Wednesday, October 10, 2012

የሚበሉህን ጅቦች የመውደዱን አባዜ

There is a new article posted on Ethiopian Semay facebook under the title
ሃዋሳ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹመት ከወሰንሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ)You need to open the facebook posted below to the right on the audio-video section all the way to the bottom that showed Getachew Reda Ethiopiansemay face book.


\

\
ለአንባቢዎች ማሳሰቢያ(1የፖለቲካ ትንተና ለማንበብም ሆነ እዚህ ድረገፅ ውስጥ ተመርጠው የሚለጠፉት የቪዲዮ ማህደሮች ለመመልከት ስትመጡ በስፋት ስለሚተነተኑ “በቂ ጊዜ የለንም የምትሉ አመካኞች ንባቡን ከመጀመራችሁ በፊት ዝግጁነታችሁን አረጋግጡ።መልካም ንባብ። To read the page in wide range or bigger font, press the keyboard Ctrl with + sign (Ctrl and the + symbol sign at the same time)

(2)ሌላኛው ማሳሰቢያ፤ አውዲዮ ቪዲዮ ለምታዘጋ ሰዎች፤ድርጅቶች። እብአካችሁ፤ እባካችሁ የምትቀርጿቸው ቪዲዮ ዶክዩመንቶች ቀራጪው ወይንም ባለቤቱን ለማሳየት የምትጠቀሙባቸው የትሬድ ማርክ (መለያ) ጹሑፎችና ምልክቶቻችሁ ቅጥ ባጣ በትልቁ ማሃል ላይ ስለሚጻፉ የተናጋሪዎቹ ምስል/ፎቶ እየሸፈነ በጣም ስላስቸገረን ፎሮግራፍ ቀርጾ ለማውጣም ሆነ ለመመልከት አስጋሪ ሆኖ ስላገኘነው፤ “ስትጽፉ ምልክቶቻችሁ በትንሹ እጐኖ ላይ ወደ ታች ጫፍ በኩል ብታስቀምጧቸው ለተመልካች በጣም የተሻለ ጥራት አለው እላለሁ። ይህ ችግር በሁሉም የምናው ችግር ነውና ይታሰብበት። ታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ)





የሚበሉህን ጅቦች የመውደዱን አባዜ ጌታቸው ረዳ
(www.ethiopiansemay.blogspot.com) Email getachre@aol.com
እህል ሲበላሽ በሰበሰ ወይንም ነቀዘ አንለዋለን። እህልን የሚያነቅዘው ነቀዝ የተባለ ከእህሉ ጋር ተደባልቆ የሚኖር ተባይ ሊሆን ይችላል ወይንም የአየር ጠባይ ነው። ሕብረተሰብስብም ልክ እንደ እህል ይበሰብሳል? የነቅዛል? አዎ። ሕብረተሰብንስ የሚያነቅዘው ምንድነው? መጥፎ መሪ እና መጥፎ ሥርዓት። እነዚህም የሕብረተሰብ ተውሳኮች/ተባዮች ናቸው።
ዛሬ ያላንዳች መሸፋፈን ልክ ካሁን 16 ዓመት በፊት ይህ ሕብረተሰብ የተነበረከከ ፤ሽንፈት የተቀበለ ሕበረተሰብ ነው፡ ብዬ ስል ‘ሕብረተሰብ እየዘለፍክ ነው’ ተብዬ አንደተጨኾብኝ ሁሉ ዛሬም በድጋሚ እንድትጮኹብኝ ለመጋበዝ ነው። በግልጽ አማርኛ  በውጭ ያለውም ሆነ በውስጥ  ያለው ሕብረተሰባችን ከመበስበስ ባሻገር እርከኑን ተሻግሮ በእንግሊዞቹ እንደሚሉት “ራትን/ሮትን” (Rotten) ሆኗል። እኛ ትግሬዎች “እጋል” እንደምንለው። ውሃ ሲሸት “አጊሉ” አንለዋለን። ሳይንቀሳቀስ እንስራ ውስጥ የኖረ ውሃም ሆኖ ነፋስ እየመታውም የሚሸት የኩሬ ውሃ አጋጥሟችል? ውሃ የሚያሸተው ምነድነው? ብዙ፤ ብዙ ምክንያት አለው። ሕብረተሰብም እንዲሁ ይበሰብሳል። ሕብረተሰብ ሲበሰብስ አፍንጫን አይደለም የሚሰነፍጠው።  የታዛቢን ዓይንና ሕሊናን ያሸማቅቃል።    

ሕብረተሰብ መበስበሱን የምንፈትሽባቸው መንገዶች ልክ እንደ እንቁላል በሃይለኛ የብርሃን/የጸሃይ ጨረር ውስጥ እንደምንፈትሸው ሕብረተሰብም በእዛው የመፈተሻ ብርሃን ውስጥ ገብቶ ካልተፈተሸ መበስበሱ ተሎ አያስታውቅም። እናቶቻችን እንቁላል ሲገዙ “ማገሉን” (መበስበሱን/እርግዝና ይዞም እንደሆነ ‘ፕላዝማው/ውሃው’ የጫጩቱ አንግዴ ልጅ)አለማገሉን ለማወቅ እያንዳንዱ እንቁላል ወደ ዓይናቸው በማስጠጋት ወደ ሰማይ በማንቃረር ወደ ጸሐይዋ አቅጣጫ በማነጣጠር መሃል ያለው የውሃው ንጣት ወይንም ጥቁረት  በመመልከት ‘ብልሹ/የበሰበሰ’ አንቁላል ወይንም ‘ጤነኛ’ መሆኑን ያረጋግጣሉ። ወይንም ወደ ጆሮ አስጠግቶ አንቁላሉን በማነቃነቅ (ሼክ በማድረግ) ከውስጥ  ያለው ውሃ ካልተነቃነቀ ረግቷል እና የበሰበሰ ነው ማለት ነው።  እንደዛ ካላደረጉ እንቁላል ከላይ ንጣቱን ብቻ በማየት መበስበሱን አለመበስበሱን ማወቅ አይቻልም።የተበላሸ እንቁላል ሲሰብሩት በጣም ይገማል። ውሃም ሲገማ ለሰው ልጆች ለምግብነት አይፈለጉም። በዛው ትይዩ ሕብረተሰብ ሲነቅዝም ሂደቱና ባሕሪው በመለወጥ ራሱን ወደ ሞት ሂደት ያሸጋግራል። ራሱን ያበሰብሳል። ራሱን ያበሰበሰ ሕብረተሰብ ለመምራት እልክ አስጨራሽና አስተዋይ መሪ ይፈልጋል።
ሕብረተሰብ ሲበሰብስ ‘ተንቀሳቃሽ ግኡዝ’ ስለሚሆን ሲሰለብ አይታወቀውም። የበሰበሱ መሪዎች የበሰበሰውን ሕብረተሰብ ለመስለብ እንዲያመቻቸው ሕብረተሰቡን ማበስበስ አለባቸው። ያንን ካላደረጉ “የሚጫኝ አህያ አይሆንላቸውም”።ልክ ግምበኞች/የሕንጻ መሃንዲሶች አልፈርስም ብሎ ‘ነክሶ’ ጠንክሮ  የየዘ መሰረት “ውሃ” እያፈሰሱ፤ እንዲረጥብ እያለሳለሱ አንደሚያፈርሱት ጠንካራ መሰረት ጠንካራ ሕብረተሰብንም ለማበስበስ የተለያዩ ዘዴዎች በማስተዋወቅ አንደዋለሃ (ዋልካ) ተፍረክርኮ “ሊጥ ሆኖ  እስከሚታጠፍላቸው ድረስ” ሃይለኛ ስራ ይሰራሉ። የሚታጠፍ ነገር “ጥንካሬ ስለሌለው”  “ሃይል” ያጣል።የሚታጠፍ ሰው ሰብእናውና ሞራሉ ደካማ ስለሆነ የበታችነት ስሜት ተሰምቶት ልጠፍህ ለሚለው ክፍል ሁሉ በቀላሉ ይታጠፍለታል።ተስፋ የሚባል ትርጉም የገባው ከሆነም፤ ምህረቱና ተስፋው በዛው ክፍል ይጥላል።ያችን የተነጠቀውን ተስፋውና ሰብእናው ለማግኘት በራሱ መቆም ስላልቻለ ሰላቢዎች ወደ ጠመዘዙት ለመጠምዘዝ ምቹ ሆኖ ይገኛል።

ሕዝባችን በውጭም በውስጥም ይህ የመበስበስ በሕሪ ተጠናውቶታልና በራሱ የቀመ መሰረት የለውም።መሰረቱ የፈረሰ ሕብረተሰብ ስለሆነ ማንኛውም “ገምቢ እና ቤት አጣሪ” የጥበቡ ክረዲቢሊቲው (ንጣቱን/ኩዋሊቲው) ሳጣያጣራ “ልገንባህ/ልጠርህ” ለሚለው የፖለቲካ ግምበኛ ሁሉ በሚሰጠው የግምባታ ፕላን  “ፈቃደኛነቱን” ይገልጻል። እሺታ እንጂ መደራደርና መርምሮ መግባት ተስፋውን የሚያጨለምበትና የሚያራዝምበት ስለሚመስለው “የተሎ ተሎ ቤት’ ግምባታ ውስጥ ይገባል። የኢትዮጵያ ሕበረተሰብ (ምስኪኒ የገጠር ሰው ከውይይታችን ወደ ጎን አኑረን) አብዛኛው ከተማ ቀመስ ዜጋ 21 ዓመት ሙሉ በስብሷል።አሁንም እዛው በበሰበሰው ጎዳና ይርመጠመጣል። ለምን?ወያነ ትግራይ በባእዳን አጀንዳ እየታጀበ የሕዝባችን መሰረቶች የሆኑት “ድምበሮቻችን፤ወደቦቻችን፤ሰንደቃላመችን፤ባሕል፤ሃይማኖት፤ ብሄራዊ ቋንቋ፤ይሉኝታና ሉአላዊ ፍቅር”(ማሕበራዊ ተቋማት የሚባሉ)መሰረታቸው አነቃንቆ እንዲፍረከረኩ አድርጓል። የተማረው ግብዝና ያልተማረው ግብዝ ሁለቱም ክፍሎች “ኢትዮጵያን” የሚመለከቱበት  ዓይናቸው በቁስ (ማቴሪያል) ሸፍኖ፤ የምዕራቡን ዓለም ግብረገብ (ዌስተርን ማስ ካልቸር)ተከታይ እንዲሆን አድረጓቸዋል።

ኩፍኛ በመበስበስ ያለው የኢትዮጵያ ማሕብረተሰብ ወደ ፖለቲካ መድረክ የሚመጡ መሪዎቹ የጀርባ ማሕደራቸው የማጣራት እስፈላጊነት አስፈላጊ ሆኖ አላገኘውም። ምክንያቱም በመበስበስ (ዲካድነት) ሂደት ውስጥ ያለው ሕብረተሰብ የሚመሩት መሪዎቹ ነብስ በማጥፋት፤ ሃብት በማካበት፤መብት በመጋፋት፤የአገር ሉአላዊነትን በማራከስና በመክዳት፤ ግጭትና ጦርነት በማስፋፋት ስነ ምግባር ላይ የተሰማሩ መሪዎች መሆናቸውን እያወቀም ቢሆን “ሕብረተሰቡ” እነኚህን አጸያፊ ስነምግባሮች የፈጸሙ ሰዎች በሕግ ፊት ቀርበው ተጠይቀው ሲቀጡ ስላላየ ከነከሱት ጅቦችጋር አብሮ መኖር ለምዶታል።ከመልመዱ የተነሳ የመውደድ አባዜ የተጠናወተው ይመስላል።
ሓረር አካባቢ ማታ ማታ ሲመሽ ጅቦች የሚቀልቡ ፡አድቨንቸሪስቶች” (ጀብደኞች) አሉ። ይህ ጉደኛ ትዕይንት የወያኔ ዓይነት ጅቦች ዓይነት ታሪክ ይመሳሰልብኛል። ዛሬ ዛሬ ከመቸውም በበለጠ የጐብኚዎች መስህብ እየሆነ በካሜራ እየተቀረጸ መጥቷል። ቀላቢውም ሆነ ተመልካቹ  የሳቱት ነገር ቢኖር ጅቦቹ የቀላቢውም ሆነ የተመልካቹ ህይወት “ቀሳፊዎች” እና ተቀናቃኞች መሆናቸው የመገንዘብ ሕሊናቸው “በጊዜያዊ የመጠጋጋት የጀብደኝነት እርካታ” ውስጥ ገብቶ ስለተማረከ፡ ከመጋቢያቸው እያሽካኩ በጓደኝነት ባሕሪ  የሚመገቡት “ጅቦች” ቀላቢ ሲያጡ “የገዛ ቀላቢያቸውን እንደሚበሉት ቀላቢዎቹ የተረዱት አይመስሉም።

ጅቦቹ ከቀላቢያቸው የሚፈልጉት ነገር ቢኖር ‘መመገብ’ ነው። ቀላቢዎቹ ከጅቦቹ የሚፈልጉት ነገር ደግሞ “መናከሳችሁን” አቁሙ ነው። የመጠጋጋቱ የጨዋታው ትርጉም ሲመረመር ከዚህ  ያለፈ አይሆንም። መጋቢዎቹ የዘነጉት ጉዳይ ሺ ሰንጋ ቢታረድላቸውም ልጆቻችንና ከብቶቻችንን መናከስና መብላታችሁን አቁሙ ስለተባሉ “ጅቦቹ” መናከሳቸውን ያቆማሉ ወይ?” ነው ጥያቄው።

የሁለቱ ፍጡራን ትካት (ኢንስቲንክት) የጭምትነት ባሕሪ የጎደላቸው ስለሆኑ “ነካሹም” “ተነካሹም” የተፈጥሮ ባሕሪያቸው እንደማይገጥም እያወቁ ሁለቱም እየተጠጋጉ እና “ፈራ ተባ” እያሉ በማያዛልቅ ጨዋታ ገብተው “የበይ እና የተበይ” የመገዳደል ጨዋታቸው እያሳመሩ ጅቦቹ ከጀብደኛ ቀላቢያቸው አፍ ጥርስ ተነክሶ የተንጠለጠለላቸው ስጋ “ጠጋ” ብለው በመንጠቅ ይጎርሳሉ። ይህ አስገራሚ የገዳይና የተገዳይ ጀብደኛ ጨዋታ በካሜራ ተቀርጾ ለዓለም ሕዝብ እየታየ ነው።የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ባሁኑ ሰዓት  ሕግ የማያከብር ቡድን ሥልጣን ላይ መኖሩን እያወቀ ሕብረተሱም አብሮ ሕግ አፍራሽ በመሆን የበሰበሰ እይታ ያለው ጎዳና በመጓዝ ድርድር ከማያውቅና ከሚበላው አራዊት ጋር ተጠጋግቶ የበይና የተበይ የጨዋታ ሕግጋት እያሳመረለት ለሚበላው አራዊት ሲያሞግስና ሲያለቅስለት እየታዘብን ነው ።
መለስ ዜናዊ ሲሞት በዓለም መድረክ ኢትዮጵያን ያስጠሩ እና ያኮሩ የስፖርት ባለሞያዎች ስቅስቅ ብለው ሲያለቅሱለት፤ካንደባታቸው የተናገሩት ፍሬ ነገር ሲመዘን አገራቸውን ወክለው በዓለም መድረክ የላቀ ውጤት ሲያስመዘግቡ ሲስሟት የነበረቺው ሰንደቃላማችን እና የሃይማኖታችን ምሰሶ የሆነቺው ቅድሰት ማርያም ምስል ከጉያቸው እያወጡ ሲሳለሙ ምድሪቱን ተንበርክከው የሰገዱላት፤ሃይማኖት፤ ምድር እና ሰንደቅ ላይ መለስ ዜናዊ በኮሚኒስታዊ የፋሺስት አጀንዳው የፈጸመው ሕገ ወጥ ሥራ ከሕግ አኳያ የመመልከት አቅማቸው ደካማ መሆኑን ያሳያል።

እነ ደራራቱ ወይንም መሰረት ደፋር ….የመሳሰሉ ሯጮች ሲሮጡ ሰንደቃላማ ይዞ አብሮ ልባቸው የሮጠው ውጭ አገር ያለው ኗሪ ግለሰቦቹን ስለሚያውቃቸው ሆኖ ሳይሆን “ሰንደቃላማ እና አገር” ያስከብራሉ በሚል ነበር። ወያኔ ያሰራው ሰማያዊ የካልት ኮከብ ያለበት ሰንደቃላማ ካልሆነ ነባሩ እና ሕጋዊው ለዘመናት የቆየ የተውለበለበ ባለ ሦስት ቀለም ሰንደቃላማ ማውለብለብ “ሕገ ወጥ” ነው ብሎ ላወጀው “ፋሺስት” መሪ ስቅስቅ ብለው ማልቀስ፤ የሕገ ወጥ  ቡድን ተባባሪ መሆን ነው።ሕብረተሰብ ሲበሰብስ ሕገ ወጥ ተግባሮችን ሕግ ነው ብሎ ይቀበላል። ማሰብ ያቆማል። የበሰበሰ ሕብረተሰብ ወንጀለኞች በዘረጉለት ሃዲድ ስለሚጓዝ “ሞራል ፕርንሲፕል” በመጣስ “ላገር ታማኝነትን” ያቆማል። ምልክት በሌለው ባጭበርባሪ ጎዳና የሚጓዝ ተጓዥ ለአደጋ እንደሚጋለጥ ሁሉ፤ይህ ሕብረተሰብ ለከፋ የሞራል መበስበስ ተጋልጧል።

አትሌቶቹ ባገኙት የተፈጥሮ መታደል ባካበቱት ንብረት መርቅነዋል። ሚድል ክላስ ከሚባለው “የበሰበሰው ክፍል” ውስጥ ታቅፈዋል እና ስንደቃላማ ከመሳም ወዲያ የሰንደቁ ትርጉምና ዓለማ በጥልቀት ስላለገባቸው “አገር ምን ማለት መሆኑን” ጉዳያቸው አይደለም። ልጆቻቸው በድቁስ ጨው የተነሰነሰ ምሳ በልተው ሆዳቸው ከሚጮህ የድሃ ልጆች ከሚማሩበት ት/ቤት አስወጥተው “አይስክሪም” እንደመጫወቻ በሚወራወሩበት “ከወያኔ የሞጃ ልጆች” ት/ቤት ነው እያሰተማርዋቸው ያሉት። የመለስ ዜናዊ እና የነኚህ አሳፋሪ አትሌቶች ልጆች ት/ቤት እና አኗኗር የተመጣጠነ ነውና ፈረንጆች “ተርም ኦይል” የሚሉት አዲስ ሕይወት ውስጥ ስለገቡ አስተሳሰባቸውም የተለየ “ካምፕ” ውስጥ በመግባቱ የመደብ አጋራቸው (ፔቲ ቡርዣ ክላስ) በሆነው መለስ ዜናዊ ሞት ልባቸው ተነክቷል። ዶላር ዶላር የሚሸተው መኖሪያ ግምባቸው በሽቶ የታወደ ሳሎናቸውና ያካበቱት ንብረት ሁሉ በራሳቸው ጥረት እና በሕዝቡ የሞራል ድጋፍ አበረታቺነት መሆኑን ዘንግተውት፤ መለስ ዜናዊ ያመነጨላቸው ውጤት/ አኮምፕሊሽመንት ነው ብለው በበሰበሰው አስተሳሰባቸው ማመን ጀምረዋልና ተንሰቅስቀው አልቅሰውለታል።

ካነበብኩት አንድ መጽሐፍ ውስጥ ከ1500 አመት በፊት የሮም መሪዎች በመበስበሳቸው ለታላቋ የሮም መንግሥት መበታተን ምክንያት እንደሆነ አንብቤአለሁ። የበሰበሱ መሪዎች አገር ሲመሩ የበሰበሰ ሕበረተሰብ ያፈራሉ። አገር ባይፈርስም በውስጧ የታቀፈው ሕብረተሰብ አቅፈውት ሲጓዙ የነበሩት ተቋማት (ሰትራክቸሮቹ) ስለሚፈርሱ የሕሊና መፍረስ ስለሚገጥመው ባስተሳሰቡ “መካን” እና “የበሰበሰ” ማሕበረሰብ ይሆናል ማለት ነው። ሕብረተሰብ አንዴ ከበሰበሰ “ሕግ፤ፍትሕ፤ሉአላዊነት” የሚባሉ የነፃነት ሃዲዶች ቦታ ትርጉም አይሰጡትም።

ስለሆነም ነው ባንዳንድ ስበሰባዎች ላይ ‘ፍትሕ’ ለሚጠይቅ ሰው በማናናቅ በዝቅተኛ ሚዛን የሚታየው። በሚገርም ሁኔታም ከሰብሰባ እንዲወጣ ግፊት ያደርጋሉ። ይህ ነጸብራቅ በቅርቡ ዋሺነግተን ዲሲ የኢሃፓ ወጣቶች እነ ገብሩ እና እነ ስየ፤መረራና ተመስገን የተገኙበት የመድረክ ስብሰባ ላይ “ስየ አብርሃ” ለመናገር ሲሞክር ወያኔዎች የገደሏቸው ፤የሰወሯቸው የኢሕአፓ አባሎች የት አንዳደረጓቸው ሁለቱ ወጣቶች ለብሰዋቸው በነበሩት ከናቴራዎች የሚታዩ የሰለባዎቹ ፎቶዎች እያሳዩ፤ ስለ እነሱ ጉዳይ ስየ አብራሃ  እንዲነግራቸው ሲጠይቁት፤ በጣም ከሚገርመው ነገር ተሰብሳቢው ( “የበሰበሰ በመሆኑ” (ሁሉም ባይሆኑም) ለተሰወሩት ወገኖች ከማዘን ይልቅ ለስየ አብርሃ በመወገን “ብልግና በተሞላበት” ቃል “አስወቷጧቸው” የሚል ድምጽ ነበር የተሰማው። ስለ ጠየቁ? ለምን?

 Photo above Angry and reasonable wise Ethiopian asking  questions to TPLF's puppet Minister Mekonne Demeke in Atlanta meeting which forced the mind of the the TPLF puppets to look each other for lack of answer. 
ይሄ ጥያቄ ትዝ ይላችሗል? በቅርቡ አትላንታ ውስጥ የወያኔ ካድሬዎች መጥተው ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ስለ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ድምበር ጉዳይ ስለጠየቁ ብቻ “አንድ ምስኪን “የወያኔዎቹ ቦዲ ጋርድ” (አጋፋሪ) “አስወጣቸዋለሁ” ብሎ ነበር ለአለቆቹ የተናገረው። ደግነቱ ግን አለቆቹ ጥያቄውን አልወደዱትም ነበር እና ስብሰባው ቀጠለ። ተቃዋሚ ሚዲያዎች ግን ቪዲዮውን ሲለጥፉት የጠየቁት ትክክለኛ   ጥያቄ  “ለምን” ስለጠየቁ? ብሎው ነበር የጠየቁት። በመድረክ ስብሰባ ግን በአንጻሩ እነኚህ ወጣቶች እራሰቸው ባይቀመጡ ኖሮ ተገፍትረው ይወጡ ነበር ማለት ነው። አስወጣው! ማለት ምን ማለት ነው? ለምን? ስለጠየቁ? ወያኔዎች ሲመጡ በየአዳራሹ የምትጮኹ ተቃዋሚዎች “ተቀመጡ” እና “አዳምጡን” ከዚያ ጠይቁን ሲሏቸው አይደለም ወይ “መጀመሪያ የኛን ጥያቄ መልሱ” የምትሉት? የናንተ መሪዎች ሲመጡ እንዴት ያልሆናችሁትን ልትሆኑ ፈለጋችሁ? ለሚል ጠያቂ ምንድነው መልሳቸው? መበስበስ ማለት ሌላ እኰ አይደለም። የሕብረተሰብ ንቅዘት ማለት “የፍትሕ” ትርጉም አሳንሶ መመለክት ማለት እኮ ነው።
በጣም ሲዘረዘር ደግሞ ‘የፖለቲካ መበስበስ’ ታዛዥ ሰራዊት አደራጅቶ ሥልጣንን/ብረትን/ ተገን አድርጐ የሰው ህይወት መቀንጠስ/መግደል፤ አገርን ለአደጋ ማጋለጥ፤ የአገር ክብር እና ምስጢር ለጠላት አሳልፎ መስጠት፡ የመሳሰሉ ወንጀሎን መፈጸም ማለት ነው።ታዲያ እነ ስየ አብርሃ እነ ገብሩ በሥልጣን ጊዜያቸው የፈጸሙት እና ሲፈጸም የተመለከቷቸው ወንጀሎች ለሕዝብ መግለጽ የሞራልም የሕግም የዜጋነት ግዴታም ስላላቸው በዚህ ሚስጥራዊ (ሴክረቲቭ ደርጅት) ቡድን የተካሄዱት ሰብአዊም ሆኑ አገራዊ ወንጀሎች ለሕዝብ ማሳወቅ ግዴታቸው ነው። ለምንድነው ‘ ጠያቂውን አስወጡት የሚባለው? እርግጥ ለጠያቂዎች የተሰጣቸው የመጠየቅ ዕድል እኔ እንደታዘብኩት ሲያትል አዘጋጆች በበለጠ የዲሲ መድረክ አዘጋጂዎቹ የሚያስመሰግናቸው ቢሆንም አድማጩ ግን “አስወጡልን” የሚል በሽታ ለምን እየተናወጠው አይገባኝም። ለምንድነው አስወጣው’ የሚባለው? ሕዝብ የማወቅ መብት አለበት ሲባል፤ ድርጊቱ ሲፈጸም የነበሩ ወይንም የተመለከቱ ወይንም የፈጸሙ እና የተባበሩ ሰዎች የሚያወቁትን ሰነድ እና ታሪክ ለሕዘብ ማሳወቅ ግዴታቸው ነው።አናሰውቅም ካሉ ግን እነኚህ ሰዎች ሖን ብለው ምስጢርን በመሸሸግ የድርጅቱን የአድራጊዎች ማንነት በታሪክ እና በሕግ አንዳይታወቁ ደብቀዋል እና አሁንም የወንጀሉ ተባባሪዎች ናቸውና በሕግ እና በሃይማኖት ሚዛን ወንጀለኞች ያደርጋቸዋል።ስለሆነም ፍትሕ ማስተማር የሚችሉበት ሞራል የላቸውም። ራሳቸውን ስለ ፍትሕ መሰረታዊ ሕግጋት ሳያስተምሩ እንዴት ሌላውን የማስተማር ብቃት ሊኖራቸው ይችላል?

በዚህ አኳያ ሕዝብን መምራት ቀርቶ በተባባሪነት ይጠየቃሉ እና የፖለቲካ መድረኩ እንደገና እንዲበሰብስ ስለሚጥሩ “የፖለቲካ መድረኮች” በበሰቡ መሪዎች አንዳይጠለፍ ሕዝብ ነቅቶ መከታተል የጎች ግዴታ ነው እያልኩ ለአመታት የምጮኸው ለዚህ ነውይህ ግን አልሆነም። ሕብረተሰቡ መበስበሱ እነ ስየ ኣበርሃ ስወለሚያውቁት በድንፋታ “ጠያቂው ማን ነው? ተጠያቂውስ ማን ነው?” ወደ እሚል የንቀት እና በጣም የወረደ መከላከያ ውስጥ ስዬ ሲመልስ አድምጬዋለሁ። ይባስ ብሎ “ጠያቂው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፤ ፍርድ ሰጪውም ሕዝብ ነው” ብሏል። ሕዝብ ማለት ማን ነው? ሕዝብ ብለን የምንጠራው ከጠየቁት ወጣቶች ጀምሮ የሕዝብ አካሎች ናቸው። ግለሰቦች ካልቆሙ ሕዝብ የሚባል ነገር አይኖርም። ግለሰቦች ሕዝቡን የገነቡ የግንቡ አካሎች ናቸው። ግለሰቦች የሚጠይቛቸው ጥያቄዎች ባግባቡ መመለስ የፖለቲካ አዋቂነትን ያመለክታል።አዳራሹ የነበረው ተሰብሳቢ ግለሰቦቹ አንድ ባንድ ከወጡ “ተሰብሳቢ’ አይኖርም። እንደ ሕዝብ ለመጠራት የግለሰቦች ስብስብ ወደ ክምር ግምባታ በመዞር ሕዝብ የሚባለው ማሕበረሰብ ይሰራሉ።
ስዬ ለተጠየቀው  ጥያቄ መሸሻ ሲመልስ “የተጠየቀው ፍትሕ ለማምጣት ሁላችንም የምንዳኝበት ሥርዓት መጀመሪያ መመስረት አለብን፤ ከዚያ ሁላችንም እንደየሥራችን እንፋረድ” ብሏል። የበሰበሰው የሕብረተሰቡ ክፍል የስየ የመደበቂያ መልስ “በጭብጨባ ደግፎታል”። ይህ የበሰበሰ የተለመደ መልስ “ባስቸኳይ” መቆም ይኖርበታል። በተለይም በጣም በከፍተኛ ሃላፊነት የነበሩ መሪዎች የማምለጫ መልስ ሆኖ ስላገኙት እና “የበሰበሰው ሕብረሰተብም” እየተቀበለና ድጋፍ እያገኘ ስለሄደ “ያላንዳች ፈሪሃ እግዚአብሔር” በዚህ በበሰበሰ መልስ የጠያቂዎችን አፍ ሲያስዘጉ ብዙ ጊዜ ታዝብያለሁ።

አንደኛው ወጣት ‘ወንድሜን የት አደረሳችሁት?” ብሎ ሲጠይቀው “መንግሥት ስንመሰርት እንፋረዳለን፤ያኔ እንነጋገርበት” ብሎ መመለስ ምን ማለት ነው? እንዲህ ብሎ ለጠየቀ ዘመዱ የሞተበት የተሰወረበት ቤተሰብ መልሱ የኼ ነው? ሕዝብ የማወቅ ግታ አለበት ሲባል ስየም ሆነ ገብሩ ወያኔን በሚመሩበት ወቅት በጣም በርካታ ምስጢሮች በብዕራቸው አስተናግደዋል። ስየም ሆነ ገብሩ ከወያኔ ጋር ተጣላን ሲሉን “ስለ ወያኔ ‘ምስጢራዊ ሕይወት” አልነገሩንም፡ ለምን? አስገደ ገብረስላሴ ሦስት መጽሐፍ ጽፎ በጣም አስገራሚ ሚስጥሮች እና የወያኔ ማንነት ነግሮናል። የማከብረው ጓደኛዬ ገብረመድህን አርአያም የወያኔ እርቃን ገልጦ አስተምሮናል። ሁለቱም የወያኔ አጥንት እና ስጋ ምን እንደሚመስል ያለ ምንም ፍርሃት በኢትዮጵያዊነት ግዴታቸውን ተወጥተዋል። ታዲያ ስየም ሆነ ገብሩ ከአስገደ ገብረስለሴም ሆነ ከገብረመድህን አርአያ ያነሰ አውቀት እና ስልጣን ስለነበራቸው ይሆን እስካሁን “ስለ ወያኔ ባዬግራፊ/ምስጢራዊ ህይወት ላለመንገር የተቸገሩትበት ምስጢር ምን ይሆን? የድርጅታቸው ማንንት ላለመንገር የሚሸሹት ምክንያቱ ፍርሃት ነው ወይስ ምንድነው? ወያኔ አንዳያስራቸው ነው? ወይስ እጃቸው ስላለበት ነው? በግልጽ ቢነግሩንም አንድ ነገር ነው።
ስየ አብርሃ እኔ ያላነበብኩት መጽሐፍ ጽፏል ተብሏል፡ በዚያ መጽሐፍ ውስጥ ብዙ ሰው የጠበቀው “የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ የህይወት ታሪክ፤ ሞገደኛነት፤ ወንጀል እና ድብቅ ባሕሪይ’ ይነግረናል ብለን ብዙዎቻችን ስንጠብቅ “ስለ ታሰረበት” ትረኪ ምርኪ ነበር ጽፏል ብለው ያነበቡ ሰዎች መጽሐፉን የገመገሙት። ሕዝቡ 21 አመት የወያኔ አውሬነት እና ከሃዲነት አውቆታልና ስለዚህ የኔን መናገር አያስፈልግም፤ ወያኔ 21 አመት ምንነቱ ተረድታችሁታል ሊለን አይችልም (ገብሩም ሆነ ስየ)። ስዬ አብርሃ “በመለስ ዜናዊና በነስዬ የተመራው ወ ኔ 21 አመት የሰላም እና የምጣኔ ሀብት እምርታ አሳይቷል” ሲለን አንድ ኢትዮጵያዊ በሳል ዜጋ ከሲያትል የስዬ አብርሃ 100 ዲግሪ መለወጥ ገርሞት “አንዴት ነው ነገሩ ካለፈው ንግግርዎ በጣም የተለወጡ ሰው ሆነው ነው ያገኘኸዎት። ንግግርዎ ሁሉ የተቃዋሚ መሪ ሳይሆን የመንግሰት ዲፕሎማቲክ ልኡክ ከሚናገረው ንግግር የሚለይ ሆኖ አላገኘሁትም”። በማለት ብዙ ሰው ግራ ያጋባና መፍታት ያቃተው እንቆቁልሽ በቀጥታ ስዬን ጠይቆታል፡፤ ጠያቂው እጅግ የሚመሰግን አስተዋይ ዜጋ ነው። አንዲት እመቤትም በሚመሰገን ሁኔታ ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርባለች (እዛው ሲያትል ስብሰባ ውስጥ )። ታዲያ ይህ የበሰበሰ ሕብረተሰብ ጆሮው እየሰማ  ዋሽንግተን ስበሰባ ውስጥ ሲያትሎች ያሸተቱት ግማት ማሽተት ስላልቻለ “በሚገርም ሁኔታ”እያጨንጨበጨበ ነበር ያዳመጠ። ያውም ትግል ትቶ በትምህርት ዓለም ያለ የድርጅት መሪ። ይህ የበሰበሰ ሕብረተሰብ ምን ብለው ቢነግሩት ነው የበሰበሱ መሪዎችን ማምለክ የሚያቆመው?ለበሰበሰው ሕብረተሰብ መጪው የፍትሕ ዘመን ሳይጠብቅ አሁኑኑ የወያኔ ገበና ማሕደር ሊነገር በሚፈለግበት አንገብጋቢ እና አስፈላጊ ወቅት ካልተነገረው ጉዳቱ ከሚገባው በላይ አድርሶ ሕብረተሰቡ በስበሶ ከሞተ በሗላ ስዬ አብርሃ የወያኔ ገበና ምስጢራዊ ማሕደር ቢነገረን ምን ይፈይዳል።

አስገደ ገብረስላሴ ህይውት የለውም? ቤተሰብ፤ልጆች የሉትም? ገብረመድህን አርአያ አሰቃና አስፈሪ የመግደል ሙከራ ጥይት እየተተኮሰበት ከወያኔዎች ግድያ በታምር ሲተርፍ “ህይወት የለውም? ቤተሰብ ልጅና ዘመድና የሚወዳቸው ጓደች የለውም?”  ያንን መሳይ ቆራጥ እርምጃና መስዋእትነት ወስደው የወያኔ ገበና ሲያጋልጡ ህይወት እና ኑሮ መኖር የጠሉ ይመስላችሗል?  ለምሳሌ አስገደ ገብረስላሴ ‘በሰበቡ እንግልት” እየደረሰበት ባለበት ባሁኑ ሰአት ስየ አብርሃ ፤ ገብሩ ፤ አረጋሽም ሆነች ፤ተወልደም ሆነ አለምሰገድ ወዘተ….ወዘተ እሱን ለመደገፍ “በደም የጨቀየው የበሰበሰው የወያነ ትግራይ ድርጅት” የድርጅቱን ምስጢራዊ ገበናዎች  በመጽሐፍ እና በመድረክ ቢያጋልጡ ከኔ ጀምሮ ምን ያህል ከበሬታ በተጎናፀፉ ነበር።  የደበቁትና የፈሩት ምስጢር አለ። ቋንቋው ግልጽ ነው። እየተደበቁበት ያለው ምስጢር “ፍርሃት” ነው።

ማንን ነው የፈሩት? እነ ስብሓትና ስዩም እንዳያስሯቸው? አይደለም። “እውነትን” ነው የፈሩት። እውነት ለመናገር “ፍርሃትን” ሰብሮ የሚያስወጣ ጠንካራ መንፈስ ያስፈልጋል። አብዛኛዎቹ የበሰበሱ የፖለቲካ መሪዎች “ጥይት፤መታሰር፤ሞት” አይፈሩም። የሚፈሩት ከዛ በላይ ሃይለኛ ጨረር አይናቸው ላይ የሚበራ አይን የሚወጋ ‘ጨረር’ አለ።ሲያይዋት የምታንሸዋርራቸው። እውነት ትባላለች። የተኛ ሰው ሃይለኛ የላምባዲና መብራት አይኑ ላይ ስታበራበት ብንን ብሎ ዓይኑን በመከላከል ባንተ ላይ በቁጣ የሚቧርቀው ምን ይመስላችሗል? ጨለማ ውስጥ የተደበቀ ሕሊናው ስለቀሰቀስከው ‘ያንን ሃቅ፤ያንን ብርሃን መጋፈጥን ይፈራዋል”። እነ ስየ አበርሃም ሆኑ እነ ገብሩ የሚጓዙት ዓለም ከብርሃን ውጭ  ነው። እነሱ ብቻ አይደሉም ‘በቸኛውና በድብቁ ዓለም” ውስጥ አብሯቸው የሚጓዝ ሕብረተሰብ አለ። አብሯቸው ነቅዟል።ለዚህ ነው በየአዳራሹ “ውጣ” “አስወጣ” የሚባሉ ቃላቶች በማስተጋባት “ከተኙበት” የሰላም እንቅልፍ  የሚቀሰቅሳቸው ሰው የማይወዱት።

በጣም ጥልቅ ኢትዬጵያዊ እውቀት ያላቸው ጠንካራ አገር ወዳድ ምሁራን ኢትዮጵያውያን እንደ እነ ዶክተር ዶ/ር ማንከልክሎት ሃይለስላሴ እና እንደ እነ አሰፋ ነጋሽ (አምስተርዳም የሆላንድ አገር ኗሪ) በጥልቀት ያነበቧቸው የሕብረተሰብ የስነልቦና መበስበስ እና የፖለቲካ ንቅዝና ሕብረሰቡን እንዳያስተምሩ  ባገር ወዳድ ሚዲያዎች እየተገኙ የሚያስተምሯቸውንም ትምህርቶች ለሰፊው አንባቢ ሕብረሰተብ እንዳይዳረሱ ሆን ተብሎ እየተደረገ ያለው “ጉንጎና” (ኮንስፒራሲ) የኢትዮጵያ ታሪክ ሊመዘግበው ይገባል።   

የበሰበሱ መሪዎች እና ሚዲያዎቻቸው ተሽቀዳድመው የሚያጠቋቸው እና የሚያፈርሷቸው የእነኚህን አገር ወዳድ ምሁራን ትምህርታዊ ቅስቀሳዎን ማፈን ነው። ተቃዋሚው ሚዲያም ወያኔ የሚያደርገው አፋና በባሰ መልኩ እነሱም እየፈጸሙት ነው። እንኚህ ሚዲያዎች ወያኔ አፍኖናል ብለው ወደ ውጭ አገር መጥተውም  ህይወት መዝራት የሚችሉበት አገርም ሆነው (በስደት) ለጥቂት ግለሰቦች እና ቡድኖች በአድልዎ ለማገልገል የሚያሳዩት ፈቃኝነት (ሰልፍ ስረቭቱድ) እጅግ አስገራሚ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።
እነ ገብሩ፤እነ ስዬ እነ መረራ ጉዲና  በየ እስቴቱ በየዓለማቱ ያን ያህል ወጪ እየከፈሉ ሲያመጧቸው ‘ተቋማት/ሚዲያዎች” እነ መረራ ጉዲናም ሆነ እነ ስዬ መድረክን እየወከሉ የበሰበሰ ትምህርት ሲያስተምሩም ሆነ ታዋቂ ግለሰቦች በየሚዲያቸው እየጋበዙ የሚያስተጋቡት ውሸቶች ከማስተጋባት ሌላ ውጭ “በተሰነዘሩት ውሸቶች” ላይ ሂስ ከመሰንዘር ለምንድነው የሚቆጠቡት? እነኚህ ጋዜጠኞች ነን የሚሉን ሰዎች የሚተቹት ትችት “ስለ መለስ ዜናዊ እና ስርአቱ” ብቻ አንጂ “እራሳቸው በስብሰው ሕብረተሰቡን” ለተጨማሪ መበስበስ ትልቅ ‘ቧንቧ’ በሚከፍቱ አበስባሾች ላይ የሚያሳዩት አቋም አፍ የሚያስይዝ አስገራሚ ክስት ነው። ለምን?


ለምሳሌ ባለፈው ሰሞን ሜነሶታ ዲሲ ውስጥ በተካሄደው የመደረክ ስብሰባ፡ የመድረክ ድርጅት ወይንም አገር ውስጥ ያሉት ተቃዋሚዎች “ፈሪዎች ናቸው፤ ስርዓቱን ለመጋፈጥ ድፍረት ያንሳቸዋል” እየተባልን ውጭ አገር በሚኖሩት ዜጎች  አግባብ  በሌለው ሂስ እየተወቀስን ነው፡ ድፍረት አላነሰንም፤ቆራጦች ነን። ብሏል። ለምሳሌ ለቆራጥነት እና ተጋፋጭነታቸው ምልክት እንደምሳሌ የሰጠው መረጃ “አቶ ተመስገን የተባሉት አባላችን ፓርላማ ውስጥ ገብተው ስለ ፍሲካል (አመታዊ የገቢና የወጪ ባጀት) አስለመልክተው የምጣኔው ሃብት ጉዳይ ሲተነትኑ ‘ፊሲካል’ የሚለው ቃል ሲጠቀሙ በድምጽ አጠቃቀማቸው ሆን ብሎ በማሾፍ ‘ፊዚካል እና ፊስካል’ ለየብቻ ናቸው ብሎ ከጠቅላይ ሚኒሰትሩ አቶ ተመስገን አወዴ ላይ ሲያሾፍባቸው፤ “መለስን” ስትፈልግ “አፋጭበት” በማለት መለስ ሰጥተውታል።  ይህ የደፋርነታችን ምልክት ነው።ሲል መልስ ሰጥቷል።



Above photo is an angry reasonable audience from Seattle confronting Siye's distorted view on TPLF system

ሌለው ደግሞ  ዶ/ር መረራ ጉዲና የተጠቀመበት የደፋርነት ምልክት “ፕረዚዳንት ጊዳዳ መለስ ዜናዊን ‘መንግሥቱ ሃይለማርያም’ መሰልከኝ እሳ’ ብለው ተናገረውታል፡ ይህ ሌላው የደፋርነታችን ማሳያ ነው። ከዚህ ወዲያ ደፋር መሆን ምን ትፈልጋላችሁ? ሲል በጣም አስገራሚ የሆነ “የድርጅት ድፍረት” ግለሰቦች ከመሪዎች ጋር የሚያደርጉት ንትርክ አንካ ስላንትያ መተርጎም እውነት እነዚህ ተቃዋሚ መሪዎች ናቸው? ያስብላል። ስየ አብርሃ ሲያትል መድረክ ስብሰባ ላይ 21 አመት የወያኔ ስርዓት ሰላምና  ዕድገት የታየበት ዘመን ነው ብሎ የበሰበሰ ትምህርት ሲያስተምር ውጭ የሚኖሩ የተቃዋሚ ሚዲያ ጋጠኞጠች በዚህ ጉዳይ የጻፉት አንድም ነገር አልነበረም። ለምን?አነኚህ የበሰበሱ መሪዎች በስበሶ ያለው ሕብረተሰብ አንድያውን እያበሰበሱት ናቸው የምልበትም ለዚህ ነው። ዶክተሮች ወይንም (ትራድሺናል ሂለርስ) የተባሉ የሃይማኖት መሪዎች ፤በጠበላቸውም ሆነ በመድሃኒታቸው ፈውስ ፍለጋ በበሽተኞቻቸው ላይ ከሚያሳዩት ንቀት/አብዩዝ ጋር ይመሳሰላል።     
የፖለቲካ መሪዎች ከግለሰብ ንትርክ አልፈው “we have had enough of it” ወይንም “በቃ” የሚሉበት ሕዝባዊ አመጽ ካላዘጋጁ ‘ግለሰዎች ከበሰበሱ መሪዎች ጋር የሚመላሱበት አንካ ስላንቲያ ወያኔን በምን ሚዛን ነው ሊያስወግድ የሚቻለው?” የበሰበሰው የወያኔ ፋሺስት ስርዓት “እንካ ስላንትያው ለፖለቲካ ህልውናውና ፕሮፓጋንዳው እጅግ የሚጠቅመው መሆኑን ዶ/ር መረራ እንዴት መረዳት አቃተው?”
ይኼውላችሁ! እየሰደቡንም ፤ጠቅላይ ሚኒስተራችንን እየደፈሩብንም ቢሆን ፓርላማ ውስጥ ተቀምጠው ደሞዝ እየተከፈላቸው መብታቸው ተጠብቋል፡ የሚሉበት የፋሺስቶቹ የውሸት የመብት ማስከበር ቱልቱላ ዶ/ር መረራ አልተረዳውም ማለት አልችልም።ቀደም ብየ የገለጽኩላችሁ የእውነት መብራት በተኛው ዓይን ላይ ሲበራ ማምለጫ አጥቶ መንቃት ላለመፈለግ “አበራህብኝ”  ብሎ እንደሚጋፈጥ ሰው እነዚህ መሪዎችም “የግለሰቦችን አንካ ስላንትያ መደፋፈር” የሕብረተሰብ ማዕበል አስመስለው በማቅረብ የበሰበሰው ሕዝብ ሲያሞኙትና ሲያንጨበጭቡት ውጭ አገር ያሉት ጋዜጠኞች ወይንም ባለ ቴሌቪዢኖች ከመተቸት ይልቅ ዝምታ መምረጣቸው እነሱም ከበሰበሱት ውስጥ አንደኞቹ መሆናቸውን ታሪክ ጸሐፊዎች መዘገብ ይኖርባቸዋል። የበሰበሱ ፖለቲከኞች ላለማፍራት ሚዲያዎች መንገዱን የሚያጥሩበት መንገድ ካላበጁ ‘የበሰበሰው ሕብረተሰብ’ ከበሰበሰበት ጎዳና ተጠምዝዞም ራሱን ነፃ ማውጣት እንዴት ይቻለዋል?
የመለስ ዜናዊ ሞት ያሳየኝ ነገር ቢኖር “ታምቆም ሆነ ተደብቆ የነበረው በሽተኛ ሕብረተሰብ ክፍል የመበስበሱ መጠን ምን ያህል እንደሆነ የታዘብኩበት አጋጣሚ ነው። ተቃዋሚውም የወያኔ ደጋፊም፤ ወላዋዩም (ማሃል ሰፋሪ ይለዋል ሌሊን ነው?) የመበስበሱ ልክ ‘አሳፋሪና መጠነ ሰፊ ነው። አሜሪካዊው አንትሮፖሎጂሰት ኦስካር ሉዊሰ “ካልቸር ኦፍ ፖቭረቲ” እንደሚለው የሕሊና መበስበስ በውጭም በውስጥ አገርም ያለው ሕብረተሰባችን ቀፍድዶ ይዞታል።
መደምደሚያ እና መፍትሄው፡
(1)ምስጢር ይዘው የሚጓዙ ከፍተኛ ባለስልጣኖች የነበሩ ሰዎች የፖለቲካውን ባቡር እንነዳዋለን ካሉ መጀመሪያ ማድረግ ያለባቸው ከእውነት መሸሽ የለባቸውም። መልካቸው ማንነታቸው ምስጢራቸው ፤ሲሰሩት የነበረው የፖለቲካ ልምድ እና ወንጀል/ጥፋት/ስሕተት፤የድርጅታቸው ባህሪ ምንነት ለሕዝብ ማሳየት አለባቸው። ማንነታቸው ካላሳዩን የመንጃ ፈቃዳቸው በተለመደው ተአምሩ አምላክ ከሚነጥቃቸው ይልቅ የእውነት ጮራ እንዲያዩ በሙሉ ልቦናቸው ጥረት ማሳየት ይጠበቅባቸዋል። ለታሪክም ለሃገርም ለነሱም በጐ ስም ሲሉ።
ሌላው ነጥብ፦ መድረኮችም ሆኑ ሌሎቹ የተቃዋሚ ድርጅቶች በየአገሩ እየመጡ ከሚደሰኩሩና ትምህርት ቤት እየገቡ የሕዝብ መሪዎች ነን ማለታቸውን አቁመው ነገ ጥዋት ወደ አገራቸው በመመለስ ሕዝቡ ከበሰበሰው ጎዳና ለማሰወጣት አባሎቻቸውን አስተባብረው “እስላሞቹ” አያደረጉት እንዳለው ቆራጥ መነሳሳት በበለጠ ማዕበል አስነስቶ የበሰበሰው ስርዓት ጠረጴዛ ላይ አስቀምጦ ‘አደብ እንዲገዛ’  ለማድረግ ወጣቱ በሚማርበት ተቋማት ለአመጽ እንዲነሳ ሰለማዊ ሰልፍ እንዲፈቀድ፤ የመጻፍ ነጻነት እንዲከፈት፤ የታሰሩ እንዲፈቱ ለማድረግ “ዋል እደር ሳይሉ” ከረሃብ አድማ ጀምሮ እስከ ወያኔ የሚፈራውን ሕዝባዊ ማእበል ሕብረተሰቡ አንዲነሳ በቁርጠኝነት መጋፈጥ አለባቸው።ከተጓዙበት የተለየ መንገድ ቀይሰው ለመስዋእትነት ዝግጁነታቸው ከላሳዩን መሪዎች ናቸው ብለን መቀበል ያስቸግራል። በበሰበሰው ጎዳና መጓዝ አሁኑኑ ማቆምና ከእዛው ጎዳና ዘልሎ መውጣት የወቅቱ ጥያቄ እና የተቃዋሚ መሪዎች ፈታኝ ምዕራፍ መጥቷል። በዚህ ፈታኝ ምዕራፍ አዲስ ስልት ይዘን መጥተናል የሚሉበት የትግል ስልት ካለ ሳይውል ሳያድሩ ህይወታቸው ለሚስጡት የተዘጋጁ ካሉ (እነ ስየም ሆኑ እነ ገብሩ እና መረራ እና ማንም ሰው) የተለመደው የህሊና ድጋፌ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ። ማትኮር ያለብን ጥያቀው ግን አንዚህ በተደጋጋሚ ፈተና ውስጥ ገብተው አንደ ደካማ አህያ ዳገቱን መውጣት አቅቷቸው ሸብረክ እያሉ ሲሉ የነበሩት ተቃዋሚ መሪዎች ‘ከመለስ ዜናዊ’ ንትርክና እንካ ስላንትያ ያለፈ፤ ከበሰበሰው ጐዳና ወጥቶ “ሕዝባዊ ማዕበል የሚያስከትል ሰላመዊ አመጽ” ማስነሳትና መምራት ይችላሉ ወይ? ነው ጥያቄው። የፖለቲካ ፕሮግራማቸው/.መመሪያቸው እና የአመራር ብቃት ማህደራቸውን ስንፈትሽ  ያልጠበቁት እፊታቸው ላይ ድንገት ተገትሮ  የቆመ ፈታኝ ምዕራፍ በቆራጥነት በርግዶ የማለፍ  ብቃትና ዝግጅት ስለሌላቸው የሞትና የሽረት ፈታኙኑ አስፈሪ ፈተና ባሸናፊነት የሚወጡ መሪዎች አይደሉም።
የበሰበሰውስ ሕብረተሰብ ምን  ይጠበቅበታል?
ወንጀለኞችን የመውደድና ለፋሺስት መሪዎች የማልቀስ አባዜውና ከእንቅልፍ ሲባንን እፊቱ  ቦግ ብሎ በመብራት ላይ ያለው የታሪክ “ባወዛ’ ከታሪክ ምሰሶ ጋር እንዳያገጨው ምንድነው ማድረግ ያለበት? ማድረግ ያለበት ፋሺስቶቹ ካጠመዱት ወጥመድ ካሁኑኑ ተሎ ራሱን ማውጣት ካልሞከረ፤ ቅድመ አያቶቹ እና አያቶቹ የተውለትን የተከበረ ባህል፤እምነትና አገር ለልጅ ልጆቹ ማስረክብ አንደሚያቅተው ጠንቅቆ ማወቅ ይርኖበታል። አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ  getachre@aol.com ድረገጼን ለመጐብኘት www.Ethiopiansemay.blogspit.com ይጎብኙ።