮ ማስጋዙ ብቻ መስሎታል። ለወያኔ ሥርዓት አይበጁም የተባሉ ለፓርቲዉ ዓላማ ዕንቅፋት ናቸዉ የሚባሉ የሕክምና፤የሳይንስ፤የሕግ፤የኢኮኖሚክስ፤ወዘተ፤ባለሞያዎችና ጋዜጠኞች በረቀቀ ስልት አገራቸዉን ለቀዉ እንዲሄዱ ግፊት ተደርጎባቸዉዋል። ቢወጡም ጤና አይሰጡኝም ያላቸዉን ምሁራንም በሰበብ አስባቡ ወህኒ አጉሯቸዋል። እንዲህ ዓይነቱ አፈራሽ ዕርምጃ አገሪቱን ያወደማት መሆኑን በዛዉ በጉቶዉ ጭንቅላት ዉስጥ የለም።
ይህ ሁሉ ምሁር በእኛዉ የስሜት ቅስቀሳ በቃለት ድርደራ ከተጋዘ እማ ዶክተርነቱ ለእነ ምርጫዉ ለእኛዉ ለተራ ህዘቦች እንጂ "ለጉቶቹ አይገባም ማለት ነዉ።
ያች አገር እየተገዛች ያለችዉ በዉጭ ሃይሎች የተደገፈ አገር አፍራሽ “ኤርትራዊ ቡድን” መሆኑን እናዉቃለን። ለዚህ ነዉ አየር መንገዱ ቢወድቅ ነጮች ቢሊዮን ዶላሮች ወያኔን (አሱ ኢሕአዴግ ይለዋል) በማግስቱ ያሰታቅፉታል። የሚለን “ዶክተር በሉኝ” ዶክተር ክንፈ ሚካኤል አስራት-!
ህዝቡ “ኤርታረዊዉ የጭራቁን ቡድን” የተቆጣጠራቸዉ ምጣኔ ሃብት በማእቀብ ሲያንቀዉ ፈረንጆቹ ከረዱት ለፈረንጅ ያደረን መንግሥት አታሰወግዱትም አትድከሙ፤ ጊዜዉ ዛሬ አይደለም፡ ሌላ 17 ዓመት አስቲ ስጡት፡ የፈለገዉ ይንቀባረርበት!ብሎ የሕዝብን ትግል የሚያጣጥል አደናቃፊ “ምሁር” በቁሙ የተገነዘ ተንቀሰቃሽ ሬሳ መሆኑን መቀበል አለበት።
ይሄን ትልቅ ከረጢት ክፈቱና ያገሪቱን ችግር ዳስሱት። በዝሁ ልሰናበታችሁ። “ከትልቁ ያገሪቱ ዩኒቨርሲቲ 42 ሙሁራን << በብቃት ማነስ> ሽፋን ተባርረዉ ከአለም ቀዳሚ በሆኑት ዩኒቨርሲቲዎች በአዉሮፓ እና አሜሪካ ምድር መጥተዉ ሲቀጠሩ አገር እንዲፈርስ ያደረገዉ የተባረሩት ምሁራን ወይስ “ጉቶዉ” አትንኩት እያለ እተካላከለለት ያለዉ “የጉቶዉ” አለቃ “ወያኔ”?
ቅድም ያነሳሁዋቸዉ ምሁር አቶ ወለዳይ ሃይሌ በወያኔ ምክንያት ሙሁራን እየተሰደደዱ አገሪቱ እየፈረሰች እንዳለች ያመለከቱበትን አንዱን ልድገም እና ላጠቃል።”በእርሻ ኢንዱስትሪ ልማት በባንክ ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉ 15 የሚሆኑ የድርጅቱ ከፍተኛ ባለሞያዎች ተባርረዋል። እነዚህ ባለሞያዎች በምጽዋትና በእንስሳት ሳይንስ ስምንት የመጀመሪያ ዲግሪያቸዉ አራት ሁለተኛ ዲግሪያቸዉ የፈጸሙና ሦስት በዶክትሬት ደረጃ የተመረቁ ናቸዉ። ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚደርሱ ዜጎች ኑሮአቸዉ በአሜሪካ እና ባዉሮፓ መስርተዉ ዕዉቀታቸዉም ለባዕድ ሲሳይ ስለመሆኑ ይታወቃል።
ይህ ጉድ ያሳሰባቸዉ አንድ የመንግሥት ባለስልጣን እንዲህ አሉ። የተባለዉ እናንብበዉ
የኢትዮጵያ የትምህርት በጀት በሙሉ ለአሜሪካ ትምህርት በጀት ድጋፍ ሰጪ ከመሆን ዉጭ ምንም የፈየደዉ ነገር የለም ብሎ ማሰብ ይቻላል። ምክንያቱም ለኢትዮጵያ ሃብቷ ያዋለችዉ ወደ አሜሪካ ለሚነጉደዉ ዕዉቀት ነዉና። ይህም ከተማረዉ ሰዉ ሃይል ዉስጥ የተሻሉትን የሚነጥቅ ሂደት ነዉ' ይላሉ።
እንግዲህ በወያኔ ንግድ እና የገቢ ምንጮች ማእቀብ ማስተላለፍን አገር ያፈርሳል ወይስ ግማሽ ሚሊዮን ምሁር እና 4ሚሊዮን ኢትዮያዊ ዜጋ ለስደት ዳርጎ፤ሀገሪቱን ምርጥ ምሁራኖቿን አሳጥቶ ሀገሪቱን እያፈራረሰ ያለዉ ቅጥረኛ ስርዓት የሚያደርሰዉ ጉዳት ይበልጣል? “ጉቶዉን” ትቼ ፍርዱን ለናንተዉ ለአንባቢያን ልተዉ።
!አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅ! www.ethiopiansemay.blogspot.com