Monday, December 12, 2022

27 አመት በወያኔ ትግሬዎች 4 አመት በ ኦሮሙማ ኦሮሞዎች በውስጥ በቅኝ ግዛት (Internal Colonization) እየማቀቅክ የምትገኝ ኢትዮጵያዊ ሆይ ዘሬስ ቀለበት ውስጥ እንዳስገቡህ ገባህ አይደል? ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay) December 12, 2022

 

27 አመት በወያኔ ትግሬዎች 4 አመት ኦሮሙማ ኦሮሞዎች በውስጥ በቅኝ ግዛት (Internal Colonization) እየማቀቅክ የምትገኝ ኢትዮጵያዊ ሆይ ዘሬስ ቀለበት ውስጥ እንዳስገቡህ ገባህ አይደል?

ጌታቸው ረዳ

(Ethio Semay)  Decmber 12/2022

በድጋሚ እንዲለጠፍ የተጠየቀው ትንታኔ ይኼው ለጥፌዋለሁ።


በድጋሚ እንዲለጠፍ የተጠየቀው ትንታኔ ይኼው ለጥፌዋለሁ።

በርዕሱ እንደምትመለከቱት 27 አመት በትግሬዎች አሁን ደግሞ በኦሮሞዎች 4 አመት ሙሉ በውስጥ የቅኝ (በአፓርታይድ) ግዛት አስተዳደር ውስጥ ተይዛ ከጣሊያኖች በከፋ ሁኔታ ሕዝቧ ፍዳውን እያየ እንደሚገኝ እንደ ዱሮው “አሌ ብላችሁ” ልትሞጉቱኝ እንደማትችሉ እርግጠና ነኝ። አሌ የሚሉ ቢኖሩ በየፌስቡኩ እና አገር ውስጥም ያው የአፓርታይዱ እበላ ባይ ወይንም ግብዝ ሕሊና የተሸከሙ ምናምነቴ አሽከሮች እዚህም እዛም አሉ። ጥያቀዬ  የወቅቱ ፓለቲካ አልገባ ብሎአቸው በአዝጋሚ ሂደት እንደምትጓዘው “tortoise/ኤሊ”  የሚንፏቀቁትን ሳይሆን ለ27 አመት ወያኔ ዛሬም ለ4 አመት ሙሉ በወያኔ እግር የተተካው የወንጀለኞችና የሽብርተኞች ስብስብ ቡድን (አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ሲመጣ ፓርላማ ተብየው ውስጥ በአንደበቱ “አሸባሪዎች ገራፊዎች ነን” ብሎ እንዳመነው እና ዛሬም ሽብሩን እየቀጠለበት ያለው የወንጀለኞች ስብስብ) ኦሮሞ ሪፑብሊክ ለመመስረት አገራችንን በቅኝ ግዛት ይዞ ወደ ማፍረስ አደጋ ሊወስዳት ነው ብየ ስናገር አላምንም ብላችሁ ስትፋክቱ ለከረማችሁ ኢትዮጵያዊያን ነው ጥያቄየን እንድትመልሱ የምጠይቃችሁ። አሁንስ የዚህ የወንጀለኞች ስበስብ ቡድን ምንነት ገባችሁ?

ይህ ቡድን የወያኔ አሽከር ሆኖ ለ27 አመት የሕዝባችንን የባሕል፤የሞራል እሴቶቹ እንዲላሽቅ በማድረግ ወጣቶችን ተሰምቶም ታይቶም በመይታወቅ የግብረገብ ውድቀትና የውጭ ባሕል ወረርሺኝ ተጠቂ ሆኖ፤ ወላጆቹ ያቆዩለትን ሰፊ አገር እና የባሕር ወደብ ከነሰንደቃላማዋ ጋር እየናቀ፤ የኢትዮጵያ ጠላቶች ባንዴራ እያውለበለበ “ወንድማማች ነን እያለ” የተገዢነት ባህል እንዲያዳብር ተደርጎ አሁን ላለው  ምስቅልል እና ውርደት ተዳርጓል።

ሰው አደባባይ ላይ ከነነበሱ በመኪና እየጎተቱ፤ ነብሰጡር በቢላዋ እየቀደዱ ሽል ፍጥረት ገድለው የእናቶችን ኩላሊት በካራ በጥሰው መብላት የማይሰቀጥጠው ትውልድ ተከስቶ በአይናችን እያየን ይኼው ኢትዮጵያ በዚህ ዘመን ትድናለች በማይባልበት እርከን ገፍተርዋታል። አሁንስ የተከበብክበት ቀለበት ምን እንደሚመስል ጎብቶሃል? ለዚህስ ተጠያቂው ማን ነው?

ቀዳሚ ተጠያቂው ለበርካታ አመታት “ይህ ሕዝብ በጠላት ቀለበት ውስጥ ተከብቦ መግደያ መሬት ውስጥ ገብቷል እና ከጠላቶቹ  ጋር አትሞዳሞዱ “ስል ስጮህ” እኔን እየዘለፈ አጋሰሱ ምሁር አልሰማ ብሎ ይኼው የዋሁን ሕዝባችን ለስቃይ በመዳረግ ዛሬም ሐፍረት ሳይሰማው  ከገዢዎች ጋር እየጨፈረ አልመከር ብሎ አንዳንዱ አማራ ላይ “ጀነሳይ አልተፈጸመም እያለ፤ አንዳንዱም “ኦነግዋ ከንቲባ” አዳነች አበቤን “የዓድዋዋ አርበኛ እተጌ ጣይቱ ነች” እያለ ሲያሽቃብጥ፤ አዝማሪውም “የአፍሪካ ምልከት” እያለ ክራር ሲከረክር፤ አንዳንዱም “ክቡር ጠ/ሚኒስተራችን አብይ አሕመድን እደግፍ ነበር አሁን ሙሉ በሙሉ ባልደግፈውም አንዳንድ “ራሺናል” አስተሳሰቡን አሁንም እደግፋለሁ” ወዘተ…እያለ ከዚያው አሽከርነት ላልመውጣት እንደ አሳማ ጭቃ ውስጥ እየተጨማለቀ አሽቸግሯል።

ትናትም ዛሬም አገራችን በቅኝ ግዛት እንድትያዝ ያደረገው ይኸየው ዝግምተኛው “ኢቮሊሽኑ” ያላገባደደው ምሁር ነኝ ባዩና ጋዜጠኛ ነኝ ባዩ  አንደ “ቶረተይልስ/ኤሊ” እየተንፏቀቀ የወንጀለኞቹ ፎቶግራፎችና ንግግሮችን በየፌስቡኩ እያዳመቀ ያለ ምንም ሐፍረት  የሚለጥፈው “በግብዝነት የሚንሿዋሻው” መንጋ ካድሬዎቹም  አብረው እያጫፈሩ አፓርታይዱ መሪ  የመኪና ማቆሚያ “ፓርኪንግ’ መርቆ ሲከፍት በመቦረቅ ላይ ነው።

የአማራው ወጣት ሰንፍና እ’ማ “አይወራ” ነው። ተከታታይ ሰላማዊ ተቃውሞ ማድረግ እርሙ ነው። ካደረገም አንድ ቀን አሳይቶ በማግስቱ ይተኛል።

ብዙውን ጊዜ ለአፓርታይዱ አሽቃባጭ ሆኖ የሚታየው የአማራው ምሁር ነው። ይህ ሆዳም ምሁር በውስጥም በውጭ አገርም ጀሮ ዳባ ባለበት ወቅት፤ አማራው እንዲነሳ እና ራሱን ከሞት እንዲከላከል ብዙ መጣጥፎች መጽሐፍቶች ጽፌአለሁ።ብዙ ስደብ ፤ብዙ መነጠል ደርሶብኛል፤ አገር እንዳልገባ ተከልክያለሁ። ብዙ መስዋእት ከፍያለሁ።  ያልገባኝ ነገር እሁንም፤አሁንም ሳስበው ያልገባኝ የውርደቱ ተጠቂ እና የውርደቱ አጥቂ እራሱ አማራ ሆኖ  ዛሬም እዛው እየተላወሰ ሳየው ዛሬም እንቆቁልሹ አልፈታ ብሎኛል።

(አማራ ስል (ገበሬውን አደለም) ምሁሩንና ወጣቱን ነው። ነፃነት የሚባለው ‘አስቂኝ ነፃነት’ የሐፍረት ማቅ ለብሳ “እርቃንዋ ሆና በምትወዛወዘዋ ኤርትራ ምድር” ድረስ ሄደው በ1984 ዓ.ም አስመራና ከረን ከተሞች ተገኝተው “ለኤርትራ ስቃይ” እኛ አማራዎች ነን እና “ ይቅርታ እንድታደርጉለን ይቅርታ  እንጠይቃለን’ ብለው ጥቂቶች ከጎጃም እና ከአዲስ አበባ የተመረጡ ሆዳም አማራዎች  እና ብአዴን ውስጥ የተሰገሰጉት ኤርትራኖች በሆኑት እነ ታምራት ላይኔ (አማራ) ፤ አዲሱ ለገሠ (ኦሮሞ) ተፈራ ዋልዋ (ኤርትራዊ ጌድኦ) ፤ በረከት ስምኦን (ኤርትራዊ) ፤ ታደሰ ካሳ (ትግሬ/የሰቆጣ አገው)፤ ካሳ ተክለብርሃን (ትግሬ/የሰቆጣ አገው) ፤ሕላዌ ዮሴፍ (ኤርትራዊ) በአማራው ስም ይቅርታ ጠይቀዋል። ዛሬ ከነሱ የባሱ በጋዜጠኛነት ስም የተሰገሰጉት ለስርዓቱ  ባደረው በብርሃኑ ነጋ መሪነት (የድሮ ኢሳት ባልደረቦች እና የግንቦት 7 ኣባሎች) የሚመራው ኢዘማን በመከተል እነ ሲሳይ አገና (ዋሺነግተን ዲሲ)፤ ፋሲል የኔአለም (አምስተርዳም) ፤ ግዛው ለገሰ (ሜሪላንድ)፤ ወንድማገኝ ጋሹ፤መሳይ መኮንን፤ እንዲሁም በግላቸው ታማኝ በየነ ፤ የሕግ መምህር አለማየሁ ገበርማርያም (አልማርያም) ፤ ጸሐይ ማተሚያ ቤት ባለቤት “ኤልያስ ወንድሙ” ፤ ሳሙኤል ፈረንጅ (የድሮ ጋዜጠኛ)፤ ዮናስ ብሩ (የቀድሞ አለም ባንክ ሰራተኛ)  ንአምን ዘለቀ ፤ የሕግ ጠበቃ ደረጀ ቡልቲ (አባቴ የዛች ሰዓት መጽሐፍ ደራሲ ፤ በደረግ ዘመን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ አድርገው ኤርትራ ውስጥ ከተገደሉት አንዱ የነበሩት የአርበኛው ኢትዮጵያዊ ኮለኔል ቡልቲ ልጅ) ፤

 ….ወዘተ..ወዘተ…የመሳሰሉ ሰዎች ስርዓቱን ሲከላከሉ ታጋዮችን እያንቋሸሹ ብዙ የጣሩ ናቸው።

ስርዓቱን እየመሩት ባሉት ”የኦሆዴድ ብልጽግና እና በየክልሉ የተሾሙት የአብይ አሕመድ “ሳተላይቶች” የተቀናጀ የወንጀለኞች ትብብር ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠር አማራ ለስደት፤ ለሞትና ለስቃይ ተዳርጎ እያለ፤ ከ4 አመት በፊት ወንጀለኞች ነን ብለው አምነው “ምለው ጥለው” አይደግመንን ብለው ሕዝብን አሞኝተው ወደ “ሥልጣን ዕርካብ” ከወጡ በኋላ የከፋ ጭፍጨፋ አድርሰውበት እያለ እያም ቢሆን  ዛሬ የባሰውኑ የአማራ ወጣት (ትንሽ መሻሻል ቢያሳይም) ከፉከራ ውጭ ያሳየው ተጨባጭ ትግል የለም።

አማራው የዘር እና የሃይማኖት ጭፍጫፋ ተካሁዶበታል። በርካታ የዩኒቨርሲቲ አማራ ወጣት ሴቶች ታፍነው ጠፍተዋል። ዛሬ ድግሞ አርደው ከገደልዋቸው በኋላ በሞቱት ወንዶች ላይ “ግበረሰዶም እየፈጸሙ እንዳለ ታውቋል። በወንዶች ላይ ኦሮሞ ነፃ አውጪ ነን የሚሉ ታጣቂ ቡድኖችም “በወንዶች ላይ ግበረሰዶም እንደሚፈጽሙ” እራሱ ኦሮሞ ክልል መሪ የሆነው ሺመልስ አብዲሳ በአደባባይ የተናገረውን አውድዮና ቪዲዮ በመረጃ ቲቪ ዲያቆን ዘመድኩን በቀለ (ነጭ ነጭዋን) አቅርቦታል። ይህንን የወንጀለኞች ስርዓት በጀግንንት የተጋፈጡ እንደ እነ እስክንደር ነጋ ታምራት ነገራ ፤ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፤ መስከረም አበራ፤ የባልደራስ ምክትል ሓላፊ ስነታየሁ ቸኮል የመሳሰሉ ብዙ አርበኞች ሲታሰሩ ሲፈቱ የነበሩ በመጨረሻ ታምራት ነገራ አገር ጥሎ ለመውጣት ሲገደድ እስክንድር ነጋ ደግሞ “ታፍኖ” ይሁን ወይንም “የት እንዳለ” አይታወቅም።

 በጎንደር እና በጎጃም የተነሳው “ፋኖ” የተባለው አልገዛም ብሎ የደፋሮች ተዋጊ ሃይል እርቅ በሚል ሰበብ አኮላሽተውት እና እምቢ ያሉትንም በሆዳም አማራ ትብብር ታድነው በጥቆማ እየተገደሉና እየተያዙ ናቸው። ደብረማርቆስ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳለ ይነገራል፤ ሆኖም “ቀጣይነት ይኖረዋል ወይ? የሚለው የዘወትር ጥርጣሬየ ነው።አዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ለተቃውሞ እንደተነሱ ተዘግቧል፤ ቀጣይነት ይኖሮው ይሆን? ሓኪሞች ተቃውሞ አስሰምተው በአፓርታይዱ መሪ አስነዋሪ ስደብና ውርደት ከደረሰባቸው በኋላ አንዳንዱ አገር ጥለው ሄደዋል ብዙዎቹም ወደ ተቃውሞ አልተመለሱም። ታዲያ እንዴት እንዲህ ሊቀጥል ይቻለዋል?  

የአማራ ወጣት የዘመናችን ኢትዮጵያዊ አስገራሚ ጀግና አሳምነው ጽጌ የመሰለ “የወንዶች ልክ” ለሞት ተዳርጎ እያወቀ የአማራ ወጣት ከፉከራ እና ከሙዚቃ ቀረርቶ ያለፈ አገር አንቀጥቅጥ ሕዝብን የሚያነሳሳ የቁጭት እና የቁጣ የይለይለት ትግል አላደረገም። ለምን? መልስ ስጡ ልስማችሁ! ዘመነ ካሴ ታስሮ መሬት አርዕድ ተቃውሞ ከማሰማትና ብረት ይዞ ጫካ ከመግባት ይልቅ “እኔም ዘመነ ካሴ ነኝ” ብሎ “እራሱን እቤቱ ውስጥ አስሮ” ቁጭ ያለ ቦቁባቋ አማራዊ ወጣት በማየት የሚገርም ትዕይነት ውስጥ ደርሰናል።

በብአዴን ተረከዝ እየተጓዘ ያለው አብን የተበለው “ጉድ ፎር ናቲንግ”  የአማራ እናቶች፤ህጻናት እና አረጋውያን የእንሰሳት ህይወት መስሎት የአማራ እናቶች ደም እና ሬሳ ሳይደርቅ፤ ሬሳቸው አፈር ሳይለብስ  ከአማራ ገዳዮች እና ጸረ ኢትትዮጵያ ሃይሎች ጋር እየተሞዳሞደ ቁጭ ብሎ ከእባብ የዕርግ እንቁላል ሲጠብቅ ማየት እጅግ የሚገርም አስደንጋጭ ክስተት ነው (አንዳንዶቹም ኦነግ በተሰገሰገበት ፓርላማ ውስጥ ገብቶ የማይረባ ልፈፋ ሲለፍልፉ አብይ አሕመድ ሲያሾፍባቸው ይውላል)። አንዳንዱ ደግሞ “ፖለቲከኞች ስለሆኑ ለነሱ እንተው” የሚሉ አማራ ወጣቶች የሚጽፉትን ሳነብ “ይህ አርግፍ አድርጎ ፖለቲከኞን የማመን፤ፖለቲከኞችን ያለመወጠርና ሁሉም ነገር በነሱ ላይ የመተው  “ሲንድረም” መቼ እንደሚተው ሳስበው ችግሩ የሚፈታ አይመስለኝም።

27 አመት በወያኔ ትግሬዎች 4 አመት በኦሮሙማ ኦሮሞዎች በቅኝ ግዛት እየማቀቅክ የምትገኝ ኢትዮጵያዊ  ሆይ! ዘሬስ ቀለበት ውስጥ እንዳስገቡህ ገባህ አይደል? ጉሮሮየ እስኪደርቅ ሌት ተቀን ስነግርህ የነበረው ማስጠምቀቂያ እወን አልሆነም ልትለኝ ነው? የምፅአተ አማራ ደራሲ ክቡር አቶ ተክሌ የሻው እንዳሉት “ሁልጊዜ ጉድ፤ ዘወትር ጉድ፤ ዝምታና ጉዱ እስከመቸ?”

ጽሑፉን ላላነበበ እንዲደርሰው አዳርሱት

ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)