Wednesday, January 25, 2023

የኢሳያስ ወታደራዊ ሃብሪስ ፣ ናርሲሲዝም እና ደደብነት ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 1/25/2023

 

የኢሳያስ ወታደራዊ  ሃብሪስ ፣ ናርሲሲዝም እና ደደብነት

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

1/25/2023

በርዕሱ ላይ የተጠቀሱት የእንገሊዝኛ ቃላቶች ትርጉማቸው ኋላ በምጠቅሰው ሃተታ ታገኝዋቸዋለችሁ። እያደረ የሚገርም ትዕይንት እየመጣ የምናርፍበት ጊዜ አጣን።፡በኦሮሙማው መሪ አብይ አሕመድ ጋባዥነት ወደ ትግራይ ገብተው የነበሩት የኢሳያስ ወታደሮች በተፈጠረው ድንገተኛ የቶከስ አቁም ስምምነትና በወያኔ ታጣቂዎች ላይ “ወሳኝ የሚባሉ የጦር መሳሪያዎች”  የማስፈታት ሂደት ተከትሎ ዱርየዎቹ የኤርትራ ወታደሮች ሰሞኑን ከትግራይ ሲወጡ በዘረፉዋቸው መኪኖች ላይ  GAME OVER THAT IS WHO WE ARE!!”………. (ጌም ኦቨር እኛ እነደዚህ ነን) የሚል ጽሑፍ ለጥፈው በሚያልፏቸው  የትግራይ ከተሞች ጎዳና ላይ ይህንን በገሉህ ለጥፈው በትግራይ ሕዝብ ላይ ያሳዩት ንቀት “ትምክሕታዊ እኔነታቸው” ካየሁ በኋላ፤ ወያኔም ሆነ ትግራይ ውስጥ ለወደፊቱ የሚበቅል ታጣቂ የሽምቅ ወታደር ከተፈጠረ የኢሳያስ ወታደርን ብቻ ሳይሆን የኢሳያስን ስርዓት ሰላም የሚያሳጣ ተዋጊ ሃይል ቢፈጠር ተቃውሞ የለኝም። ያውም ድጋፍ እሰጣለሁ።

 

ይህ ብቻ ሳይሆን ባድሜና የቀይ ባሕር ወደባችንነ ያለ ሕግ የነጠቀው መሬትም የሚያስመልስ ተዋጊ መመስረት የግድ ነው።  

ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ወያኔና  የኢሳያስ አፈወርቂ የጭን ገረድ (አብይ አሕመድ በኢሳያስ ግራ ጣት ላይ ቀለበት ሲያስገባለት ፎቶግራፍን አትርሱ) የሆነው “አብይ አሕመድ” ቢሆንም፤ ለወደፊቱ ኢሳያስን የሚቀጣ የሽምቅ ወታደሮች ከትግራይ ቢመሰረት የትግራይ ሕዝብ ድጋፉን መስጠት አለበት። ሌላ ታጣቂ ሃይል እንዲከሰት እስክጠይቅ ድረስ ያደረሰኝ እንዲህ ያለ የሻዕቢያ ብልግና ምን ያህል እንዳበሳጨኝ ማየት ትችላላችሁ።

ወያኔ የሚባል የፋሺሰት አመራር በአማራ ላይ ያለው ጥላቻ ከማርገብና አብይ አሕመድ ላይ እንዲያተኩር ከአማራ ሕዝብ ጋር ዘላቂ ሰላም ፈጥሮ የጋራ ተዋጊ ፈጥሮ ያገሪቷን ጦር ሳይነካ አብይ አሕመድን ለመገርሰስ ከመጣር ይልቅ “ያገሪቱን ወታደር በተኙበት አፍኖ በመጨፍጨፍ” ጸቡ እንዲባባስ አድርጎ በራሱ ላይ ሞት በመደገስ  ለኢሳያስ አፈወርቂና ለአብይ አሕመድ ምቹ ጊዜ እንዲያገኙ አደረገ።

ከዚያም ኢሳያስ ዘው ብሎ ከገባ ወዲህ በትግራይ ሕዝብ ሕይወት ምን በደል እንዳደሰራ በዝርዝር የማውቀው ባይኖረኝም፤ እላይ የጠቀስኩትን በመኪናው ላይ የለጠፈው አስነዋሪ ብልግና እና አንድ ደደብ ኤርትራዊ  እስላም (የፋሺሰት ዘረኛ ቃላቶችን ሁሌም የሚጠቀም ጋዜጠኛ ይሁን ፌዘኛ) አክሱም ሃውልት ላይ ቆሞ ፎቶ ተነስቶ “እኛ እንዲህ ነን የሚለው ከንቱ ጉራ ሳየው “ኤርትራኖች በትግራይ ውስጥ የዘር ማጥፋትም ሆነ ሌብነትና የሴቶች አመጽ” ማድረጉን አልጠራጠርም። ለዚህ ደግሞ መጪው ጊዜ ኤርትራኖች ከባድ ዕዳ እንደሚያስከፍላቸው መገመት ይቻላል።

የኢሳያስ ወታደራዊ ሃብሪስ” (እብሪት) ፣ናርሲሲዝም” (እዩኝ እዩኝ ባሕሪ)  እና ደደብነትን የሚያስተነፍስ ሃይል ከትግራይ የሽምቅ ተዋጊ እንዲመሰረትና የምስራቅ አፍሪቃ ጎብለል የመሆን ፍላጎት የነበረው ሕልመኛው  ወሮበላው ኢሳያስ ልክ በ1998 እራሱ በጫረው እሳት ማኘክ ከሚችለው በላይ ሃፍርት የተከናናውን ያህል ለወደፊቱም እንዲከናነብ ማንኛውም ታጣቂ አለሁ ካለ ድጋፌን እሰጠዋለሁ

ኢሳያስ ይህን ጽሑፍ በወታደሮቹ በኩል መልዕክት እንዲለጥፉ በማድረጉ ኤርትራ በራስዋ ላይ ፋታ የማይሰጥ የወደፊት ቅዠት እንደፈጠረች ማወቅ አለባት። ኢሳያስና አብይ አሕመድ በሰሩት የጦር ወንጀል በዓለም አቀፍ ፍርድ እንዲከሰሱ የሚያደርግ ማንኛውም የህግ ቡድን ድጋፌን እሰጣለሁ። ያ እስኪሆን ግን ትግራይ ውስጥ ኢሳያሰን የሚቀጣ አፈንጋጭ የሽምቅ ተዋጊ ቡድን እንዲመሰረት ጥሪ አቀርባለሁ። ኢሳያስ በቅርቡ በፈጣሪ ወይንም በራሱ ዕብሪት ይወገዳል። ዕዳ ከፋዩ ግን ሕዝቡ ሆኖ ማየት ያሳዝናል።

አመሰግናለሁ፡