Saturday, July 25, 2020

በኢሳያስ አፈወርቂ ትዕዛዝ በኢትዮጵያ ውስጥ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ተወካይ በሆነው በአብይ አሕመድ ዓሊ ተባባሪነት ኢትዮጵያዊ ትንታጉን ልደቱ አያሌውን አስሮ እያሰቃየው ነው! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) Saturday, July 25, 2020



በኢሳያስ አፈወርቂ  ትዕዛዝ በኢትዮጵያ ውስጥ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ተወካይ በሆነው በአብይ አሕመድ ዓሊ ተባባሪነት ኢትዮጵያዊ ትንታጉን ልደቱ አያሌውን አስሮ እያሰቃየው ነው!
ጌታቸው ረዳ
(Ethiopian Semay)
Saturday, July 25, 2020



እንዴት አብይ አሕመድ ኢሳያስ ሥር የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ተወካይ ሊሆን ይችላል ብላችሁ ግራ ሊገባችሁ ለምትችሉ አንዳንድ አንባቢዎች ይህንን የአብይ አሕመድ የራሱን ቃል ልጥቀስላችሁ፡
“ ኤርትራን በሚመለከት በተለያየ መድረክ ስናገር ከሰማችሁ ዛሬ “ኦፊሻሊ” ክቡር ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር ሥራ  እንድሰራ ሥልጣን ስለሰጡኝ በየሄድኩበት ቦታ አቶ ኡሰማንን ወክየ የሥራ መዛባት እንዳይመስላችሁ!”   (አብይ አሕመድ)  ከኢሳያስ ፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ሲናገር በደምጽ ከቀዳሁት ማሕደር።


ይህንን ከተናገረ በሗላ ኢሳያስ በበኩሉ ስለ አብይ ውክልና እንዲህ ሲል አረጋግጦለታል፤
“በተደጋጋገሚ፤ በተደጋጋሚ ብያለሁ፤ ሊደረግ የሚገባው የሆነ ነገር ሲኖር ውክልና ሰጥነሃል። ወኪላችን አንተ ነህ” (ኢሳያስ አፈወርቂ)  ለተሸላሚው ለኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለአብይ አሕመድ ያደረገው ንግግር በደምጽ ከቀዳሁት ማሕደር”


ከላይ አንዳደመጣችሁት ኢሳያስ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያደረግ የሚፈለገውን ነገር ሲኖር በወኪሉ በአብይ አሕመድ በኩል ይፈጸማል ማለት ነው። በውክልናው መሰረት አንጀቴን እጅግ ያዘነለትን ወንድሜን ልደቱ አያሌውን ሊገድለው ባለመቻሉ በትዕዛዙ መሰረት እስርቤት ከትቶታል። ይህ ማፈሪያና ወራዳ ግለሰብ ኢትዮጵያን የምታክል ታላቅ አገር እጁ ውስጥ ገብታ ኢትዮጵያን በክብር ከመምራት ይልቅ ኢትዮጵያውያንን በመጨፍጨፍ እጁን በደም የጨቀየን ግለሰብ ወኪል ነኝ ብሎ መሳቂያ አድርጎናል። ይህ ኢትዮጵያን የምታክል ታላቅ አገር የመሪነት ባሕሪ የለውም ስንል የነበረውም ለዚህ ነው።  ስለዚህ ኢትዮጵያን እየመራት ያለው ኢሳያስ ሆኖ በውክልና- አብይ አሕመድ እየተመራች ነው  የምንለው ለዚህ ነው።  የትግርኛ ተናጋሪዎች አንድ አስገራሚ ነገር ስንታዘብ የምንለው ነገር አለን  ‘ን ኣዳም ገረሞ” (ለአዳም/ ለዓለም ሕዝብ ያስገረመ)። ልደቱ አያሌው ለምን እንዳሰረው አሁን ግልጽ እንደሚሆንላችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።


ይህ ታላቅዋን ኢትዮጵያ በድንገት እጁ ውስጥ የገባች አገር አንዲህ እያዋረዳት ያለውን ድሮ ከነ ተስፋየ ገብረአብ ሆኖ ለኦነግና ለኢሳያስ ምስጢር እያሳለፈ ሲሰልል የነበረውን ወንጀል   በመቀጠል የኢሳያስ የስለላ ውክልናውን በግሃድ አስታውቋል።በዚህ ውክልናው ለኢትዮጵያ መቅሰፍት ሆኗታል። በሁለት አመት የሥልጣን ጊዜው “የሲኦል በሮችን” ከፍቶ “የሲኦል ጭራቆችን” አስገብቶ አገሪቷን ለዋይታ ለጭፍጨፋ እና ለስቃይ ዳርጓታል። ጦርነት ሲነሳም ሆነ በተለያዩ መንገዶች “የሕዝብ ዕልቂት” ሲፈጸም ሥልጣንን ለሚጎመዡ እንደ አብይ አህመድ የመሳሰሉ “ሥግብግብ” ፍጡራን የሥልጣን ማጠናከሪያ እና የዝና መድመቂያቸው ያደርጉታል። ይህንን ተንተርሶ የሚቃወማቸው ተቃዋሚን በማሰር በመግደል ይጠቀሙበታል። አብይ አሕመድ ልደቱን ለመግደል የነበረው ሴራም ሆነ ለማሰር የሄደበት ርቀትም ይህንኑን አጋጣሚ በመጠቀም ነው።


ሰው ይሳሳትል፤ ከስሕተቱ ይታረማል። በዚህ መልክ ልደቱ ላይ የነበረኝ አንዳንድ ትችቶች ከብዙ አመታት ጀምሮ ስተቸው የነበረ እና ስቃወመው የነበሩ አቋሞቹን ይቅርታ ጠይቆ በአዲስ መንፈስ ተነስቶ በሚገርም ሁኔታ ባለው ተፈጥሮአዊ ብልህነት የአብይ አሕመድን  ሥርዓት በመቃወም ኮለኔሉ “የለበሰው የአፓርታይድ  ካባ” በመግፈፍ እርቃኑን ስላስቀረው “የተቃውሞ ድምፅ ሲሰማ መንፈሱ ተሎ የሚረበሸው”  የእነ ተስፋየ ገብረአብ የስለላ መረብ አባል የነበረው፤የሁለት አለም ሰው ሰላይ አብይ አሕመድ “ልደቱን” በኢሳያስ ትዕዛዝ ለመግደል ሲሞክር ‘ትንታጉ” ልደቱ ተሎ ስለነቃ የተከታታዮቹን የመኪና ታርጋ ጽፎ እየተከታተሉት እንደሆነ ለሕዝብ ግልጽ በማድረጉ ሳይገድለው ሲቀር ለእስር ዳረገው።


ለዚህ ሁሉ በር ከፋቾችና ትግሉን ያስጠለፉት “ተደማሪ ተቃዋሚ የሚባሉት” የነልደቱን መታሰር ለአፓርታይዱ መሪ፤ ለአብይ አሕመድ “መደላድል ማዳበሪያ” እንዲሆነው ድጋፍ እየሰጡ አብይ አያስርም አይገደልም ሲሉ የነበሩት ቀንደኛ ተጠያቂዎች ናቸው።


 በድፍኑ ከመሄድ ለአንባቢዎቼ  መጥቀስ ስለሚያስፈልገኝ  ከተደማሪ ተቃዋሚ የአብይ አሕመድ አዲሱ “መናፍህ’ ከሆነው አንደኛው “አማራ ለብቻ ተለይቶ የተጠቃበት ጊዜ የለም” እያለ በዋሾነቱ ለሚታወቀው “የብርሃኑ ነጋ” አዳማቂ የኢዜማው “አንዱአለም አራጌ” የመሳሰሉትን በዚህ ወቅት መጥቀስ አስፈላጊ ነው።


አንዱአለም  አገዛዙን የደገፈበትን አሳፋሪ ቃለ መጠይቁን ልጥቀስና ልደቱ እንደ አንዱአለም አራጌ “የአፓርታይድ መናፍህ” ባለመሆኑ ለእስርና ለግድያ ሴራ ተዳርጓል። አንዱአለም አብይን ብቻ ሳይሆን ጸረ አማራው ኦነጉ የኦሮሞው ክልል መሪ ሽመልስ የተባለውንም ሲደግፍ አድምጠናል።
'

 ብርቱዎቹ ዜጎቻችን ይህንን “የኦሮሙማው አፓርታይድ” ሲጋፈጡ ተደማሪው አንዱአለም አራጌ የሚከተለውን መናፍህ ሲያቦካ ነበር፡

አንዱአለም አራጌ እንዲህ ይላል፦

“ድሮ የነበረው ሰራዊት ፤ ፖሊስ እንዳለ አለ፤ “ስትራክቸሩ” አለ፤ ነገር ግን ሰዎች እንደፈለጉት ሃሳባቸውን በነፃ ይገልፃሉ፤ እንደ ድሮ የሚገድላቸው የለም፤ የሚያስራቸው የለም።”” እያለ ከዋሸ በሗላ ሕዝቡን እንዲህ ሲወነጅል ላስሰማችሁ እና ወደ ሚቀጥለው ልግባ፤
አንዲህ ይላል፡

“አንገቱን ለገዢዎች ጫማ የሚያመቻች ሕዝብ ባለበት አገር ነፃ መንግሥት ሊኖር አይችልም።” 
እንግዲህ ይህ ማፈሪያ ከድሮ ጀግንነቱ ተለውጦ ወደ ሎሌለነት ተገልብጦ “አንገቱን ለገዢዎች የሚያመቻች ሕዝብ ስላለ እንጂ የአብይ አሕመድ ጥፋት አይደለም” በማለት ጥፋቱ የሕዝብ መሆኑን ይጠቅሳል። ንግግሩ ልክ ቢሆንም፤  ልደቱ፤ ይልቃል፤ አስቴር፤ እስክንደር… ወዘተ,፣ ወዘተ, የመሳሰሉ ዜጎች  “አንገታችንን ለገዢው ለአብይ አሕመድ ጫማ አናመቻችም ስላሉ ይኼው “አብይ አሕመድ” አስሮ እየደበደበ ፤ በርሃብ እያሰቃየ ፤ ከኮረና ቫይረስ ታማሚ እስረኞች ጋር አስሮ ሊገድላቸው ወስኗል።

እንግዲህ “አንገቴን ለአብይ አሕመድ እና አንደኛ ደረጃ ጠላት ለሆነው ለኢሳያስ አፈወርቂ ጫማ አላመቻችም ብሎ በግልጽ “የኩሊው የአብይ አሕመድ” አለቃ “ኢሳያስ አፈወርቂን” በመቃወሙ “አለቃየን ደፍርክ” ብሎ “አዲስ አባባ ውስጥ እንደ “አሸን የፈሉት የኤርትራ አፋኝ ነብሰ ገዳዮችን” አሰማርቶ ልደቱ አያሌውን ሊያስገድለው ሲከታተለው እንደነበረና “ልደቱም የተከታታዮቹ ዕቅድ ወዲያውኑ ስለደረሰባቸው “የመኪናዋ መለያ ቁጥር”  መዝግቦ ልደቱ ለሕዝብ ይፋ አድርጎ እንደነበር የሚታወስ ነው።

የነብሰገደዳዮች ስብስብ ጠ/ሚኒሰትር ነኝ የሚለን አብይ አሕመድ “አለቃውን ኢሳያስን” ስለተቃወመበት “በክርክር የማይችለውን” ልደቱ አያሌውን “እስር ቤት” አስገብቶ ምክንያት እያሳበበ በተፈጥሮም ሆነ በመርዝ ወይንም ልክ እንደ ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት “በኮረና ቫይረስ” እስረኞች እንዲገናኝ በማድረግ ባጭር ዐድሜ ይህ ወጣት ፖለቲከኛ ሊቀጨው ይችላል። በዚህ አጋጣሚ ይኼው “ልደቱ አያሌውም ይታሰር እንጂ ጠበሉን ይድረሰው” እያሉ በየፌስ ቡክ እየለጠፉ “ልደቱን የሚያክል ወጣት ፖለቲከኛን በፋሺስቶች እጅ እንዲወድቅ” መሪያቸውን አብይ አሕመድን ሲወተውቱት የነበሩ ሻዕቢያዎች እና የአብይ ተከታይ ኢትዮጵያዊያን አነሆ መሪያቸው የሎሌዎቹን ውትወታ ሰምቶ ልደቱን አስሮታል። የልደቱን መታሰር የኛ መታሰር ነውና በመታሰራችን እነሆ “አንኳን ደስ አላችሁ” እላችሗለሁ።

እንደምታውቁት ‘ጥርቅም የነብሰገዳዮች መንግሥት’ የኮሮና ቫይረስን ለመጋፈጥ ሰፊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅእና “የመግዛት ሀይል” እንዲሰጠው በአባላቱ አማካይነት በህግ አውጪ ሎሌዎቹ በኩል ሰፊ ዕድል ካገኘ ወዲህ የመብት ተሟጋቾች፤ፖለቲከኞችና የተቃዋሚ አባሎች ለመቅጣትና “የሕዝብ ሚዲያ/ቲቪ/ቴሌፎን መስመሮችን” በበላይነት ተቆጣጥሮ ያሻውን መናፍህ (ቅስቀሳ) እያሰራጨ  ይገኛል። አሻንጉሊቱ የሕግ አውጭውና የሕግ ተቀወዋም ተብየው አካልም እንዲሁ “ከአፓርታይዱ ስርዓት ጋር ወግኖ የውሸት መረጃ አስደግፎ”፡የሀሰት ውንጀላ በማሰራጨት በልደቱ ላይ ዘምቷል።

አብይ ወደ አገር አስገብቶ ለስሙ “ሂዩማን ራይትስ” ጉዳይ ተከታተሉ ብሎ በሹመት ወደ አገር ያስገባቸው እንደ እነ “ዶ/ር ዳኒኤል በቀለ” የመሳሰሉ ማፈሪያዎችም ሁለት አመት ሙሉ የገዢው መገልገያ ከመሆን አልቦዘኑም፡፡ሥልጣናቸው ወርውረው ወደ ነበሩበት ውጭ አገር ተመልሰው “ለዓለም ሕግ ጽ/ቤቶች የኮለኔሉን አፓርታይዳዊ ጭካኔ” ለማጋለጥ  ፍላጎት አላሳዩም። አሁንም ቅምጦች ሆነው ሲዘባርቁ እያደመጥን ነው።

“የነብሰ ገዳዮች ስብስብ” ጠ/ሚኒስትር ድምፅ በመሆን የሚያገለግሉ ውጭ አገር የሚገኙ ደጋፊዎቹም በመሪያቸው አብይ አሕመድ ላይ ትችት ወይንም ምላሽን የሚሰነዘር ጋዜጠኛም ሆነ የፖለቲካ መሪ  በሓሰተኛ ወንጀል ተከስሶ ሲንገላታ/ስትነገላታ/ አይተው “ደስታቸውን የሚገልጹ ድኩማን ፍጡራን እየተባዙ ነው።

ብልጽግና ብሎ ራሱን የሰየመው ይህ የወንጀለኞች ስብስብ ፓርቲ “አገሪቱን በቁጥጥር ስር አውሏታል” ፣ ይህም ማለት የተቃዋሚ ዕጩ ዘመቻ ማካሄድ አይችልም ፡፡ ነገር ግን በቁጥጥሩ መዳፍ የበሰባቸው የአፓርታይዱ የሕግ እና የፍትህ ዘርፎችን ፤ የዜና ማሰራ የቴሌቪዥን ስርጭቶችና ቴሌፎን መልዕክቶችን እየተጠቀመ የፓርቲው ‘መናፍህ’ በስፋት እያካሄደ ነው፡፡


የአብይ አሕመድ የክፉ አዕምሮን ውስጣዊ ስራዎች ልደቱን የሚያክል ወጣት በማሰር አብይና ሥርኣቱ የወሮበላዎች የዱርየዎች የመንጋ ሥርዓት መሆኑን አሳይቷል። በ 1970 ዎቹ አመተምህርት ወቅት የኡጋንዳ ጨካኝ መሪ የነበረው ኢዲ አሚን ዳዳ ፣የገደላቸው የፖለቲካ ጠላቶቹ ጭንቅላቶች “በማቀዝቀዣው” ውስጥ እንደቆየና “የሰውን ሥጋ ለመብላት እንደሞከረ” ተናግሯል፡ ሲቀምሰው ግን “በጣም ጨው ጨው” የሚል “ጫውማ” ሆኖ  ማግኘቱን ሲናገር ዓለምን ሁሉ በድንጋጤ ያስገባ ክስተት አንደነበር ያነበብኩት መጽሐፍ  ይገልጻል፡፡ አብይ አሕመድ እንደ እነ ኢዲሚን ባይሆሆንም የተቃወሙትን ሰላማዊዎችን በማሰር በኮረና በሽታ እንደለከፉ በማድረግና የሰው ስጋ የሚበሉ ግብረሰዶማውያን የኦነግ ተዋጊዎችን ያለ ምንም የመቆጣጠሪያ ውል “ወደ አገር አስገብቶ” ኦነግን የሚቃወም ሰው “ግብረሰዶም እንደሚፈጸምነትና “የገዛ ሥጋው” ተቆርጦ በማስገደድ  እንዲበላ ተደርጓል የሚል ከአፓርታይዱ የኦሮሞ ክልል ባለሥልጣኖች  ሲናገሩ አድምጠናል (አውድዮውም አለ)። ሥጋታችን የከፋ የሚያደርገው የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ወኪል በሆነው አብይ አሕመድ ትዕዛዝ ኦነጎች በሚያስተዳድሩት የፍትሕ ተቋማትና በሚቆጣጠርዋቸው እስርቤቶች ውስጥ የተወረወረው  “ኢትዮጵያዊው ዜጋችን ልደቱ አያሌው” ከዚህ በሗላ ምን እንደሚደርሰው ስጋታችን እጅግ ይጨምራል። ተቃውሞኣችን ግን ይቀጥላል!
ትንታጉ ወንድሜ ልደቱ አያሌው ዛሬ ግን ከጎንህ ቆሜአለሁ!
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ የኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ