Tuesday, December 31, 2019

የሐመልማል አባተ ባንዳዊ ተልዕኮ በኤርትራ! ከጌታቸው ረዳ (Ethio Semay) January 1, 2020


 ሐመልማል አባተ ባንዳዊ ተልዕኮ በኤርትራ! ከጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)
January 1, 2020
ከዚህ በታች የምትመልከቱዋቸው ወታደሮች ከ18 አመት በት ባቀረብኩት ትችት እቅርቤው የነበረው ማሕደር ውስጥ ነው። ፈቶግራፎቹ የምታየዋቸው ሙርከኞች፤ ሻዕቢያና ወያኔዎች በአሜሪካኖች የስለላ ሳተላይት መረጃ እየታገዙ ባገኙት ዕድል አርበኞች ኢትዮጵያዊያን፤ ወታደሮች ለሻዕቢያ ምግብ እንዲያዘጋጁ በተገደዱበት ወቅት እንጀራ ሲጋግሩ።ኢትዮጵያ ምርኮኛ ወታደሮች ለሻዕቢያ ምግብ አቅርቦት በቆላማ በረሃ ውስጥ በዶሮ ዕርባታ ያሰማራቸው አርበኞች ወታሮቻችን።ኢትዮጵያ ወታደሮች በሳሕል በረሃ ውስጥ አትክልት እየተከሉ ፍራፍሬ በመልቀም ለሻዕቢያ ምግብ እየለቀሙ ተክል ለቀማ ያሰማራቸው ጀግኖች። ሻዕብያ በሰሓል ሐሩራማ በረሃ ውስጥ በጉልበት ሥራ በአስፋልት ስራና ጉድጓድ ቁፋሮ ያሰማራቸው ናቸው።
ካሁን በፊት ነጭ ባንዴራ አውለብላቢዎች በሚል ተከታታይ ክፍሎች ያሉት ጽሑፍ ማቅረቤ ይታወሳል። በነዚህ ክፍሎች ውስጥ በርካታ የኢትዮ-ሰማይ አንባቢዎች “ነጭ ባንዴራ አውለብላቢዎች ምን ማለት ነው ብለው ጠይቀውኝ ነበር። ዛሬም ያልገባቸው ቢኖሩ ሁለት ትርጉም ያለው ቢሆንም ፖለቲካዊ ትርጉሙ ግን ሰላማዊያን ማለት ሳይሆን “ከሃዲዎች/እራሳቸውን ለምርኮ እጃቸውን ያስረከቡ/ ማለት ነው። በ2011 ዓ.ም ጸረ አማራ የኦሮሞዎች መንግሥት የመሠረተው የኦነጉ ኮሎኔል አብይ አሕመድ ከነገሠ ወዲህ ‘ነጭ ባንዴራ’ እያውለበለቡ ከውጭደ አገርና ከውስጥ አገር እጃቸውን ለሙርኮ ያስረከቡ በርካታ ሰዎች የተቸሁበት በ4 ክፍል የተከፈለ ትችት ማሳተሜ ይታወሳል።

ነጭ ባንዴራ የሚያውለበልቡ የፖለቲካ ሰዎች ለምሳሌ “የአንዱአለም አራጌ” ንግግር “አብይ አሕመድ እንደኛ ሰው ነው “በሆነ አጋጣሚ ወደ ሥልጣን የወጣ እንደ ማንኛውም ፍጡር ሰው የሆነ እንጂ የተለየ ክንፍ የለውምና እባክችሁ ታገሱት”  ያለው ምግግሩ እንደምሳሌ ስትመለከቱ “ህጻናት እና አረጋውያን በጎስታፖው “በኦነጋዊያን ኦፒዲኦ ፖሊሶችና ከንቲባዎች” ከቤቶቻቸው እየታነቁ ወደ ጎዳና የተወረወሩ፤በቡልዶዘር ለፈረሰባቸው እርጉዞች፤ እናቶች፤ ቤቶቻቻው ስለፈረሰባቸው ‘ትምህርታቸው የተጓጎለባቸው ህጻናትን” እና እምባ ለሚያቀርሩ አዛውንቶችን!! ነው “ታገሱት” የሚለው ተማጽኖ ስትመለከቱ የነጭ ባንዴራ አውለብላቢነት ጥሩ ምሳሌ ነው። “ፕረዚዳንት ለመሆን ወደ ምርጫ እገባለሁ” የምትለን ምላስዋ ከሰሞን ወደ ሰሞን የሚለዋወጠው ግማሽ ኦሮሞ ግማሽ አማራ የሆኑት ‘አስቴር በዳኔ” ም ሆነች ‘መሰረት አበራ’፤ እንዲሁም ታማኝ በየነ፤ አል ማርያም፤ሳሙኤል ፈረንጅ፤ኩኩ አቤሰሎም… ወዘተ የመሳሰሉ ምሁራን በዚያ ረድፍ ሰይሜ የተቸሁባቸው 4 ምዕራፎችን ማየት ይረዳል።

ከተማሩ ሰዎች ውጭ የኪነት ሰዎች የባሰ አሽቃባጮች ሆነው የሕዝባችንን ሰቆቃ እንዳይደመጥ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ሥልጣን ላይ ያለው ፋሺስታዊና ወንጀለኛው የኦፒዲኦ መሪዎችን እየካቡ ፍጹም ወደ ሙሴነት በመለወጥ በሙዚቃና በግጥም እያጀቡ ሰቆቃው እንዲታፈን በማድረግ ሚና ተጫውተዋል።

ካሁን በፊት አዝማሪና ዳንኪረኛው “መኳንንት መለሰ” ምርጥ ኢትዮጵያዊ እየተባለ  አገር ውስጥም ዋሺንግቶን መጥቶ በነበረበት ወቅት "የካቡት" የወያኔ አፋሪም “በግንቦት ወር ውስጥ ፋሺስታዊ ስርዓት” ይዞልን የመጣውን ወያኔ ወደ አዲስ አባባ የገባበትን ወር ለመዘከር በሚል “ዘር ማጥፋት ወደሚካሄድበት” “ራያ” ወደ ተባለው የወያኔ ጎራ ‘በመሄድ ሲጨፍር በቪድዮ የተሰራጨውን መተቸቴን ተከታታዮቼ የምታስታውሱት ነው።


በኪነት በኩል በርካቶቹ በፈረንጆች ዘመን አቆጣጠር በጁን 2018 “የሰላም መሪ”  ብሎ የዘፈነው ሻምበል በላይነህም ፤ፋሲል ደሞዝ ፤ መስፍን በቀለ  የመሳሰሉ ከፍተኛ የሕሊና አጠባ አዲሱን ትውልድና ባጠቃላይ ማሕበረሰባችን በማጃጃል ስራ የተጫወቱት ሚና ብዙ ነው። አንዳንዶቹ ኢሳያስን በማወደስ አብይ ከመምጣቱ ፊት ኤርትራ ኤርትራ እያሉ ሲደልቁ የነበሩ በርካታ አዝማሪወች አሉ። ከዚያም አብይና ኢሳያስ በሉአላዊነታችንና በተሰውት አርበኞች ወታደሮቻችን ህይት እየተሳቁና እየተቃቀፉ ሲቀልዱብንም አዝማሪች እጃቸውን አስገብተው ለመሳለቁ ድምቀት ሰጥተዋል። ዛሬም እንደ እነ ሓመልማል አባተ የመሳሰሉ ቀባጣሪዎች ኤርትራ  ድረስ በመሄድ በተሸናፊነት መንፈስ እየተነዱ ብሔራዊና ሰብኣዊ ወንጀል ተጠያቂ ለሆነው ‘ቅጥረኛውና ጸረ ማራው የፋሺስቱ’ የአብይ አሕመድ ተልዕኮ ለማሳካት “ሸብረክ” ብለው በመቀበል  መለስ ዜናዊ የተባለ ‘ኤርትራዊው ሻዕቢያ’ በሥልጣን እያለ ለሻዕቢያ የቆመውን ጥብቅናው ተግባራዊ ለማድረግ መለስ የፈረመውን አገር የመሸጥ ‘ሕገ ወጥ’  ስምምነት በሙዚቃ በማጀብ የሻዕቢያን ሉኣለዊነት ለማሞገስ “በታላቁ የወያኔዎችና ኦሮሞዎች ሴራ” ተካፋይ ሆነው የአገራችንን ታላላቅ ሉዓላዊ ጥያቄዎች እንዲዳፈኑና አርበኞቻችን እንዲረሱ፤ ከቶውኑ አዲስ ትውልድ ኢትዮጵያ የተበደለቺውን “የሕግና የታሪክ አመጽ” እንዳያወሳ  ተጨማሪ እንቅፋት ለማጠናከር ሃመልማልና አብረዋት የሄዱት አደግዳጊዎች በአንክሮ ታዝበናቸዋል።


ዳላስ ቴክሳስ አሜሪካ የምትኖር  አርበኛዋ የሐረር ወረቅ ጋሻው (ኢትዮጵያ ወርቅ ጋሻው) የኢትዮጵያ ሙርከኞች ወታደሮች ለማስፈታት ከኢሳያስ አፈወርቂ ዘንድ ለመደራደር ወደ መረብ ምላሽ (ኤርትራ ምድር) ሄዳ ስትደራደር  የለበሰቺው የሃገርዋን ኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ነበር። እንደዚህ ያሉ አርበኞች አንስት አርበኞቻችንም ስናስታውስ ኩራት ሲሰማን እንደ እነ ሃመልማል አባተ የመሳሰሉ ደግሞ ማፈሪያዎች ሆነው ታሪክ ይመዘግባቸዋል። 

የነ ሓመልማል ወደ ‘ባሕረ-ነጋሽ’ ዘልቆ የጠላት ባንዴራን ማውለብልብ ቅጂው መሰሪው ‘መለስ ዜናዊ” አዝማዎሪዎቹን ወደ አስመራ እየላከ “ኤርታዊት ኣዶ እዚ’ኹሉስ ኣይሳላኽንዶ” (ኤርትራዊት እናት ይህ ሁሉ ጀግንነትና ድል ያንቺ የማህጸንሽ ፍሬ እኮ ነው”  እያሉ የኢትዮጵያን እናቶች ግን “ጀግኖች የማይወልዱ” እያሉ ወንጀል ሲሰሩት እንደነበረው ሁሉ ዛሬ በባለተራዎቹ በኦሮሞዎች መንግሥት የተላከቺው ሓመልማልና መሰል አለቅላቂዎች “በወንድማማችነት ሴራ ስም” ባለፈው ሰሞን ተመሳሳይ የጸረ ኢትየጵያ ፕሮፓጋንዳ ሥራ የሰራቺው (ደባራ- ደረቅ ፊት) ‘ሓመልማል አባተ’ የተባለች አሽቃባጭ አዝማሪት “ከረንን ያላያ፤ምፅዋን ያላየ ይፍረደኝ” እያለች ስለ ከረን ጀግንነት እና ስለ ምፅዋ  ስታወድስላቸው መስማት እጅግ አንጅት ያሳርራል።

ይህ እንዳይበቃት  ሲነማ ኦዴን በተባለው ጣሊያን በገነባው የሲኔማ አዳራሽ ተገኝታ “ፈልጌ እጥቼው የነበረው ጉብል ፤ በሩ ሲከፈት አገኘሁት ጉብል“ (ፓራፍሬዝ) እያለች “በረከት መንግሥትአብ” እንወዳሃለሁ! እናከብርሃለን!” እያለች ጸረ አማራና ጸረ ኢትዮጵያ  ግጥም ሳይጨምር የማይዘፍን የሻዕቢያው ሎሌ “በረከት መንግሥትአብ”  በሕዝብ ፊት እየዘለለች ስታሽቃብጥለት መስማት የማሃይምነትዋ መጠን ቀይ መስመር ያለፈ ነበር።

ያ አልበቃ ሲላት ፡በሻዕቢያ ፍቅር የተለከፈ “ፍቅር ዩቱብ” የታባለ አብይና የሻዕቢያ አሕመድ ፕሮፓጋንዳ ክፍል” ስለ ጉዞዋ ምን አንደተሰማት ጠይቋት “በማታውቀው የፖለቲካ ስራ ገብታ ስትፈተፍት” መስማት ደግሞ ሌላው አስገራሚ ነገር ነበር።

ስዘፈነፈላችላቸው ኤትራኖች እያለቀሱ’ ነበር ስትል ፡  የምትላቸው ‘ስለ ኢትዮጵያ ያለቀሱ’ መስሏታል (የኤትራኖች ስነ ልቦና የማያውቁ የመሃል አገር ሰዎች ሁሌም ይገርሙኛል)። አለቀሱ የምትላቸው “ብዙዎቹ አባቶቻቸው ኤርትራ ለውግያ መጥተው እዛው ደቅለዋቸው ፤ ፋታ ባልሰጣቸው ባስቸጋሪው ወቅት ቤተሰቦቻቸውን መስብሰብ ሳይችሉ ቀርተው እዘው ባሕረ ነጋሽ  ትተዋቸው የሄዱ የወታደር ልጆች ናቸው። እያሰለፉት ያለው ነውረኛ ዘረኛነት አስናፋቂው የኢትዮጵያ ሙዚቃ ተጨምሮበት ወላጆቻቸው የጠፉባቸው ዜጎቻችን ‘አምባቸው ሲያቀርሩ’ አይታ “ነፈዝዋ ሓመልማል አባተ” እንደምታወራው “ለኢትዮጵያ ፍቅር አድሮባቸው አይደለም።

የሚገርመው ደግሞ ኤርትራኖች ድሮም ዛሬም ለኢትዮጵያ ያላቸው ፍቅር አልተለወጠም ትላለች።
እስኪ ላስታውሳት ኤርትራኖች በ1983 ምን እንዳደረጉ።

ከመጽሐፌ ቀንጭቤ ላስነብባችሁ፤-ለመረጃ እንዲሆናችሁ ከዚህ በታች የማቀርበው አጭር ቃለ መጠይቅ ተደርጎላቸው የመሰከሩት የ ‘ዋ! ምፅዋ' ደራሲ  “የኦሮሞ ተወላጅ ናቸው”
“ዋ ምፅዋ” ደራሲ መቶአለቃ ታደሰ ቴሌ እንባ እየተናነቃቸው ከካሳሁን ሰቦቃ (አውስትርአሊያ ራዲዮ) ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ስለ ኢሳያስ ፖሊሲ እናስታውስሽ።
እንዲህ ይላሉ፤-

“በተለይ ደግሞ የአማራ ብሔረሰብ የሆኑትን ለብቻ ለይተው ድንጋይ ፍንቀላና መንገድ ስራ ያሰሯቸዋል።አማረኛ ተናጋሪ ከሆንክ ለብቻ ያደርጉና እናንተ ናችሁ ለኤርትራ ጦርነት ምክንያት የሆናችሁ ይሎቸዋል።ሁሉም ሰው አማራ ላይ ይበረታል ።አማራ ብሔረሰብ ሲመዘገብ አማራ ነኝ ብሎ ስለሚመዘገብ  አማራ የሚባለው ዘር ፋይል ለብቻ አለው። ፋይሉን ለብቻ አውጥተው ነበር የሚጠቀሙበት። በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ እጅግ በጣም የከረረ ፣አንድ ቃል በመናገሩ አንድ ጥይት የሚሰጡበት ሁኔታ ነው የነበረው።” ይላሉ። 

ይህ ሁሉ ወንጀል እንዴት ተደርጎ ድሮውንም ኤርትራኖች ለኢትዮጵያውያን ፍቅር ነበራቸው ተብሎ በአለቅላቂ አዝማሪዎች በእንደ እነ ሀመልማል አባተ ይሰኮርብናል። ኢትዮጵያ በደለቻቸው? እንዴትስ ተደርጎ ይህ ሁሉ በአማራ ላይ ግፍ ይፈጸማል። በምርኮኞች እንኳ አማራ ወታደሮች እየተለዩ በልዩ መዝገብ እየተለዩ ለሥቃይ እንደተዳረጉ ከሙርኛው ኦሮሞ ታደሰ ተሌ አይን ምስክርነት ሰምታችኋል። አዝማሪዎች አደብ አድርጉ! ምፅዋ ላይ አልጌና ላይ ከረን ላይ ባረንቱ ላይ ባድመ ላይ የፈሰሰው ደም እና የተዘራው አጥንታቸው በላያቸው ላይ ስትጨፍሩ  እሾህ ሆኖ ይውጋችሁ!

የነ ኮለኔል ተሾመ ተሰማ ጥይት ምጽዋ ባሕር ውስጥ ሆኖ ዛሬም ጥሪው ህያው ሆኖ ያስተጋባል!
ድል ለኢትዮጵያ! ውርደት ለሻዕቢያ ባንዴራ አውለብላቢዎች!
አመሰግናለሁ
የፈረንጆች ዓመት ለምታከብሩ ዜጎች መልካም አዲስ አመት ያድርግላችሁ!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ)