Sunday, April 1, 2012

የናታቸው መቃብር የሚያሳምሩ አራቱ እንሰሳዎች

Able Seaman TeKeste Abraham

Deportee Amhara Children from Benchi Maji Ethiopia sheltered inside AEUP (all Ethiopian Unity Party   
የናታቸው መቃብር የሚያሳምሩ አራቱ እንሰሳዎች
ጌታቸው ረዳ
Those of you who wants to purchase my book, few copies are left call (408) 561-4836

በመጀመሪያ ዜናዎች
(1)  

ኤርትራ ውስጥ የ60 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ኤርትራኖች ወደ ወታደራዊ ስልጣና እንዲገቡ መመሪያ ተላልፏ::

(2)ባለፈው ሰሞን በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ጽ/ቤቶች(መኢአድ) ተጠልለው የሚገኙ በደቡብ ኢትዮጵያ ከቤንቺ ማጂ ዞን(ዞን ያርገው ወያኔ ያገሪቱን የቦታ ስም አጠራራር አውራጃ የሚለውን ትቶ “ዞን” እያለ በጌቶቹ በእንግዝ ቋንቋ ይጠራዋል) በጉራ ፍርዳ ወረዳ ሲኖሩ የነበሩት ኢትዮጵያዊያን በአማራነታቸው ብቻ መመዘኛ ተደርጎ ደቡብ “ክልል” ውስጥ አገራችሁ አይደለም መኖር አትችሉም ተብለው በወየኔ አሽከሮች እና በተገንጣይ ቡድኖች የውስጥ አርበኞች ስለተፈናቀሉ አማራዎች ጉዳይ በሚመለከት “ኢሳት” በተባለው ቲቪ ታማኝ በየነ አንዳንድ ተቃዋሚ ጋዶቹ የሚያካሂዷቸው  ተቃዋሚ ድረገፆችና የፖለቲካ ቡድኖች፤ የዘር ሰለባ የሆኑት የቤንቺ ማጂ ተፈናቃይ ሰለባዎች ለምን እንዳልዘገቡት ቅሬታውን እንደሚከተለው ገልጿል። “….በተለያየ ጊዜ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ድምፅ የሚያሰሙ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በዚህ ነጥብ ላይ ዝም ማለታቸው አልገባኝም እኔ። በኢትዮጵያም ውስጥ ያሉ የትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች በውጭ አገርም ያሉ ይሄ ዘር የማጥፋት ስራ ሲሰራ ዝም ማለት አግባብ አይመስለኝም።………………”። ሲል ወቀሳውን ሰንዝሯል።
የቅንጅት ተገንጣይ ቡድን የነበረው የብርቱካን እና የብርሃኑ ነጋ ቡድንን ለማጠናከር ንቀቱን ለማሳየት ቲማቲም ወርውሮ ተቃዉሞውን ለማሳየት ወርውሮባቸው ነበር በሚባሉት  ክቡር ኢንጅኔር ሃይሉ ሻውል የሚመሩት የ“መኢአድ”ን ድርጅት እና አባሎቹ እንኳ  ተፈናቃዮቹ ማጥለላቸው እና መንከባከባቸው ማመስገን ሲገባው እነሱንም ጭምር በጅምላ መውቀጡ አግባብ አይደለም። “በሙሉ” ማለት ምን ማለት ነው? ኢንጂኔሩ የሚመሩት መ ኢ አ ድ የታማኝ በየነ የጓደኞች የብርሃኑ እና የብርቱካን የፖለቲካ ባላጋራ መሆናቸው ስለሚያውቅ እሳቸውንና ድርጅታቸውን ማመስገኑን ሰቅጥጦት ሆኖ እንደሆን እንጂ እንዳውም ሕዝብ ፊት ማመስገን በተገባው ነበር። ያ ግን መ ኢ አ ድ ከታማኝ አይጠብቅም። ቤተክርስትያን አትጠለሉም ተብለው ሜዳ ላይ ሲጣሉ ማን ጽ/ቤት ሄደው ነው ህፃናቱ እና እናቶች የተጠለሉት? መ ኢ አ ድ ትልቅ ምስጋና የሚቸረው ድርጅት ነበር፤ ግን ያ ግን መኢአዶች ከታማኝ የሚጠብቁት አይመስለኝም። ድሮውም መኢአድ የአማራ ድርጅት ነው እያሉ ሲፈጩት፤ ስለ አማራ መጮህ ተቃዋሚውም አስነዋሪ፤ አስወቃሽ ሆኖ በተገኘበት በወያኔ ዘመን የነበረ ስለሆነ አሁን አንድያውን እስቲ ይውጣላቸው እና መኢአድ አማራን ለምን አጠለለ ብለው ይውቀሱት! (መርዓስ ይቐረያዋ ዓዳ ትኽረም” ይላሉ ትግሬዎች (ሰርግስ ይቅርባት አገሯ ትክረም) ይላሉ። ምስጋናውስ ይቅርባቸው “ስለ አማራ ጥብቅና ቆሟል እያሉ የሚወቅሱትን ወቀሳቸው ቢያቆሙላቸው መልካም ነው።
እናቴ  የምትለው ምሳሌን የታማኝ እሮሮ አስታወሰኝ “ዓሻ መን ሽምካ እንተበሉዎስ ከም መዛውርተይ” (ሞኝ ማን ነው ስምህ ቢሉት እንደ ጓደኞቼ) አለ ይባላል። አቶ ታማኝ  በየነ የአማራ ሕብረተሰብ የተጨፈጨፈው አሁን ብቻ መስሎታል (ዛሬ ብቻ እንዳልሆነ አሳምሮ ግን ያውቃል)። ከወያኔ ባልተናነሰ አማራን ያስጨፈጨፉና የጨፈጨፉ ኦነጎችና የግንቦት 7 እነ አንዳርጋቸው ጽጌ አብረውት ሲዞሩ በሚዞርባቸው መድረኮች ላይ አንዲት ፍሬ ቃል እንዳያስተነፍስ እየተጠነቀቀ ከርሞ፤መጨረሻ ላይ "ከአህያ ጋር የዋለ ኰርማ ሕላ (እንደ አህያ መጮህ) ባይማር “ፈስ” ይለምዳል" እንደሚባለው፤ የምኒልክን ገበና በማጋለጥ አጫፍርልን ሲሉት፤ ከ18 ክፍለ ዘመን “በፊት” ኦሮሞዎች በሐረሮች፤ባማራዎች፤በሃድያዎች፤በክርስትያኖች፤በገዳማት…በጠቅላላ ባገሪቱ ላይ ያደረሱትን ጭፍጨፋ እና የተዘረጋ የጥቃት ወረራ ሳይናገር (ልክ እንደማያውቅ ሆኖ) ከ18ኛው ክፍለ ዘመን “ጀምሮ” ያለውን የነገሩትን የኦነግ መሰሪ የቅስቀሳ ታሪክ ከጎንደር ወረራ ብቻ እያስተያየ በየአዳራሹ ሲያደምቅላቸው፡ኦነጎች "ኢትጵያውያን አይደለንም" ብለው እራሳቸው በመታገያ ደብተራቸው የመዘገቡት መረጃ እንዳለ እያወቀ፤ የራሳቸው ባንዴራ የፈጠሩ ተገንጣዮች መሆናቸው እያወቀ  “ኦነጎች ኢትዮጵያውያን  አይደሉም” (ይህ ጥቅስ የራሱ ቃል ነው) “ኦነጐች ኢትዮጵያ አይደሉም”  የሚሉዋቸው “አክራሪዎች” ብሎ እኛን “አክራሪዎች” ብሎ ሲሰድብ  እንዲሁም “አማራው” በበደኖ መንደር ሲጨፈጨፍ፤ ከነ ነብሳቸቸው ወደ ገደል ሲጣሉ የህፃናት አንገት በካራ ሲታረድ “ስትውለበለብ” የነበረችው “የኦነጎች” ባንዴራ፤ እሱ እና መሰል ጓዶቹ ከኦነጎች ጋር ባደረጉዋቸው የከአገር ላገር ኡደቶች እራሱ ቁጭ ባለበት ጠረጴዛ እና አዳራሽ ድምጽ ማጉያ በያዘበት ሰገነት ሁሉ ሳይቀር “ስትውለበለብ” በጸረ አማራና ጸረ ኢትዮጵያዊነት ስለ ቆመው ወንጀለኛው ኦነግ “አንዲት ቃል” ላለመተንፈስ ሲጠነቀቅ ከርሞ ዛሬ በወያኔ  ላይ የክስ ማህደር ይከፈት ብሎ መናገሩ የሚያበረታታ እና የሚመሰገን እና “የዘገየ” ቢሆንም፡ በወያኔ ብቻ ዓይኑን ማነጣጠሩ ሰውየው አሁንም ብዙ የሚቀረው እንዳለ ልነግረው እፈልጋለሁ። ወያኔ ስር የተሰማራው “ኦሖዴድ” (ኦነግ መሆኑን እወቁ”” የጀኔራል ገልቱ ኦሆዴድ ውስጥ እያለ “ኦነግ” እንደነበረ እራሱ ባመነው የድምፅ ምስክርነትን አትርሱ)፤ “ብአዴን” ማለት ደግሞ “ኤርትራኖች የሚመሩት” ማለት ነው። ስለዚህ ሂሳቡን ስታሰሉት ኦነግን ላለመንካት ዳርዳር እያላችሁ በአማራ ህፃናት ልጆች ደም የተጨማለቀው አብሮአችሁ የሚዘለውን “ዋናው የወያኔ የፖለቲካ ውሽማ የነበረው “ኦነግን” ላለማስቀየም “በወያኔ ብቻ” የክስ ፋይል ይከፈት የምትሉ የዋሃን/አድርባዮች/ተጠራጣሪዎች ብዙ መንገድ ልትጓዙ ነው። ምክሩን አሁንም እየለገስን ነው (የሚሰማ ጀሮ ካለ!) ኦነግ ማለት “ኦሮሞ ሕዝብ ማለት አይደለም። ኦነግ የፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል “በኦሮሞ ሕዝብ ይሁንታ ነው” የምትሉ ካላችሁ መረጃችሁን ንገሩን። ስለዚህ ኦነግን ላለመንካት ዳር ዳር የምትሉ አድረባዮች፤ከቆማችሁበት ጭቃማ አቋም በድፍረት ውጡ።
(2)  አንዳንድ ድረገፆች ወቀሳውን ፈርተው እየዘገዩ ዜናውን አውጥተውታል። ነግር ግን ለመሆኑ  ታማኝ የሱ ጓዶች እንዳይወቀሱለት ሰግቶ ነው ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለገው? “ውስጥና ውጭ አገር ያሉ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች እና ድረገጾች በሙሉ ” ብሎ ማለፉ ተገቢ ነው? እሱ ማጋለጥ ካቃተው እኔ ላጋልጥለት። አንድ መረጃ ልስጣችሁ።
የሲያትሉ የኢትዮ ሚዲያው ድረገጽ አዘጋጅ “አብርሃ በላይ” ለግንቦት 7 ንና ለኦነጎች ያሳየው ስግብግብነት ለብዙ አመታት የታዘባችሁ እንዳላችሁ አምናለሁ። ድረገጹ በእነሱ ዜና እና ቪዲዮ ሁሌም ሲጣበብ ለአማራው ሕብረተሰብ በደል ግን ብዙም አያስጨንቀው አላየነውም። ለምን? ለምሳሌ የአማራ ተፈናቃዮቹ ዜናውን ሲያሰረጩ የነበሩ ልባቸው ያዘነ ኢትዮጵያዊ ያሰራጩትን ዜና ለእኔ እና 9ኝ ለሚሆኑ ለጓደኞቹ (ለእነ አልማርያም ጭምር)  የላኩልን ደብዳቤ/ኢመይል ምን ብለው እንደጻፉልን ስማቸውን እና የተላከላቸውን ሰዎችንም አድራሻ ሳልጠቅስ መልእክቱን ብቻ ላስነብባችሁ። እንዲህ ይላል፦“…As you know I have sent the news of the current Amhara eviction from Benji Maji Zone to Ato Abraha Belai of Ethio Media and asked him if he can publish it on his web site. This was on March 26, 2012, but I have yet to see any kind of coverage done about it by ethiomedia.com.”
ኢትዮ ሚዲያ ለኦነጎች እና ግንቦት 7 ለምን እንደሚስገበገብላቸው የማውቀው ነገር ባይኖረኝም ለእስላሞቹ አቤቱታ ግን ልዩ ስፍራ ሰጥቶ በአማራው ሕብረተሰብ ላይ ጭፍጨፋ እና መፈናቀል ሲደርስ አስቸኳይ የዜና ስርጭት እንዲያደርግ ስዕለ ድምፅ እና የጽሑፍ ዘገባዎች ሲላክለት ግን አላወጣውም።
ሰውየው አማራዎችን በሚመለከት በተደጋጋሚ “ጀሮ ዳባ” እንደሚል ይህነን በሚመለከት አምናም አማራዎች ተመሳሳይ መፈናቀል ደርሶባቸው ዜናውን እንዲያሰራጭ ጠይቄው አሻፈረኝ ብሎ “በምትኩ የደስ አይበላችሁ፤የግብርይውጣ” እልክ ይዞት “በአንድ ኬኒያዊ ሶማሊ የተቀነባበረ እፍኝ የሚሞሉ የኦነግ ሽምቅ ተዋጊ ባንዴራ እየተውለበለበ የቡድኑ ጥንካሬ ለማሳየት ግመል ጥለው/አርደው የግመሉን ደም እየተቀባበሉ ሲጠጡ የሚያሳይ ቪዲዮ በመለጠፍ ፕሮፓጋንዳቸውን ሲለትፍላቸው አይቼ ፡ የተላከለትን የአማራው መፈናቀል ዜና ዋጋ ሳይሰጥ የኦነጎችን ዜና ቅድሚያ መስጠቱን ቆጭቶኝ (ካንድ ዓመት በፊት) በሁለታችን መሃል የተላላክናቸው ምልልሶች ኢመይል) እና እሮሮየ ለሕዝብ  ገልጬ እንደነበር ይተወሳል። ዛሬም ከመስመሩ አልተነቃነቀም። ለምን?
 4- ዛሬም ምስጢሩ ያልገባን ሌላው የሲያትሉ ዜና ላስነብባችሁ። የሲያትሎች ጉድ ምስጢሩ ብዙ ነው። የሰሞኑን የአማራው በደል እየገረመን በባንዴራችን መታየት የሚቀኑ/የሚፈሩ/የሚጠየፉ (ቃል ፈልጉለት) ቪድዮ ቀራጮች ሴራ አንድ ልበላችሁ። የጥምረት፤ኦነግ፤ግንቦት7 የስያትሉ ስብሰባ ቪድዮ ተመልክታችሗል? “አረንጓዴ ቀለም” የተቀባ አውዲዮ ቪዲዩ ለኦነጉ ተናጋሪ ለአሚን ጃንዳይ ተቀርፆ ሲተላለፍ፡ ልብ  አድርጉ! በጥምረት ተናጋሪው በአቶ ንአምን ዘለቀ ቪዲዮ ንግግር ላይ ግን በአዳራሹ ግድግዳ እና በመናገሪያው  ሰገነት/ፖዲዮሙ ላይ በግልጽ የሚታየው ለብሶ እና ተሰቅሎ የነበረው የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ (መናገሪያ ፖዲዮሙ የለበሰው ሰንደቃላማ የተጨማደደ እንኳ ቢሆንም) እንደሚታይ ሆኖ ተቀርፆ  በግልጽ (ለንአምን ዘለቀ ብቻ) እንዲታይ ሆኗል (ያ የሚያስመሰግን ነው)። ለኦነጉ ተናጋሪ  ላይ ሲደርስ ግን የተሰራጨው ቪዲዮ የቀረጸው “ተንኰለኛ ሰው” በኦነጉ ጃንዳይ አሚን ንግግር ቪዲዮ ላይ  ያለው የአገሪቱ ሰንደቅአላማ የሌለው፤ሆን ተብሎ ከኦነጎች አጀንዳና ባሕሪ ጋር እንዲሄድ ተብሎ+ ያገሪቱ ሰንደቅ የሆነቺው ምልክት እንዳትታይ ተናጋሪው አረንጓዴ ቀለም ብቻ እንዲያደምቀው ተደርጓል። ስያትሎች እንዲህ  ያለው አስቀያሜ ሴራ ሲያደርጉ የመጀመሪያቸው አልነበረም። ካሁን በፊት “የኦነግ ባንዴራ” ካልተሰቀለ “የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ”ም መሰቀል የለበትም በሚል ተስማምተው እንዳይውለበለብ አድርገዋል። የኢትዮጵያዊው ንአምን ዘለቀ እና የኦነጉ ጃንዳዩ ሲያትል የተደረገበት የስበሰባ አዳራሽ አንድ አዳሯሽ ውስጥ ቢሆንም የተቀረጹት ቪዲዮዎች የሚታዩት በአቶ ንአምን ዘለቀ ንግግር የተቀረጸው ቪዲዮ ያገሪቱ ሰንደቃላማ ያሸበረቀ እና በኦነግ ግን “ተጀምሮ ሲያልቅ” አረንጓዴ እንዲለብስ ለምን ተደረገ? የቪድዮው አዘጋጅ ኢትዮጵያዊ ነው ወይስ የኦነግ ቱልቱላ ? ወይ አገሬ!
5- ግንቦት 7 ስለ ኤርትራ ድምበር መጣስ ተቆርቁሮ ሲጮህ፤ ስለ አማራው መፈናቀል እን ደመምህራን አድማ እና የእስላሞች አቤቱታ በድረገጹ ላይ ሰፊ ቦታ ተሰጥቶት በግልጽ አይታይም። በዚህ ላይ ዜናውን ያሰራጩት ሰዎች የላኩዋቸው የተፈናቃዮች ፎቶግራፎች ለጥፎት አይታይም? ለምን? ጥምረት ከኦነግ ጋር “ምናምን ስምምነት ፈርመናል” ያለንን ጋደኛው “ኦነግ”  ስለ አማራው መፈናቀል ለምን መግለጫ አላወጣም ብየ እንድተች ግን እንደማትጠብቁኝ አምናለሁ!
አሁን ወደ ዋናው ትችታችን እንግባ።
የናታቸው መቃብር የሚያሳምሩ አራቱ እንሰሳዎች
ጌታቸው ረዳ
ውጭ ያለው ተቃዋሚን በሚመለከት ትችታችን እንጀምር።ይሄ ተቃዋሚ የሚባለው ለምድነው ወያኔን እንጂ እኛን አትንኩን የሚሉን? ሕብረተሰብ በጅምላ ጨፍጭፈው እና አስጨፍጭፈው ያለ ማፈር እንደገና “ኢትዮጵያ ይቀርታ ትጠይቀን” የሚሉ፤የራሳቸው እንጂ ያገሪቱን ሰንደቃላማ የማያውለበልቡ “ተቃዋሚዎች” በምን ሂሳብ ነው የማንተቻቸው?
ወያኔን እንጂ እኛን አትንኩን የሚሉ የወያኔ ባሕሪ/ፖሊሲ እና ፖለቲካ የሚያዥጎደጉዱ ጉደኞች ከነባንዴራቸው ተገትረው ዓይናችን ሳይታወር እያየናቸው፤ነገ ስልጣን ስይዙ የሚተክሏትን ባንዴራቸው በግልጽ እየነገሩን “አትቃወሙን” ማለት ምን ማለት ነው? ወያኔ ከዚህ ወዲያ ምን አደረገ?
ወያኔ ማለት እኮ ኦነግ፤አብነግ/የኦጋዴን ነፃ አውጪ ማለት እኮ ነው። ትግሬዎች እንዲህ ዓይነት አስገራሚ ነገር  ሲገጥማቸው የሚሉት ነገር በምሳሌ ልንገራችሁ።“እንተለገበስ ዝተኸድነ ይመስሎ” (የተቦጫጨቀውን ሱሪውን አጥፎ (በቀዳዳው ላይ እራፊ ጨርቅ ለጥፎ ቢለብስ ) አዲስ ልብስ የለበሰ ይመስለዋል።) ይላሉ። መገንጠል አቁመናል ስላሉ ብቻ ሁለመናቸው “ኢትዮጵያዊ ልብስ የለበሱ መስሏቸው፤ ሲዋሹ አብሯቸው የሚዋሹ፤ ሲፈሱ አብሯቸው የሚፈሱ፤ሲየስነጥሱ አብረው  የሚያስነጥሱ የግንቦት ሰባት “ሹካዎች” እና የጥምርት “ፈርኬታዎች” በእጃችን ይዘናቸዋል ብለው፤ ሁላችንም የያዙን መስሏቸው “ለምን ታርሙናላችሁ/ትነቅፉናላችሁ/ታጋልጡናላችሁ” የሚሉት አዲሶቹ ኦነጎች ከየስበሰባቸው የሚያስተላልፉት እሮሮ እና ዘለፋቸውን ሳዳምጥ ዛሬም ነቀፌታ መፍራታቸው እና ያለመማራቸው እየገረመኝ ፤ አማራውን ሕብረተሰብ ከመግደል ልምዳቸው ተያይዞ ስልጣን ሲይዙ ከወያኔ የባሱ ነቀፌታ የሚፈሩ አምባገነኖች እንደሚሆኑ ምንም አልጠራጠርም።በተለይ አማርኛ እና ትግርኛ ተነጋሪ ሆነህ አንድ ቃል ብትሰነዝርባቸው ምን እንደሚከተልህ ከወዲሁ መገመቱ አያዳግትም።
ነቀፌታችን ይጠቅማቸዋል እንጂ አይጎዳቸውም። ግን ውሸት ልማድ ስላደረጉት እንደ የእነሱ ሹካዎች አብረን ስላልዋሸን እንጂ እኛ የምንለውና ካሁን በፊት ያልነው ሁሉ ከእውነት ርቃ አንድም ጠብ አላለችም። እንዲያውም እነሱ ሲዋሹ አብረው የሚዋሹን እቃዎቻቸው እንኳ ሳይቀሩ ምላሳቸው “ሁለት” ጊዜ “ሲቆረጥሙ” አይተናቸው  ያለማፈራቸው እና ስለመዋሸታቸው ማብራርያ ያለመስጠታቸው እየገረመን ተመልሰው እኛን ለምን ይቃወሙናል ሲሉን “አብደዋል እንጂ የጤና እንዲህ አይሆኑም ነበር” እላለሁ።
ለምሳሌ አራቱ እንሰሳዎች (ምሳሌዎቹን ወደ  ሗላ አመጣዋለሁ ተከታተሉኝ) ማለትም ኦነግ፤ግንቦት7፤ጥምረት እና “ሪሞርኪዬ” (ተጎታች) የምላቸው ውሸት ሲሰሙ በውሸት ስሜት ሰክረው በየአዳራሹ የሚያንጨበጭቡላቸው፤ ብትመለከትዋቸው፤ ቀደምት ወላጆቻችን ትግሬዎች “ሁለት ጊዜ በልተው የሚተፉ” “ሁለት ጊዜ ዋሽተው የሚያስከፉ” ዓይነቶች ናቸው ብለው በምሳሌ የሚገልጿቸው ዓይነቶች ናቸው።
አራተኛው ረድፈኞቹ  (ሪሞረኪዮዎቹን/ተጐታቾች) እናቆያቸው እና ሦስቱን ዋና ዋና እንሰሳዎቹን እንመርምራቸው። ለምሳሌ ኦነግ የሞባለው አንደኛው እንሰሳ የሚናገረው ሁሉ ውሸት ለመደበቅ ሲል በየጊዜው የሚምታታበት ዋዣቂ እንሰሳ ካሁን በፊት በየ አዳራሹ የተናገረው ንግግር አንመርምር። “ኦነግ የመገንጠል ጥያቄ ጥይቆ አያውቅም!” ሲለን እነ ዶ’ር ዜሮ (ጌታቸው በጋሻው) እና መሰሎቻቸው ደግሞ “ኦነግ የመገንጠል ጥያቄ ጠይቆ አያውቅም!” ሲሉ እነሱም ከኦነግ ጋር አብረው ሲዋሹ ታስታውሳላችሁ። እኔ እና መሰል የአንድነት ኢትዮጵያውያን ሃይሎች ደግሞ ውሸታቸውን ስናጋልጥ “ኦነግ በታኝ፤ ጸረ ኢትዮጵያ፤አማራን የገደለ ወንጀለኛ፤የላቲን ፊደል ያነገበ ፤ሕጋዊቷን የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ሳይሆን ራሱ የሰፋው ባንዴራ የሚያውለበልብ “ኦሮሞ” እንጂ “ኢትዮጵያዊ” ወይንም ኢትዮጵያ ከምትባል አገር አይደለሁም የሚል ነው! ለዚህም ጽሑፉም ፕሮግራሙም ንግግሩም፤ደብዳቤውም ፤ቅስቀሳውም  የሚያረጋግጠው ይሄንኑ መረጃ ነው” ብለን መልስ ስንሰጥ ታማኝ በየነ፤ ኦነጎች እና ሪሞርኪዮዎቻቸው ስለ ኦነግ ጥብቅና ገብተው “ኦነግ ኢትዮጵያዊ ነው” “ኦነግ ከሌላ ተሻግሮ አልመጣም” (አክራሪዎች/ነፍጠኖች ናችሁ እንዲህ የምትሉ እንጂ ” “የመገንጠል ጥያቄ ጠይቆ አያውቅም” “የምትዋሹት እናንተው ጊዜ ያለፈባችሁ ፖለቲከኞች እንጂ ኦነግ አይደለም” ብለው እኛን በይፋ እንደዘለፉን የምታስታውሱት ታሪክ ነው።
ይህን በተናገረ ምላሳቸው ትንሽ ሳይቆዩ በፈረንጅ አቆጣጠር  1/2012 ዓ.ም “ኦነግ ለ30 ዓመት ሲጠይቀው የነበረው  የመገንጠሉን ጥያቄ አንስቷል!” ሲሉ “የመገንጠል ጥያቄ ጠይቆ አያውቅም” ብለው በዋሹበት ምላሳቸው ለሁለተኛ ጊዜ ምላሳቸውን በይፋ በጥርሳቸው“ቆረጠሙት”። እንደዋሹ አረጋገጡልን። “እየዋሹ ነው” ስላልን ብቻ “ስራችሁ መቃወም ብቻ ነው” ተብለን ገና አሁን በትግል ዕድሜው 3 ወር ያልሞላው ከጃንዋሪ 1/2004 (በፈረንጅ አቆጣጠር) ጀምሮ ከኢትዮጵያዊያን  ጋር ተቀላቅሎ የቅስቀሳ ኡደት ትግል የጀመረው “የ3 ወር ቬተራን ታጋይ” የኦነጉ አቶ አሚን ጁነዲ “ኑ ታገሉ…. እምብየው፤ ኑ ኢትዮጵያዊያን ሁኑ….. አምብየው ....የሚሉ” በማለት በእኛ ላይ ሲመጻደቅ ሰምቼው ሲያንጨበጭቡለት ሰምቼው እንዲህ ዓይነት ሞላጫነት ሲደመጥ ከመሳቅ ወዲያ ምን ይባላል። ዛሬም ሆነ “ያኔ ሲዋሹን” “በእኛ ላይ የወረደው ዘለፋ፤በየቪዲዮው እና የኢንተርኔት ጽሑፍ የተለቀቀው ስድብ ቢመረመር “በጣም አሳዛኝ ዘለፋ ነበር ሲወርድብን የነበረው”።
አሁንም እየዋሹ እንደሆነ ብዙ መረጃዎች አሉን “ዘ ኢትዮጵያ” የሚባለው ዋሺንግቶን የሚታተም ጋዜጣ የኦነጉ ዶ/ር ኑሩ ቃለ መጠይቅ አንብቡ እና አዲሱ ኦነግ ከነበረው አጀንዳ ፈቀቅ እንዳላላ መረጃው ማየት ትችላላችሁ። ሪሞረኪዮዎቻቸው ግን አሁንም ስካሩ አልበረደላቸውም።  እሱን አንድ ቀን (በፒዲኤፍ በመሆኑ ለመለጠፉ ችግር ስለሆነ) በማይክሮሶፍት ወረድስ ጽፌ አስነብባችሗለሁ፡ጉዳቸውን ታያለችሁ።
አለማፈራቸው ግን “ዋሽተናል እና ስለዋሸን ይቅርታ ጠይቀናል” ሳይሉ፤ እንደገና ዛሬም እኛ ከይሲዎች (ዘ ባድ ጋይስ) እነሱ ደጋጎች(ዘ ጉድ ጋይስ) ተደርገን አንድንታይ ያልፈነቀሉት የውሰሸት ድንጋይ የለም።ጃንዳይ የሚባለው የኦነጉ ተነጋሪ ስያትል የተናገረው አድምጡ። (ካሁን በፊት የዋሸውን ሳይሰማው ዛሬም ሌሎቹን “የውሸት ታጋዮች/ስራቸው መቃወም ብቻ” ብሎ ሲቀደድ ካሁን በፊት የዋሸውን ውሸት ሳይሰማው ዛሬም ትንሽ ታርሞ ውሸቱን የሚደብቅበት ቀዳዳ እንኳ ይዞ አልመጣም።) የሚገርመው ደግሞ ሲዋሽም በሞራ ያበጠ መዳፍ ይዘው ወደ አዳራሹ የገቡ አንጨብጫቢ ሪሞርኮዎች/ተጎታቾች “በደስታ ታፍነው ሲያንጨበጭቡለት” ስመለከት የባሰውኑ አሳቁኝ።
ወያኔን ብቻ ውቀሱ፤ወያኔን ብቻ እናጥፋ ፤እኛ የፈለገው ብንዋሽ ብናጭበረብር፤ብናሞኛችሁ፤ አትንኩን ማለት ምን ማለት ነው? ተቃዋሚው “ቅዱስ” ነው? ኦነግ ቅዱስ ነው? የማይነካ የማይገሰስ ቡድን ነው ብሎ ያላቸው ማን ነው? ወያኔ ተቃዋሚ እያለ በድርጅቱና በካባቢው ያሉት የገጠር ኗሪዎች ሲቃወሙት “ዘረባ ግደፍ!” (ንግግር/መንሾኳሸክ/መቃወም አቁም!) የሚሉት የመናገር ነፃነት ማገጃ መፈክር ነበራቸው ( ከብዙ ዓመታት በፊት ዘረባ ግደፍ የሚል የትግርኛ መጽሐፍ ጽፌ ግማሽ እንደደረስኩ ለምን እንዳቆምኩት በማላውቀው ሁኔታ አቁሜው ቅጁ እቤት ይኑር አይኑር ተቀምጦ ያለ ይመስለኛል)። ዛሬም “ዘረባ ግድፍ” የሚሉን ተቃዋሚዎች ጠንከር ብሎ የለበሱት የውሸት ነጠላቸውን ገፍፎ ትከሻቸውን የሚገልጥ ጸሐፊ ከተገኘ የተሸከሙትን የሃጥያት አቧራ እንደሚያቦንባቸው በእርግጠኝነት ስለሚሰጉ ተቃወሚ ነን የሚሉን የዘመኑ ተቃዋሚዎች “ደርግን እንጂ እኛን አትቃወም” ይለው እንደነበረ የወያኔ  “ዘረባ ግድፍ” ባሕሪ ተቃዋሚውም  ገና ስልጣን ሳይዝ “ዘረባ ግደፍ” ማለቱን ጀምሯል።    
ይሄ ብቻ እንዳይመስላችሁ ኢትዮጵያ ጉድ ፈልቶባታል። ተቃዋሚው ወያኔን ስለሚጠላ ብቻ ሁሉንም ነገር መቃወም ስልት መስሎታል። ይህ ጉድ አንብቡ፤ ጥልመት ይለዋል ትግርኛ አማርኛው “ክሕደት” መሰለኝ።Eritrean Nationalist Opposition Organizations joined the Eritrean people and other organizations in condemning the military incursion into and attacks on Eritrea. “ (Eritrean opposition website.) ኢትዮጵያውያን ተቃዋሚዎች ደግሞ ከኤርትራ ተቃዋሚዎች የማይለያቸው አንድ ባሕሪ ደግሞ ከታች ተመልከቱ።
(1)   “ባለፈዉ ኃሙስ መጋቢት 7 ቀን 2004 ዓም የወያኔ ሠራዊት የአለም አቀፉን ህግ በመጣስ የኤርትራን ግዛት ወርሮ ማን አለብኝነት የተሞላበት ወታደራዊ ጥፋት ፈጽሟል።….ስለሆነም ግንቦት 7  የአገሮችን ለዓሊዊነት የሚጥስ ወረራ በትዕግስት ዝም ብሎ እንደማይመለከት የተባበሩት መንግስታትን …….በግልጽ  ማሳወቅ እንዳለበት  ያሳስባል።(ከግንቦት 7 ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ መጋቢት 13 ቀን 2004 )
(2)  ጥቃት ሊፈጸምብኝ ይችላል በሚል መሠረተ ቢስ ፍራቻ ላይ በመመስረት እየተነሳሳ የጎረቤት አገሮችን ድንበር ከመድፈር ተግባሩ አንዲቆጠብ የሚያደርግ እርምጃ  እንዲወስድ ይማፀናል። (ከግንቦት 7 ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ መጋቢት 13 ቀን 2004 )።

(ፍራቻ እንጂ ሻዕቢያ በኢትዮጵያ ላይ ምንም የጥቃት፤የብቀላ፤የማሰናከል፤የጥላቻ ሴራ አይሰነዝርም ይለናል ግንቦት 7። የሻዕቢያ አማካሪ ወይንም ዲፕሎማት መስሎ ነው ያስተጋባው። ትግራይ ድምበር ላይ ያሉ የኔ ዘመዶች ምን ጥቃት እየደረሰባቸው እንዳለ ግንቦት 7 የሚያውቅ አይመስለኝም። ቢያውቅም ልቦናው ከሻዕቢያ ጋር ነውና፤ሻዕቢያን የሚኮንን መግለጫ አያወጣም።)
(3)  his Government has crossed an International border and murdered in cold blood…. …Those that still lament the ‘loss’ of Eritrea and would jump on any band wagon ……that dreads Shabia and would like the Meles regime to do the job before it ceases to exist…. The whole idea of crossing an International border and killing is not a normal or acceptable behavior.…. A few Ethiopians will use the occasion to open old wounds and wave the flag.(Ethiopian and winds of War By Yelma Bekele March 2012)  እነኚህ ኤርትራኖች የድምበራቸው ጉዳይ ሲነሳ የሚጣበቁላቸው ፍጡራን አያጡም፡ የታደሉ ናቸው። እርይ በይ አገሬ! ያሰኛል፡ አይመስላችሁም?
(4)  ሌላው ዜና ደግሞ "አዲስ ነገር" ሲባል የነበረው ጋዜጣ አዘጋጅ አብይ ተክለሃይማኖት የተባለው ጉደኛ ደግሞ በአማራ ደም የታጠበው ወንጀለኛውና አማርኛ መናገርን የሚጠየፍ ኢትዮጵያን የካደ የኦነጉ ሽማግሌው ሌንጮ “አስተዋይ፤ አዋቂ፤ የሰከነ ፖለቲከኛ” በማለት አድናቆቱን በመግለጽ  እንግሊዞች እያሰለጠኑት ያሉት ጋዜጠኛ ተብየው” ይህ ወጣት የዱክትርና ማዕረግ ከሚያሰለጥኑት እንግሊዝ አገር  Oxford University ውስጥ “መድረክ” አዘጋጅቶ ሕዝብ ጠርቶ የሌንጮ አድናቂ መሆኑን እና የሌንጫ  ጨዋ ፖለቲከኛነት መሆን  ሕዝቡ እንዲያውቅለት እየጣረ እንደሆነ ከተላኩልኝ መረጃዎች ማወቅ ተችሏል። ወይ አገሬ ! እጅግ ይገርማል! አማራ ሞኙ ሁሉም ከዳህ; ምን ይሻላሃል!
ከዚህ ቀጥሎ ያለው የ 4ቱ እንሰሳዎች ታሪክ ከትግርኛ ወደ አማርኛ ተርጉሜ እላይ የጠቀስኩዋቸው ተቃወሚ እንሰሳዎች በእናት አገራቸው ላይ ለምን እንዲህ ዓይነት አስቀያሚ ስራ ይሰራሉ? ብሎ ለሚል ጠያቂ  እና ለምን እንዲህ እየዋዠቁ እንዳሉ፤ እየተጓዙበት ያሉትን ጐዳና ምን እንደሚመስል መልስ ያልተገኘለትን ጥያቄ  በእንሰሳ ምሳሌ ላሳያችሁ።
እንደምታውቁት በዙርያችን በየቀኑ የሚፈጸሙ ክስተቶች ቁጥራቸው ብዙ ነው። አንዳንዶቹ ሳንጠይቅ እና ሳንመራመርባቸው በገዛ ራሳቸው መልስ የሚያገኙ ናቸው። በተቃራኒ። አንዳንዶቹ ደግሞ በተቃራኒ ጠይቀህ ተመራምረህ ተጨቃጭቀህ ቀላል መልስ የማይገኝላቸው ናቸው።የሰው ልጅ ግን ለሁለተኛው መንገድ (ቀላል መልስ የማይገኝላቸውን) በወላጆቻችን ምሳሌዎች ያስቀመጡትን ላስረዳ።
ስለ 4ቱ እንሰሳዎች ታሪክ

(1)በትግርኛ “ጥፍንቕ” በአማርኛው  እንሽላሊት/ገበሎ (ሊዛርድ)

(2) በትግርኛ በቋል የምትባል “ወፍ” በአማርኛ ድርጭት

(3)በትግርኛ ጭርናዕ በአማርኛ "ጫት" ከብት ጀርባ ላይ ቆማ የበሬውን ማገር በሹል አፏ እየጠቀጠቀች ደም የምትመጥ ወፍ፤

(4)ጥምብ አንሳ(ጆቢራ) ናቸው። በአማርኛ የላወቅኳቸው የነዚህ እንሰሳዎች ስሞች በኢመይል ወይንም በስልክ ደውላችሁ ስለነገራችሁኝ በጣም አመሰግናለሁ።
የነዚህ እንሰሳዎች ተግባር እና የተቃዋሚዎቹ ተግባር እና ባሕሪ እንመልከት። ጥምብ አንሳ ደረቱን ዘርግቶ በየቦታው ሲንጎዋለል፤ እንሽላሊት/ገበሎ በድንጋይ የተካበ ካብ እና አለታማ ተራራ ላይ በስንጥቅ ድንጋዮች እንደ እባባ አንገቱን ብቅ አድርጎ በነድር/በቁጣ  እራሱን እየነቀነቀ “ቆይ አባህ/ቆይ አባሽ” ሲል፤ በቋል /ድርጭት (ቆቅ/ጅግራ) ደግሞ ከተደበቀችበት ዱር በድንገት ወጥታ በመብረር የመንገደኛን ልብ አስደምብራ ሰውን በፈርሃት ስታስሮጥ፤ "ጫት" የተባለቺው ደም መጣጭ ወፍ ደግሞ  እየተመላለሰች እየጠቀጠቀች ምንም ሳትበድላት የላሚቷን ጀርባ ስታቆስልና ስታሰቃይ ያላየ ሰው አይኖርም።
እነኚህ እንሰሳት ለምነድነው ግን እንዲህ ዓይነት ተግባር እና ባሕረይ የሚፈጽሙት? ቀላሉ መልስ አንዳንድ ሰዎች “ተፈጥሮ ስለሆነ! ” የሚል መልስ የሚመልሱ ሊኖሩ ይችላሉ።ከላይ የተሰጠው መልስ ግን በሕብረተሰቡ/በወላጆቻችን ግን የሚመልሱት ለየት ያለ በሌላ መንገድ ነው መልሱን የሚነግሩን።መልሱም እንደሚከተለው ነው።
በጥንት በደጉ ዘመን እነኚህ የተጠቀሱ እንሰሳት ካንድ እናት ማህፀን የወጡ ወንድማማቾች ነበሩ ነው የሚባለው። እናታቸውን በህይወት እያለች ስላላስደሰቷት በስተእርጅናዋ መሞቻዋ ሲደርስ “እናቴ ይህን አላደረግሽሊኝም፤ከኔ ይበልጥ ለእገሌ ብዙ ተንከባክበሻል; እንዲህ አደረግሺኝ፤እንዲህ በደለሺኝ…ለእገሌ አቀፍሽ፤…” እያሉ በድካም ላይ ድካም የውስጥ ብስጭትና ጫና ጨምረውባት ስለነበር፡ ስትሞት “አይ ልጆቼ፤ ልጆቼ አይደላችሁም እንዳልል ካንጀቴ የወጣችሁ ናችሁ፤ከኔ በፊት ሞት ይስጣችሁ እንዳልል ልጆቼ እንድትሞቱብኝ አልሻም፤ ነገር ግን “ወደዚህ  ዓለም ሳመጣችሁ ስንት ተጨንቄ ፤ደም አፈስሼ፤ ቆሻሻችሁን አቅፌ፤በጀርባየ አዝዬ፤ሽንታችሁ ጀርባዬን አርሶት፤ ያደረግሁት ጥረትና እንክብካቤ ከምንም ሳትቆጥሩት፤በስተርጀናየ ልቤን ስላሳዘናችሁት፤ረግሜአችሗለሁ ‘የተረገማችሁ ሁኑ” ብላ ረገመቻቸው። ምንስ ብትበድላቸው!  እናታቸውን የማያከብሩ ተብለው በሕብረተሰቡ ተነጠሉ።
እነሱም እሷ ከሞተች በሗላ ቆጭቷቸው፤ ወላጅ እናታችን በህይወት እያለች  ወቀሳ አብዝተንባት ስላላስደሰትናት ዛሬ “መቃብሯ” እንዲያምር መቃብሯን አቆነጃጅተን ሠርተን እንካሳት በማለት ተስማሙ።
በስምመነታቸው መሰረት፤ ጆቢራ (ጥምብ አንሳ) ለመቃብሯ የሚሆን የተመቻቸ ቦታ ፈልጐ ጉድጓድ እንዲቆፍር ተነገረው።
ድርጭት (ቆቅ በሏት ለጊዜው) ለመገነዣ የሚሆን ነጠላ እንድታመጣ ተነገራት።
ጠበቕ/ እንሽላሊት/ገበሎ (ሊዛርድ) ደግሞ ለመቃብሯ ንጣፍ እና ክዳን የሚሆን ሰፋፊ ድንጋዮች እንዲሰነጥቅ ተነገረው።
ጭርናዕ/ጫት  ደግሞ ለተስከር የምትሆን የሰባች ላም እንድትፈልግ ሃላፊነት ተሰጣት።
በዚህ ምክንያት ነው፤  “ጆቢራው” ፡ የናቱን መቅበሪያ ጉድጓድ ፍለጋ በየገደሉ እየተንከራተተ የምናየው።
ጠበቕም (ሊዛርድም)፤-  “ይህች ከብ ድንጋይ ትሻላለች ወይስ ይህች ጠፍጣፋ ድንጋይ?” እያለ በየድንጋዩ፤ በየካቡ እና በየቋጥኙ እየዘለለ ሲዞር የሚታየው።
ጭርናዕ/ ጫት (ወፊቷ ) ደግሞ ፦ ለተስካር የምትሆን የሰባች ላም ፍለጋ ፤ ላሚቷን በሹል አፏ ደም እስክትወጣ እየጠቀጠቀች “የሰባች መሆኗን” እና አለመሆንዋን ለማየት ነው ካንዷ ላም ወደ ሌላው በሬ ስትዘል የምትታይ።
ቦቋል/ድርጭት ደግሞ፦ አምጪ የተባለችውን መገነዣ ነጠላ  ለማግኘት ስትል ከዱር፤ጫካ  ወስጥ ተደብቃ ቆይታ መንገደኛ ወደ ሩቅ ጉዞ ሲጣደፍ ጠብቃ ሲያልፍ ‘በድንገት” ብር ብላ ከጫካው ወጥታ የመንገደኛውን ልብ እስከትወጣ እያስደነበረች፤ምን መጣብኝ ብለው በፍርሃት ነጠላቸውን ጥለው ሲሸሹ አምጪ የተባለችውን የመገነዣ ነጠላ ባገኝ ብላ ነው፡ በየጫካው ተደብቃ የሰውን ልብ ስታስደነብር የምትኖረው።
ድሮውስ ቢሆን “መርገም ወላዲ ተዘይቀተለ የዕነኒ” (ድሮውስ ቢሆን “የወላጅ እርግማን ካልገደለ ዝር ማንዝር እንድትሆን ያደርጋል”) የሚባለው ምሳሌ ስለደረሰባቸው ነው እንጂ እንዲህ ባለው ባሕሪ ሊሰማሩ ባልበ። ብለው ወላጆቻችን ለጥያው መልስ በእንዲህ ይመልሱታል።
 አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ Getachre@aol.com  Those of you who wants to purchase my book, few copies are left call (408) 561-4836 www.ethiopiansemay.blogspot.com