Sunday, April 23, 2023

ትግራይ ውስጥ የእነ ታደሰ ወረደ ልጃገረዶችን የመድፈር አዲስ ዜና ስትሰማ በተደፈሩ የኢትዮጵያ ልጃገረዶች ላይ ስታሾፍ የነበረቺው ነፃነት ብሌን ዛሬ ምን ትል ይሆን! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 4/23/23

 

ትግራይ ውስጥ የእነ ታደሰ ወረደ ልጃገረዶችን የመድፈር አዲስ ዜና ስትሰማ በተደፈሩ የኢትዮጵያ  ልጃገረዶች ላይ ስታሾፍ የነበረቺው ነፃነት ብሌን ዛሬ ምን ትል ይሆን!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

4/23/23

    

ሰሞኑን በየትዊተር እና ፌሰቡክ ላይ በቅጽል ስሙ Ztseat Saveadna Ananya ሕጋዊ ስሙ የሕክምና ዶ/ር የሆነው ዶ/ር ጎይተኦም አናንያ በስደት ከሚኖርበት አገር (እኔ እስከማውቀው ድረስ ኬኒያ ከዚያም ሩዋንዳ የሚኖር ይመስለኛል) Ztseat Saveadna Ananya በሚለው ፌስቡኩ ላይ “የትግራይ ሕዝብ ጉድህን ስማ!” በሚል ርዕስ 250 የ TDF ሴት ተዋጊ ልጃገረዶች በወያኔ TDF ጀኔራሎች እና የፖለቲካ ሃላፊዎች ተደፍረው ምስጢሩ እንዳይወጣ በዩኒቨርሲቲ እና መለስ ዜናዊ አካዳሚ በሚባሉ አዳራሾች ውስጥ የቁም እስር “በር ተዘግቶባቸው” እንዳሉ ያጋለጠው ምስጢር የሰማችሁ ይመስለኛል።

በነገራችን ላይ ዶ/ር ጎይተኦም አናንያ ማለት እጅግ ክፉ ፋሺሰትነት ተጠናውቶት የነበረ ዛሬ ከዚያ ዕብደቱ ትንሽ ቀዝቀዝ ያለ ይመስላል Ztseat Saveadna ማለት ፡<< ጎጃም ከሚለማ ሲናይ በረሃ ቢለማ ምርጫየ ነው>> ብሎ የተናገረ ጸረ አማራ የትግራይ ጠባብ ብሔረተኛ ነው። ሆኖም ዛሬ እንደተከታተልኩት ካሁን በፊት እኔ ብዙ ጊዜ ለትግሬ አዝማሪዎች ከዚያ ዕብደታቸው እንዲቆጠቡ ስመክር እንደነበረው ዛሬ ዶ/ር ጎይተኦም በተመሳሳይ መስመር ዘፋኖቹን ሲመክር ስለተገነዘብኩ በዚህ መንገድ ከቀጠለ ከዚያ ባሕሪው ትንሽ እየተሻሻለ የመጣ ይመስለኛልና በአዲሱ ባሕሪው እንዲቀጥልበትም በርታበት እላለሁ።

የሴቶች መደፈር በሚመለከት የወያኔዎች የሴት መድፈር ታሪክ በ17 አመት የበረሃ ታሪካቸው እነ ስዩም መስፍን እና እነ ስብሓት እንዲሁም እነ አባይ ወዘተ… ሴቶችን እያማገጡ አንዳንዶቹም ምስጢር እንዳያወጡ እንዲገደሉ እያደረጉ እንደነበር እነ ገብረመድህን አርአያ እንዲሁም እነ አስገደ ገብረስላሴ ይህንን ባሕሪያቸው በሚመለከት ጽፈውታል። እንደምታስታውሱት ወያኔዎች በፈረንጅ 2017 ዓ.ም የዋልድባ ሴት መነኮሳት እያስገደዱ እንደደፈርዋቸው ኢሳት ያደረገላቸው ቃለ መጠይቅ መነኮሳቱ መስክረዋል።

አዲስ የሚያደርገው ግን ይህ የጎይተኦም አዲስ ዘገባ ስመለከት ካሁን በፊት በፈረንጅ 2022 የለጠፍኩት አስገራሚ የሴቶች መደፈርን የሚያሾፉ የወያኔ ሴት ጀሌዎችን አስታወሰኝና በድጋሚ ላስታውሳችሁ ብየ ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሜ እንደገና ያላለነባበችሁት ብትኖሩ ይህንን አንብቡ እና “ወያኔነት” ሰዎችን ምን ያህል አራዊታዊ የጭካኔ ባሕሪ እንዲያድርባቸው እንዳደረገ ከሰብአዊነት ስሜት ማዕቀብ ስሜት ውጭ ርቀው አረመኔ እንዲሆኑ እንዴት እንደቀጸረጻቸው ማስረጃ ይሆናልና ይህንን ካሁን በፊት የለጠፍኩትን አስገራሚ ክስተት አንብቡ እነሆ።

ሴት በሴት የመጨከን የወያኔ አራዊታዊ መስሕብ

ጌታቸው ረዳ

2022 January 7

“ነጻነት ብሌን” ትባላለች።

 

<<በእስልምና የሴት ልጅ እግርዋን አነባብራ መቀመጥ ነውር ነው። ቀሽም ተዋናዮች>>። ትላለች።

Netsanet Blen Lives in Philadelphia, Pennsylvania from Enticho, Tigray, Ethiopia) January 4, 2022

 

በተደፈረቺው ህጻን ላይ እንዲህ ያሾፈች ሴት “ነጻነት ብሌን” ትባላለች። ፌስቡክዋ Netsanet Blen ይባላል። በዚህ በፌስቡክዋ የለጠፈቺው አስነዋሪ “ማሾፍ” የ14 ዕድሜ ያላት የእስልምና እምነት ተከታይ የሆነች ታዳጊ ልጃገረድ ፤ በወያኔ ተዋጊዎች መደፈርዋን በሰይፉ ፋንታሁን መድረክ ተጋብዛ በወያኔ ተዋጊዎች የደረሰባትን የጾታ ጥቃት ለሕዝብ በመግለጽዋ አሜሪካ ውስጥ በፊላደልፊያ በፐልሰልቬኒያ ከተማ ኗሪ የሆነች የወያኔ ተከታይ ወ/ሮ ነፃነት ብሌን “በእስልምና የሴት ልጅ እግርዋን አነባብራ መቀመጥ ነውር ነው። ቀሽም ተዋናዮች” በማለት በሴት ልጆች የሚደርስ አመጽን ስታጣጥል ማንበብ ይህች ሴት ምንኛ ዕብደት ውስጥ እንደደረሰች ስንታዘብ እጅግ አሳዛኝ ነው።>> የዚህ ዕብደት መነሻ ደግሞ የምትከተለው ድርጅትዋን ወያኔ በወቅቱ TDFን ከወንጀሉ ለመከላከል በሚል ከአደገኛ “የካልት” ባሕሪ በመነሳት እንደሆነ የለጠፍኩት ነበር። ወያኔዎችና ተከታዮቻቸው እስከዚህ ርቀት ድረስ ሊሄዱ እንደሚችሉ እና ይህ ጉድም አለ ለማለት ነው።

አመሰግናለሁ

 ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)