Thursday, March 31, 2011

ነብስ ይማር ፕሮፌሰር አለሜ እሸቴ

ነብስ ይማር ፕሮፌሰር አለሜ እሸቴ My Condolences ስለ ፕሮፌሰር አለሜ እሸቴ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማኝ ሐዘን ጌታቸው ረዳ getachre@aol.com March 31/2011 ፕሮፌሰር አለሜ እሸቴ በፈረንጆች አቆጠጠር March 28, 2011ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል የሚለው ዜና ethiopia.org ከተባለ የህዋ ሰለዳ ተለጥፎ አንብብያለሁ።ቀጥሎም ሳይበር ኢትዩጵያ/ዋርካ በተባለው የሃሳብ መለዋወጫ አምዶች ላይ ተመሳሳይ ዜና አንብብያለሁ። ቀጥየም የቅርብ ጓደኛየ ደውየ ስለ ዜናው እርግጠኛነት ጠይቄው እሱም መሞታቸውን እንደሰማ ነገረኝ። የነበረኝ የቤታቸው ስልክ የት እንዳስቀመጥኩት ለጊዜው ስላጣሁት ፤ዜናው በርግጠኝነት ማወቅ ባልችልም፡ እውት ከሆነ፡ ሐዘኔን በዚህ አጋጣሚ እገልጻለሁ። ፕሮፌሰር አለሜ ጣሊያን አገር ማኒላ ውስጥ ነበር የሚኖሩት። በሚኖሩበት አገር የኢትዩጵያውያን ስደተኞች ማሕበር እና የሰብአዊ ጉዳዩች ዳሬክተር ነበሩ። ፕሮፌሰሩ በጣሊያን ዩኒቨርሲቲ በሙያቸው ሙሉ ፕሮፌሰር ሆነው አገልግለዋል። ፕሮፌሰር አለሜ በኩላሊትና በአዝማ በሽታ ሲሰቃዩ ቆይተው በመጨረሻ ተሸንፈው ወደ እዚህ ዓለም ዳግም ላይመለሱ በሞት ተሸንፈው እንደ ሆነ እገምታለሁ። ፕሮፌሰር አለሜ እሸቴ ምሁር ከመሆናቸው ሌላ አምስት ዓለም አቀፍ የውጭ ቋንቋዎች መናገር ይችሉ ነበር። የጥንታዊ እና የዘመናዊ ታሪክ ጥናቶች፤ የፓለቲካና የማሕበራዊ ጉዳይ ስነ ምርምር ሊቅ ነበሩ። ፕሮፌሰር አለሜ ከማውቃቸው የኢትዩጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ግምባር ቀደም በመሰለፍ የተለያዩ የኢትዩጵያ ጠላቶችን ባላቸው እውቀት ስለ ኢትዩጵያ ሞግተዋል።ፕሮፌሰር አለሜ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እያሉ የጻፏዋቸው የአማርኛ መጻሕፍቶች እንደንበሩ አሁን ስማቸው ከዘነጋሁት አንዲት የሴቶች ማሕበራዊ ጉዳይ ተመራማሪት ኢትዩጵያዊት እመቤት ተነግሮኝ እንደ ነበር አስታውሳለሁ። የአማርኛ መጻሕፍቶቹ ስም በውል አላስታውሳቸውም። በእንግሊዚኛ የተጻፉ ጥናቶች በርካታ ሲሆኑ ለምሳሌ Ruralness and rural transformation in Ethiopian history (1976) Cultural Situation in Socialist Ethiopia: Studies and Documents on Cultural Policies (1982) የሚሉና በመጽሐፍ መልክ እንዲታተም እዚህ አሜሪካን አገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዩጵያውያን ማተሚያ ቤተቶችን አነጋግረው በርካታዎቹ የማተሚያ ባለቤቶች ድፍረት ስላጡ ዶክዩመንቱ በመጽሐፍ መልክ ሳይታተም ቀርቷል። እሳቸው እንደፈለጉት ያለ ምንም እርማት ወይንም የአታሚው አርትኦ ሳይደረግበት እንዳለ እንዲያትሙላቸው ከተጠየቁት መካከል አንዱ ሎስ አንጀለስ ከተማ ካሊፎርኒያ ውስጥ የሚገኝ ፀሐይ ማተሚያ ቤት አንዱ ነበር። የኢመይሉ ልውውጥ ለታሪክ እንዲሆን ፋይልህ ውስጥ አስቀምጠው ብለው የላኩልኝ ማሕደር አሁንም በእጄ አለ። በእድሜና በበሽታ እየደከምኩ ስላለሁ አዙረህ የምትጠይቀው አስተማሪ እንዳታጣ ብለው ጠቃሚ የታሪክ ማሕደሮችንም ሰጥተውኝ በክብር አሁን በእጄ አሉ። አንዳንዶቹም እሳቸው እያሉ በድረገጽ ምህዋሮች እንድለቃቸው ነግረውኝ ተለቅቀዋል። የተለቀቁ ዶክዩመንቶች የብዙ አገር ወዳድ ኢትዩጵያውያን ዜጎች የማሰብ ችሎታ እንዲዳብር ረድተዋል። እርግጠኛ መሆኑን ባለውቅም፡ የፕሮፌሰሩ ሞት ስሰማ እጅግ ከፍተኛ ድንጋጤና ሐዘን ነበር የተሰማኝ። እኔ ከማውቃቸው የታሪክ ምሁራን የተለያዩ የኢትዩጵያ ጠላቶችን በድፍረት የሚጋፈጥ ኢትዩጵያዊ ምሁር ያየሁት ፕሮፌሰር አለሜ እሸቴ ነበር።የፕሮፌሰሩ ጽሑፍ በጣም ጥልቅ ምርምር ያዘሉ ስለነበሩ ጠላቶች መልስ ለመስጠት ስለሚቸገሩባቸው ሙግታቸው በተራ ስድብ ሲሸኙዋቸው እንደነበር ይታወቃል። የታተመው መጽሐፌ ከመታተሙ በፊት በጠና ታመው እንደነበርና በማጋገም እንዳሉ ነግረውኝ በመጽሐፌ ላይ አስተያየት እንዳላቸው እንዲያክሉበት ልኬላቸው ዜናውን ሲሰሙ በጣም ደስ ብሏቸው እንደሚያነቡትና አስተያየታቸው እንደሚሰጡበት በኢመይል ነግረውኝ ሲያበቁ ድንገት ከግንኙነት ተቋረጥን።ግንኙነታችን ከተቋረጠ በኋላ አገር ወዳድ ኢትዩጵያውያን ስለሁኔታቸው የሚታወቅ ነገር እንዳለ ጠይቄአቸው እነሱም መረጃ እንደሌላቸው ከነገሩኝ በኋላ ለብዙ ጊዜ ሲጠፉብኝ በጠና መታመማቸውንም ጠረጠርኩ። ሰው ነበሩና አምላካችን አዳም ሆይ! አንተ አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ እንዳለው ሁሉ እሳቸውም ቀናቸው ደርሶ ከሆነ ተለይተውናልና ማዘን ይኖብናል። የኢትዩጵያ ልጆች በጠና ማዘን ይኖርባችሗል። ጠላቶች ደስ ብሏቸዋል፡ምክንያቱም በጥልቅ እውቀታቸው አፋቸው የስከድኗቸው እንደነበር ስለሚያውቁ እንደሳቸው ሆኖ ፊት ለፊት የሚገጥም ደፋር የታሪክ ተመራማሪ እንደሌለን ያውቃሉና በዚህ ረክተዋል። ፕሮፌሰሩ “From Baron Prochazka to Benito Mussolini "Legge Organica" the "Charter" for the Tribal Dismemberment of Ethiopia” የሚለው ጽሑፋቸው ለሕዝብ ይፈ ሲሆን ወያኔዎችና ዘረኞች ምን ያህል ራዕድ/ፍርሃት ድንጋጤ እንዳደረባቸው ጽሑፉን ያነበባችሁ ዜጎች የምታስታውሱት ይመሰልኛል። በዓይን መታወክ ምክንያት ከሕዝባዊ መድረክ ድንገት የተሰወረው እውቁ ምሁር የትግራይ ተወላጅ (ዓጋመ አውራጃ) ካናዳ ውስጥ የሚኖር ዶ/ር ሐጎስ ገ/እየሱስ ኢትዩጵያውያን ረስተውት ስንገነዘብ እኔ እና ዶ/ር አለሜ እሸቴ Where's the great Hagos Gebreyesus? Message May 8, 2007 (ጉጉል ብታደርጉት ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ) በማለት ዶ/ር ሐጎስ በሕይወት መኖሩን አወቅን። ደ/ር ሐጎስ የሚታወቀው በብዙ ትግሎችና ጽሑፎቹ ቢሆንም ከነሱ ውስጥ The Two Headed Hydra, National Self Hatred and Nihilism …" የሚለው ኢሕአፓ፤ መኢሶን ወያኔና ሻዕቢያ ያወገዘበት የብሔር ብሐረሰብ ጉዳይ ነበር። ዶ/ር ሐጎስ የፕሮፌሰሩ አውነት ሆኖ በሞት መለየታቸው ሲሰማ እንደሚያዝን እርግጣኛ ነኝ። በዚህ አጋጣሚ በቅርቡ የሚታተመው መጪው መጽሐፌ ለዶ/ር አለሜ እሸቴና ኤርትራ ውስጥ የባሕር በራችንን ላላማስነጠቅ አሰቃቂ ሞት የተጋፈጡ የምፅዋ ጀግኖችን መታሰቢያ እንዲሆን ለግሻለሁ። ፕሮፈሰር በሞት ቢለዩም ስራቸው ህያው ነውና የተቀረነው ትጋለቸውን በድፍረት ኢትዩጵያዊነትን ለማስከበር ትግላችን ይቀጥላል። እየተሰራጨ ያለው ዜና ውሸት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡ ሞተውም ከሆነ ይህ የሐዘን መግለጫ ያነበቡ ቤተሰቦቻቸው እውነቱን እንደሚነግሩን ተስፋ አደርጋለሁ። መረጃ ስላልተገኘ ተብሎ ስጋታችንን ሳንገልጽ ቢታለፍ ይቆጫል። ነብስ ይማር ጌታቸው ረዳ የኢትዩጵያን ሰማይ አዘጋጅ www.ethiopiansemay.blogspot.com getachre@aol.com

ነብስ ይማር ፕሮፌሰር አለሜ እሸቴ

ስለ ፕሮፌሰር አለሜ እሸቴ ከዚህ ዓለም በሞት መየት የተሰማኝ ሐዘን ጌታቸው ረዳ getachre@aol.com March 31/2011 ፕሮፌሰር አለሜ እሸቴ በፈረንጆች አቆጠጠር March 28, 2011ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል የሚለው ዜና ethiopia.org ከተባለ የህዋ ሰለዳ ተለጥፎ አንብብያለሁ።ቀጥሎም ሳይበር ኢትዩጵያ/ዋርካ በተባለው የሃሳብ መለዋወጫ አምዶች ላይ ተመሳሳይ ዜና አንብብያለሁ። ቀጥየም የቅርብ ጓደኛየ ደውየ ስለ ዜናው እርግጠኛነት ጠይቄው እሱም መሞታቸውን እንደሰማ ነገረኝ። የነበረኝ የቤታቸው ስልክ የት እንዳስቀመጥኩት ለጊዜው ስላጣሁት ፤ዜናው በርግጠኝነት ማወቅ ባልችልም፡ እውት ከሆነ፡ ሐዘኔን በዚህ አጋጣሚ እገልጻለሁ። ፕሮፌሰር አለሜ ጣሊያን አገር ማኒላ ውስጥ ነበር የሚኖሩት። በሚኖሩበት አገር የኢትዩጵያውያን ስደተኞች ማሕበር እና የሰብአዊ ጉዳዩች ዳሬክተር ነበሩ። ፕሮፌሰሩ በጣሊያን ዩኒቨርሲቲ በሙያቸው ሙሉ ፕሮፌሰር ሆነው አገልግለዋል። ፕሮፌሰር አለሜ በኩላሊትና በአዝማ በሽታ ሲሰቃዩ ቆይተው በመጨረሻ ተሸንፈው ወደ እዚህ ዓለም ዳግም ላይመለሱ በሞት ተሸንፈው እንደ ሆነ እገምታለሁ። ፕሮፌሰር አለሜ እሸቴ ምሁር ከመሆናቸው ሌላ አምስት ዓለም አቀፍ የውጭ ቋንቋዎች መናገር ይችሉ ነበር። የጥንታዊ እና የዘመናዊ ታሪክ ጥናቶች፤ የፓለቲካና የማሕበራዊ ጉዳይ ስነ ምርምር ሊቅ ነበሩ። ፕሮፌሰር አለሜ ከማውቃቸው የኢትዩጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ግምባር ቀደም በመሰለፍ የተለያዩ የኢትዩጵያ ጠላቶችን ባላቸው እውቀት ስለ ኢትዩጵያ ሞግተዋል።ፕሮፌሰር አለሜ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እያሉ የጻፏዋቸው የአማርኛ መጻሕፍቶች እንደንበሩ አሁን ስማቸው ከዘነጋሁት አንዲት የሴቶች ማሕበራዊ ጉዳይ ተመራማሪት ኢትዩጵያዊት እመቤት ተነግሮኝ እንደ ነበር አስታውሳለሁ። የአማርኛ መጻሕፍቶቹ ስም በውል አላስታውሳቸውም። በእንግሊዚኛ የተጻፉ ጥናቶች በርካታ ሲሆኑ ለምሳሌ Ruralness and rural transformation in Ethiopian history (1976) Cultural Situation in Socialist Ethiopia: Studies and Documents on Cultural Policies (1982) የሚሉና በመጽሐፍ መልክ እንዲታተም እዚህ አሜሪካን አገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዩጵያውያን ማተሚያ ቤተቶችን አነጋግረው በርካታዎቹ የማተሚያ ባለቤቶች ድፍረት ስላጡ ዶክዩመንቱ በመጽሐፍ መልክ ሳይታተም ቀርቷል። እሳቸው እንደፈለጉት ያለ ምንም እርማት ወይንም የአታሚው አርትኦ ሳይደረግበት እንዳለ እንዲያትሙላቸው ከተጠየቁት መካከል አንዱ ሎስ አንጀለስ ከተማ ካሊፎርኒያ ውስጥ የሚገኝ ፀሐይ ማተሚያ ቤት አንዱ ነበር። የኢመይሉ ልውውጥ ለታሪክ እንዲሆን ፋይልህ ውስጥ አስቀምጠው ብለው የላኩልኝ ማሕደር አሁንም በእጄ አለ። በእድሜና በበሽታ እየደከምኩ ስላለሁ አዙረህ የምትጠይቀው አስተማሪ እንዳታጣ ብለው ጠቃሚ የታሪክ ማሕደሮችንም ሰጥተውኝ በክብር አሁን በእጄ አሉ። አንዳንዶቹም እሳቸው እያሉ በድረገጽ ምህዋሮች እንድለቃቸው ነግረውኝ ተለቅቀዋል። የተለቀቁ ዶክዩመንቶች የብዙ አገር ወዳድ ኢትዩጵያውያን ዜጎች የማሰብ ችሎታ እንዲዳብር ረድተዋል። እርግጠኛ መሆኑን ባለውቅም፡ የፕሮፌሰሩ ሞት ስሰማ እጅግ ከፍተኛ ድንጋጤና ሐዘን ነበር የተሰማኝ። እኔ ከማውቃቸው የታሪክ ምሁራን የተለያዩ የኢትዩጵያ ጠላቶችን በድፍረት የሚጋፈጥ ኢትዩጵያዊ ምሁር ያየሁት ፕሮፌሰር አለሜ እሸቴ ነበር።የፕሮፌሰሩ ጽሑፍ በጣም ጥልቅ ምርምር ያዘሉ ስለነበሩ ጠላቶች መልስ ለመስጠት ስለሚቸገሩባቸው ሙግታቸው በተራ ስድብ ሲሸኙዋቸው እንደነበር ይታወቃል። የታተመው መጽሐፌ ከመታተሙ በፊት በጠና ታመው እንደነበርና በማጋገም እንዳሉ ነግረውኝ በመጽሐፌ ላይ አስተያየት እንዳላቸው እንዲያክሉበት ልኬላቸው ዜናውን ሲሰሙ በጣም ደስ ብሏቸው እንደሚያነቡትና አስተያየታቸው እንደሚሰጡበት በኢመይል ነግረውኝ ሲያበቁ ድንገት ከግንኙነት ተቋረጥን።ግንኙነታችን ከተቋረጠ በኋላ አገር ወዳድ ኢትዩጵያውያን ስለሁኔታቸው የሚታወቅ ነገር እንዳለ ጠይቄአቸው እነሱም መረጃ እንደሌላቸው ከነገሩኝ በኋላ ለብዙ ጊዜ ሲጠፉብኝ በጠና መታመማቸውንም ጠረጠርኩ። ሰው ነበሩና አምላካችን አዳም ሆይ! አንተ አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ እንዳለው ሁሉ እሳቸውም ቀናቸው ደርሶ ከሆነ ተለይተውናልና ማዘን ይኖብናል። የኢትዩጵያ ልጆች በጠና ማዘን ይኖርባችሗል። ጠላቶች ደስ ብሏቸዋል፡ምክንያቱም በጥልቅ እውቀታቸው አፋቸው የስከድኗቸው እንደነበር ስለሚያውቁ እንደሳቸው ሆኖ ፊት ለፊት የሚገጥም ደፋር የታሪክ ተመራማሪ እንደሌለን ያውቃሉና በዚህ ረክተዋል። ፕሮፌሰሩ “From Baron Prochazka to Benito Mussolini "Legge Organica" the "Charter" for the Tribal Dismemberment of Ethiopia” የሚለው ጽሑፋቸው ለሕዝብ ይፈ ሲሆን ወያኔዎችና ዘረኞች ምን ያህል ራዕድ/ፍርሃት ድንጋጤ እንዳደረባቸው ጽሑፉን ያነበባችሁ ዜጎች የምታስታውሱት ይመሰልኛል። በዓይን መታወክ ምክንያት ከሕዝባዊ መድረክ ድንገት የተሰወረው እውቁ ምሁር የትግራይ ተወላጅ (ዓጋመ አውራጃ) ካናዳ ውስጥ የሚኖር ዶ/ር ሐጎስ ገ/እየሱስ ኢትዩጵያውያን ረስተውት ስንገነዘብ እኔ እና ዶ/ር አለሜ እሸቴ Where's the great Hagos Gebreyesus? Message May 8, 2007 (ጉጉል ብታደርጉት ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ) በማለት ዶ/ር ሐጎስ በሕይወት መኖሩን አወቅን። ደ/ር ሐጎስ የሚታወቀው በብዙ ትግሎችና ጽሑፎቹ ቢሆንም ከነሱ ውስጥ The Two Headed Hydra, National Self Hatred and Nihilism …" የሚለው ኢሕአፓ፤ መኢሶን ወያኔና ሻዕቢያ ያወገዘበት የብሔር ብሐረሰብ ጉዳይ ነበር። ዶ/ር ሐጎስ የፕሮፌሰሩ አውነት ሆኖ በሞት መለየታቸው ሲሰማ እንደሚያዝን እርግጣኛ ነኝ። በዚህ አጋጣሚ በቅርቡ የሚታተመው መጪው መጽሐፌ ለዶ/ር አለሜ እሸቴና ኤርትራ ውስጥ የባሕር በራችንን ላላማስነጠቅ አሰቃቂ ሞት የተጋፈጡ የምፅዋ ጀግኖችን መታሰቢያ እንዲሆን ለግሻለሁ። ፕሮፈሰር በሞት ቢለዩም ስራቸው ህያው ነውና የተቀረነው ትጋለቸውን በድፍረት ኢትዩጵያዊነትን ለማስከበር ትግላችን ይቀጥላል። እየተሰራጨ ያለው ዜና ውሸት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡ ሞተውም ከሆነ ይህ የሐዘን መግለጫ ያነበቡ ቤተሰቦቻቸው እውነቱን እንደሚነግሩን ተስፋ አደርጋለሁ። መረጃ ስላልተገኘ ተብሎ ስጋታችንን ሳንገልጽ ቢታለፍ ይቆጫል። ጌታቸው ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com getachre@aol.com ነብስ ይማር ፕሮፌሰር አለሜ እሸቴ

ነብስ ይማር