Sunday, November 7, 2021

የኢንተር ሃሙዌው የድንቁርናው ቡድን “የኦሮሙማው ፓወር” የመሪያቸው ፎቶ “እንደ ክርስቶስ” ከፍ አድርገው ሲያውለበልቡት ዋሉ! ጌታቸው ረዳ ዕለተ ሰንበት 11/7/2021+ Ethio Semay

 

 

የኢንተር ሃሙዌው የድንቁርናው ቡድን “የኦሮሙማው ፓወር” የመሪያቸው ፎቶ “እንደ ክርስቶስ” ከፍ አድርገው ሲያውለበልቡት ዋሉ!

ጌታቸው ረዳ

ዕለተ ሰንበት

11/7/2021+

Ethio Semay


ኢትዮጵያ ጉዳይ ወደ ውስጠኛው ገደል ወደ ጥልቁ ጭለማ የመግፋቱ ጉዳይ እያደረ የሚገርም ክስተት እየታየ ነው። የ27 አመት የወያኔዎች ደጋፊዎች ድንቁርና  ቅጅ ዛሬም በኢንተርሃሙዌው የ ኦሮሙማው ፓወር ደጋፊዎች አዲስ አበባ ውስጥ ከ 4 አመት የወያኔ መውደቅ በሗላ እንደገና ተደግሟል።

ልክ እንደ አሜሪካኖቼ “ይት ፓወር” የነጭ ሥልጣን አስጠባቂ ቡድን ሁሉ ኢትዮጵያ ውስጥም ሥልጣን የተቆጣጠረው የአብይ  አሕመድ  “ኦሮሙማ ፓወር” አማራዊውን ኢንተርሃሙዌው ቅርንጫፍ ግምባር ቀደም  በማስሰለፍ “አንጨብጫቢ” በማድረግ ትናንት አዲስ አባባ ከተማ የታየው የጦርነት ድጋፍ የአብይ አሕመድን “ስብዕና ለመቅረጽ” የተደረገ ስልት መሆኑን ኢንተርሃሙዌው “የድንቁርና ቡድን” ያሳየው ባሕሪ ለአለም ታይቷል።

የሚገርመው ደግሞ ያንን በማስታከክ የሩዋንዳው “የሁቱ ፓወር” ትክክለኛ ቅጅ የሆነው ኢትዮጵያዊው “የኦሮሙማው ፓወር” ስለ የቀድሞ ሠራዊት አባላት ወደ ጦርነት መመልመል ጥሪ ያስተላለፈው ሌላው አስገራሚ አዋጅ አንብበናል።

ይኼውም ለቀድሞ ወታደሮች ጥሪ ባስተላለፈው የጥሪ አዋጅ ላይ የተጠቀመበት “ሕዝቦች”  የሚለው የወያኔ ቃል እንዳለ ሆኖ፡  አብይ አሕመድ  ያወጣቸው ለቀድሞ ሠራዊቶች ጥሪ ሁለቱ ዋና ዋና  መለኪያዎቹን  ከዚህ በታች የጠቀስኳቸውን መለኪያዎችን ተመልከቱልኝ፡

“1.1. የኢፊዴሪ ሀገመንግስትን  የተቀበሉ

1.3. ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ የሆኑ ፣”

የሚሉት ሁለት ነጥቦች ስትመረምሯቸው ዋነኛው ትርጉሙ፤

“ለአገር መስዋእት ለመሆንም የአብይ እና የወያኔ ሕገ መንግሥት ካልተቀበለ” ወያኔን ተፋልሞ መስዋዕት ሆኖ ማለፍ “አይፈቀድም”። ይህንን በድጋፍ ተቀብለው “ለኦሮሙማው ፓወር” ሲያንጨበጭብ የዋለው የኢንተርሃሙዌው ቡድን የድንቁርናው መለኪያው ሚዛን የሚገርም ነው።

ጥሩ እና ታላላቅ አስተማሪዎች ሁሉ ሲሞቱ፣ ድንቁርና ከተኛበት ነቅቶ የድንቁርና ተማሪዎችን በደንብ ያስተምራል። የድንቁርና ተማሪዎች ሁሉንም ነገር ባለማወቅ፣ በማይታሰብ ደስታ እና ብርታት በዋዠቅ ወደ ጥፋት የሚመራቸው የጨቋኝያቸውን እና የገዳያቸውን ባንዴራ በደስታ ያውለበክባሉ!" የሚለውን የወጣቱ ቱርካዊው ፈላስፋ ፤መሕመት” እውነተኛነት ኢትዮጵያ ውስጥ በደምብ ታይቷል።

እንግዲህ ይህ የ “ኦሮሙማ ፓወር” አዋጅ ትግሬ የሚባል በሙሉ እስከገደለላቸውና እስካጎረላቸው ድረስ “አማራዊው ኢንተርሃሜው” የኦሮሙማው ፓወር መሪያቸው ፎቶግራፍ በማውለብለብ ለፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ ሆነው ቢታዩም ጉዳያቸው አይደለም።

ጌታቸው ረዳ 11/7/2021