Tuesday, May 5, 2015

የመርዶ ዜና

የመርዶ ዜና
Dr.Mesfin Araya
የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሚዲያዎችም ሆኑ ኤርትራ ተቃዋሚ ሚዲያዎች ያልዘገቡት የእውቁ ምሁር ደ/ር መስፍን አርአያ ‘ሕልፈተ ሞት’ ከዚህ ዓለም መለየት እጅግ አዝኛለሁ። እናንተ አንባቢዎቼም ይህንኑ አሳዛኝ ዜና ስትሰሙ በኢትዮጵያዊነቱ ኮርቶ አስገንጣይ ባንዳዎችንና ከሃዲ ተገንጣዮችን በመድረክ በግልጽ ሲቃወም ስለነበረው ይህ ተወዳጅ ኤርትራዊ ኢትዮጵያዊው ምሁር ለምታውቁት ከዚህ ዓለም በሞት ስለመለየቱ እንደምታዝኑ እርግጠኛ ነኝ።

ደ/ር አርአያ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ የሰማሁት ትላልንት ነው። የሞተበት ቀን በFebruary 2015 ነው።
ደ/ር መስፍን አርአያ ነው።
እዛው ኮለጅ አብረውት የሚያስተምሩና የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን እንዳሉ አውቃለሁ። አንደኛው በየኢንተርኔቱ የሚጽፍ ሰው ነው። ለምን ስለ እሱ ዜና ዕረፍት ለሚዲያዎች አላስተላለፈም፤ እጅግ ገርሞኛል።

ደ/ር መስፍን ሲያስተምርብት በነበረበት የትምህርት ተቋም የዮርክ ኮሌጅ ድረገጽ ስለመስፍን የዘገበው የሃዘን መግለጫው ላይ እንዲህ ይነበባል;-

 “It is with great sadness that I share with you that Dr. Mesfin Araya passed away in February 2015. Dr. Araya served as Associate Professor of Black Studies in the Department of Social Sciences at York College from 1994 until his retirement in March 2013. He earned his Ph.D. in Political Science in 1988 from the CUNY Graduate Center and his BA in Political Science and Economics from Haile Selassie University , Addis Ababa, Ethiopia.” መስፍን አርአያ እዚህ እኔ ካለሁበት ሳንሆዘ ካሊፎርኒያ ውስጥ ካልተሳሳትኩ በ March 2010 ኢትዮ/ኤርትራ ወዳጅነት ውይይት (?) በሚል ኮንፈረንስ ተደርጎ በነበረበት ወቅት ጋዜጠኛ አበበ ገላው የመስፍን አርአያ የአማርኛ ንግግር ወደ እንግሊዝኛ በተረጎመው ዘገባው ላይ ፤መስፍን አርአያ እንዲህ ብሎ ነበር ““It was merely the EPLF’s agenda that was carried out with TPLF. The intellectual class never demanded a public debate over the cost and benefits of independence,” …..”It was merely the EPLF’s agenda that was carried out with TPLF. The intellectual class never demanded a public debate over the cost and benefits of independence,” The Eritrean middle class that blindly rallied around Isaias Afeworki and the Eritrean People’s Liberation Front committed a “collective suicide in post-independence Eritrea.”” ሙሉን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ።https://www.york.cuny.edu/news/the-passing-of-dr-mesfin-araya 

ለመላ ቤተሰቦቹና ወዳጆቹ ጽናቱን እመኝላቸዋለሁ። ስለ ኢትዮጵያ ሲከራከር እድሜው በሙሉ ያሳለፈው አገር ወዳዱ ከዚህ ዓለም ቦት ሲለይ፤ የተቃዋሚ የዜና ድረገፆች ስለ ሕይወት ታሪኩና ሞቱ አንዲት ቅጠል ሳይለግሱለት በማለፋቸው እጅግ ያሳዝናል። ይህ ክስተት በደ/ር መስፍን አርአያ ብቻ የተከሰተ ሳይሆን፤ ካሁን በፊትም በዶ/ር አለሜ እሸቴም ሚዲያዎቹ የሐዘን መግለጫ ለማውጣት ሆን ብለው ነፍገዋቸዋል (የኢትዮጵያን ሪቪው አዘጋጅ ኤልያስ ክፍሌ እግዚሃር ይስጠው እሱ በስተቀር አብዛኛዎቹ ታዋቂ ሚዲያዎች ዜናውን ከሰሙም በሗላ አልዘገቡትም ነበር)፤አሁንም ተልኮላቸው አላወጡትም።ለተለየን ወንድማችን ብቻ ሳይሆን፤ በትዕቢት አንተባበርም ብለው ዜና ዕረፍቱን ያፈኑት እየኖሩ እየመሰላቸው በቁም የሞቱት፤የቁም ሙታንም ይታዘንላቸዋል።

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ)።getachre@aol.com