Saturday, April 13, 2024

ክፍል 2 የወያነ ፍቅር ሰግጦ የያዘው የአማዞንን ገበያ ያጨናነቀው……የያሰው ሽመልስ መጽሐፍ.... ከሚል የቀጠለ.... ከጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 4/13/2024

 

ክፍል 2

የወያነ ፍቅር ሰግጦ የያዘው የአማዞንን ገበያ ያጨናነቀው……የያሰው ሽመልስ መጽሐፍ.... ከሚየቀጠለ....

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

4/13/2024

ባለፈው ክፍል 1 ደራሲው ያየሰው ሽመልስ ባሳተመው “የራ እርካብ የደም መንበር” መጽሐፉ ውስጥ ስለተጨፈጨፈውና ስለተከዳው የሰሜን ዕዝ የኢትዮጵያ ሠራዊት (ደራሲው የተማረከው የሚል ቃል ይጠቀማል) በሚመለከት ደራሲው ሆን ብሎ ያዛባቸው ‘ዘገባዎች’  ምን እንደነበሩ ለአጠቃላይ ዝርዝር በክፍል 2  እንደምገልጻቸው ቃል ገብ ነበር፡፡

  የማቀርበው ላብዛኛው ትግሬዎች መመኪያና መፎከሪያ የነበረው ትግዎች የተቆጣጠሩት የ27 አመት ጨካኝ ሥርዓት በፖለቲካ እስረኞች ላይ የፈጸሙት ግፎች <<የፍትሕ ሰቆቃ>> በሚባለው ብዙዎቻችንን ያስደነገጠ የግፍ ዘገባ (ፊልም) (በ Ethiopian Semay በዚህ ድረገጽ ወደቀኝ በኩል የምታዩት ፎቶ “ዮናስ” የተባለው ‘ፓራላይዝ’ የሆነበትን የግርፋት ታሪክ የሚያሳይ የተለጠፈው ቪዲዮ) አለመፈጸሙ ደራሲው ያየሰው ሸመልስ “ድራማ” በማለት ያጣጣለው  ክርክሩ ነኛ ስላልመሰለኝ ለታዛቢ ልተወው፡፡ ዛ የማሳያቸው ግን በገባሁት ቃል መሠረት ሎች ክሕደቶቹን (ውሸቶቹን) እንመለከታለን፡፡

በያየሰው ሽመልስ መጽሐፉ በገጽ 54 በተጠቀሰው ንባብ ላስታወሳችሁ

 << (ወታደሩ) ሲኖትራክ ተነዳበት ወዘተ፣ የሚል ፕሮፓጋንዳ ያመጣው የሕዝብ ልብ ለመግዛት በሚል ነበር፡፡ ደግሞም ተሳክቷል፡፡ ይህ ሁሉ እንዳልተፈጸመ የትግራይ አመራሮች ብቻ ሳይሆኑ ዐብይም፤ብርሃኑ ጁላም ሆነ አዳምነህ መንግሥቴ (የሰሜን ዕዝ ሲማረክ ምክትል አዛዠ የነበረው ያውቃል፡፡>> “የራ እርካብ የደም መንበር (ገጽ 54)”

ጦሩ አምበጣ ሲያባርር እና የትግራይ ድሃ ተማሪዎች ደብተር መግዣ ሲያዋጣ ውሎ ደክሞት በተኛበት ወቅት አዘናግተው በመላ ትግራይ በተዘረጉት ወታደራዊ ካመፖች ከብበው በድንገት በጭካኔ በጥቅምት 24 2013 እንዴት እንደጨፈጨፉት እና በርካታ ካምፖች የትግራይ እናቶች ሠራዊቱ ሲታፈን ፈንድሻ እየበተኑ፤ቀ እየነሰነሱ ከበሮ እየመቱ የሠራዊቱን አስኬን እምቧለሌ እየዞሩ እንደጨፈሩበትናገድላችሁ ደማቸውን አሳዩንያሉ የእናት አንጀት የሌላቸው እናቶች ደግሞ ወጣቱን አነሳስተው ሠራዊቱን አስጨፍጭፈዋል። የሚል የወታደሮቹ እሮሮ መስማታችሁ እገምታለሁ፡፡

በዚያ ጭፍጨፋ የትግራይ ሕዝብ ሱታፌና ታጣቂ የትግራይ ሠራዊት ምን እንደፈፀመ ከጭፍጨፋው በተአምር የዳነው የዓይን ምስክር ደራሲ የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ የሆነ ፤ የአምሳ አለቃ ጋሻዬ ጤናው (ቻቻው) ከጻፈው መጽሐፍና ካጠናቀራቸው የሰለባው ዓይን ምስክሮች በያየሰው ሽመልስ የተካደ ከላይ የተጠቀሰው ጉዳይ አጋራችለሁ።

ጦርነቱ በሁለቱም ፋሺስት ቡደኖች መካክል የተከሰተው ፍትግያ ምክንያት ቢሆንም ለጦርነቱ መከሰት ዋነኛው ቆስሽና ናፋቂ “በተፈጥሮ ስጦታ  የተቸረን ጥንታዊ የነጋሽና የአንጋሽነት መንበረ  ሥልጣናችን ከተቀማን ያለ ትግራይ መኖር የማትችለውን ኢትዮጵያን በትነን “ሃገረ ትግራይ” ለመመስረት እስከ ጦርነት ድረስ እንሄዳለን ብለው እየዛቱ እንደነበር ከጦረነቱ በፊትና ጦርነቱ ሲካሄድ ብዙ የጽሑፍና የንግግር የስብሰባ ቪዲዮዎቻቸውን ማቅረቤ አንባቢዎቼ ታስታውሱ ይሆናል፡፡ ሰለዚህም “ሥልጣናችን ከተቀማን ወደእየ መንደራችን እንበታተናለን” ባሉት ዛቻ መሠረት ያየስው “ከጥቂት ቀናት በፊት አብይ ተቀደመ እንጂ ...” እያለ የጦርነቱ ናፋቂዎችና ጫሪዎች ወያዎች እንደነበሩ በማያሳጣው ብልሃት ለመከላከል ቢሞክርም ፈላጊዎቹ “ጦርነት ለትግራይ ሕዝብ ባሕሉ ነው” ባዮቹ ነበሩ፡፡

በዚህም “ተቀደመና ተማረከ” እያለን ያለው ሊነግረን የለገመብን የያየሰው ብዕር ጠልቆ ሊነግረን ያልፈለገው አሰቃቂው የወያነ ወንጀል በዓን ምስክሮችና ተጠቂዎች የተነገረ ታሪክ ግን ፤ የሃገሪቱ ብቸኛ ሠራዊት ተኝቶ ባለበት ከባድ መሣርያ በቦም፤በአርቢጂ(ላውንቸር)፤በመትረየስ ከነ ሕጻናት ልጆቻቸውና ሚስቶቻቸው ታርደው ተጭፍጭፈዋል፡ አንገታቸው በቢላዋ ተቀልቶ፤ ሴት ወታደሮችም ጡታቸው ተቆርጦ ፤ ሕዝብ በተሰበሰበበት ምን ዓይነት ግፍ በሠራዊቱ ሕይወትና ክብር እንደተፈጸመ ነው፡፡ ያንን እንመለከታለን፡፡

 ታዲያ ያየሰው ለወያኔ ካለው ሥስ ልብ ይህንን ጉድ በመዝለል “አልተፈጸመም” ወይንም ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የተነገረ ነው” በማለት በወያኔ አጥር ተንጠላጥሎ ጮክ ብሎ ይናገራል በመጽሐፍ ውስጥ፡፡

ከተፈፅሙ ጭፍጨፋዊ ስልቶች ወታደሮችን በታንክና በሲኖትራክ ጨፍልቆ መግደልን በሚመለከት በላ የምንመለከተው ቢሆንም የጭካኔ አገዳደል ስልቶችን በማንና የት ቦታ እንደተፈጸሙ በ “ቻቻው” መጽሐፍ (በየተከዳው የሰሜን ዕዝ መጽሐፍ) በህወሓት የግፍ በትር ጥቅምት 24 እና እሱን ተከትሎ በነበሩ ቀናት በግፍ ለተጨፈጨፉ የሰሜን ዕዝ ጓዶች>> ከሚለው አስገራሚ መጽሐፍ ውስጥ ሰለባዎቹ ታሪክ እንዲዘግብላቸው ወታደሮቹ ያጋጠማቸው አሳዛኝ ግፍ እንዲህ በማለት ይነግረናል፡፡

<<ምንም የሌለበት በረሃ ውስጥ በሀገራቸው በህዝባቸው ተከበው ህዝብ ናፈቃቸው፡፡ ተስፋ ቢያደርጉም ፤ቢመኙም፤ቢሳሉ፤ ቢፀልዩም የሚረዳቸው፤ አይዟችሁ የሚላቸው፤ የሚደርስላቸው አልነበረም፡፡ ዙርያቸው ትናንት ሲጠብቋቸውና ሲሞቱላቸው የነበሩ ክሀዲዎች ጠላት ሆነው ሊበሏቸው ሊሰለጥቋቸው ደርስዋል፡፡ ወታደሮቹ ወደ ሰማይ ቢያነጋጥጡ ወደ ምድሪቷ ቢያፈጡ መውጫ መንገድ መድበቂያ ጉድጓድ የላቸውም..፥ የደካሞችን ሰብል ሲያጭድና ሲሰበስብ ፤አምበጣ ሲያባርርላቸው የዋለው የደከመው ሠራዊትን ወጣቶቹ “የአብይ አምበጣ ካገራችን ውጣ” እያለ አስጨነቀን  ...’’ በማለት አስቸጋሪው ነብስ ግቢ ፤ ነብስ ውጪ በሆነበት ለማንበብ ቢሚያስጨንቅ ከባድ ሁታ ይገልጽና እናቶችም “የነዚህ አምበጦች ደም አፍስሳችሁ አሳዩን” እያሉ እናቶቸ ራሳቸው ወደ ሠራዊቱ ድንጋይ መወርወር ጀመሩ .... እያለ ከህደት 1 2 3 4... እያለ ሠራዊቱ ላይ የተፈጸሙ ገፎች ይዘረዝራል፡፡

አንባቢዎወታደሮቹን በታንክና በሲኖትራክ መጎተትና መጨፍለቅ እንደተፈጸመ አልረሳሁትም ለሚቀጥለው ላቆይና ይህንን ግፍ እንመልከት፡፡

 “ገርሁ ስርናይ” በተባለ ከተማ/ገጠር ትግራይ ውስጥ ነው፡፡ (ትርጉሙም ‘’የስን ሮ” ማለት ነው፡፡

<<ጥይት አልቆበት እጅ መስጠቱን የተበሳጨ አንድ ጓድ፤ አውሬ የሆኑ የጁንታው ደጋፊ ሕዝብና ታጣቂ ከነሻለቃው የተሰው ጓዶችን ሬሳ ሰበሰቡ፡፡ ክአስከሬናቸው ላይ ልብሳቸውን አወለቁ፡፡ የሰራዊቱ ክበብ ውስጥ የነበረ ቢራና ልዩ ልዩ መጠጦችን አወጡ፡፡ ራቁቱ ባደረጉት አስከሬን ላይ የሰራዊቱን ቢራ እየጠጡ ፤ ከበሮ እየመቱና የደስ ደስ ጥይት እየተኮሱ ጨፈሩ፡፡ ይህንን ያደረጉት ከሞት የተረፈው ሠራዊት ቆሞ እያየ ነው፡፡ ፍርድ የኢትዮጵያ አምላክ! ይላል ደራሲው “ቻቻው በሐዘን”፡፡

በመቀጠልም፤

“ይህ አልበቃ ሲላቸው እዛው ገርሁ ስርናይ ከተማ  እጅ በሰጡ ሴት ወታደሮች ላይ የተሰራው ግፍ ሕሊና ያቆስላል፡፡ እጅ ከሰጡት ውስጥ ሴት ወታደሮችን ልብሳቸውን አስወለቁ፡፡ ወደ ብልታቸው እንጨት እየከተቱ አሰቃዩዋቸው፡፡ ስቃዩን መቋቋም ሲያቅታቸው ለመንፈራገጥ ሲሞክሩ ፅጉራቸውን ይዘው መንገድ ላይ ጎተትዋቸው፡ ይህ አልበቃቸው ሲል ራቁታቸውን እንደሆኑ የከተማው ሕዝብ እያያቸው እንዲሮጡ አደረጉ፡፡ ይህን የሚያደርጉት ክበሮ ይዘው እይጨፈሩና ራቁታቸው የሆኑትን ሴቶች ፎቶ እያነሱ ቪዲዮ እየቀርፁ ነው፡፡

በበደል 3 የጠቀሰው አሳጥሬ ላቅርበውና “ቻቻው” እንዲህ ይላል፡፡

<< የተወስኑ ጋዶች አንድ ላይ ሆነው ወደ ኤርትራ ለመሻገር እየተጓዙ እያለ ለሚሊሺያማ እጄን አልሰጥም በማለት የራሱን ከላሽ ወደ ጭንቅላቱ ተኩሶ ራሱን አጠፋ፡፡ በሌላ አቅጣጫ የሚጓዙ ጋዶችም እንዲሁ ሚሊሾያዎች አገኝዋቸው፡፡ በገጀራም አላረዷቸውም፡፡ አካባቢያቸው ወዳለው በድንጋይ ወደ ተሞላ ጥልቅ ገደል ወሰድዋቸው፡፡ ተራራው ጫፍ ላይ ሆነው ተፈጥፍጠው እንዲሞቱ ወደ ገደል ወረወሯቸው፡ ይኸኔ ወደ ገደል ከተወረወሩት “ብቻየንማ አልሞትም” ያለው ሀ/አለቃ አማረ አጠገብ ሆኖ የገፋውን ሚሊሺያ ይዞት ወደ ገደል ተወረወረ፡፡ሚሊሺያውም እርሱም ገደል ውሰጥ ተፈጥፍጠው ሞቱ፡፡>>

ከዚህ ቀጥሎ የምንመለከተው ትግራይ ውስጥ “ዓዲ ምኢቲ” በሚባል ወታደራዊ ካምፕ ኮረብታማ አካባቢ፤ ርሃብ ሳይበግረው፤ረዳት ሳይኖው የካሃዲው ወያ ሠራዊትን ሳ በሳ እያደረገ የነበርውን እሳታዊ ሠራዊት ጥይት አለቀበትና ምንም የማይችል ተራ ሰው አደረገው፡፡የጥይት ያለህ! ቢል ጥይት የለም፡፡

ግድ አጅ መስጠት ሆነና ሠራዊቱ  በልዩ ሃይል እጅ ወደቀ፡፡ ከዚያ የሆነውን እንመልከት   

<<ከሠራዊቱ ጋር ሆነው ሲዋጉ የነበሩት የትግራይ ተወላጆች ሾልኮው ከልዩ ሃይሉ ጋር ሲቀላቀሉ፤ ቆስለው የነበሩት ደግሞ መታወቂያ እያዩ እየመረጡ ሲያወጡ ቆስለው መትረፍ ሊችሉ የነበሩትን የላ ብር ተወላጆች የሚያነሳቸው አጥተው ደማቸው እየፈሰሰ እየጮሁ ወድቀው ቀሩ፡፡ በህይወት የቀሩትንም መሳርያ፤ጩና ገጀራ የታጠቁት ልዩ ሃይሎች ለናንተ ጥይት አናባክንም በማለት እጃቸው የሰጡትን ማረድ ጀመሩ፡፡

አምስት ጋዶችን አንገታቸውን እየቆረጡ፤ሆዳቸውን እየዘከዘኩ፤ዓይናቸውን እያውጡ፤የወንዶችን ብልት እየቆረጡ፤የሰውን ገላ እንደጨርቅ እየተረተሩ በታተኑት፡፡

ከገደሏቸው ውሰጥ የአስር/አለቃ ስንታየሁ “እውነተኛው አኖ” ነው፡፡ መጀመሪያ ጡቶን ቆረጡ፡፡ቀጥሎ አንገትዋን ቆረጡ ፤ አንገንና ጡቶን ዛፍ ላይ አንጠለጠሉ፡ ይህን ሲያደርጉ ሠራዊቱ ያያል፡፡ ድምበር ተሻግረው ወደ ርትራ የተሻገሩት ተደራጅተው ተመልሰው እያጠቁ ቦታው ላይ ሲደርሱ እነኚህ የታረዱ የዶችን ሳ በቦታወ አገኙት፡፡የስንታየሁ ጡትና ጭንቅላትም ዛፍ ላይ  እንደተንጠለጠለ ተገኘ፡፡ ይህንን የባድመ ግንባር እየመሩና እያዋጉ የነበሩት ሪር አድሞራል ክንዱ ገዙ መስክረዋል፡፠.። >>

እያለ የተከዳው የሰን እዝ ደራሲ የ፶ አለቃ ጋሻዬ ጤናው የተፈጸሙ ወንጀሎች ነግሮናል፡፡

እንግዲህ ይህ ጉድ ሲፈጸም ያየሰው ሽመልስ ገና “መብረቃዊ ጥቃት ብለው ወያዎች የሚጠሩት” ዓለም ዓቀፍና ብር ተኮር የጭፍጨፋ   ወንጀል ሲፈጸም ፤ የትግራይ ታጣቂዎች ብር ለይተው እንዳላጠቁ በገደምዳ ለመሸሽ  የሞከረው በብር ለይቶ የተፈጸመ ግድያ መግደል ገና አልገባሁበትም “ከአማራ ሕዝብ ላይ ጠብ የለንም ይላሉ በሌላ በኩል ደግሞ የአማራን ልጆች ከጦሩ እየለዩ ሲረሽኑ ነበር።” የሚለው የወታደሮቹ አስለቃሽ ታሪክ ገና አላቀረብኩም፡፡

<< (ወታደሩ) ሲኖትራክ ተነዳበት ወዘተ፣ የሚል ፕሮፓጋንዳ ያመጣው የሕዝብ ልብ ለመግዛት በሚል ነበር፡፡ ደግሞም ተሳክቷል፡፡ ይህ ሁሉ እንዳልተፈጸመ የትግራይ አመራሮች ብቻ ሳይሆኑ ዐብይም፤ብርሃኑ ጁላም ሆነ አዳምነህ መንግሥቴ (የሰሜን ዕዝ ሲማረክ ምክትል አዛዠ የነበረው ያውቃል፡፡>> የሚለው “የራ እርካብ የደም መንበር (ገጽ 54)” ደራሲና ጋጠኛ ያየሰው ሽመልስ፤ ፈጣጣ የታሪክ ማዛባት በክፍል 3 አቀርባለሁ፡፡

እስከዛው ሰላሙን ለናንተ ይሁን፡፡

ጌታቸው ረዳ