Sunday, January 30, 2022

ሰበር ዜና ባሕርዳር ከተማ በናዚ ማጎርያ አዳራሾች የታሰሩ የንጹሃን ትግሬዎች ሁኔታ ጌተቸው ረዳ ETHIO SEMAY 1/30/2022

 

ሰበር ዜና

ባሕርዳር ከተማ በናዚ ማጎርያ አዳራሾች የታሰሩ የንጹሃን ትግሬዎች ሁኔታ

ጌተቸው ረዳ

ETHIO SEMAY

1/30/2022


እንደምታውቁት በዕብዱ በሽተኛው አብይ አሕመድ የሚመራው “በናዚዎች ርዕዮተ   ዓለም ኢትዮጵያዉያን ትግሬዎችና የአማራዎችን  ዘር በማጥፋት አጀንዳ” ሌት ተቀን  የሚሰራው “የኦሮሙማው መንግሥት” በተባባሪ አሽከሮቹ እነ ተመስገን ጥሩነህ እና የኢሳቱ “ካቡጋ” (génocidaire መሳይ መኮንን) እንዲሁም መሰል አሽከሮቹ በንጹሃን ትግሬዎች የታወጀው የዘር ማጥፋት አወዋጅ ያደረሰው ስቃይ እየተከታተልኩ ካሁን በፊት ለአንባቢዎቼ ማቅረቤ ይታወሳል።

ንጹሃን ትግሬዎችን ከገበያ፤ ከሆስፒታል ከየመንገዱ እና ከየሞኖርያ ቤቶቻቸው እየታፈሱ ወደ “ኮንሴንትሬሽን ካምፕ” ታስረው መሰቃየት ከጀመሩ በርካታ ወራት ሆኗቸዋል። አንዳንዶቹ 10 ወራት አስቆጥሮዋል፤ አንዳንዶቹም አዋጁ ከታወጀ ወዲህ ያለ ምንም ማስረጃ ታስረው እተሰቃዩ ናቸው።

ጥፍር እየነቀለ እና የሴት ማሕጸንና እና  የወንድ ብልት ሲያኮላሽ የነነበረው የጌታቸው አሰፋ የወያኔ መንግሥት የጽጥታና የምርምራ ምክትል ሃላፊ የነበረው “ኦሮሞው ያሬድ” ሰሞኑን እንደፈታው ሰምተናል። ቀደም ብሎም እነ ጃዋር እነ በቀለ ገርባ እና ስብሓት ነጋ እና ስንት የሽብር፤የግድያናየ የጥላቻ ቅስቀሳ ሲያስፋፉ የነበሩ ቁንጮ “ሽብርተኞችን” ያለ ምንም የበደል እና የይቅርታ ማስፈርም ከወህኒ ቤት ሲፈታቸው ያልደነገጠ የልተገረም ሰው አልነበረም።

አስገራሚ ያደረገው ግን “ቁንጮ ሽብርተኞችን” ፈትቶ ምንም የሌሉበትን ንጹሃን ኢት ጵያዊያን የትግራይ ተወላጆችን በአዋጅ ለቅሞ ያሳራቸው እስካሁን ድረሰ ታጉረው እንዳሉ ታውቃላችሁ። የእንቆቁሉሹ አስገራሚውም ነገር አንዱ ይህ ነው።

በኦሮሙማው ናዚያዊ ጸረ ትግሬ የዘር ማጥፋት አዋጅ መሰረት ባሕርዳር ውስጥ የታሰሩ ንጹሃን ትግሬዎች ወደ ማጎርያው አዳራሽ በመሄድ ታሳሪዎችን አንድ ባንድ እያነጋገሩ  “ልትፈቱ ከፈለጋችሁ በድለናል አዎ ወያኔ ነኝ ብላችሁ ፈርሙ” እያሉ ስማቸው አድራሻቸው ቅጽ አስሞልተው እንዲፈርሙና እንዲለቀቁ በግድ እያስገደዱዋቸው ነው።

እምቢ ካሉ መውጣት አይችሉም። በሚገርም ሁኔታ “እንዴት በማናውቀው ፖለቲካ አባል ነን፤ ድጋፍ እንሰጥ ነበርን ብለን ያላደረግነውን አድርገናል ብለን እንፈርማለን? ይህ ነውር አይደለም ወይ? ብለው ሲጠይቁ፤ “ከፈለግክ/ከፈለግሽ/ ፈርም /እዚህ ፈርሚ/ካልሆነ ግን እዚሁ ትበሰብሳታለህ/ትቀምሳታለህ” እያሉ ንጹሃንን በማስፈራራትና በማስገደድ ላይ እንዳሉ አረጋግጫለሁ።

እንግዲህ ፍረዱ። ፍርድቤት ሳይሄዱ፤ሳይጣራ፤ ማስረጃ ሳይቀርብባቸው “በአዋጅ ታፍሰው” የታሰሩ ምስኪኖችን በግድ እያስፈራሩ ፈርም እያሉ እስረኛን ማስገደድን “በሕግ” ቶርች ወይንም “ኮሆርዥን” እንደሆነ  እየታወቀ በሽተኛው አብይ አሕመድና የግል አሽከሩ የሆነው ተመስገን ጥሩነህ ለትግሬዎች ያላቸው ጥላቻ ለማሳየት እየተበቀሏቸው ይገኛሉ።

ለዚህ ነው ማንም ድርጅትና ግለሰብ የሕግ ምሁር “አብይንና ተመስገን ጥሩነህ ከመላ አማራ ብልጽግና አማራር አባል” በዘር ማጥፋት ወንጀል አብይና አሽከሮቹ ለዓለም አቀፍ ፍርድቤት ካልተከሰሱ፤ ብዙ ጥፋት ያስከትላሉ የምለው ለዚህ ነው።

አሳዛኙ ብቀላ ድምበር እንደሌላው የሚያሳየን ደግሞ የሚከተለው አሳዛኝ ብቀላ ነው።

እነዚህ ንጹሃን ፈርመው ቢለቀቁም “ሥራቸው በሌላ ሰው ተተክቶ” ስለሚቆያቸው አብይና ተመስገን ጥሩነህ ከተቀሩ የአማራ ብልጽግና አማራሮች፤ “ትግሬዎች በረንዳ እንዲወድቁ ባቀዱት መሰረት” ‘በረንዳ አዳሪ’ ይሆናሉ።

በዚህ የሕይት ምስቅልቅል ትግሬዎች ሲሰቃዪ ማየታቸው የነዚህ እኩያን ሰዎች የዘር ማጥፋት ዕቅድ እርካታ እና ስኬት ለረዢም ጊዜ ዘላቂ ጠባሳ ትቶ የሚሄድ ብቃላ ነው ማለት ነው።

ቢሆንም የጊዜ ጉዳይ እንጂ እነሱም በሰፈሩት ቁና ይሰፈራሉ!

“እንድትፈቱ ከፈለጋችሁ እኔ ወያኔ ነኝ፤ ዕርዳታም እሰጥ ነበር፤ በወንጀል ተካፍያለሁ..…ብላችሁ ፈርሙ ካልሆነ አንፈታችሁም” እያሉ የሚያደርጉት ድርጊት ከመሪዎቹ መፈታት ስታነጻጽሩት እነ አብይና የአማራ ብልጽግና አመራር አባሎች ብቀላቸው ከተራው የትግራይ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ትግሬ እንጂ ከወያኔ መሪዎች ጋር እንዳልሆነ ከሚሰሩት አስነዋሪ “የመስገደድ ፌርማ” እናንተም በቤተሰቦቻችን ሕይት ላይ እየደረሰ ያለ የዘር ብቃላ ወንጀል እንድታውቁት ብየ ነው ይህንን ዜና ያካፈልኳችሁ።

ታሪክ ይዘግባል፤ሕይወትም ይቀጥላል።

አመሰግናለሁ።

ጌታቸው ረዳ  ETHIO SEMAY 1/30/2022