Sunday, September 4, 2016

ኢትዮጵያዊያኖች ‘በዘረኛነት ባሕር እየዋኙ ነው’! ይህ እንዴት ሊከሰት ቻለ? ጌታቸው ረዳ (የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) Editor Ethiopian Semay (ክፍል ፩)



ኢትዮጵያዊያኖች ‘በዘረኛነት ባሕር እየዋኙ ነው’! ይህ እንዴት ሊከሰት ቻለ?
ጌታቸው ረዳ (የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) Editor Ethiopian Semay
(ክፍል )
Getachew Reda Editor Ethio Semay
ለበርካታ አመታት በእርግጠኛነት ለ25 አመት ኦነጎችና ወያኔዎች የዘረጉት የጎሳ እና የጥላቻ ፖለቲካ ውጤት አሁን በመላ አገራችን የምናየው አሳፋሪ የዘረኛነት ባሕሪ እና እርምጃ ሥራውን እየሰራ ነው። ጥላቻ በርትቷል። “ቡሀሉም ወገን” ዘረኞች ከመቸውም በባሰ መልኩ እየጎሉ፤ እየተራቡ መጥተዋል። ይህ ክስተት አመዛኙ  እውጭ አገር ባሉት ኢትዮጵያዊያን በተደረገ ቀጣይ የጥላቻ ቅስቀሳ ሲሆን ውጤቱ አገሪቷን አዳርሷል። ጎንደር ውስጥ በፉከራ እና በቀረርቶ “ትግሬ የዛ የመቀሌ የአምበጣ ቆርጣሚ ልጅ” እየተባለ ይህም ሕጋዊ ሆኖ በዩቱብ እና በየተቃዋሚ ሚዲያዎች በይፋ ተለጥፎ እያየን ነው። ትግራይ ውስጥም የትግሬ ደናቁርት ዘፋኞች በአማራው መሬት በወልቃይት መሬት ቆመው በትዕቢት ተወጥረው አማራውን ‘እናሳያቸዋለን’……..፤ እያሉ ሲፎክሩ፤ አምስተርዳም አውሮጳ ውስጥም “ሃምሳ ቢወለድ ሃመሳ ነው ጉዱ ትግሬ አንድ በቃል፤ ይደቁሳል ክንዱ” እየተባለ ሌለውን በሴትነትና በዝቅተኛ ደካመነት የሚመድብ በጣም ፋሽታዊ ትምክሕት የተሞላበት እብሪት በሰለጠነ ዓለም ውስጥ ሆነው የሚጨፍሩ ትግሬዎችና ዘፋኞቻቻው ለማየት በዩቱብ ተዘርግቶ እያየን ነው።

ይህ የደናቁርት ቅስቀሳ ከምንም የሌሉበት ሰላማዊ የዋሃን ዜጎችን ሊያስጠቃ አስቸሏል። ። ታናሽ ወንድሜ ትግሬ በመሆኑ ብቻ አሁን ንቅስቃሴ በተደረገባቸው የአማራ አካባቢዎች  ‘በሞቦች/ዱርየዎች’ ኩፉኛ ተደብድቦ የአልጋ ቁራኛ ሆኗል። አልታጠቀም ምንም አላለም፤ መንገድ ሲራመድ አገኙት፤ ደበደቡት። ታላቅ ወንድሙ ‘ጌታቸው ረዳ’ እዚህ ስለ አማራ መብት ይታገላል፤ አማራዎቹ  ደግሞ ትግሬ ሰለሆነ ደበደቡት። ዜናው እንዳልሰማው ተብሎ ከቤተሰብ በሚስጢር ታፈኖ ስለቆየ፤ የተነገረኝ አሁን ገና ሲያጋግም ነው። ወንድሜ ከሚኖርበት ከተማ ወደ ትግራይ እንዲለቅ መክሬዋለሁ። የወያኔ ፖለቲካ ይህንን እልቂት ንደሚያስከትል ስለማውቅ ነው ለረዢም አመታት ወያኔን አምርሬ የታገልኩት ምክንያት ይህ እንዳይከሰት ነው። ምን እየመጣ እንደሆነ አመላካች ስለሆነ፤ ሁሉም የጥላቻ ዱርየዎች በሕግ እንዲከሰሱ ጥሬየን አቀርባለሁ። በየቱብ ላይ ፎቶአቸው/ቪዲዮአቸው ያለ ስጋት ተከታታይ የጥላቻ ቅስቀሳ ሲቀሰቅሱ እያየናቸው የተወሰደባቸው የሕግ እርምጃ የለም ነው። 

የሕግ ባለሞያዎችና የሲቪክ ማሕበራት በሰለጠ አገር ሆነው ይህን ኢንተርሃሙዌ ቅስሰቃ የሚያካሂዱ ዱርየዎች እንዴት ሊያቆሙዋቸው አልፈለጉም? የጥላቻ መንፈስ በመላ አገሪቱ ተዳርሷል። ኦሮሞችን፤አማራዎችን፤ትግሬዎችን ያካተተ ነው። አብሶም ተጠያቂ የማደርጋቸው እዚህ ውጭ አገር የሚኖሩ ከብትሩ የራቁ በምቾት የሚኖሩ ‘የፓልቶክ እና የዩቱብ ኢንተርሃሙዌ ቡድኖችና ግለሰቦች’ ለጥለቻ ዘመቻው ቀዳሚ ቀስቃሾች ናቸው ። ባጠቃላይ በዚህ ክስተት የተጠቃለሉ ዘረኞች ወደ አገር ቢገቡ አገራችን ወደ ሩዋንዳ የግድያ መስክ ስለሚለውጣት፤ እዚህ ባሉበት  አለም ቢቆዩ እመኛለሁ።


‘ፓልቶክ’ እና ‘ዩቱብ’ የ ኢንተርሃሙዌ ቡድች እና ግለሰቦች መጨፈሪያ ጫካዎች እና ሜዳዎች ሆነዋል። ባብዛኛው የደነቆረ ማሕበረሰብ የሚሰዳደብበት ብቻ ሳይሆን፤ ዘረኝነት እና የሃይማኖት ጥላቻ የሚሰብኩ ሃይማኖት ተከታዮች፤ በግልጽ ተቀባይነት አግኝቶ የተስፈፋበት እና የሚሰበክበት መድረክ ሆኗል። በኢትዮጵያ ውስጥ እየታየ ያለው ለውጥ በነዚህ ዘረኞች ፈሩን እየሳተ ሄዷል። አሁን የተነሳው ለውጡም ባጭር እንደሚቀጨውና መልኩንም እንደሚያስቀይረው አልጠራጠርም።

ስጋቴም እዛው ላይ ነው። የናዚ ሚዲያዎች እጅግ ተንሰራፍተዋል። በ ‘ዩቱብ’ የሚለቀቁ ዘረኛ ቅስቀሳዎች የሕግ ባለሞያዎች አይተው እንደላዩ ዝም ብለዋል። እነሱ ብቻ ሳይሆኑ የኦሮሞ ሕዝብ፤የአማራ ወይንም የትግሬ ሕዝብ እንጨፈጭፋቸዋለን እየተባለ ዘረኞች በሞርሟራ ምሰላቸው /ፎቶግራፎቻቸውን/ምስላቸውን በቪዲዮ’ ቀርጸው በዩቱብ ለጥፈው በግልጽ ሲቀሰቅሱ “የሕግ ባለሞያተኞች ብቻ ሳይሆኑ በቸልተኛነት የሚመለከትዋቸው፤ እንጨፈጭፋችሗለን የሚባልላቸው የጎሳ አባላትና ማህበሮቻቸውም ሰምተው እንዳልሰሙ በቸልተኛነት ያሳልፉዋቸዋል።
እዚህ አውጭ አገር ሕግ በተንሰራፋበት የሕግ ባለሞያ እና የሲቪል ማሕበራት በተመሰረቱባቸው አገሮች ለግድያ/ለጭፍጨፋ የታጩ ማሕበረሰቦች፤ ማሕበሮቻቸውን አጠናክረው ተጠያቂዎቹን ለሕግ ማቅረብ ቀርቶ፤ የሚለጠፉት እጅግ የሩዋንዳ ዓይነት በጎሰኛነት የተለከፉ በሽተኞች የሚያሰራጩትን ቪዲዮ አብየቱታቸውን ወደ ‘ዩ ቱብ  እና ፓልቶክ ክፍል አስተዳደሮች እና ተቋማት’ ክስ መስርተው ከ ‘የ ቱብ’ እና ፓልቶክ ድረገጻቸው እንዲሰረዙ ማድረግ አልቻሉም። ይህቺኛዋ ቀላልዋ ነገር እንኳ ማድረግ አልቻሉም።
 
እነዚህ በሽተኞች ናቸው፤አልተማሩም፤ ጀሮ አለመስጠት ነው፤ እያሉ የሚሰብኩ ግብዝ ምሁራኖች አጋጥመውኛል። ‘የሩዋንዳ ዱርየዎች’ በቸልተኛነት በመታየታቸው ሲጀምር በተደራጀ መልኩ የጥላቻ ራዲዮኖች ማስቆም ስላልተሞከረ፤ ወደ ከፋ እልቂት አምርቶ አንደነበር እናስታውሳለን። አሁን እየተከሰተ ያለው ትግል አቅጠጫውን ቢስት ተጠያቂዎቹ እነዚህ የሕሊና በሽተኞች ሳይሆኑ ተጠያቂዎቹ የሕግ ባለሞያዎች እና የፖለቲካና የሲቪክ ማሕበራት መሪዎች እና ምሁራኖች ናቸው።በዚህ መልክ ቢቀጥል፤ አንድ አገር ለማየት እጅግ አስቸጋሪ ሊሆን ነው። ካአሁን በፊት በተለያዩ ጽሁፎቼ እንደገለጽኩት ለ25 አመት የተካሄደው  “የሳብ ቨርሲቭ” / አገርን/አንድነትን ለማናጋት የሚደርግ ያስተሳሰብ/ የህሊና አጠባ/ እውን ሆኖ መምጣቱ ግልጽ ነው።

ለዚህ ደግሞ ፖለቲከኞችና ምሁራን፤ ለዚህ ሚና ከፍተኛ ሚና አድርገዋል። ምሁራኖች “በአየር ላይ የለቀቁ አለም አቀፍ ሚዲያዎች “ለፓልቶክ እና ለዩቱብ ኢንተርሃምዌ ዱርየዎች” ለቅቀዋቸዋል። አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ አብዛኛዎቹ ምሁራኖች ቃለመጠይቅ የሚያደርጓቸው ጎሰኛነት በግልጽ በሚለፈፍባቸው፤ ቁጥጥር ባማይደረግባቸው ፓልቶክ ክፍሎች ውስጥ እየተጋበዙ ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ሃሳብ እንዲሰጡ የሚደረገው በእነዚህ የኢንተርሃሙዌ የፓልቶክ ክፍሎች ውስጥ ነው።

ወጣም ወረደም እንደ እሳት እየተቀጣጠለ ያለው የጥላቻ አየር፤ ግምባር ቀደም ተጠያቂዎች ቀድም ብዬ የጠቀስኳቸው ሁለት ቡድኖች ማለትም ‘ወያኔ እና ኦነጎች እንዲሁም ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ እንዲሰብኩን በየፓልቶኩ እና በድረገጾች ቦታ ተሰጥቶአቸው በግንቦት 7 ደጋፊዎች እና አስተናጋጆች በኩል ተፈቅዶላቸው የተሰገሰጉ ‘ጸረ ትግሬ’ የሻዕቢያ አለቅላቂ ኤርትራኖች እንደሆኑ ላሰምርበት እወዳለሁ። እኔ እንደ ትግሬነቴ ስለ አማራ ሕዝብ ብሶት እያስተጋባሁ ዕድሜየ ሙሉ በግምባር ቀደም የቆምኩት ሰው በመሆኔ እንጂ ኢትዮጵያዊ በመሆኔ ወይንም ትግሬ ወይንም አማራ፤ሶማሌ… በመሆኔ አይደለም። ሰው በመሁኔ ብቻ ነው። 

ስለ አማራዎች መብት ስከራከር የትግሬ ሕዝብ እንዲዘለፍ ወይንም እንዲጨፈጨፍ ብየ አይደለም። በዚህ ላይ መተማመን ይኖርብናል። አንድ ጎሳ ለይቶ ሌላውን ጎሳ የመጨፍጨፍ፤የመዝለፍ ፖለቲካ ከተራመደ፤ በጣም በቅርብ የምንቀያየም ይመስለኛል። የግንቦት 7 ኤፍሬም ማዴቦ አማውን ‘ነፍጠኛ” እያለ ኤርትራኖች ጋር ሆኖ አማራውን ሲዘልፍ እስካሁን ድረስ ከሰውየው ራስ ልወርድ ያልቻለኩበት ምከንያት አማራ ስለሆንኩ ሳይሆን ‘ሰው’ በመሆኔ የተሰማኝን በቃወም ነው። የትግሬ እናቶች ሸርሙጦች፤ ቅማላሞች፤ አምበጣ በሊታዎች፤ እየተባሉ በየ ዩቱብ እና ፓልቶኩ ሲሰደቡም ትግሬ በመሆኔ ሳይሆን እንደ ሰው ሰው በመሆኔ ነው፤ የምቃወመው። ይህ መቀጠል የለበትም! እኔ ስለ ሕዝብ ስቆም፤ እኔ ስለ አማራ የቆምኩት የገዛ ወንድሜ ትግሬ ስለሆነ በጥላቻ የተነሱ ዕውራን እንዲደበደብ አልነበርም ። እዚህ ላይ የአማራ ሕበረተሰብ ወጣቶች የኔን ጽሑፍ ማንበብ ይጠበቅባችል። ከብዙ አመታት በፊት ትዝ ይለኛል፤ አንድ ቡና ቤት ውስጥ ካንድ ወዳጄ ጋር ለመዝናናት ጋብዞኝ ስገባ የትግሬ ምልክት ስላለኝ በጥላቻ የተመለከቱኝ ሰዎች አጋጥመውኛል። ይህ ከፍተኛ ችግር ውስጥ  ይከተናል። መደጋገፍም የሚያሳጣ ይመስለኛል።

የአማራ ምሁራን እና ወጣቶች ወዴት እየገሰግስን ንደሆነ ማስተዋል እና ሉጓም እንዲደረግለት ከፍተኛ ሃላፊነት አለባችሁ። ይህ ስል ትግሬዎችም ኦሮሞዎችም፤ በየጎሳችሁ ያሉት የጥላቻ ዱሩየዎች ማስወገድ ይጠበቅባችሗል። በየፓልቶክ እና በየ ዩቱብ በቸልተኛነት የምታይዋቸው ዱርየዎች ሕዝብን እና አገርን ስለሚያናጉ፤ በጠቀናጀ መልኩ፤ በጉልሕ የተለጠፉ የጥላቻ ቅስቀሳዎች  ወደ ሕግ እንዲቀርቡ ማድረግም ይጠበቅባችሗል። በየ ማሕበራቱ የማብባቸው “ፕሬስ ርሊዝ” የማሕበር ውሳኔዎች አልኩኝ ለማለት ካልሆነ ምንም የሚረቡ አይደሉም። ከዚያ ይልቅ በየፓልቶክ እና ዩ ቱብ የተለጠፉት እና የጥላቻ አየር የሚነዙ ግለሰቦች ለቅማችሁ ወደ ሕግ እንድታቀርቡ ብታደርጉ፤ትግሉ ፈር ይይዛል፤ የሕዝብ ሰላምና መረዳዳት ሊሰፍን ይችላል። በተለይ ትግሉ እቅጣጫውን አይሰትም። ይህ ምክር አበክራችሁ አኑት።


የሽገግር መንግሥት መሥርተናል ብላችሁ ሥም ዝርዝር ከማውጣት ይልቅ፤ የሽግር መንግሥት እንዳይመሰረት እንቅፋት ሊሆን የሚችለውን አገር ለማናጋት እየተሰራ ያለው የጥላቻ ኢንተርሃሙዌ ግለሰቦች እና ቡድኖች ተሰባስባችሁ የሕግ ባለሞያዎች አሰባስባችሁ ክስ መስርታችሁ በሕግ አንዲጠየቁ ብታደርጉ የሚፈለገው ግብ ይገኛል።ዞሮ፤ ዞሮ ሕዝቡ ለዚህ ደረጃ መዳረጉ ከላይ የጠቀስኳቸው እነዚህ ሁለት (ኦነግ እና ወያኔ) ሃይላት ለ25 አመት (ከዚያም በላይ) ከፍተኛ አፍራሽ እና አናካሽ የጥላቻ ሕሊና አጠባ አስፋፍተዋልና ሕዝቡን ለዚህ አስከፊ የባሕሪ ለውጥ ከፍተኛውን ሚና ተጫውተዋል። ስለሆነም ሕዝቡ የተማረውን እና የተነገረውን፤ የተቀሰቀሰበትን ትምህርት እና ባሕሪ ነው እያንጸባረቀ ያለው። በዚህ ለዛሬ በሰፊው እንመለከታለን።

በነገራችን ላይ፤ ለዛሬ ልተችበት  ያቀድኩት ርዕስ የነበረው ሌላ ርዕስ ነበር። ይኼውም ስያትል ከተማ በግንቦት 7 ዘፋኙ/አርቲሰት/ ፋሲል ደሞዝ የታጀበበት እና የመሳሰሉት እንገዶች  የተካሄደው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ማሕበር “አስራት ወልደየስን” ሳይሆን “የጎሳ ፌደራሊዘም’” /ኤትኒክ ፌደራሊዝም” እንዲያብብ የታገለ ““No single region should be allowed to trespass.” የሚለውን የወያኔ እና የኦነግ ‘አፓርታይድ ሕገመንግስትን’  የደገፈ፤ አማራን/ኒሊክን የሚወንጅል በቀለ ገርባ፤ "ጀግና" ተብሎ፤  የበቀለ ገርባ ፎቶ የታተመበት ከናቲራ እና ምስል የጀግንነት ተምሳሌ ተወስዶ እኩል ከሰንደቃላማችን በራፍ አዳራሽ መግቢያው ላይ በገንዘብ ሲሸጥ፤ ጀግናው ‘ሐኪም ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን” ያገለለ/የረሳ/ አስገራሚ ስብሰብ ኢትዮ-ሚዲያ ስለ ተለጠፈው የስበሰባው ዘገባ በየቁርጥ ቀን ወዳጄ በደራሲ በአቶ አማረ ብሻው ተጽፎ ያነበብኩትን ነበር ላቀርብ ያቀድኩት። ሆኖም  ያንን  በይደር ብየዋለሁ እና ሌላ ቀን ጊዜ ሲፈቀድ ትችቴን አቀርባለሁ። 

በግልጽ ልነግራችሁ የምፈልገው፤ አስራት ባብዛኛው ኢትዮጵያዊ እንዲረሳ ሆን ተብሎ ተሰርቶበታል። የዘመናችን አርበኛ ተብሎ በእነ የነፃነት ራዲዮ አዘጋጅ (አቶ አለም ፈቃደ) የሚጠራው የዘመናችን አርበኛ አስራት ሳይሆን ‘አንዳርጋቸው ጽጌ’ ነው፤ ለሌሎቹ ደግሞ የዘመኑ ጀግናቸው ብርሃኑ ነጋ (ለአሜሪካኖቹም! ጭምር) ነው…….. ዛሬ ደግሞ የሲያትል የጎንድር ማሕበር የታየው፤ ጎሳቸውን ከአገር በፊት የሚያስቀድሙትን ‘የኦሮሞ ፈረሰት/ የጀግኖች ተምሳሌት እነ “በቀለ ገርባ እና እነ ኦልባና ለሊሳ” ናቸው። 

ይህ ካርታ/መልክዓ ምድር/ የምታዩት እነ በቀለ ገርባ እና እነ ኦልባና ለሊሳ አበክረው የተቀበሉት እና ለወደፊቱም እንዲጸና እየታገሉለት ያሉት የኦነግ እና ወያኔ የአፓርታይድ ፌደራልዝም ካርታ ነው።
The illegal map designed by Apartheid Ethiopian Government map

ስያትል ውስጥ  ንዲህ ያሉ ክስተቶች ማየት ይህ አዲስ ክስተት አይደለም። ክስተቱ በፖለቲከኞች ሳይወሰን፤ የውሸት አርበኞች ወደ ላይ ከፍ ብለው እንዲታዩ የማድረግ የሕሊና አጠባው በፖለቲከኞቹ ብቻ ሳይወሰን በአዝማሪዎችም የተንሰራፋ ነው። የግንቦት 7 ዘፋኞች ጎንደሬዎቹ እነፋሲል ደሞዝ እና ሻምበል በላይነህ ስለ እነ ብርሃኑ ነጋ ጎሩሮአቸው እስኪሰነጠቅ ድረስ ቢጮኹም፤ “ትግሉን የሎኮሶው” ወልቃይት አማራ ሳይሆን “ኦሮሞ ነው” ቢሉም፤ እነ ‘ዶክተር ዜሮ’፤ እነ ‘ሌንጮ ለታ’  ሲያትል ውስጥ “ኦነግ የመገንጠል ጥያቄ አንሰቶ አያውቅም’ ሲሉ በደራ ጭብጨባ ‘የእውነት እውነት’ ተብሎ ሲንጨበጨብላቸው፤  አማራን ከጨፈጨፈ የወንጀለኛው ኦነግ ባንዴራ ካልተውለበለበች እና የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ እኩል ከበሬታ ተሰጥቷቸው በተዘጋጀው ሕዝባዊ ስብሰባ የኦነግ ካልተውለበለበ ኢትዮጵያ ሰንደቅም አይውለበልብም በሚል ሲያትሎች “ሁለቱም እንዳይውለበለቡ ውሳኔ ተላልፎ” እቅዱን እውን ያደረጉ የስያትል ፖለቲኸኞች አስገራሚ ዜና በሰማንበት ጀሮ፤ የዛሬው የስያትል የጎንደር ማሕበር ስብሰባ ‘አስራትን፤ ታየ ወልደሰማዕትን’ መርሳት፤ በቀለ ገርባንና እነ ኦልባና ለሊሳን ማቆላጰስ ለወደፊቱ ገና ‘ስያትል’ ብዙ ትዕይነት ታሳየናለች። ትዕይነቱ ይቀጥላል። 

ታሪኩን እንደገና ልድገምላችሁ! በቅርቡ የጎንደር አብየተኞች በየአደባባዩ የወያኔን ባንዴራ  እያወረዱ የኢትዮጵያን ሰንደቃለማ በምትኩ ሲሰቅሉ ታዝበናል! አይደለም እንዴ? ስያትሎች ግን ከኦነጎች ጊዜያ እፍ እፍ ፍቅር ይዞአቸው የኦነግ ባንዴራ ካልተሰቀለ የኢትዮጵያም አይሰቀለም በሚል ተስማምተው ካሁን በፊት፤ አሰፋሪ ታሪክ ማስመዝገባቸው ስያትል ያሉት አገር ወዳድ ተብየዎቹ አገር ውስጥ ካለው ወጣቶች ላገራቸው ሰንደቃላማ ያለቻወን ክብር ለስያትሎች እና ለተቀሩት የዲያስፖራ ተቃዋዎች አስተማሪ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ። 

አሳዛኙ ነገር፤ ፖለቲካኞች እና ማሕበራት እውነተኛ ሰንደቃላማ እና እውነተኞች እና ጅግኖችን መለየት አቅቶአቸዋል። በዚህ ላይ ሌላ ቀን እስክመስበት ዛሬ ዘረኝነትን አፍጥጦ ወደ መጣብን ዓይኑ ምክንያቶቹና መነሻዎቹ እንዲሁም የአገራችን የሕሊና ጥንካሬ እና ድክምት፤ በምን ምክንያት አሁን ወደ ደረሰበት ደረጃ ሊደርስ እንደቻለና አብሮነታችን እንዴት ሊሸረሸር እንደቻለ፤ እንዲሁም ተገንጣይ እና የጥላቻ ምንጮች የሆኑ፤ የኦሮሞ፤ የሶማሊ፤የሲዳማ አርነት ቡድኖች ጹሑፎችና አላማ  በየድረገፆቻችን ማስተናገድ ሳይበቃ፤ የአማራ መንግሥት ለመመስረት ነው ዓላማችን  ብሎ ለሚነሳ አዲስ ቡድን ጭምር፤ ሚዲያዎች አገርን ለማፍረስ ለተነሳና ለተነሱ ቡድን/ቡድኖች ጭምር መድረክ ፈቅደዋል። ይህ ለምን ሊሰከሰት ቻለ? 

ሚዲያዎችን የሚያስታነግዱ ሰዎች እራሳቸው የሕሊና አጣባው ዘመቻ ሰለባዎች ናቸው? መልሱም አዎ ናቸው፤ ነው። ጥያቄው ለመመለስ፤ እነሱም በማሕበሩ ውስጥ የተካተቱ ስለሆኑ ባጠቃላይ ማሕበረሰብ እንዴት እንደሚፈርስና እንደሚለወጥ ደረጃዎቹን፤ እንድትመረምሯቸው በጥልቀት እንመልከት። አሁን ላለው አስፈሪ አገርን የማፍረስ ዘመቻ በየሰው ሕሊና እንዴት ተቀረጸ? አንድ ዩሪ የተባለ የሶቭየት ሕብርት የስነ አእምሮ እና የስለላ ሊቅ እንዲህ ይላል፦ 

አንተነትህ የሚወስደው ቅርጽ አንተ በምትመገበው ምግብ የሚሰጥህ የአከላት ቅርጽ ሲሆን፤ ሕሊናህም የሚቀረጸው “ሆን ተብሎ” ያለ አማራጭ ሌት ተቀን  ወደ ኣእምሮህ “በሚቀዳ” የቴሌቪዥን መረጃዎችን ነው።”   ይላል (ትርጉም የራሴ)። በግልጽ ንደምንከታተለው፤ በየ ዩቱብ እና ፓልቶክ እየተዘረጋ ያለው በጣም አራዊታዊ የሆነ፤ “የኢትዮጵያዊያን ኢንተረሃሙዌ ዱርየዎች ሚዲያ” ቅስቀሳ ወጣቱን ቀስ በቀስ እየበከለው አስተሳቡንም እየቀረጸው መጥቷል። ስለሆነም ለምን እንዲህ ባደባባይ ሚዲያ ዓይኑን አፍጥጦ ተከሰተ? …….  ይቀጥላል………… ክፍል 2 በቅርቡ ይለጠፋል። Ethiopian Semay getachre@aol.com