(Getachew Reda Editor Ethiopian Semay) ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)
ክፍል (1)
ማሳሰቢያ፡ (July 4/2014)
ይህ ትችት ሞረሽን የሚወክል ወይንም
ማንኛውንም የፖለቲካ ቡድን የሚወክል ሳይሆን የኔው የራሴ የጌታቸው ረዳ አቋም እና ቅሬታየን የሚገልጽ ነው። ይህ ከዚህ በታች በማሳሰቢያ
የጨመርኩት ለወደፊት የምተችበት ትችት፤ በሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት ሳንሆዜ ከተማ በካሊፎርኒያ ስቴት July 3/2014 በእንግዳነት
ተጋብዤ ያዘጋጀሁትን ንግግሬን ከጨረስኩኝ በሗላ እቤት ሄጄ ለአንባቢዎቼ የጨመርኩት እንጂ በስብሰባው ያደረግኩት ትችት አይደለም።
ይህ ትችት በሚቀጥለው ጊዜ ሳገኝ በሰፊው ለአንባቢዎቼ የሚቀርብ ነው።
ዛሬ ያየሁት ጉድ ካሁን በፊት በወሬ ስሰማው የነበረውን ወሬ በእርግጠኛበነት “ኢሳት” የተባለው ሚዲያ በማፊያዊ የፖለቲካ አቋሙ የወያኔ ማፊያን ቡድን ይተካል የሚባልለት የግንቦት 7 ቡድን አገልጋይ መሆኑን እና ኢትዪጵያዊ ማሕበረሰብን “በከፋፍለህ በትናቸው” ሴራ እንደተሰማራ ባይኔ ያየሁትን ዝርዝር ትችት አቀርባለሁ።
የሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት ስብሰባ በተካሄደበት ቀን እና ቦታ እንዲሁም ሰዓት “ኢሳትም ” ያንኑን በመተናኰል የራሱን ስብሰባ ጠርቷል። ይህ ኢሳት የተባለው በውጭ ሃይላት እና በውስጥ ሃይላት እየተደጐመ “የኢትዮጵያን ሶሻል ኦርደር ለማናጋት በተሰለፉ ሊሂቃን” በኩል በተቀነባበረ ጮሌነት እና ሴራ ሕዝብን እያጃጃለ ያለው የሳተላይት ጣቢያ “የአማራውን ችግር” ኢትዮጵያዊያን አንዳያዳምጡ የሞረሽ ዝግጅት “ሰዓቱን፤ዕለቱን እና ቦታውን በተንኰል ተጫርተውታል።
ይህ ይቅር የማይባል ወያኔ “በስፖርት፤በፖለቲካ እና በፈስቲቫሎች” የሚያደርገው “የመጫረት እና የብተና ሴራ” ኢሳት እና መሰል ተቃዋሚዎችም “ወያኒያዊ” ስልት በመቅዳት የአማራውን ሕብረተሰብ ችግር እና እሮሮ “ሞረሽን” በመጫረት እንዳይደመጥ ሙከራ ማድረጉ ኢሳት እና ግንቦት 7 የማያውቅ ሰው የሚያስገርም ቢሆንም፤ የኦሮሞው ነገድ ተወላጅ የሆነው ጸረ አማራው እና የሻዕቢያው “አፈኛ” የነበረው አንዳርጋቸው ጽጌ እና ‘ብርሃኑ ነጋ’ ቅንጅት ለሁለት ከከፈሉት በሗላ የተከተሉት “የብተና ሴራ” ለምናውቅ ብዙም አላስገረመንም።
ከጐንደር የአማራ ነገድ የተወለዱ እነ ታማኝ በየነ እና አበበ ገላው ወያኔ ያዘጋጀው ስብሰባ ይመስል የአማራውን ሕብረተሰብ ስብሰባ “በጐን በጐሪጥ” እየተመለከቱ አዳራሹን እየጣሱ እነሱ ወዳዘጋጁት አዳራሽ ሲያመሩ አይቼ ከመደንገጤ የተነሳ ማመን አቅቶኝ ጋዜጠኛው አበበ ገላውን “ሰላም አበበ፤ ጌታቸው ረዳ ነኝ ብየው” እንደሌላ ሰው ጨብጦኝ ሊሸሸኝ ሲል “ሆን ብዬ፤ በግድ ጐትቼ ስሜው” እንዳላነጋግረው ሰግቶ ይሁን ወይንም ነገሩ በልገባኝ ወደ ኢሳት ስብሰባ ተጣድፎ ሄደ። በነገራችን ላይ እኔ እና አበበ በአካልም በኢመይልም (እስከ ትናንት በስቲያ በታማኝ በየነ የግል ጉዳይ የተነሳ በኢመይል ተገናኝተናል) በደምብ የምንተዋወቅ ሰዎች ነን ለማለት ነው። ጋዜጠኛ አበበ ገላው ስለ ሰብአዊ መብቶች መለስ ዜናዊን እና ኦባማን የተቋቋመ ሰው የራሱን ነገድ የሆነው “አማራ ባዘጋጀው አዳራሽ ላለመገኘት፤ላለመዘገብ፤ትችት ላለመስጠጥ ያገደው ምን ይሆን?”
የኢሳቱ እና የግንቦት 7 ሰው ነው የሚባልለት አቶ ታማኝ በየነ ለዚሁ ጉደኛ ጣቢያ ገንዘብ አሰባስባለሁ በሚል ከሁለት ወር በፊት አውስትራሊያ (ሜልቦርን) ድረስ ሄዶ ሳለ “ሁለት የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ” አረጋዊያን በቃለ መጠይቅ ባነጋገራቸው ጊዜ “ስለ የወልቃይት አማራ ሕብረተሰብ መከራ ሲገልጹለት፤ ካሁን በፊት ሰምቶት አንደማያውቅ ሳይሸሽግ ሲነግራቸው” በሰማሁት ጊዜ አንድ የትግርኛ ምሳሌ አንዳስታውስ አደረገኝ። ምሳሌውም አንዲህ ነው። “ዓሻ ጽቡቕ አሎ- ዘመድ ዓሻ ከፊኡዎ አሎ” (ሞኝ ተስማምቶታል፤ የሞኙ ዘመድ ከፍቶታል።” ይባላል።
ቃለ መጠይቁን በራስዎ ጀሮ እንሆ ያድምጡ፦ESAT Tikuret/Focus - Tamagn Beyene talks to elders from Wolkayit/Tegede in Australia | April 2014 “በጭምጭምታ ነው የምንሰማው እያለን ያለው ታማኝ የራሱ የጎንደር ወገኖቹ የወልቃይት አማራ ሕብረተሰብ ችግር እሱ ባይከታተለው እንጂ “በጨምጭምታ” ሳይሆን በሰፊው ከኔ ጀምሮ እና ሌሎች ወገኖች እና የወልቃይት ሰዎች በየደረገጾቻቸው ለብዙ አመታት ዘግበውታል”። የወልቃይት መሬት ተቆርሶ ለትግራይ ተሰጠ ሲባል “የተከተለው የአኔክሰሽን” ስቃይ አቶ ታማኝ አያውቅም? ተያይዞ የተከተለው ጥቃት እንዴት አላወቀም? የራሱ ነገድን ችግር እንዴት አያውቅም? የነገዱን ስቃይ በጎን እያየ አሻግሮ ማዶ መመልከት ያስከተለው “እንግዳ ጆሮ” ማፈር ያለበት ማን ነው? በአካል የማላውቃቸው የወልቃይት ሰዎች ወደ እኔ እየደወሉ “እግዚሓር ይባርክህ ሲሉኝ” የነበሩት ከብዙ አመት በፊት ነው። ታማኝ የገዛ ጐንደሮቹን ችግር እንዴት ሊሰወረው ቻለ? ታማኝ እኔ ሁሌም የምለውን እሱ በትከክል እንዳለው “ሚዲያው የአማራው ህብረተሰብ ለ22 ዐመት አልዘገበውም”፤ በአድርባዮች እና በአጥቂዎች የሚመሩ የተቃዋሚው ሚዲያዎች ለ22 አመት ሲዘግቡ እና ሲያጃጅሉን የነበሩት “ስለ ዲሞክራሲ” ስለነበር አማራው የደረሰበት የዘር ማጥፋት ጥቃት ባለመዘገባቸው እና ተከታታይ ትኩረት ባለማድረጋቸው ለግዝገዛው እና ለጥፋቱ ዘመቻ አብዛኛዎቹ ተቃዋሚዎች እና ሚዲያዎቻቸው ተጠያቂዎች ናቸው። ስለዚህም ታማኝ እና ሚዲያዎች ዛሬስ ምን እያደረጉ ነው? የአማራውን ጥቃት እንነጋር ለሚሉ የወገኖቻቸው ጥሪ እየጣሱ እና በጐሪጥ እያዩ መሄድስ “ሚዲያዎች አልዘገቡትም” ከሚለው የሽፋን ሰጪ ምክንያት ጋር ምን አገናኘው?
አማራው ታማኝ፤ አማራው አበበ ገላው (አማራ አይደለንም ካላሉኝ በቀር) በኢሳት ጣቢያቸው ስለ አማራው ችግር አለፍ ፤አለፍ ብለው አንደ ሶርያ እና ኢራቅ ዜና በሚለቁት የ3 ደቂቃ የአማራ ሕብረተሰብ የነገዳቸው ዜና (እርግጥ አላደረጉም ሳይሆን፤ አንዳንድ ጊዜ የሚገባ ሽፋን አድርገዋል። እንኳን እንኳን ኢትዮጵያዊያን የናጄሪያዋ ኰመዲያን ‘አዲዮላ’ ም ተገቢው ሽፋን ስለ አማራው ዘር ማጥፋት ሽፋን ሰጥታቸዋለች) በቂ መስሏቸው እንደሆነ ታማኝ እንዳለው “እኔ እስካሁን ድረስ ይንን ችግር አንዲሁ በጥቂቱ በጭምጭምታ እንጂ አለውቀውም ነበር” ያለውን በእነዚህ አረጋዊያን ፊት የተናዘዛው ኑዛዜ እውነትም “የነገዳቸው ችግር አያውቁትም”። አውን ስላላወቁት ሆኖ ይሆን፤ በሳንሆዜ ከተማ በተዘጋጀው ስብሰባ የአማራውን ችግር ላለመዘገብ፤ወይንም ላለመገኘት ሆን ብለው ‘የስብሳባውን አዳራሽ” አንደጠላት ስብሰባ አይተው “በጐሪጥ እየገላመጡ” ወደ “ሳተላይት ቄያቸው” ያመሩት?
ትግሬዎች እውነትም “ዓሻ ጽቡቕ አሎ- ዘመድ ዓሻ ከፊኡዎ አሎ” (ሞኝ ተስማምቶታል፤ የሞኙ ዘመድ ከፍቶታል።” አውነት ነው። ሊሂቁም ሚዲያውም፤ተቃዋሚውም “በወያኔ የጨዋታ ስልት” ገብቶ፤ በጥቃቱ ዘመቻ ተካፋይ በመሆን “አማራውን በመገዝገዝ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ” በየመድረኩ እያደረገው ያለው “ሕዝቡን የማጃጃል እና የአንድነት ደለል በመሸርሸር እየተጫወተው ያለው ሴራ” በሰፊው በቀጣዩ ትችቴ ይቀጥላል። ተቃዋሚው እና በተቃዋሚው ልብ እና ሳምባ የሚተነፍሰው “ነፃ ያልሆነ፤ ነፃ ሚዲያ” ቅንጅትን ካፈረሰው የተጠናወተው በሽታው ዛሬም በፍፁም ሊድን አልቻለም። ለሰፊው ትንተና በሚቀጥለው ጽሑፌ ይጠብቁኝ።
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ
አዘጋጅ) (Ethiopian Semay) getachre@aol.com