Friday, January 22, 2016

ቅር ሳይላቸው የሚናደፉ መርዝ ፖለቲከኞች (ክፍል 1) ጌታቸው ረዳ(Ethiopian semay ድረገጽ አዘጋጅ)ቅር ሳይላቸው የሚናደፉ መርዝ ፖለቲከኞች
(ክፍል 1)
ጌታቸው ረዳ(Ethiopian semay ድረገጽ አዘጋጅ)
Ethiopia Greeting you to all -Ethiopian Semay

 “የኦነግ ሽምጥ ተዋጊና አመራር አባል የነበረው” ዛሬ “ኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግምባር” ፡ በሚል ከኦነግና ከወያኔ የፖለቲካ መስመር ያልሸሸ የፖለቲካ መርሃግብር (ፕሮግራም) ነድፎ የኦሮሞን ሕዝብ ቋንቋን መሰረት ባደረገ “በክልል” እና “የነገድ ፌዴራሊዝም” መርህ “ራስን በራስ ማስተዳዳር” የሚባል ስርዓተ ስልት ለማስፈን እንዲያመቸው ከኦነግ ተነጥለናል ከሚሉን ኦሮሞ ብሄረተኞች “አንዱ ዶ/ር በያን አሶባ” ባለፈው ሰሞን አዲስ ድምጽ ራዲዮ እንግድነት ቀርቦ ስለሰነዘረው አመለካከት እተቻለሁ።

በያን አሶባን ማሞገስ የማያቆመው አበበ በለው የተባለው የአዲስ ድምፅ ራዲዮ አዘጋጅ ፤ከዶ/ር በያን በተጨማሪ፤ ዶ/ር አረጋዊ በርሄን እና የሞረሽ አማራ ሲቪክ ድረጅት ፕረዚዳንት ክቡር አቶ ተክሌ የሻውን ሦስቱንም ጋብዞ በወቅቱ “በኦሮሚያ ኬኛ” እንቅስቃሴ ያላቸው እይታ ለሕዝቡ እንዲያካፍሉ ጋብዞአቸው አድምጬአለሁ። ሁለቱም የብሔር አቀንቃኞች ቢሆኑም ከነሱ ሚጠበቅ ንግግር አስደምጠውናልና ብዙም አልተገረምኩም። አቶ ተክሌ ግን መካካለኛ መልስ ቢሰጡም ኦነግ መስማት የነበረበት ወንጀሉን ከመናገር ተቆጥበዋል። ይህም ከራዲዮኑ ባለቤትና ከመድረኩ ለዘብተኛነት ሊፈቅድላቸው እንደማይችል እንደሆነ እገምታለሁ። አስገራሚው ደግሞ፤ ‘ኢትዮ-ሚዲያ’ የተባለው ድረገጽ “መደመጥ ያለበት” ተደናቂ ውይይት ሲል በድረ ገጹ ለጥፎታል። መደመጥ ያለበት እምኑ ላይ እንደሆነ አልገባኝም።

ዶ/ር አረጋዊ ወዳጄ ቢሆንም፤ ለሌሎች መውቀስ ያለብኝን ለእርሱም መንገር ስላለብኝ በአረጋዊ ንግግር ልጀምር። ስላለፈው በደል አናንሳ የሚል ቅኝት አስደምጦናል።
ለምሳሌ አቶ ተክሌ ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን አማራውንም እየተበደለ ነው እና ኢትዮጵያዊ ጉዳት ነው ብለን ለሁላችንም በሚያስተሳስር መልኩ መንገድ እናስይዘው፤ ብለው ኦሮሞው ብቻ ሳይሆን አማራውም በየቦታው እንዲሁም በቅርቡ ወር/ሳምንት በዛው በሸዋ ምድር የደረሰበትን መከራ ለመናገር አንዲት “የለሰለሰች ሐረግ” ለመሰንዘር ሲሞክሩ፤ ዶ/ር በያንም ‘በእስላሞች በዓል ት/ቤቶች ሳይዘጉ እንደነበር” ሲናገር፤ “አረጋዊ በርሄ” ያለፈው አልፏል፤ “ስለ ትናንት ክረምት ቤት አንሰራም፤ ስለመጪው ክረምት እንጂ” ሲል ሁሉንም ዝም ለማሰኘት ሞክሯል።ነገሩ በክፋት ባይሆንም፤ ግን የተዘነመጋ ነገር አለ።

በአማራ ሕብረተሰብ ላይ በኦሮሞ ነፃ አውጪዎችና ኦሮሞ እንወክላለን በሚሉ “መርዝ ፖለቲከኞች/venomous politicians” እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ እየተንገላቱ ያሉ፤ የነዚህ ግምባሮች  “ሰለባ” የሆኑ የአማራ ሕብረተሰብ ገበሬዎችና ሰራተኞች ሰቆቃ በምንና በማን  ምክንያት ለጥቃት እንደተጋለጡ እንዳናዳምጥ፤ “ዝጋ ዝጋ ፖለቲካ” በማስቀደም፤ “ፖለቲካውን ብቻ እንነጋር የሚለው አይጥመኝም።

ያንን መንግሥት ስንመሰርት እንነጋገርበት” ዓይነቱ አነጋገር፤ ጥቃቶችን፤በደሎችን “ከፖለቲካው አንድነት” በፊት ድርጅቶች የፈጸሙዋቸው ወንጀሎች እንዳይነገሩ “ገበናዎች ሁሉ፤ ሁሌም ለወያኔ እየተሰጠ” ለመሸሽ ከተሞከረ “ፖለቲካው የተቃና አያደርገውም።ምክንያቱም ሆድ እየተቀየመ ጠረጴዛ ላይ አብሮ ለይስሙላ መቀመጡ፤ ዘለቄታ የለውም።እንደዚህ ከቀጠለ፤ እያታለላችሁ ነው የሚል ስጋት አለን። ይህ ደግሞ ለናንተና ለፖለቲካው እረፍት አይሰጥም።

ምክንያቱም “ዋች ዶግስ/watchdogs” የምንባል ክፍሎች እና ኢንተርኔት ሚዲያ  እስካለን ድረስ ነገሩ ሊታፍቡት ከቶ አይቻላችሁም። ድርጅቶች በወንጀለኞች ተሞልተዋል፤ ሕዝብ እንዲባረር፤ እንዲጨፈጨፍ ያደረጉ የድርጅት መሪዎች ዛሬም ተመቻችተው “በውጭም በውስጥ አገርም ፖለቲካውን እየመሩት ነው” ። አረጋዊ በርሐ ነገሩን ሊያስተኛ የሞከረ ይመስለኛል። ልክ አይደለም። “በሗላ ፤በሗላ እንነጋገርበት” ተበዳዮች፤ “አታልቅሱ፤አፋችሁን በመሃረም-ዝጉ፤ አታስነጥሱ” የሚለው ስልት እጅግ ከሚያበሽቀኝ ንግግር ቢኖር ይህንን መሳይ ንግግር ነው። ይህ ደግሞ ብዙ ጊዜ እስኪሰለቸኝ ድረስ አድምጨዋለሁ።

 ያለፉት ስርዓቶች የፈጸሙት ወንጀል ሲነሳ “ያበቃለት ነው”፤ “ጊዜው አልፏል”፡ ወያኔ እያደረሰው ያለው “ወንጅል” ብቻ ለሕዘብ ተናገሩ የሚለው ፍትሓዊ  ንግግር አይደለም። ተከሳሾቹ የሉም፤ ከሳሽም የለም ማለታችሁ ነው።

ከሳሽና ተከሳሽ በምትሰበስቧቸው አዳራሽ ውስጥ አብረው ዓይን ለዓይን እየተያዩ እያወቃችሁ፦“ተጠያቂዎቹ በሞት እስኪለዩ ድረስ፦ “ዝም” በሉ፡ በሞት ሲለዩ በሗላ “እሪታችሁን አስሰሙ”፤ ወይንም “አሁን ስላለው ስርዓት ብቻ ጩዅ” ወይንም እኛ የሰራነውን ወንጀል ‘ከጻፋችሁ/ከተናገራችሁ’ ሕብረት አይኖርም። የሚለው ንግግር እጅግ ያስገርመኛል። መቸ ነው የሕዝብ ዕምባ በሰፊው ለሕዝብ የመናገር መብት የሚከበር?

ስልጣን ስትይዙ ደግሞ “ዕርቀ ሰላም/ሪኮንስሊየሽን” ላማምጣት ነው እና  ሕብረተሰቡ ሳናረጋጋ “አክራሪዎች” እባካችሁ አትንጫጩ “ዝም” በሉ፤ እንደምንባል የታወቀ ነው። መፍትሄ ስጡን አንጂ!

አሁን ስላለው ስርዓትና አሁን ስላላችሁት የድርጅት መሪዎች የሰራችሁት ገበና አለ። ስለሆነም ‘ወያኔ የፈጸመው ወንጀል ብቻ’ እንጂ ስለ የእኛ ገበና ማሕደር  “ነገ” ጠይቁን ማለት ምን ማት ነው? እናንተ ያስለቀሳችሁት ደም እምባ እያለቀስ የሚገኝ ‘ሕዝብ/ግለሰብ’ አለ፡ ንብረታችን፤ሚስቶቻችን ተነጠቀን፤ ተባረርን የሚል አለ። 

አለመታደል ደግሞ ያንን መከራ ለመድገም፤ ወያኔ የሚከተለው “ኤትኒክ ፌደራሊዝም” ስርዓት እንደገና እንደ አዲስ በተጠናከረ “ዲሞክራሲ” የሚል ቅጥያ ስም ጨምረንበት ያንኑ “ፌደራሊዘም” የሚባለው “ራስን በራስ ማስተዳዳር” አናካሂዳለን “ከዚያ ፍንክች አንልም” የሚሉ የነ ዶ/ር በያን አመራሮች አሁንም በይፋ እየተናገሩ ነው (በሚቀጥለው እትሜ ሰሞኑን እመለስበታለሁ)።

 የነ ኦነግ፤ የነ በያን አሶባ፤የነ ሌንጮ “ራስን በራስ ማስተዳዳር ስርዓት፤ ለመድግም በግልጽ በመርሃ ግብራቸውና በልሳናቸው ሲነግሩን፤ አሁንም አድማጩ “ግብዝነቱን” ለማጎልበት የሚዲያ ባለቤቶች፤ጋዜጠኞች “መደመጥ ያለበት” እያሉ ሕዝቡን ያደናግሩታል። 

ይህ “የሴቶች፤የነብሰጡሮች፤የሽማግሌዎች የህጻናት እሪታና ልቅሶ ድምጽ” ማን ፈጠረው? በምን ዓይነት ስርዓት? እንዴት ተነሳ? ካሁን በፊት ማን ተካፈለበት? ተካፋዮችስ እንዲህ ያለ አሰቃቃ ድርጊት እንዳይደገምስ ምን እርምጃ ወሰዱ? ለምንስ ዝምታ ተመረጠ?  በወያኔ ብቻ ሳይሆን በኦነግ የተፈጸመ በደል የለም እያሉ ጋዜጠኞች የኦነግ መከታ እና ጠለላ እየሆኑ ነው። ይህ እኛም እናውቃለን። አስከመቸ ሳንነጋገርበት ይቀጥላል?

ወንጀልና ፖለቲካ አብረው ሲሄዱ የሚያስከትለው መዘዝ ጋዜጠኞች ሕዝቡን ሊያስተምሩት አልቻሉም። አለመታደል ሆኖ ሕዝብን በማተራመስና በመጨፍጨፍ የተካፈሉ ድርጅቶች፤ባለፈው ገበናቸው ሳይጸጸቱና ሳይነግሩን፤ ጋዜጠኞች እየተከላከሉላቸው፤ ‘በማሞገስ’ የልብ ልብ እንዲሰማቸው እያደረጉ ዛሬም፤ ለወደፊትም አገሪቱ እንዲያምሱ የተመቻቸ መድረክ እየሰጧቸው ነው። በማሞጋገስ!በማሞካሸት!። ወንጀል ስለፈጸሙ ድርጅቶች በመከላከል ጋዜጠኞች አሳፋሪ ባሕሪ ውስጥ እየገቡ ነው።

ለምሳሌ አንድ ማስረጃ ልስጥ፦ 

 ዘሐበሻ የተባለው ድረገጽ ሰሞኑን የዘገበው አሳፋሪ ባሕሪ ልንገራችሁ።- የመጀመሪያዎቹ ሰልጣኞች ኤርትራ ከሄዱ በሗላ ግንቦት 7 ግፍ ፈጻሚ ነው ብለው ከድርጅቱ ሸሽተው የመጡ ተዋጊዎች ነበሩ። ግንቦት 7 ሰቆቃ ፈጽሞብናል፤የሰው መሰወር/ግድያ/እስር/ድብደባ አደረሶብናል፤የድርጅቱ መሪዎች ባሕሪም እጅግ ከጠበቅነው በላይ የተበላሸ ነው፤ በማለት ስለ ድርጅቱ ያዩትን መጥፎ አሰራር ለመግለጽ ሚዲያ ተነፍጓቸው የነበሩ ግፍ ደረሰብን የሚሉ የግንቦት7 ተዋጊ የነበሩ ግለሰቦች፤ “ለግንቦት 7 ሳተላይቶች- ‘ለኢሳት እና ዘሐበሻ’ እንዲሁም ለሌሎች ሚዲያዎች ደብዳቤ ጽፈው በይፋ የግንቦት 7 መሪዎችና እኛን ጋብዛችሁ በሕዝብ ፊት አነጋግሩን ሲሉ ‘ነጻነት ተነፍጓቸው፤ ሻዕቢያ እና ግንቦት 7 በየሱዳን አገሩ ሲፋልጓቸው ከዚያ በሗላ፤ነብሳቸውን ለማዳን ‘ሲጨንቃቸው’ ሸሽተው ወደ ወያኔ እጃቸውን ሰጥተው ከቆዩ በሗላ፤ ሰሞኑን “ቤን/ኢትዮጵያ ፈረስት” በሚባል የወያኔ አለቅላቂ  ቱልቱላ ድረገጽ “ቀርበው” የግንቦት 7 ወንጀል ሲናገሩ አይተናቸዋል።

 ዘሐበሻ የተባለው “የግንቦት7 እና የኦነግ ሳተላይት” ሚዲያ “ግንቦት 7” ለመከላከል “ምስክር አድርጎ” እንደ አስረጅ የዘገበልንን “በወቅቱ ወንጀሉ ሲፈጸም አሜሪካ ውስጥ ሲኖሩ  የነበሩትን “የሻዕቢያ አለቅላቂዎች” ኤፍሬም ማዴቦና ንአምን ዘለቀን ምስክርነት እንደመከላከያ አድርጎ ከአንድ አመት በፊት ስለ እነዚህ ሰዎች ተጠይቀው “መልስ” የሰጡኝ ብሎ ያገኘውን “ሐረግ” መዝዞ የእነ “ማስረሻ ፤ የነ አባስ” ዕምባ ለማሳነስና “ወያኔዎች” ናቸው ለማለት በቪዲዮው ቃለ መጠይቅ እግርጌ ለጥፎ ነበር “ሰሞኑን”። እንዲህ ይላል፤

“ይህን ቭዲዮ ለተመለከታችሁ ሰዎች አንድ መረጃ ለመስጠት ነው ከላይ ያለችውን መግቢያ የጫርኩት።” ብሎ የዘሐበሻ ዘጋቢ ለግንቦት 7 ጥብቅናውን ግልጽ ለማድረግ የጀመረው ጽሑፉ ይቀጥላልና፦ “..“ይህን ቭዲዮ ለተመለከታችሁ ሰዎች አንድ መረጃ ለመስጠት ነው ከላይ ያለችውን መግቢያ የጫርኩትማስረሻ ባንደጋ ከሁለት ዓመት በፊት በሱዳን በኩል የጠፋ ሰው ነበር:: ሱዳን እንደገባም አንዱን የዘ-ሐበሻ ሪፖርተር አግኝቶ ቃለ ምልልስ መስጠት እንደሚፈልግና የተለያዩ መረጃዎች እንዳሉት ገለጸጉዳዩን ለማጣራት የዘ-ሐበሻ ሪፖርተር በወቅቱ ወደ ግንባሩ አመራሮች አቶ ኤፍሬም ማዴቦ እና አቶ ነአምን ዘለቀ ጋር ደውሎ ነበር:: የተፈጠረው ነገር ምንድን ነው? ሱዳን ገቡ የተባሉት ሰዎች ስለግንባሩ የሚናገገሩት ነገርንስ ምን ትሉታላችሁ? ሲል ጥያቄ አቀረበ:: በቴሌኮንፈረንስ ከነአምን ዘለቀና ከኤፍሬም ማዴቦ ጋር የተወያየው የዘ-ሐበሻ ዘጋቢ የተሰጠው ምላሽ የሚከተለው ነው::
 ሱዳን ገቡ የተባሉት እነዚሁ ታጋዮች (እነ ማስረሻን) ካምፕ ውስጥ ሴት እያመጡ ሲያስቸግሩ ንቅናቄያችን ብዙ ቅጣት የተጣለባቸውና አውቀን እንዲጠፉ ወደ ሱዳን እቃ ግዙ ብለን የላክናቸው ናቸው:: በየትኛውም ዓለም እንዲሁም እስካሁን በኢትዮጵያ ውስጥ የትጥቅ ትግል ያነሱ ኃይሎች ለጥንቃቄ ሲሉ አንድ ወታደር በካምፕ ውስጥ ሴት እንዲያስገባ አይፈቅዱም:: የኛም ንቅናቄ እንዲሁ:: ከዚህ በፊት ጫካ የነበሩ ኃይሎች ሴት ጋር ግንኙነት ያለውን ወታደር እስከ ሕይወት  ማጥፋት  ድረስ የሚደርስ የዲሲፕሊን እርምጃ ይወስዱበት ነበር:: የኛ ንቅናቄ ግን በሕይወታቸው ላይ እርምጃ ሳይሆን የወሰደባቸው ንቅናቄያችንን ጥለው እንዲወጡ ወደሱዳን እቃ እንዲገዙ በመላክ መንገዱን አመቻችተንላቸዋል ነው ያሉን::

ይህች ሐረግ እስኪ አጥኗት። ካምፕ ውስጥ ሴት እያመጡ ሲያስቸግሩ ንቅናቄያችን ብዙ ቅጣት የተጣለባቸውና አውቀን እንዲጠፉ ወደ ሱዳን እቃ ግዙ ብለን የላክናቸው ናቸው።:”ይላል።    ይህንን ስታነቡ አልተገረማችሁም? መልስ ከማጣት የመነጨ መሆኑን ህፀጻን አንኳ መገመት ይችላል። አስቂኝ አልሆነባችሁም? ካምፕ ውስጥ ሴት በማስገባት የተባረረውማስረሻ በአሁኑ ወቅት ቭላ (ቪላ ለማለት ነው መሰለኝ) ቤት ተሰጥቶት በአዲስ አበባ የተንደላቀቀ ኑሮ እየኖረ ዛሬ ለወያኔ ሚድያዎች የሚናገረው የሚከተለውን ነውቭዲዮውን ይመልከቱት::ይላል፤ ዘጋቢው። እንዲህ ብሎ ስማቸውን እየበከለ ያለው ማን ነው? ግንቦት 7 ሳይሆን ስለ ግንቦት 7 ተከራካሪ ሆኖ እየሞገተ ያለው ዘጋቢው “ዘሐበሻ” ነው። ርዕሱ “ከዘሐበሻ ዘጋቢ” ይላል።
አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ ዘጋቢው እንዲህ ይላል፤ “ሱዳን እንደገባም አንዱን የዘ-ሐበሻ ሪፖርተር አግኝቶ ቃለ ምልልስ መስጠት እንደሚፈልግና የተለያዩ መረጃዎች እንዳሉት ገለጸ::” ይላል። ዘጋቢው ግን በተጠየቀው መሰረት ፤ቃለ ምልልስ አላደረገለትም; አምቢ አለው። 

በወቅቱ እነ ማስረሻ ለሚዲያዎች የጻፉት እሮሮ ላቀርብላችሁ እችላለሁ። ኢሳት አምቢ ብሏል።ዘሐበሻ አምቢ ብሏል። ጋዜጠኞች ጠልቀው የድርጅት ስራ ሲሰሩ፤ የተበደሉ ሰዎች አምጥተው ቃላቸውን እንዳይደመጥ እየከለከሉ፤ ጠላት ሲጠቀምባቸው ግን “ቪላ ተሰጥቷቸው ነው” እያሉ ጋዜጠኞች እንዲህ ሲጨማለቁ ማየት፤ ምን ጋዜጠኛነት ሙያ አየተሰራ እንደሆነ ግራ አጋቢ ነው።) አዲስ ደምጽም እንዲሁ ፤በያን በያን፤ በያን….እያለ ሙገሳው አስደንቁሮናል።

ለማጠቃለል፤ የድርጅት መሪዎች በሕግ ባትጠየቁም በታሪክ ፊት ቆማችሗልና፤ ገበናችሁ በተበደሉ ክፍሎች፤ወይንም ጠበቆቻቸው መነገሩ ሊያስከፋችሁ አይገባም። ምክንያቱም ዕደለኞች ናችሁ “እሰር ቤት አልገባችሁም”። እስከዚህ ድረስ ሊከፋችሁ አይገባም። ችግሩ እናንተ ሳትሆኑ፤ “እባካችሁ ስለተበደሉት አታውሩ፤አታንሱ!” የሚሉን እንግሊዞች “ሚዲዮከር/mediocre” የሚሏቸው “ሄዶ የማይጎዳ ቢመጣም የማይረባ” ፤ የሚሉት ዓይነት፤ አማርኛው “መናኛ” የሚላቸው “የተቃዋሚ ሚዲያዎችና ጀሌዎቻቸው” ናቸው መሃል ላይ ሆነው አፋችን እንድንዘጋ እየተከላከሉላችሁ ያሉት።

ሕዝቡ እንደፈረደበት፤ እናንተው ወደ ሥልጣን መጥታችሁ በፈቃዳችሁ “ፍርዳሁችን ስጡን”-ብላችሁ-“እገሌ ገድያለሁ፤ ደብደቤአለሁ፤ አሰቃይቼአለሁ፤ አስሬአለሁ….. አፈናቅያለሁ፤   እንዲሞት ለፍረድ ወስኜበታለሁ” ብላችሁ “የራስን በራስ” የምትሉት “ገነታዊ መስተዳድራችሁ” እና ዳኝነታችሁ እስኪነግረን ድረስ እንዳመጣብን አፋችንን ዘግተን እንጠብቃለን። አሜን ይሁና! 

ታጋዩ ገብረመድህን አርአያ እንኳ ሳይቀር ‘ላደረግኩት ጥፋት ይቅርታ’ ብሎ በኢትዮጵያ ምድር አይሮጵላን ጣቢያ ቦሌ ላይ ሲወርድ መሬቷን ሰግዶ ተሳልሟል። አገር ማለት ፤ሰው ማለት፤መጸጸት ማለት አይገባችሁም? ፓለቲካ ምን ማለት ነው? አጎንብሶ ተሸፋፍኖ መራመድ?  ውሸት፤ወንጀልና ፖለቲካ? እስከ መቸ?  

አንድ ነገር ትዝ አለኝ። አንድ ወዳጄ “ዳሉል ትግራይ እሳተ ጎመራ” በምድረበዳው ላይ ስንጓዝ፤ አንዲት ዥንጉርጉር “ሚዳቋ” (የሜዳ ፍየል) በዛው በተንጣለለው ፀሃያማ በረሃ ላይ ስንጓዝ፤ በጣም በቅርብ አጠገባችን ቆማ “ዓይን ዓይናችን አፍጣ እያየች”፤ ረዢሙን ቆንጅዬ አንገቷን አሰግጋ “ምን ታመጡ!” ብላ ስታፈጥብን  አይተናት ወዳጄ በድፍረቷ ተገርሞ፤ “ቆይ አባሽ ሌላ ቀን!!!” ያላትን የተስፋ ቀቢጽ አነጋጋሩን አስታወሰኝ።  እኛ ደክሞናል፤ እንኳን እሷን ተኩሰን ገድለን ቀቅለን ለመብላት እጃችን ሁሉ ዝሏል፤ውሃ ጥም ይዞናል፤ከንፈራችን ደርቋል። ፖለቲከኞቻችንም፤ በየመድረኩ ቆመው ዓይናችሁን ጨፍኑ ሳይሉን እያየን አፍጠው ሲዋሹን “አቅም የለንም” ምን እናድርግ፡ “ቆይ አባታችሁ” አንላቸው ነገር፤ ምን ይደረግ! ዜግነት መጥፎ ነው፤ ወንድሞቻችን ናቸውና!   

ዶ/ር አረጋዊን እንተውና ዶ/ር በያን ምንድነው የሚለው? “ኢትዮጵያ ትኑር አትኑር ጉዳዬ አይደለም” “ለኔ አንገብጋቢ ጥያቄ አይደለም” ብሎናል ካሁን በፊት በዛው ራዲዮ ላይ። “ዩኒቲ ኢን ዳኢቨርሲቲ” ነው ኢትዮጵያ ማለት፤ ሲል አቶ ተክሌን “አንድ ነገድ/ጎሳ” ይግዛችሁ ያሉት ባስመሰል “ኢትዮጵያ፤ኢትዮጵያ የምትሉት ነገር ምን ማለት ነው? ለኔ ኢትዮጵያ “ዩኒቲ ኢን ዳይቨርሲቲ” ነው ሲል፤ ደርጅቱ በዩኒቲ ኢንዳይቨርሲቲ” እንደሚያምን አስመሰሎ አድማጭ ሊያሳስት ሞክሯል።

“Unity in diversity” የሚለው የበያን አሶባ ድርጅታዎ እምነቱ እንደዚያ ከሆነ! ወይንም የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግምባር ፕሮግራሙን ስታነብቡት ምን ይላል? “የዛሬቷ ኢምፓየር ኢትዮጵያ በምኒሊክ ወረራ አማካይኝነት በ19 ክ/ዘመን ነው የተመሰረተቺው” ይላል። ኢትዮጵያ ማለት ለበያን ትርጉሙ ያ ነው። ያ ብቻ አይደለም፡ ኢትዮጵያ ማለት ለኔ ‘ዩኒቲ ኢን ዳይቨርሲቲ’ ነው ብሏል። ፕሮግራሙ ግን “ተጻራሪው ነው የሚነግረን። “ዩኒቲ ኢን ዳይቨርሲቲ” የሚለው ሁለት ቢላዋ አለው። አንዱ የድርጅቱ መርሃ ግብር ከዚህ አባባል ጋር ይጻረራል፤ ዋነኛው የዚህ አባባል መልእክት ግን ምን ማለት አንደሆነ ልንገራችሁ፤

ዲቨርሲቲ ማለት በቃሉ “ውሸት ማለት ነው”። ምን ማለት ነው? ይህ ቃል ወያኔዎች፤እና ኦነጎች እንዲሁም “መናኛው ተቃዋሚ እና ምሁሩ ክፍል” ሁሌም የሚያዥጎደጉደው ቃል ነው። ይህ ቃል እየገፋው ያለው እና እየተጠቀመበት ያለው ማን ነው? ይህ የፖለቲካ ዕብደት ነው። እስኪ እንገሊዝኛው ላዥጎድጉደው በቀላሉ ቢገልጽልኝ። 

Diversity! This is mental derangement in the planet Ethiopia! What is the concept of diversity? It is a fascinating term. Few of us now started to understand how amonos/ብርቅዬ/ this term is becoming. It is nefarious. It is a word to stigmatize the Amahara. These liars are telling you “this country needs more diversity”; do you know what it means? All of you will immediately understand when these secessionists use that term,- it means “there are too many Amhara ruling this country or there are many Amhara in planet Ethiopia, therefore, let us dilute them by replacing them by other ethnic on their place. That is what it means? Do you understand me? So diversity means “chasing the remained Amhara mass or Christians who were ruling the country for million-um replacing by others. This is anti Amhara genocide scum, especially when these narrow nationalists are using it intentionally, to say ‘Amhara is the only ruler” in Ethiopia! Therefore, need diversity. I hope this is clear for you. That is the expression of using this term by the secessionists.

ከመቸ ወዲህ ነው ተገንጣዮች የኢትዮጵያ “ሕብረትና አንድነትን የወደዱትና ያደነቁት”? “ኮሎኒያሊሰት/ኢምፓየር” የምትባለዋን አገር? ተገንጣዮች ደብልቅነትን አይወዱም፤ የህ ግልጽ ነው። እየተዋወቅን? “ኦነጎችና ወያኔዎች” እንዲሁም ተገንጣዮች ይህ ቃል አጥብው የሚጠቀሙበት ግን ከላይ እንደገለጽኩት “አንድነትን” ስለፈለጉ ሳይሆን ‘ሥልጣኑ፤ንብረቱ፤አገሪቱ አማራና ክርስትያን በተባለ ነገድና ሃይማኖት ስለተያዘ/ስለተመራ/ስለበዛ፤ቦታውን ሌሎቹ ይተኩት ማለት ነው። ‘ዩኒቲ ኢን ዲቭረሲቲ’ ማለት ትርጉማቸው “ጀነሳይድ” ማለት ነው (በተገንጣዮች አጠቃቀም)።አማራን ዳይሉት/ማመናመን ማለት ነው። ይህ ነው።

ካልሆነማ አማራውን ለምን በ genocide መልክ ሊያጠፉት ሞከሩ? ማን ይሙት እነ በያን አሶባ ናቸው ፤እነ ኦነግ ናቸው “ዩኒቲ ኢን ዳይቨርሲቲ” የሚወዱት? ያ ከሆነ፤  
 ለምን
 
“አዲስ አበባ ወደ ኦሮሞ እየገፋች መጣችብንኦሮሞ ቋንቋውን ባሕሉን በአዲስ መጤዎች ሊደባለቅ ነውባህላችን ሊበረዝ ነው፤” 

ማለት ፈለጉ? አንዲያ በሚል አይደለም “ማስተር ፕላኑን” እነ በቀለ ገርባ እነ በያን የተቃወሙት? እንዴት ነው ነገሩ! እንነጋገር እንጂ? “ዩኒቲ ኢን ዳይቨርቲ”? ኦነግ ነው ደግሞ ይህንን ቃል የወደደው? ከመቸው?!!!!!  

በሌላ መልኩ ግን “ዩኒቲ ኢን ዳይቨርሲቲ” የሚለው ትርጉሙ የበያን ድርጅት በፕሮግራሙ ሲጻረረው ደግሞ  እንዲህ ይነበባል፤-

የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግምባር የድርጅት ፕሮግራም
ይላል ርዕሱ፡ ቀን አመተምህረት የለውም። 

* “በቆራጥ የኦሮሞ ልጆች መስዋእትነት ራሱን የቻለ አስተዳዳር ክልል አግኝቷል፤ (ይህንን ምን ይጠቁማል? “ዩኒቲ ኢን ዳይቨርሲቲ” ሳይሆን፤ አስተዳደሩ “የራሱ”፤ “የኦሮሞ ብቻ”እንደሚሆን እየነገረን ያለው።ማንም ሊያስተዳድረው አይችልም።)
 * “እንዲጠፋ የተፈረደበትን ቋንቋው ኦሮምኛ የስራና የትምህርት በመሆን ባጭር ጊዜ ውስጥ  ከፍተኛ ዕድገት ደርሷል። 

(ዳይቨርሲፋይድ የሆነ አገር በቀል ቋንቋ አይደለም የነ በያን ድርጅት ‘በትምህርት ቤቶችና በስራ ቦታዎች ሊገለገልበት የሚፈቅደው ቋንቋ፤ “ኦሮሚፋ” የሚለው ቋንቋ ብቻ ነው። ኦሮሞ ውስጥ ሕብረተሰቡ እንዲገለገልበት በሕግ ሚደነግገውና  የሚያገለገልበት መገበያያ መረዳጃ ብቸኛ ቋንቋ ኦረምኛ ብቻ ነው። ዳይቨርሲቲ የሚለው ዓረፍተ ነገር ቋንቋ ላይ ሲመጣ አፍሪካዊ /ኢትዮጵያዊ ያልሆነ “ባዕድ” የሆነው “ላቲን” ብቻ ነው የተፈቀደው!-- አማርኛ “ዳይቨርሲቲ” በሚባለው የውሸት መጠቀሚያ “ላቲን” እንዲተካውና፤ አማርኛ እንዲጠፋ አድርጓል። ዩኒቲ ኢን ዳይቨርሲቲ ተግንጣዮችና የጎሳ ብሔረተኞች ስራ ላይ ሲያውሉት፤ ስትመለከቱ፤ ቋንቋ እንኳ በላቲን ተክቶታል /”ዳይሉት”/ እንዲሟሟ/ አድርጎታል የምላችሁ ከላይ አስተውሉ። አማራ ብቻ ሳይሆን አማርኛ ቋንቋም ጭምር “ጀነሳይድ” ተፈጽሞበታል።
·      
 “ኢትዮጵያ ከኢምፓየር ባሕሪዋ ተላቅቃ፤የሕዝቦች እስርቤት መሆኗን ተላቅቃ፤… (ይላል። ኢምፓየሩ ማን ነው? ኢትዮጵያና አማራ! አሳሪው ማን ነው? አማራ! እንዴት ነው የታሰሩት? “ኦሮሞ ለኦሮሞዎች ብቻ እንድትሆን ስላለደረገ”። ሕዝቦች ይላቀቁ የሚለውስ እንዴት ይለቀቁ? አማራን በ“ዩኒቲ በዲቨርሲቲ” ዘዴ በሌሎች ነገዶች በቦታው በመተካት ይሆናል። ሶማሌ፤ሻዕቢያ፤ኦጋዴኖች አብረው ባንዴራቸው ሲያውለበልቡ በየድረገጹ አይታች ል (ግምባር ፈጥረው!) የጋራ ጠላት ያደረጉት “አትዮጵያና፤አማራ፤ሰንደቃላማችንን ነበር” - ‘ዩኒቲ ኢን ዲቨርሲቲ’ መተካካት ማለት ትርጉሙ ይኼ ነው)። ከስራ በማፈናቀል ንብረቱ በመቀማት፤ሚሰቱን በመቀማት፤በመግደል፤በማባረር…..ሃይማኖትም ከሆነ እስልምና፤ፔንጤ፤…..ጫት፤ ዳንስ፤ብልግና፤ሌብነት፤ንቅዘት…….ሞራለ-ቢስ ማሕበረሰብን “ማባዛት….” በምትኩ እነዚህ ሁሉ እንዲተኩት በማድረግ”።
·        እደጃፍ ቤተክርስትያኑ ላይ መስጊድ ማስሰራት ወዘተ…ወዘተ… ። ዩኒቲ ኢን ዲቨርሲቲ ስራ ላይ ሲውል ይህ ነው! ዲቨርሲቲ-ዎቹ ሲተኩት /አሳሪዋ/ኢምፓየሯ/ እንድትጠፋ፤ “ጀነሳይድ” ተፈጸመባት ማለት ነው።
 ከዚያ “ታሳሪው” ከእስር ቤትዋ ፤ከኢምፓየሯ “ተላቀቀ” ማለት ነው።በምን ዘዴ? ‘በዩኒቲ ኢን ዳይቨርሲቲ’ ስልት! 

·       “ከዚህ እስር ቤት ለመለቀቅ የጋራ አገር ሆና መዋቀር ይኖርባታል፤

(እንዴት ትዋቀር? የሚለው ጥያቄ ደግሞ ሲመልሱ መልሱ “በዩኒቲ ዲቨርሲቲ”!!!!!) 

የጋራ አገር ሆና እንድትዋቀር/ ዩኒቲ ኢን ዳይቨርሲቲ” የሚለው በያን እና ፕሮግራሙ ባጭሩ እያሉን ያሉት (የሚከተለውም ፕሮገራማቸው ነው)

፡-“ኢትዮጵያ የሁሉም ብሔር፤ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች አገር ናት። የኦሮሞ ሕዝብ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መርሕ ያድሳል፡..የራስን በራስ የመወስን መብት ስንል “ልናሰምርብት የምንፈልገው “አንጋፋው ድርጅታችን ኦነግ” የተጎናጸፋቸው እጅግ አኩሪ ድሎችን ተነተርሰን መሆን እንዳለበት ልናሰምርበት ይገባል።ይላል።

 (ምንድነው አኩሪ ድል የተጎናጸፈው? ‘ዩኒቲ ኢን ዲቨርሲቲ’ የሚለው የማታለያ መፈክር “ሳይሆን” *ኦሮሚያ ለኦሮሞዎች ብቻ* ፤ አሮሞ በራሱ ልጆች እንጂ አማራ፤ትግሬ፤ሶማሊ፤ጋምቤላ በመሳሰሉ ኢትዮጵያዊያን ሃኪሞች አስተዳዳሪዎች፤መምህራኖች ፈራጆች.. መሃንዲሶች፤ ዜጎች መታደዳር የለባትም ነው፡” እያሉን ያሉት።

አኩሪው የራስ በራስ አስተዳዳር የሚሉት” እንግዲህ እነ በያን አሶባና ኦነጎች… “ዩኒቲ ኢን ዲቨርሲቲ” እያሉ በሚዲያ ለማስመሰል የሚዋሹትና በፕሮግራማቸው ያጸደቁትን እና የሚታገሉለት ግን ተጻራሪ መሆኑን ተመልከቱልኝ። እኛ ኦሮሞዎች “አስተናጋጆች ስንሆን፤ በመሬታችን ደግሞ እንግዶቹ ኢትዮጵያዊያን የሚባሉ ዜጎች ናቸው” ብሎናል ለምሳሌ ጸጋዬ አራርሳ የተባለ አስገራሚ አውስትራሊያ አገር የሚኖር ዓይን ያወጣ “ድንቁርቁር” ያለ “የሕግ ተማሪ!” እንዲህ ይላል፦

 the State operated in Addis Abeba as an occupying force of settler colonialists bent on pushing out and displacing the indigenous Oromo peoples. Because the settlers generally spoke Amharic and confessed the Ethiopian Orthodox faith and because of the disproportionate concentration of modern urban facilities in Addis Abeba, it became increasingly different culturally from its surroundings………. ‘For most of the 20th century, the Oromo, although historically the host, was forced to live like the alien and the guest in what was their own homeland” Tsegaye R Ararssa 

ይህ ሰውዬ “ኦሮሞዚያን” ብየ ከምጠራቸው “የኦሮሞ ናዚዎች” አንዱ ነው።  የኦሮሞ ጸሐፊ ናዚዎች  “ዩኒቲ  ኢን ዳይቨርሲቲ” ስራ ላይ ሲያውሉት ከላይ ያያችሁት ነው። በግልጽ ነው እየነገሩን ያሉት። ሆስት/ host/ እና ኤሊየን/ alien/ ማን እንደሆነ በግልጽ እየነገሩን ነው። ስለዚህ ይህ ሁሉ እያወቅን፤ የራዲዮኑ ባለቤቶችና ጋዜጠኞች፤ የተለያዩ “ኦሮሞዚያን” ወደ ሚዲያ ሲጋበዙ፤ የሚናገሩት እና ፕሮግራማቸው የሚናገረውን እያነጻጸሩ ጋዜጠኞች ወጥረው እንዲያብራሩልን መጠየቅ ይገባቸዋል።

 በዚህ አንድ ጥሩ ጋዜጠኛ አለ የማመሰግነው። ካሳሁን ይባላል SBS (?) አውስትራሊያ ራዲዮ አማርኛ ጋዜጠኛ ነው፤ ጎበዝ ነው። አጥብቆ ይጠይቃቸዋል። የተቀሩ “ጫት” የሚሸጡ ይመስላሉ። ገዢው የመረጠውን ቅጠል መርጦ ሲያነሳ ‘ዝም’ ብለው አሳልፈው ይሸጡለታል።የሚጠይቁት ልስልስ ያለ፤ ነግር ግን “ኢትዮጵያ” ብለው በሚነሱ እንግዶች ግን “ዓይናቸው እስኪፈጥ ድረስ” ይወጥሯቸዋል።

አበበ ገላው እነ በያንን ሲያመሰግን አድምጣችሁታል አይደል? ዶ/ር በያንን አስሬ ስሙን እያነሳ ሲያሞግሰው? የበያን ፖለቲካ አበበ ገብቶታል አልልም (ስሜት ስለሚያጠቃው)፤ ምክንያቱም ካሁን በፊት ‘ብዙ ጊዜ’ እነዚህ የኦሮሞ የግንጠላ ፖለቲከኞች ወደ እዛው ራዲዮ ሲመጡ “አንድነትን፤ በሕብረት መስራትን” “ለኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች” ትምሕርት ሰጪዎች ናቸው፤ ኢትዮጵያዊያን ተቃዋሚዎች ከኦሮሞ ፖለቲከኞች “ባንድነት ስለመስራት መማር አለባቸው”፤ ሲል ከሁለት ዓመት በፊት በዘባረቀው አንደበቱ በሳልስቱ “ኦነጎች” በሦስት እና አራት ተበታትነው ቁጭ ሲሉለት፤ “ኢትዮጵያዊያንን ይቅርታ አልጠየቀምና ስለ በያን ማሽቃበጡ የለመድነው ነውና የአበበን ‘ማሲንቆ ምት’ ትተተን ወደ በያን እናምራ።

አቶ ተክሌ የሻው “ኦሮሚያ” ወይንም ኦሮሞ ዩኒቨርሲቲ እየተባሉ በሚጠሩ ተቋማት ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ዜጎችም አብረው እየተገደሉ ነው። “ኦሮሞዎች ብቻ አይደሉም፤ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ልጆችም አሉ፤ ስለዚህ ሁላችንም ሊያስተባብረን ወደ ሚችለው እንቅስቃሴው “ኢትዮጵያዊ መልክ” መያዝ አለበት። ኦሮሞዎች ናቸው ከማለት “ኢትዮጵያዊያን” ናቸው ወደ እሚለው መምጣት አለብን። እርሻ ቦታቸው፤መኖርያ ቤታቸው፤አትክልት ቦታቸው ሲወሰድባቸው “የኦሮሞ ብቻ ነው” የሚያሰኝ አይደለም። ኢትዮጵያዊ መልክ/አገራዊ መልክ እንስጠው፤ሌሎች ገበሬዎችና ኗሪዎችም ተነጠቀ እየተባለ ባለበት ቦታ አብረው ተሰባጥረው እየተበደሉ ያሉ ሌሎች ኢትዮጵያዊያንም እዛው አሉ።። ከጎጆአችን ውስጥ እንውጣ ነው የምለው።” ብለዋል አቶ ተክሌ     

ዶ/ር በያን አሶባ ግን ምንድ ነው መልስ ሲሰጥ ያደመጥነው? ኦሮሞዎች ከማንም “በላይ ተጨቁነናል አንልም”፤ ይልና እንደገና “ከማንም በላይ መጨቆናችን እስር ቤቶች በሙሉ በኦሮሞ ተሞለቷል፤ እስር ቤቶች በሙሉ ኦሮምኛ ቋንቋ ነው የሚናገሩት፤ ስለሆነም ከማንም በላይ ስለተጨቆንን ተጨቁነናል አንልም” ይላል።”  አስገራሚ!

ኦነጎች አስረጅ የሚጠሩት ስዬንና ተስፋ ገብረአብን ነው። ሃቁ ግን “የኢሳያስ አገልጋዩን ተስፋ ገብረ አብን  ትተን” የስየ ምስክርነት ብንመለከት፤ ስየ አብርሃ ፤ 14 አመት ኢትዮጵያ ውስጥ ኖሮ ወያኔዎች “በእስረኛ ላይ ድብደባ /ሰቆቃ የሚፈጽሙ መሆናቸውን አላውቅም ነበር” ሲል የነገረን “ወያኔን ከእግር እስከ ራስ አውቃለሁ ሲለን የነበረው ‘ፖለቲከኛው’ ብርሃኑ ነጋ” ከስዬ ጋር ታስሮ በነበረበት ወቅት፤ “ብርሃኑ ነጋ ስዬን” “ትናንት ሌሊት ሲጮህ የነበረው አሳዛኝና አስደንጋጭ ልቅሶ ድብደባ መሰለኝ? ወያኔዎችስ እንደ ደርግ “ሰቆቃ” ያካሂዳሉ እንዴ? ብየ ስዬን ብጠይቀው “እኔም ለመጀመሪያ ጆሮዬ ነው እንዳንተው የማደምጠው፤ እንዲህ ሲደረግ አይቼ ሰምቼም አለውቅም” ሲል መልስ ሰጠኝ”። ሲል “ጎህ ሲቀድ በተባለው ለስዬ አብርሃ መታሰቢያነቱን የጻፈው መጽሐፉ ላይ መግለጹ ታስታውሳላችሁ።

በዚህ መንገድ፤ የስዬ አብርሃ “ወያኔ እስረኛን የሚገርፍ መሆኑን አይቶ ሰምቶ አለማወቁ” የውሸት ምስክርነት ባነበብንበት አንደበቱ፤ ዛሬ ደግሞ “ዶ/ር በያን አሶባ’ ስዬ አብርሃ ስለ “ኦሮሞ ቋንቋ” በብዛት እስርቤቶች ውስጥ የሚነገር ቋንቋ ነው፤ ኦሮሞዎች በብዛት ታሳሪዎች ናቸው፤ ብሎ ተናገረ ብሎ የስየን ቃል በመድገም፤ “ከማንም በላይ መጨቆናችን እስር ቤቶች በሙሉ በኦሮሞ ተሞለቷል፤ እስር ቤቶች በሙሉ ኦሮምኛ ቋንቋ ነው የሚናገሩት”፤ ሲል “ወያኔ ሰቆቃ ፈጽሞ አይቼ ሰምቼ አላውቅም” ሲል የነገረንን ስዬን “የምር ምስክር” ብለው ያችን ደጋግመው ኦነጎች ሲቀባጥሩ መስማት ሁሌም ይገርመኛል። 

ስለ ኦሮሞ ተናግሯል፤ ስለ ትግሬ ተናግሯል፤ ስዬ “መናገር ያልደፈረው “ስለ አማራው ሰቆቃ ብቻ ነው”። ወያኔና ኦነግ ወደ ስልጣን ሲመጡ እስር ቤቶች የተሞላው፤ግድያው የተጧጧፈው በማን ላይ እንደነበር፤ “በያን አሶባ እና  ስዬ አብርሃ” ድርጅቶቻቸው ማንን ለማደን (ሃንት) ለማድረግ ወደ ሥልጣን እንደገቡ በሚገባ ያውቁታል።እንደ ልማዳቸው ሊክዱ ካልሆነ በቀር ማን ሰለባቸው እንደነበር ያውቁታል። የበያን አሶባ ድርጅት ሥልጣን ላይ ወጥቶ በሺዎቹ አማራዎች እያደነ ብልታቸውን እየሰለበ፤የአማራ ሕፃናት በቢለዋ ሲያርድ፤አማራዎች ከነነብሳቸው “አማራ ገደል” ብለው ኦሮሞዎች በሚጠሩት ገደል ላይ ሲጣሉ፤ ነብሰጡሮች በቢላዋ ሆዳቸው ሲቀደዱና ሲወጉ፤ ኦነግና ኦሆዴድ ከወያኔ ጋር ሆነው በጋራ በሺዎቹ አማራዎች ሲያባርሩ ፤በያን አሶባ “አሌ የማይለው ነው”። አሌ ቢልም ከኦነግ አባልና አመራር፤ቃል አቀባይ የነበረ “የሚጠበቅ ነው”። ዶ/ር በያን የስዬን ምስክርነት እንደ “ቅዱስ ቁርኣን” ቢደጋግመው፤ ከኦነጎች ምን ይጠበቃል!

ወደ ስዬ እና ተስፋየ ግበረአብ ተልካሻ ምስክርነት ስንሄድ “ኦሮሞዎች አዲስ አበባ እስር ቤት ከሞሉ” ኦሮሞዎቹ “በብዛት አንደኛ ነን!!!” ይላሉ፤ እንዲያ ከሆነ፤እንደ ብዛታቸው እስር ቤቶቹ በሬይሾ/ባማካይ መቶኛ /ክፍልፋይ/ ቢሰላ ኦሮሞዎች ሊሆኑ ይችሉ ይሆናል። ኦሮሞ የሚናገሩ ኦሮሞዎች ወደ እስር ቤት በብዛት መምጣት ከብዛታቸው አንጻር፤ የታጎሩት ‘ሌቦች፤ነብሰገዳዮች፤ፖለቲከኞች፤ጠላፊዎች፤ወዘተ..ወዘተ….” ብዛት ያላቸው “አዲስ አበባ” ኦሮሞ አካባቢ ስለሆነ የሚጠበቅ ነው (በእዛው ላይ ኦነግ እና የመሳሰሉ ድርጅቶች ኦሮሞዎች ይሳታፋሉ እና ቢታሰሩ የሚገርመው ምንድ ነው? ይልቁንስ አማራውስ/ ኦነግ ሊነግረን ይችላል? በያን ጠመንጃ ተሸክሞ ጫካ ወጥቶ፤ የኦነግ ተዋጊ ሆኖ “የአማራ ፤የምንሊክ” አገር “ኢምፓየሯን” ሲወጋ ነበርና ፤ ኦነግ በአማራ ላይያደረሰውን ጉዳት ሊነግረን ይችላል?)። 

አነስተኛ ሕዝብ ያለበት ማሕበረስብ ከሕዝቡ አነስተኛነትና እስረኛ ብዛት የታጎረው እስረኛ (ሌላ ክ/ሀገር/) ቢጠና፤ በየቦታው ያለው እስረኛ ቢሰላ ከኦሮሞ ሊበልጥም ይችል ይሆናል። ተስፋዬ ገብረ አብና ስዬ ቃዡ ብለን እንደ እውነተኛ መረጃ ልንወስደው እንችል ይሆናል። ችግር የለውም። እነ በያን አሶባ፤ ግን ያንን እየደጋጋሙ ከኛ በላይ የተጠቃ የለም ይላሉ። አቶ ተክሌ ባንድ ቃለ መጠይቃቸው እንዳሉት፤ “እናቱ የሞተችበትና፤ እናቱ  ውሃ ፍለጋ ወደ ወንዝ የሄደችበት እኩል ያለቅሳሉ” ብለው ነበር ትክክል አባባል ነው።

ኦሮሞዎች በዚህ ሥርዓት ተጠቃሚዎች መሆናቸው ካሁን በፊት በግልጽ አስቀምጫለሁ። “በጣም ሰፊ የሆነ አገሩን ምድሩን የሸፈነ፤ ግማሹን የኢትዮጵያ መልክዓ ምድር በጉልበት ከወያኔ ጋር ተመሳጥረው “ኦሮሚያ’ ብለው ያልነበረውን ካርታ እና ባንዴራ ቀይሰው ‘ስም’ ሰይመው ተጠቃሚ ሆነዋል። ብሔራዊ ማዕድኖችና ለም መሬቶች ደኖች አገራዊ መሆን ሲገባአቸው ለራሳቸው አድርገው ተቆጣጥረውታል (በ ኦነግ አርበኛነትና አገር ወዳድንት ኮርተናል፤ ራስ በራስ ተጠቃሚ አድርጎናል በሎናል፤ያንንም እንቀጥልበታለን ብሎናል ሳይሸሽግ የበያን “ድርጅት”፤ በፕሮግራሙ ላይ)። ሌሎቻቻን ከዚያ ውጭ አስወጥተውናል። ዜግነታቸው ለይተዋል፤ ሦስት ዓይነት ባንዴራ አበጅተዋል፤ የታጠቀ መከላከያ የሚሉት እና የፖሊስ፤የጸጥታ “ኦሮሚያ” የሚባል ሠራዊት አላቸው፤ “ኦረሚያ አየርመንገድ” ፤ የሚባል ቀስ በቀስ እያስተዋወቁ ነው። ሃቅ ሃቁን አንነጋገር! 

ከወያኔ ጋር የሚያጣላቸው “ግንጠላ እና “የተቀረውን” ጠርጎ፡ ማስወጣት ነው። በያን ግራም ነፈሰ ቀኝ ነፈሰ፤ “ዲሞክራቲክ ግምባርም ይበለው፤ ምንም ይበለው፤ የራሱ ባንዴራ አለው፤ የራሱ ካርታ አለው። ኢትዮጵያ የሚባል ሰንደቃላማ በድርጅቱ ድረገጽም ሆነ ድርጅታዊ መግለጫ ፈጽሞ የለም።አራት ነጥብ!!!! አበበ በለው ይህንን እንዲያውቀው ይሁን! የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ውስጥ እየተነጋገርን ነው እያሉ እነ ሸንጎ ፤ቅብጠርጥሮሽ “ሕብረት” የሚሉት የግንጠላ መሳሪያ ወደ ቆሻሻ በርሜል መጣል ይኖርበታል!

ቢያንስ ከበያን አሶባ ድርጅት ይልቅ “ኦሆዴድ” የሚባለው የወያኔ ሰንደቃላማ ያለበት ኢትዮጵያ ሰንደቃለማ አብሮ ያውለበልባል (ያም ቢሀንን አገር ውስጥ በመኖሩ ነው) ዓይን አፍሮ ሊሆን ይችላል)። እነ ዶ/ር በያን እና እነ ሌንጮ ባቲ፤ሌንጮ ለታ፤ ነገዎ…….ኢትዮጵያ የሚባል ሰንደቃላማ ድረገጻቸው እና ድርጅታዊ ስብሰባ እና መግለጫቸው ላይ ፈጽሞ አይታይም። የሚታየው “ዓረብኛ እና ኦሮምኛ እንግሊዝኛ” ማሕተም ያለበት፤ እንደዚሁም የራሳቸው ባንዴራ ነው የሚለጠፈው፤የሚውለበለበው። “ኦሮሞ ዶሞክራቲክ ግምባር” ተብሏል እና “ኢትዮጵያዊያን ነን ብለው ስሕተታቸው አርመዋል” የሚለው “ቅዠት”፤  ዓረቦች እንደሚሉት “ያ አኽዋን! ማተልዓብ” (“ወዳጄ! ቀልደህን ተው”) እንደሚሉት_ ትግሬ “ሽጣራኻ ደውር” (ተነኮልህን ወዲያ በለው) አንደሚለው ማለት ነው። ይህንን ወደ ሗላ እመጣበታለሁ።

ስለዚህ ባልተጠና ‘ስታትስቲክ/ቆጠራ’ - “በሕዝብ ብዛት አንደኛ ነኝ፤ በእስርኛ ብዛት አንደኛ ነኝ” ፤ የሚለውን የነበያን “ሂፕክሪት/ቀኖና’ እንተውና ይልቁንስ በያን አሰቦ “የክርስትያኖች በዓል ሲከበር እስላሞች በዓል አልተከበረልንም ነበር”“ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ እስላሞች” እንባል ነበር” የሚለውን እሮሮውን እስኪ አውነታውን እንይለት። “የኢትዮጵያ እስላሞች ከመባል ይልቅ…..” ለማለት የፈለገ ይመስለኛል።

እስኪ”የኢትዮጵያ እስላሞች ከመባል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ እስላሞች፤ እንባል ነበር” የሚለውን በመጨረሻው ነጥብ እንወያይ። ግራ የገባቸው የራዲዮ ዜና ተንታኞች “ጸጉር ስንጠቃ” ካልሆነ በስተቀር “እዚህ አገር ውስጥ የምንኖር ዜጎች” እና “የኢትዮጵያ ዜጎች” ምን ልዩነት አለው? እዚህ አገር ማለት “ኢትዮጵያ ማለት ነው”” የምንኖር ማለት ደግሞ “ያለን፤ፍጡራን ማለት ነው” “ምድር ላይ ይምንኖር” ስንል ምን ማለት ነው? “አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር” ስንል “የምድር ፈጣሪነቱን” ይፃረራል ማለት ነው? አይደለም።  ለምሳሌ በእኔው ብሎግ Ethiopian Semay ላይ ወደ ቀኝ በኩል የለጠፍኩትን የኢትዮጵያ እስላም አክራሪዎች /አውዲዮ/ቪዲዮ/ ብታደምጡ እራሳቸው አክራሪ እስላሞቹ ሳይቀሩ “ኢትዮጵያ ውስጥ ያላችሁ እስላሞች” ነው የሚሉት። ማስረጃውን ልስጥ፡
The Rise of Islamic Extremism in Ethiopia

ውሸት መቸ ነው የምታቆሙት? እንዴት ነው ነገሩ ደ/ር በያን? ይህ ቪዲዮ ማስረጃ ብዙ ሳትርቁ “ቪዲዮው ሲጀመር፤ የመጀመሪያ አረፍተ ነገር የምትሰሙት “ኢትዮጵያ ውስጥ ያላችሁ እስላሞች ብሎ ነው አክራሪ መልእክቱን የሚጀምረው። ታዲያ ክርስትያኖቹ ምን በወጣቸው ነው በእነ ዶ/ር በያን ወቀሳ የሚለበጡት? ሃቅ ሃቁን እንነጋገር እንጂ “ዶክተርዬ”?
“በመተከል አውራጃ የሚኖሩ አርሶ አደሮች፤ ነጋዴዎች፤እስላሞች፤ክርስትያኖች፤መምህራኖች፤ ቢባል፤ዜግነታቸውን በምን ሂሳብ ያወርደዋል ተብሎ ይወሰዳል?  ኢትዮጵያዊያን እስላሞች “ኢትዮጵያዊያን አይደሉም”፤ ሕክምና አይፈቀድላቸውመ፤ የወሊድ ሆስፒታል ለብቻ ነው፤ ትምህርት ቤት እስላም አይፈቀድም፤ ስራ ለ እስላም አይፈቀድም፤ ሁለተኛ ዜጋ ነው፤ እስላሙ ከክርስትያኑ አብሮ በአብቶብስ እኩል ቁጭ አይልም፤ ወደ ሗላ መቀም  አለበት፤……ሲባል በያንም ሆነ እስላም ተበድሎ ነበር የሚሉ ከሳሾች ሊነግሩን ይችላሉ? ይህ ሁሉ ተደርጎ ነበር ወይንም በእገሌ መንግሥት ተፈጽሟል፡ የሚል ከሳሽ አለ? የለም!!!!!!! ዝም ስላልን ግን ;፤ሲቀደዱ 24 አመት ሰምተናቸዋል። አሁን በቃ! በቃ! ይኣክል! ይኣክል! ከላስ!ከላስ!ኢናፍ! ኢናፍ! ብለናል።

ተገንጣዮች ሁሌም “ውሸትን” ማቆነጃጀትና “ጸጉር ስንጠቃ” ይቀናቸዋልና፤ ከላይ የለጠፍኩላችሁን የእስላሞቹ የራሳቸው ቪዲዮ በቂ መልስ ይመስለኛል።አድምጡት።
ለመሆኑ፤ እስላሞች ኢትዮጵያን ሲያስተዳድሩ በክርስትያኑ ላይ የደረሰው በደል በያን ብንነግረው ቅር ይለው ይሆን? እስኪ በያንን በሕግ ምሁርነቱ የገዛ እስላም መንግስቱን ምን እንደሰራ ቅር ካላለው ስለ ግራኝ ላስታውሰው። እሱን ወደ ሗላ እምጣበታለሁ አሁን ግን በያን የሚያወራው እስላም በዓል አልተከበርም ነው የሚለን። ኦ ኦ ኦ ኦ !!!!!… ደጊጋ! ደጊጋ!! ይላል ሱዳን፤ wait a minute! Just a minute!  እንደማለት።

ወደ እስላሞች መንግስት ከመመልከታችን በፊት ‘ኦሮሞዎች” በብዛት የደርግን መንግሥት የመሩት (ኦነግ መስራቾችና መሪዎች እንዲሁም አንዳንድ አባሎቹ  በሚኒሰትርነትና በከፍተኛ የፖለቲካ ቀያሾችና ካድሬነት ጨምሮ  የተሳተፉበት ስርዓት ነው) እስኪ የሰጡንን ማርክሳዊ ሌኒናዊ የኦሮሞዎችን መንግሥት አንዲት ጎንደሬ አስለቃሽ  ምን እንዳለች በዚህ ግጥም ላስነብባችሁና ወደ ሌላው እቀጥላለሁ፡
“ቤቱን አምጡ አሉነ ቤቱንም አስረከብነ
እርስቱን አምጡ አሉነ እርስቱን አስረከብነ፤
ገንዘብ አምጡ አሉነ ገንዘቡን አስረከብነ
ማርና ቅቤ አምጡ አሉነ፤
ማርና ቅቤ አሁን የት ተጌንቶ?!
በሃይለስላሴ ተቀልጦ ተበልቶ፤
ወልደን አሳድገን ወልደን ባስተማርነ፤
የሰው አገር ሰዎች እነ ማርኮስ እነ ማኦ ሲመሰገኑበት
እኛ ተሰደብነ፤
እኛ ተገደልነ።”

ትላለች።
ኦሮሞ ያልገባበት ጀግንነት፤ያልሰበኩት ርዕዮት፤ ያልተካፈሉበት ግድያና ክህደትም፤መንግሥትም አልነበረም። ሁሉም ዜጋ ለቀውጡም፤ ለበጎም እጁን አስገብቶበታል።ዛሬ ዛሬ ግን የባሱ አሳፋሪ ኦሮሞ ነን የሚሉ አገሪቱን “እስር-ቤት/ኢመፔሪያል/ኤሊያን/አቢሲኒያ/አማራ፤ደብተራ….” አስወጣው፤ አባርረው፤ እያሉ አንድነቱን በትነውታል። ለምሳሌ ኦነጎች የተካፈሉበት፤ ኦሮሞዎች በብዛት የመሩት የደርግ ስርዓት ክርስትያኑን ብቻ ሳይሆን እስላሙንም በዚህ መንገድ “ኦነጎች/ኦሮሞዎች” ስርዓቱን በመምራት ይህንን መሳይ በደል አድርሰውባቸዋል። የሴትየዋ ግጥም እነሱን ነው ለመውቀስ የዳዳችው።

ዶ/ር በያን ባለፉት ስርዓቶች (አማራ/ክርስትያን ለማለት ነው) እስላሞች በዓል አልተከበረልንም ሲል የትምህርት ቤት ምሳሌ ሲሰጥ ሰምቻለሁ።ወንድሞቼ እኔ እኮ አንድነቱን አልጠላሁትም። ውሸታችሁን አቁሙ! ይብቃችሁ፤ ዳር ዳሩን እያላችሁ እውነታውን አትርገጡ፤ ግድያ፤ ዘር ማጥፋት፤ወንጀል ስራ ውስጥ  ተካፍላችሗል ነው የምለው። ሁሌም የምከራከራችሁ ከዚያ ለመሸሽ ስትሞክሩ “ተበደልን” እንጂ “በድለናል” የሚባል ቃል ሰምቼ አላውቅም!  ቢዚያ እስከቀጠላችሁ ድረስ እኔም አብሬአችሁ ሕዝቡን ስለ እናንተው ወንጀል አስተምራለሁ።

እስላሞች በዓላችን አልተከበረልንም ነበር እሮሮአችሁ አድምጠናል፡ይልቁንስ መንግሥት በተለወጠ ቁጥር አማራውን በኦሮሞዎች የሚገደል ንብረቱ የሚነጠቅ ለምነድ ነው? የሚለው ጥያቄአችን መልስ ስጡበት። ከጣሊያን ፤ከግራኝ ፤ከደርግ ጅመሮ ለውጥ ሲመጣ “ክርስትያኑና አማራው ለምን ይጠቃል?” እንነጋገርበታለን ወደ ሗላ። በዚህ እንተማመን እና እንቀጥል።

የክርስትያን በዓል ሲከበር የእስላም አይከበርም ነበር፤ ሲል አብሮ የነጎደው “ቀልድ ነጋሪው” አቶ ታማኝ በየነም ኦሮሞ እስላሞች ስብሰባ አዳራሽ ሄዶ ይህንን ተናገሯል። በያን ብቻውን አይደለም ለማለት ነው። ታማኝ የመጀመሪያም የመጨረሻም አይደለም፤ አይሆንምም። አቶ በሪሁን ከበደ የተባሉ የታሪክ ጸሐፊና የድሮ የንጉሡ  ዘመን የፓርላማ አባል የነበሩ፤ የጻፉትን እዚህ ለታማኝ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል እና ልጥቀስ።

“17 አመት ከሻዕቢያ ጋር የተዋጋው ደርግ መንግሥት የአማራ መንግሥት እንደሆነ ተቆጥሮ ጥቂቶች አማራዎች በወያኔ ተመልምለው ፤የአማራውን ሕዝብ ወክለው
በ“ሌንጮ ለታ” መሪነት ነሐሴ 30 ቀን 1983 ኣ.ም. ኤርትራ ሄደው ሻዕቢያን ይቅርታ እንዲጠይቁ ልቅሶም እንዲደርሱ አይተናል።ከልቅሶ ደራሾቹም አንዱ አድርባይ አማራ “መሐረሙን” ከኪሱ አውጥቶ  “እንባውን ሲጠርግ” በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አይቻለሁ።

በሻዕቢያ እጅ ላለቁት ወገኖቹ ሳያለቅስ ከኢትዮጵያ እንገነጠላለን ብለው ሸፍተው ሲዋጉ ለሞቱት ወንበዴዎች እንባውን እያፈሰሰ በመሐረሙ ሲጠርግ መታየቱ የተመለከተ የኢትዮጵያ ሕዝብ አስገርሞታል።”

ሲሉ፤ ስለ አንዳንድ “ጥልቅ ብዬ” መስካሪ ወገኖቻችን በ24 አመታችን ብዙ ፤ብዙ ታዝበናል። “ክርስትያኑ፤ አማራውን” ብቻ እንደ በዳይ “እስላሙና ኦሮሞው፤ሶማሌው” አንደ ተበዳይ እየተደረገ፤ የሚሳለው “ቅዠታዊ የማስመሰል ስዕል” እዚህ ማብቃት አለበት። እኛም ታሪኩን ለመናገር ተገድደናል እና በግድ ሳንወድ
እንድንተነፍስ ፍቀዱልን።

ሚዲያ ላይ ተንፍሳችሗልና የኛም እነሆ አድምጡ!
ሙጉት ነው እና ‘ሃቅ ሃቁን’ እንነጋገር፡

ኦሮሞዎችም እስላሞችም “መንግስት በተለወጠ  ቁጥር የአማራውን ሕዝብ የሚገድሉት፤ንበረቱን የሚዘርፉት በምን ምክንያት ነው”?

ኢትዮጵያ አንድ አድርጓታል፤የነፃነት ታጋይ፤የሰላም መልዕክተኛ ነበር ብለው  የእስላም አስተማሪዎችና መሪዎች የሚነግሩን የግራኝ አህመድ ሰርዓት አወዳሽ እስላሞች  (አሁን እስር ውስጥ ካሉት እስላሞች በርካታዎቹ፤ አንዳንዱም እያወደሱ የሸሪዓ ስርዓቱንና ክርስትያን ጨፍጫፊነቱን  በማወደስ የነፃነት ተዋጊ ብለው የጻፉለትን) እስኪ እንመልከት።

ካሁን በፊት “በሃይማኖትና በፖሊቲካ የማሻኮር ባሕሪ” ጌታቸው ረዳ የጻፍኩትን አንብቡ፤http://www.ethiolion.com/Pdf/05192013bepoletikana_behaymanote.pdf

የኢትዮጵያ ሙስሊምአክርሮጐራዴ ይዞ ቢመጣ ከወያኔ ጥይት ይልቅ የሙሲሉን ጐራዴ እመርጣለሁ እኔ።ሲል፤ ተክቢር! ተክቢር! ተክቢር! አላህ ወ አክበር!እያለ ኢትዮጵያ የክርስትያኖችን በዓል ስታከብር የእስላሞችን አታከብርላቸውም ነበር።” ብሎ ‘ታማኝ በየነም’ ምስክርነቱንና ጎራዴ ይዞ የሚመጣውን አክራሪ እስላም ከወያኔ ጥይት እምርጣለሁ እያለ “ትርጉመ ቢስ” ምርጫውን እያስሰማ ከኦሮሞ እስላሞች ጋር ሆኖ  የሰጠንን ምስክርነት ስናስታውስ፤ ዶ/ር በያን ብቻ አይደለም ይህንን እሮሮ የሚያስተጋባው።

“ኣላህ ወአክበር” የሚሉ “ክረስትያኖችንም”  እንዲያ ሲሉ ለእስላሞቹ ወግነው ክርስትያኑን ሲከስሱ አድምጠናል። ሃቁ ግን እስላሙ ብቻ አልተጎዳም፤አልተጨቆነም፤ ይልቁንም “እንጻፍ ካልን እማ”  ያለው ማነው? “ሃማ ቱማ” ነው መሰለኝ። የጻፍኩትን እነሆ ፤ ቀንጨብ አድርጌ ላቅርብ፤

የእስላሞችን ሰይፍ እንመርጣለን የሚሉን ሰዎች፤ የእስላሞች ሰይፍ በኢትዮጵያ ምድር በክርስትያኑ ሕብረተሰብ ምንን አስከትሎ ነበር ብለን ታሪክን እንጠይቅ። የራሳቸው ጸሐፊዎች እንዲህ ይላሉ።

“..in the land of infidels, nothing was to be seen but cut-off heads, spirits in the throats of death, and palms of hands flying in the air. The Muslims cried out with a mighty cry: ‘there is no God but Allah,’ and ‘God is the Greatest’ (98) Literally with the Tahlil and the Takbir’ (the Takbir is the cry Allahu Akbar”. (ምነጭ 15ኛው ክፍለዘመን ከግራኝ አህመድ ጋር የነበረ “Sihab ad Din Ahmadin Abd alQader bin Salem bin Utman ወይንም በሌላ የተጸውኦ ስሙዓረብ ፋቒሕ” ( Arab Faqih) የተባለው የመናዊው ዓረብ ጋዜጠኛፉቱሕ አል ሐበሻ” ( Futuh Al- Habasa – the Conquest of Abyssinia {16th Century} በተባለው በዓረብኛ ቋንቋ ተጽፎ ወደ አንግሊዝኛ ቋንቋ የተተረጐመ) ስንመለከት

ግራኝ አህመድ ኢትዮጵያን ሲያስተዳድር እስላማዊ አስተዳደር ነበር። እነ ደ/ር በያን አሶባ ይህንን ልንነግራቸው ይገባል። ያውቁታል ፤ዶክተሮች ናቸው፤ ሆኖም፤ ድርጅታዊ ውሸት ስለለመዱበት የተጨቆነው እስላሙ ብቻ ነው የሚል ውሸት ማናፈስ ስለለመደባቸው እስኪለወጡ ድረስ እንጠብቅ (የሚለወጡ ከሆነ?)።ተማረ ማለት የግድ እውነት ይናገራል ማለት እንዳልሆነ ብዙ፤ብዙ ምሁራን ታዝበናል።

ወደ ግራኝ ከመሄዴ በፊት እስላማዊው በቅርቡ በ1928 በጣሊያን ወረራ ጊዜ፤ የጅማ ባላባት የነበሩ እስላማዊ  “አባ ጆቢር አብዱላሂ”፤ የአማራ/ክርስትያን አንገት ቆርጦ ወደ እኔ ያመጣ “30 ጠገራ” /ብር/ እሰጣለሁ ብለው ያወጁትስ ዶ/ር በያን እና መሰሎቹ በምን ሂሳብ ሊያወራርዱት ይሆን? የእስላሞች በዓል ጊዜ “ት/ቤቶች” አይዘጉም ነበር ከሚለው እንዴት ያወዳድረው ይሆን?

የ30 አማራዎች አንገት ከተቆረጠ በሗላ ነው፤ ሕዝበ ክርስትያኑ ወደ ራስ እምሩ እየሸሸ በብዛት ተዋጊ ጦር ያገኙት። ራስ አምሩ  ‘ጎጀብ’ በሚባለው ወንዝ ለመሻገር ሲሞክሩ በጣሊያን ጦር ተከብበው እንዲያዙ ምክንያት የሆኑት በ“ኦሮሞዎች” ምክንያት ነው። አይደለም እንዴ ዶ/ር? ኢምፓየር ጣሊያን ይሻል ነበር 4ኛ ክፍል ገድቦ “አዲስ አበባ ፒያሳ” እንዳትራመዱ ብሎ “ቦይ” እና ሳህን አጣቢ ሆናችሁ ዕድሜ ሙሉ ልትኖሩ ተመኛችሁ? “እስላሞች” ሕክምና ለማግኘት፤ት/ቤት ለመማር፤አብቶብስ ለመሳፈር ከፈለጋችሁ፤ “ካቶሊክና ፕሮተስታንት” ሁኑ  ብሎ እንደ “አስማሪኖ እንደ ሓመሴኖች” “ብትኮተልኩ” ይሻላችሁ ነበር? ዕድሜ ለኦሮሞ ልጆች ለእነ ምኒሊክ ለእነ ሃይለስላሴ ብትሉ ምን ይጎዳችሗል?  ሃቁ ይሄ ነው!

ሃይሌ አባ ጠቅል እስላሙን ምን አደረጉት ነው የምትለዋቸው? ነውር ነው። ጣሊያንን አልወጋም ብለው አልዘምትም ብለው ከቀሩት አንዱ አባ ጆቢር ነበር። ይባስ ተብሎ ‘ጆቢር’ ለሰራው ክሕደት ቅጠቱን ከማግኘት ይልቅ፤ “ክርስትያኑ” ንጉሥ ሃይለስላሴ በወር $300.00 ተቆራጭ አድርገውለት በእንክብካቤ ኖረ። እስላሞች በዓል ሲሆን ት/ቤት አይዘጋም ነበር ከመለው ክስ የትና የት ነው? እንደምንሰማው ከሆነ፤ አሁንም፤ የአባ ጀቢር የልጅ ልጁ አሁንም ከወያኔ ጋር ሆኖ ኣገሪቷን ያተራምሳል ሲባል ሰምተናል። ትምህርት ቤት አልተዘጋም ነበር ቀልዳችሁን፤ ተውት!

እስኪ ወደ እሩቅ ስርዓታችሁ ልውሰዳችሁ። አስላማዊው መንግሥት መስርቶ ኢትዮጵያዊው መንግስት ሆኖ ግራኝ አህመድ፤በ15ኘው ክፍለ-ዘመን ኢትዮጵያን ሲያስተዳድር፤ለረዢም ዘመን የቆየውን ክርስትያናዊ መንግሥት ገልብጦ እስልምና ሃይማኖት ካልተቀበላችሁ እያለ ክርስትያኑን ሕዝብ ጨፍጭፎ፤ የክርስትያኑን ሀብትና ንብረት ሙልጭ አድርጎ ዘርፎ፤ ለትርኮች ከማቀበሉ በላይ ንብረቱ አልበቃ ብሎ ከሞት የተረፈውን ወጣቱን ክርስትያን ሴትና ወንድ፤ እንደ ከብት እየተመለመለ፤ እንደ ገበያ በግ እየተነዳ፤ የመን ላይ ተቀምጦ “በምክርም፤መሳርያም” ሲረዳ ለነበረው ለቱርክ  መንግሥት ተወካይ ወስዶ፤ ‘ለዘቢድ ፓሻ” በገፀ በረከትነት ሲያስረክብ፤ የተቀሩ ደግሞ ለዓረቦች እንዲሸጡ አድርጛል። በዚህ ዘመን፤ የደረሰው ግፍና የወደመው ክርስትያናዊው ህይወት ንብረትና እውቀት፤ታሪካዊ ውድ የሆኑ የማይገኙ፤ የጥንት ምስጢር የያዙ መጽሐፍትና ንብረት፤ወርቅና ጌጥ፤ እጅግ ለመመዝገብ አስቸጋሪ ጉዳትና ጥቃት ደርሷል። ትምህርት ቤት አይዘጋም ነበር? እንዴ?!! እንዴ!!

ይህንን ለማወቅ በወቅቱ ከግራኝ አህመድ ጋር በጦርነቱ ጊዜ ያለተለየው ዓረብ ፋቒሕ” ( Arab Faqih) የተባለው የመናዊው ዓረብ ጋዜጠኛፉቱሕ አል ሐበሻ” ( Futuh Al- Habasa – the Conquest of Abyssinia {16th Century} በተባለው በዓረብኛ ቋንቋ ተጽፎ ወደ አንግሊዝኛ ቋንቋ የተተረጐመ) የወቅቱ ዓይን ምስክር የነበረው የጻፈው ምስክርነት ለማንበብ “ጸሐይ ማተሚያ ቤት/ሎስ አንጀለስ/ ወይንም አማዞን አለ። ገዝተው ያንብቡ፤፡ ካልሆነም፤ በጥቂቱ ዋና ዋና ያልኻቸውን ጥቃቶቹን ክንዋኔዎች ለማየት በዚህ አድርሻ የጻፍኩትን “በሃይማኖትና በፖሊቲካ የማሻኮር ባሕሪ” ጌታቸው-ረዳ http://www.ethiolion.com/Pdf/05192013bepoletikana_behaymanote.pdf
አንብቡ። ያኔ ሃቁን ታያላችሁ። የሚቀጥለው ላብራራ እና ላጠቃልል።

በመጨረሻም  ክርሰትያኑን መክሰስ እስላሙ ተበዳይ አድርጎ በየሚዲያው እየደጋገሙ መክሰስ ይቁም። ይህ ደግሞ፤ በእነ ዶ/ር በያን አሰቦና በነ ታማኝ በየነ ብቻ የተወሰ ሳይሆን፤ ይህ የተለመደ ወደ አንድ ያዘነበለ አድሎአዊ ውሸት “እኔም አቡበከር ነኝ!” እያሉ እነ ታማኝ የሚመጻደቁበት አሁን እስር ቤት ውስጥ የሚገኘው ኡስጣስ አቡበከርም ዓይን ያወጣ ውሸቱን ለሕዝብ እስላሙን፤በተለይ ለወጣት ተከታዮቹን ውሸት ሲመግብ እንዲህ ሲል የዋሸውን አስተምህሮቱ ልጥቀስና ልደምድም።

እጠቅሳለሁ፦
የአገራችን ታሪክ አንኳ የተደረገ ታሪክ ምስክር ነው። የነ አፄ ዮሀንስ እና ምኒሊክ ታሪክ! ‘የቦሩ ጉባኤግልፅ ታሪክ ነው።የክፈር ዘመቻ ታውጆ፤ ሙሰሊሙ ካልከፈረ ተብሎ፤ሲገደል፤ እጁ ሲቆረጥየነበረ መሸይኰች እናውቃለን አይደለም እንዴ? ቁርአን ሲቃጠል፤ መሸይኮች ሲገደሉ የነበረውበነሱ’ (በሃይማኖተ ቢሶቹ፤ኩፋሮቹ) ታሪክ ላይ ነው። ቤየትኛው ታሪክ?! ኢማሙ አህመድ ወይንም ደግሞግራይ አሕመድያሉትግራይያሉትግራ የሆነባቸው ሰዎች ናቸው።ኢማሙ ታሪክ ላይትልቅ ነገርሰርተዋል፤ኢትዮጵያ ታሪክ ላይ። ኢትዮጵያን አንድ አደርገው ለመግዛት ተንቀሳቅሰዋል።ያን ተግባር ሲፈጽምኢማም አሕመድቤተክርስትያን አጥፍቷል፤አገር አጥፍቷል ይላሉ፤ እውነት ቢሆን ኖሮ፡ ኢማም አሕመድ የሚያጠፋው ላሊበላን ነበር፡ አማም አሕመድ፤ የሚያጠፋው አክሱምን ነበር፡ የክርስትያን እምብርት፤ማዕከሎች የሞባሉት። ነገር ግን፤ኢማም አሕመድ አላጠፋም፡ (ጉዳት አላደረሰም) ክርስትአናና ለማጥፋት የመጣ ጂን/(ዲን) አይደለም።አላህን ፍሩእያለ ነበር ጦሩን ያንቀሳቀሰው፤የሰው ልጅ ፍትሕን ለማስፈን፤በባጢል የተዘለበውን ማሕበረስብ በፍትሕ ላማሳደር ……በየትኛውም ዘመን ላይ ከእስልምና ዕምነት ውጭ ያደሩትና በፈትሕ የኖሩት በሰላም ያደሩትወላሂ!!” እስልምና ዓለምን በመራበት ጊዜ ብቻ እና ብቻ ጊዜ ነው። ፍትሕ ተከብሮላቸው፤ደሕንነታቸው ተረጋግጦላቸው የኖሩት፤ከጭንቀት የወጡት። እስልምናአኽላቅ አልሐርቢየጦርነት ስነ ምግባርያለው ብቸኛ ጦርነት የተስተናገደው ብቸኛው ጦርነት ነው። የተደረገው ታሪክ የሃቅ እና የባጥል ሥራ ፍጥ እውነታ ታሪካችን ይኼ ነው፤ ለማለት አንጂ፤ ደም የተሰተናገደበት በደም የተሞላበት ጦርነት አይደለም እስልምና።

በማለት ኢትዮጵያዊውን ወጣት በፈጣን ዓረብኛ ቋንቋ ቃላቶች በብዛት ጣልቃ እያስገባ ውሸት ሲመግብ ታሪክ ሲያጣምም፤ የፈጠራ ሰበካ ሲሰብክ ሃይማኖትውሸትአታስተምር የሚለውን ትምህርት እየጣሰውሸትሲሰብክ ቃል በቃል ያነበባችሁት የኡስጣስ አቡበከር የሰበካ ትምህርት ነው። በሩ ሜዳ ላይ የተከናወነው የሁለት ክርስትያኖች እምነት ተከታይ ሊቃውንቶች የተከራከሩበትና ንጉሡ ያንደኛውን ወገን ክርሰትያን አምነት ክርክር ወግነው የሌላኛውን ክርስትያን እምነት ተከታይ ተከራካሪ “ኢፍትሃዊና ዘግናኝ ፍርድ” ያስተላለፉበት እንጂ እስላሞች እንዳልሆኑ የሳቸው ታሪክ ያስረዳል።  

እንደዚህ ያሉትን ሃይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ የውሸት መሪዎችን ነው ታማኝ በየነና መሰሎቹእኛ አቡከሮች ነን! እኔ አቡበከር ነኝ!’ እየተባለ በያዳራሹ መፈክር ሲሰተጋባ የሰማነው።” እንግዲህ እነ አቡበከር “ኩፋሮች” እያሉ (ሃይማነተ- ቢስ) የሚሉንን ኢትዮጵያዊያን እስላም ወንድሞቻችን በየነፃነት አርማ አርበኛቸው “ግራኝ አህመድ” ላይ የነበራቸውና አሁን ያላቸው “ወልጋዳ” ኣመለካካት፤ ክርስትያኑ የደረሰበት  ጥቃት፤ እዛው የነበረው ዓይን ምስክር የጻፈውን እየደበቁ፤ የራሳቸው ፈጠራ የሚሰብኩ ‘እስልምና አስተማሪዎችና ፖለቲከኞቻችን” የሚዋሹት “ሃቁን እንድትመለከቱት”፤ ብዬ ነው በድጋሚ በዚህ ጉዳይ ለሁለተኛ ጊዜ እንድተችበትና የእነ ደ/ር በያን አሶባ ሚዛናዊ አልሆነ “ክስ” እውነቱን እንድታውቁት የማቀርበው።

በክፍል ሁለት፤ “በአዲስ ደምፅ ራዲዮ” እነ በያን እና አረጋዊ ስለ አንድነትና እንዲሁም ስለ የበያን አሶባ ድርጅታዊ መስመር (ኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግምባር ምንነት ውስጠ መጋረጃውን በሚያሳይ  በተጨባጭ ሰነድ ገልበን እናያለን) በክፍል -2- በሰፊው እመለስበታለሁ። እስከዛው ሰላም ሰንብቱ። ቅር ሳይላቸው የሚናደፉ ፖለቲከኞችን መናደፋቸውን/ ውሸታቸውን እንዲያቆሙ የሁላችን ብርታት እና ጥረት ያስፈልጋል። ወደ ልቦናቸው እንዲመለሱ ውሸት እንዲያስወግዱ እንድንረዳቸው፤ የኢትዮጵያ አምላክ ይርዳን! አሜን!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian semay ድረገጽ አዘጋጅ) getachre@aol.com