Thursday, April 22, 2021

ማተቡን ያልበጠሰ” ሙሉ ሰው የመውለጃው ወቅት አሁን ነው! ከጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay 4/22/2021

 

“ማተቡን ያልበጠሰ” ሙሉ ሰው የመውለጃው ወቅት አሁን ነው!

ከጌታቸው ረዳ

ኢትዮ ሰማይ

Ethio Semay

4/22/2021

እንደምን ሰነበታችሁ?

ሰሞኑ በአማራ ማሕበረሰብ የተፈጸመው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ከተጠቂዎቹ ያደመጥኳቸው ልብ የሚሰብሩ ድምጾች አደምጬ የተሰማኝ ውስጣዊ ስብራትና ሓዘን መቋቋም ስላልቻልኩየደም ግፊትስለጨመረብኝ ሓኪሜየን አነጋግሬ ዕረፍት እንድወስድ ምክር ቢሰጠኝም፤ ዛሬም አላስችል ስላለኝ በአካል ባልገኝለትም ብዕሬን አንስቼ ማንቃቴን እቀጥላለሁ። ይህ ስሜት የቅርብ ወዳጄ በዚህ ጉዳይ አነጋግሬው፤ እርሱም እንደኔው በሐዘን ልቡ ተሰብሮ እንቅልፍ እንዳጣ አጫውቶኛል። ብዙዎቻችሁ እንደኛው እንደተጎዳችሁ አልጠራጠርም። በዚህ ጭፍጨፋ ልባቸው ያልተጎዳ ሰዎች ካሉገዳዮቹና የገዳዮቹ አባሎች ብቻ መሆን አለባቸው

 

ይህ የዘር ማጥፋት ጥቃት የፈጸሙ በአብይ አሕመድ እውቅና የገንዘብም የሞራልም ድጋፍ የሚደረግላቸው ድርጅቶችኦሕዲድእናኦነግ” (ቅጽል ስሙኦነግ ሸኔ”) ናቸው። ይህም አብይበቃሉበሕዝብ ፊት ያረጋገጠልን ንግግሩኦነግ ጋር ተያይዞ ብዙ የረዳነው ድርጅት ነው፤ በገንዘብ በአቅም እንዲደራጅ ከነበረበት ሁኔታ እንዲወጣ የረዳነው ድርጅት ነውብሎ ነግሮናል። ኦነግ በደርግ ጊዜ እና ኦሆዴድ ደግሞ ወያኔ ጋር ሆነው በጠቅላላ በተከታታይ 33 አመት በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ወንጀል ፈጽመዋል። አብይ አሕመድ የስለላው (ኢንሳ) መሪ ሆኖ የኦነግ ህቡእ አባል ነበር። ሥልጣን ከያዘም ወዲህ ዛሬም በገንዘብም በሞራልም እንደረዳቸው ነግሮናል።

 

ስለዚህ የጭፍጨፋው አበረታች አብይና አርሱ የሚመራው ሥርዓትና ድርጅቱ ናቸው።  ሰሞኑን በአማራ ማሕበረሰብ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ 16ኛው /ዘመን ሊቁ መኖክሴአባ ባሕሪበዘመናቸው የተፈጸመና የተመለከቱት በጻፉትዜናሁ ለጋላተመሳሳይ ነው። አብይ አሻጋሪ ነው እያሉ በምርጫ ተመዝግበው ደፋ ቀና እያሉ ከንቱ ልፍልፋ ስለሚያደርጉ የፖለቲካ ማሃይማን መልእክቴ ይድረሳቸው። ፖለቲከኞቹ የዘር ማጽዳት ወንጀል (ጀነሳይድ) እንደተፈጸመ አምነው ቀጥታ ሕዝባዊ አልገዛም እምቢተኛነቱን መርተውጀነሳይዱንለዓለም ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል። ለዚህ ነበር ከወራት በፊት በምርጫ መግባት እንደሌለባቸው ጽፌ የነበረው።

 

ኦክተበር 6/ 2002 በፈረንጅ አቆጣጠር (19 አመት በፊት) “በዲሞክራሲ እሳት ለመሞቅ ስንሞክር የነፃነት ትርጉም እያጣን ብቸኛዋን አገር አገር ልናጣት ነውብየ አንድ ጽሑፍ አቅርቤ ነበር። ሰሚ አልነበረም። ለምርጫ ተሯሯጡ፡ ጭፍጨፋው አላስቆሙትም። ዛሬም ተደጋጋሚ ስሕተት በመፈጸም ላይ ናቸው።

 

እንደምታውቁት የዚች አገር ማህጸንአማልክቶችስትወልድ ኖራለች። የአማራ ሽማግሌዎች ፤እናቶች እና ህጻናት አማልክቶች ናቸው። ከአንደበታቸው የሚሰነዘር የተጠቂነት እሮሮእምባ የሚያስለቅስየአማልክቶች ለዛ ነው።

 

እነዚህ አማልክቶች መሬት ቆፍረው አርሰው ጎልጉለው ከዳመና ጋር ከመነጋጋር ሌላ የሚያውቁት ነገር የላቸውም። የዳመናው አገር ብየ የገጠምኩላት ኢትዮጵያ የነዚህ አገር ሰዎች ነች። ብርቱ የዋህነታቸውአማራ ማን እንደሆነ እና የት እንደሚኖር እንኳ አያወቁም ጎጃም መጠለያ ተሰጥቶአቸውእንደዚህ ያለ ብሩክ ሕዝብ መኖሩንም አናወቅም ነበርሲሉ የገዛ አማራው ሕዝባቸው ሲያመሰግኑ ማድመጥ ልብ ይነካል።

 

እነዚህ አማልክቶችዋ ነበሩ ድንጋይ ተንተርሰው ለጦርነት ሲጠሩ፤ ቆስለውም ሞተውም፤ ወልደውም ተዋልደውም ሃይማኖትዋን አስከብረውና አስፋፍተውኢትዮጵያንለዓለም ያስተዋወቅዋት። ዛሬ ከማንኛቸውም ጊዜ በከፋ ፈተና ላይ ወድቀዋል። ድንጋይ ተንተርሰው ያስረከቡንን ሰፊ አገር ደብዛዋ እየጠፋ፤ እነሱምበሙጃዎችተውጠው እነሆ በገነቡዋት አገር መኖር ተነፍገዋል።

 

እኛ የተወለድንበት ምድር ሁላችን ባንሞትላትም ገደዮችሽን እየገደልን ለነጻነትሽ እና ለክብርሽ ዘብ እንቆማለን የሚሉትን በየከተማው በቁጣ እና በቁጭት አደባባይ የወጡትን የአማልክቶቹ ልጆች ዛሬ የተነሳሳው ወኔአቸውን ለማቀዝቀዝና ለመስለብ ሙከራ እየተደረገ ነው። እንግዲህማተቡን ያልበጠሰሙሉ ሰው የመውለጃው ወቅት አሁን ነው!

አማልክቶቻችን ከሕጻናት ጋር ቆመው እምባቸው አቅርረው ወደ ሰማየ ሰማያት አቤት ብለዋል። ተኝታችሁ ነቅታችሁ ፀሐይዋን ሞቃችሁ የምትረማመዱባት አገር፤ኢትዮጵያ ሆይ በልጆችሽ ኩሪተብሎ የተዘመረላት አገር ከመና ተጠፍጥፋ የወረደች ሳትሆን ዛሬ እምባቸው እያቀረሩ ያሉ የነዚያ የአዛውንት አማልክቶቻችን ሥሪት ነች። ዛሬ አገራቸው በወረበላዎች ተይዛለች። መቆም መተኛት አልቻሉም፤፡ ስለዚህ ኢትዮጵያም ሆናችሁ አውጭ አገር ያላችሁ ዜጎች ትግሉ ለራሱ ሲል ገንፍሏል እና የኦሮሙማው ፋሺስታዊ ሥርዓት በሚያዘጋጀው በራሱ ሕግ እየተጫወትን አብይን እናስወግዳለን የምትሉ ሁሉ አሁንኑ አቁሙ!

 

አማልክቶቻችን ከነልጆቻቸው ተከበዋል፡ ግማሹም እስርቤት ገብተዋል። ይህ አደጋ ግልጽ ነው።  ስብዕና ከማያወቅ ከሰው ልጆችና ኢትዮጵያዊ ስነ ምግባር ከማይገጥም አርባ አራት ጥርሱን የነከሰብንን ጠላት በምርጫ መጣል አይቻልም። የአማልከቶችና አዛውንቶቻችንን የምንመስል ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው በምድሪቱ ላይ እየረጩት ያለውን ልብ ሰባሪእምባየማስቆም ግዴታ አለብን። ምድሪቱ ለነጻነት ትግል ጥሪ እየጮኸች ነው።ማተቡን ያልበጠሰሙሉ ሰው የመውለጃው ወቅት ጊዜው አሁን ነው! ሼር በማድረግ ሕዝቡ እንዲመለከተው አድርጉ።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ - ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay