Sunday, January 30, 2011

መሪሕ ውድብ የተባለ ፖለቲካዊ ታቦት እያለ የዓረቦች አደባባይ አብዩት ባሁኗ ኢትዩጵያ አይሰራም

ይድረስ ለጎጠኛው መምህር (አማርኛ) $25.00 እና ሓይካማ ( ትግርኛ) $15.00 መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛችሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836 (Getachew Reda P.O.Box 2219 San Jose, CA 95109) getachre@aol.com www.ethiopiansemay.blogspot.com

ብዙዎቹ-የተቃዋሚ ድረገጾች፤ የተማሩ የፖለቲካ ተንታኞች-ኢትዮጵያውያንና የተገንጣይ ቡዱኖች በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ ዓረብ ዓለም ውስጥ ካለው ሁኔታ እና ሕሊና አንድ አድርገው ሲመለከቷቸው ሰሞኑን ታዝቤአለሁ። በግብፅ በቱኒዝያ እና በየመን በኢራን በፓኪስታን በኢራቅ በመሳሰሉት የዓረብ እና የእስላም አገሮቸ ያለው የመንግሥት ጭቆና ከማንም ዓለም ጋር ካገራችንም ጭምር የሚያመሳሰሉበት ሁነታዎች ቢኖሩትም አብዛኛዎቹ ምሀራን ሲገመግሙ ወይንም ሲያመሳስሉ የጭቆናው መልክ ተመሳሳይነት በመመርኮዝ ብቻ ባገራችንም የቱኒዝያ ወይንም የየመን እና የግበጾች ዓይነት ያደባባይ በዓመጽ የታጀበ ሕዝባዊ የሥርዓት ተቃውሞ በቅርቡ እንደሚከሰት ተንብየዋል። ያ ግን ኢትዩጵያ ምድር ውስጥ አይሰራም። ለምን?

ምክንያቶቹ ብዙ ናቸው። የአረቦቹ/የእስላም አገሮች የመሰለ ሕዝባዊ የጎርፍ ዓመጽ የማይከሰትብት ቀንደኛው እንቅፋት አንዱ “አገራዊ ፍቅር አነግቦ ከእሳት ጋር የሚጋፈጥ የኢሕአፓ ዓይነት ወጣት” ኢትዮጵያ ውስጥ የለም! ለወደፊቱም አይበቅልም። ያ ወጣት ከነ ብዙ ግብታዊ ስሕተተቶቹ በምንም መልኩ የሚወዳደረው ያ ትውልድ መሳይ ጠንካራ ልበ ደንዳና ወጣት በዓፍሪካ ቀርቶ በዓለምም አይኖርም”። ስለሆነም ሕዝቡ ያ ዓይነት ወጣት በሕጋዊነት /በይፋ የሚንቀሳቀስ በብዛት ስለሌለው ክፍተቱ ሕዝቡ ለጥቃት ተጋልጦ ረግቶ ተቀምጧል። ያ ክስተት እንዳለ ሆኖ፦“የአሁኑ የዜጎች ሕሊና ከቀደምቷ ኢትዮጵያ የሕሊና አስተሳሰብ በእጅጉ የተለየ ነው”። ግበጾች፤የመኖች፤ቱኒዝያዎች አገራችን የሚሏት ዬራሳቸው አገር እንዳላቸው ያምናሉ፡ በዛሬቱ ኢትዮጵያ ያለው ዜጋ ግን አርባ ኣራት ባነዴራ ለብሶ እአውለበለበ አገሬ የሚላት አገር በሕሊናው የተቀረጸች አገር የለውም። የተምታታ ሕሊና ፤የተምታታ አገራዊ ስሜት ያነገበ ነው። አገሩ ለሱ አውራጃው እና ብሔሩ እንዲሆን ላስራ-ስምንት ዓመት ተሰብኳል፡፤ መሸጥ መንከባከብ መለወጥ ማስተላለፍ መስጠት የሚያሽችል የመሬት ባለቤትነት እትብት የሌለው ገበሬ እና የከተማ ኗሪ የዜግንት ምንነት እትብቱ በጠመንጃ ሃይልና በብሔረተኛ ክልልተኛነት ስሜት የተበጠሰበት ዜጋ ስላለቺው “አገር” ደንታ እንዳይኖረው አድርጎታል። ደንታውና አትኩሮቱ “ከራሴ በፊት ላገሬ ለሰነደቃላማዬ” ሲባል የነበረው የጥንት መርሆ ሳይሆን ከለት ዕለት ከመራሹ መነግሥት ተከራይቶ የሚያገኛት የምግብ ማስጌኛ ብጣሽ እርሻ መሬቱ ራሱን እንዴት ማስኖር እንደሚችል የታጠረ ሕሊና ውስጥ የገባ ማሕበረስብ ነው። ሕዝባዊ ዓብዮት የሚቀሰቀስ አገሬ የሚላት አገር ስትኖር ነው። ዛሬ አገሬ የሚላት አገር የሌለው የተምታታ ሕሊና “መንግሥት ለውጦ” ስለ አገር የሚቆረቆር ሕሊና የሚዋደቅ ሃገራዊ ፓን ኢትዮጵያኒዝም ማሕበረስብ የለም።ከኖረም ጥቂት ነው። ቆሞ በድፍረት ኢትዮጵያ ትቅደም ብሎ በጠባብ ብሔረተኛው ሥርዓት ፊት ዓብዮት የሚያስነሳ ሕብረተሰቡን በግምባር ቀደም መምራት የሚችል ወጣት ተቃዋሚ ስለሌለ ሕብረተሰቡ የማይንቀሳቀስ የረጋ ውሃ አድረጎታል።

ለሕብረተሰብ ግበታዊም ሆነ አዝጋሚ ለውጥ ለማምጣት ያገሩቱ ወጣት ራሱን በኢትኦጵያዊነትና በዓለም አቀፋዊ የሕዝቦች አንደነት የሚያምን ወጣት ሲገነባ ወይንም ሲኖራት ዓብዮት/ዓመጽ ሊከሰት ይችለላል። በኢትዮጵያ ሁኔታ ዛሬ ያለው ወጣት “ኢትዮጵያዊ” ወጣት ሳይሆን “ትበገራዊ”፤ “ኦሮሚያዊ” “ወላይታዊ’ ሶማሊዊ፤ በአደሬዊ…..ነት የተጠለፈ ወጣት ነው። የተለያዩ ነገዶች የምታስተናግደው በአገሪቱ ርዕሰ ከታማ የምትገኘው የቀዳማዊ ሃይለስላሴ/አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስንመለከት ተማሪው በትግራዊነትና በኦሮሚያዊነት አጥር አጥሮ ቅራኔ ፈጥሮ ሲካሰስ፤ ሲጋደል እና ሲናቆር የሚገኝ ወጣት ነው። በገጠሩ ማሕበረሰብ በኦሮሞ ገጠሮች ውስጥ ተሰማርቶ ሕጻናት ልጆቹን ጭሮ ግሮ የዕለት ምግቡ ለመመገብ የሚፍጨረጨር የአማራ አዛውንት፤ወጣት እና አመጫት በአማራነቱ እየታፈሰ እየተገደለ እመቻት ከሕጻናት ልጆቻቸው ወደ እሳት እየተጣሉ ሕይታቸው ለማትረፍ ሲሸሹ እንደ ጀግራ በጥይት ሲታደኑ ወጣቱ በየትምሕርተ ተቋዋማቱ እሱም በአማራነትነ በኦሮሚያዊነት ወይንም በትግራዊነት ዜግነት እና ማንንት ገብቶ የሚዳክር እና ወደ ገዢው ቡድን ሳይሆን ወደ ራሱ እርስ በርሱ በድንጋይ የሚወራወር እና በቢላዋ የሚጨፋጨፍ ወጣት ስላልነቃው ሕብረተሰብ ደህንነት እና እጣ ፈንታ ስለ መንግሥት አስተዳዳር ለውጥ ደንታ የሌለው አድርጎታል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ወያኔ ሰራሽ ባንዴራዎች ተሸፍኖ ኦሮሚያ ዊ ትገራዊ አደሬዊ፤ሶማሊዊ፤ጉራጌዊ፤ሃዲያዊ፤ከምባታዊ የደቡብ ሕዝቦች ብሔር ብሔረሰብና ሕዘቦች ዊ…. የማንነት ተኮር መታወቂያ እንዲይዝ ሲታዘዝ ተቃዉሞ የላሰማ ወጣት እንዴት ሲኮን አገር አለን ብለው ከሚታገሉ አንድ ሰንደቃላማ እያውለበለቡ ሁሉም አንዲቷን ሰንደቃላመቸውን እየሳሙ እና ለብሰዋትና አንድነት ከበሬታ ኪመጮኹ የግብፆች፤ቱኒዚያዎች፤ የመኖች፤ ኢራን… ወጣቶች ጋር ትይዩ አድርጎ በኢትዮጵያም ተመሳሳይ ዓብዮት ሊከሰት ነው ማለት እንችላለን?

ስለ ተቃዋሚ መሪዎች ማንሳት በሽታ ስለሚቀሰቅስ ሳይነሳ ብንተወውና በዛው በማይረባው ተቃዋሚ ባንነጋገርም ቱኒዚያዎች እና ግብጾች ያለ መሪ ነበር ተነስተው ውጤት እንዲከሰት ያደረጉና እኛም ጋር ሊከሰት ነው፤ ብለው ተንታኞቻችን ተብየዎች ቢተነበዩም፤ የነዚህ አገር ወጣት እና ሕዝብ ከኛው ጋር አይመሳሰልም፤፡ ከላይ ያስቀመጥቁት ምክንያት እንዳለ ሆኖ -የኢትዮጵያ ሕዝብ እና የ እስላም /ዓረብ አገሮች ሕዝቦች ህሊና እጅግ የተለያዩ ተጻራሪዎች ናቸው። የእነዚያ “ድፈርት” ሞት መጋፈጥ ጽድቅ ነው ይላሉ። “አላህ ወ አክበር!!!!” በማለት የጋራ መፈክር አነግበው የሚነሱ ዓመጽ ሲያስነሱ ወደ ስካርነት የሚያዘነብል ቆራጥ ሕሊና አላቸው። “አላህ ወ አክበር” የሚለው የጋራ መፈክር ሕሊናቸው የሚያስነሳ ፓርቲ/ደርጅትን ተመስሎ የን ያከል በአንድነት ስሜት ስለሚያስተሳስራቸው የሚጋፈጡት ጠላትና ስርዓት በቆራጥነት ይገፈጡታል። መንፈሳዊ የጋራ መፈክራቸው ከፖለቲካ ተቃዋሚ ድርጅት መሪ በላቀ መልኩ “በጋራ ወደፊት እንዲስፈነጠሩ ሃይለኛ መጎድ የሚፈጥር ሃይማኖታዊ የሕሊና ትጥቅ አላቸው። በግብጻች የታየውና የሚታየው በክርስትያኑ እና በሕዝብላህ (ኢስላሚክ ብራዘር ሁድ) ያለው ቅራኔ እስከመገዳደል የደረሰ ቢሆንም ቅራኔው ሃይማኖታዊ እንጂ እንደ አገራችን ፖለቲካዊ ስላልሆነ በጋራ ቆመው ስርዓቱን ይቃወማሉ። ያገራቸን ከዚህ ሁሉ የተለየ ነው።

ኢትዮጵያዊ ሕሊና ግበረገቡ ያስተማረው “ትሕትና፤አክብሮት፤ዝግታ፤ትዕግሥት፤ረጋ ማለት፤መንግሥትን፤ዓዋጅን እና ሕግን ማክበር…” ነው። ካሪዝማቲክ (ትግሬዎች ጦብላሕታ- የምንለው “ሸጋ ባሕሪ”) የሚሉት ዓይነት። ቫዮለንት/ሞገደኛነትን ይኮንነናል። ያ ባሕል እና ተፈጥሯዊ ባሕሪ ዛሬ የወያኔ ወመኔ መሪዎች ወደ ራሳቸው መጠቀሚያ በማዞር “ዕድገትና ልማት” “ሰላምና መረጋጋት” የሚላቸው በአሻጥራዊ/አታላይ ውጥመድ መፈክሮች አስገብቶ ሁሉም በነዚህ ወጥመዶች እየተታለለ “በ አልሙናይ፤ እና ባውራጃ፤ በወረዳነት አና በክለልተኛነት” ታጥሮ “መሪሕ ውድብ” (መሪ ድርጅት) ብሎ ለሚጠራው ፖለቲካዊ የሆነ ወደ “ታቦትነት” የተጠጋ “መሪሕ ውድቡ” እንዲከተል በግድም በውድም ሕሊናው ሰግጦ ይዞታል። ይህ መሪሕ ውድብ (መሪ ድርጅት) ኮሚኒስታዊ/ፋሺስታዊ በመሆኑ ሥልጣን ተዋረድ በሰንትራሊዝም/ማዕከላዊነት ስለሚንቀሳቀስ “ በአፓርታይድ ዓይነት የተዋቀሩ ክልሎች” መሪህ ውድቡ (ድርጅቱ ወያኔ/ኢሕአዴግ) የሚያዘውና የሚያስተላልፈው ሁሉ በመፈጸም “በሰላምና መረጋጋት” የማታለያ መፈክር ገብቶ ከአመጽ እንዲርቅ ትምህርት ቤቶች/መጻሕፍተ ቤቶች ብቻ በማነጽ እንዲያተኩር የፖለቲካው ጨዋታ “መሪሕ ውድቡ” ለተባለው የማይገሰስ የማይወቀስ “ፓለቲካዊ ታቦት” ሃላፊነት እና ዕምነት በመስጠት ሕሊናው በህንጻ ግምባታ ተኮር እንዲሆን ስላደረገው ሰማይ ጠቀስ ሕንጻዎች ቆሞ መጽሕፍተ ቤቶች በመጻህፍት ተሞልተው በማየት “ምርቃና” ውስጥ ገብቶ በመሪሕ ውድቡ ላይ እንዳያምጽ የስነ ኣእምሮ ሰላባ በማካሄድ “ሕሊናው ወደ መጎድ” እንዳያዘነብል “ልማትና መረጋጋት” “በመሪሕ ውድቡ” (ብቸኛ የሠርቶ አደር መሪ ድርጅቱ) እየተመራ ጥቂቶች እየተንደላቀቁ ብዙሃኑ በሰላምና መረጋጋት “ዲሲፕሊናዊ መፈክር” አስገብቶ ኢትዮጵያዊ መንግሥት አክባሪነት እና ለሕግ ተገዢነት ባሕሪው ባሰዛኝ ሁኔታ ሰልቦታል።

በቁሙ የተሰለበ ሕሊና ደግሞ አመጽ ላመስነሳት እጅግ አዝጋሚ ከመሆኑ የተነሳ አሁን ካለው የተለየ አስተሳሰብ ያለው ፓን ኢትዮጵያኒዝም ያነገበ ወጣት በታምር ካልተፈጠረ “መሪሕ ውድብ” የተባለ “ፖለቲካዊ የፋሽስቶች/ኮሚኒስቶች ታቦት” እያለ የዓረቦች ዓብዮት በኢትዮጵያ ውስጥ ሊከሰት አይችልም። የሚከሰት ከሆነ ባለፈው ጊዜ ካስቀመጥኳቸው ሦስት ዓይነት ሚሊታሪ/ወታደራዊ/ኩዴታዎች/መፈንቅለ መንግሥት ሊከሰት ይችል ይሆናል (ያ ደግሞ አሁን ሊሆን አይችልም)፡ ያ ሲሆን ደግሞ “መረሪሕ ውደብ” ተብሎ ሥልጣን ላይ ያለው “ፖለቲካዊ ታቦት” ሲደፈር ጠባብ ብሄረተኛውና ጽንፈኛው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ አመራር አባል ስብሓት ነጋ “መንደር መንደራችን” አንድንይዝ በፌርማው አጽድቆልን እሱም ወደ መንደሩ ወደ “ዓዲ ኣቡን” (ዓድዋ) ኦነግ እና ኦጋዴኒያንም ወደ ገጠሪቱ ኦሮሚያ ሪፑብሊክ እና ወደ አጋዲኒያ ምድረበዳ መንደር መንደራቸው ይዘቀው እንሱም በታራቸው ሕዘቡን ልቀትቅጥህ ብለው ህዝቡን ማስለቀስና እርስ በርስ በመንደር የሥልጣን ሽኩቻ ይቀጣቀጣሉ።

ያፍሪካ ቀንድ ተብሎ የሚጠራው ኤርትራም ውስጥ “ያሉት 9 ብሔር ብሔረሶቦች” ደግሞ ኩናማው ዓፋሩ ሳሆው ናራው ብሌኑ ትግራዩ ትግራይ ትግሪኙ የእሳቱ ጭድ በመሆን እርስ በርስ መግባባት አቅቶት “በባቢሎን ግምብ ገምቢዎች ቋንቋ” መነጋገር ይጀምራል ማለት ነው። ያ ሲሆን እንገንጠል ሲሉ የነበሩት የዲአስፖራ የግንጠላ አቀንቃኞች ልጆቻቸው በሰላም እና መረጋጋት አሜሪካ እና ኢወሮጳ በ ፒ ኤች ዲ አስመርቀዋልና “ወይ ፍንክች የአባ ዋራ ልጅ!” ከምኔሶታ ወይ ንቅንቅ! “አንድ ኢንች መነቃነቅ የለም !!!!!” አሉ አይደል ጓድ መንግሥቱ ሃይለማርያም! “ሀገረ ኤርትራ” ከተባለች “ነፃነት! ነፃነት መፂኣ! እያለ ከእልልታውና ከከበሮው” በሗላ ከጣሊያን ከአሜሪካ ከለንደን ከ አምስተርዳም ከጀርመን ከአውስተራሊያ ከሳውዲ ከኢትዮጵያ አንድ ኢንች መነቃነቅ የለም!!! ብሎ ኤርትራና! ኤርትራና! ኤሬ! ኤሬ! ብሎ የጮኸ ሁሉ “መሪሕ ውድቡ” አሜሪካና አውሮጳ አድርጎ የለ! ከሳተላይት ቲቪ ከማንደይ “ፉት ቦል” እና “ካሜሪካን አይድል ሾው” ከገነት ርቆ “የልጠተረገችውን ገጠር ኦሮሚያ” እና “ኦጋዴኒክ ሪፓብሊክ” ማን ኩራዝ አብርቶ ሊኖር? ሆ!ሆ! ሞኝህን ፈልግ!

ስለሆነም የዓረቦች የአደባባይ አብዩት የሚከሰት ከሆነ ስብሃት ነጋ እንዳለው “ሁሉም መንደር መንደሩ” እንዲይዝ ከተፈቀደለት በሗላ “ከተሞች ወደ ገጠር እና መንደርነት ሲለወጡ፤ የእርሻ ቦታዎች የወታደራዊ ማሰልጠኛ ሲሆኑ አስቀድሞ በዋሾች እና ባገር በቀል የውጭ ቅጥረኞች የተሰበከው የ “ሚልክ ኤንድ ሃኒ/Milk & Honey” ሰበካ ወደ ማይጨበጥ ሕልም ሲቀየር፤ ቁጭቱ፤ ወደ ምሬት አምርቶ ግጭት ሲጋብዝ ያኔ ‘በዋሾቹና የመንደር ልዑላን እና ነገሥታቶች” ላይ የዓረቦች የአደባባይ አብዩት የሚመስል ዓመጽና ምሬት ሊከሰት ይችላል። የሶማሌ ዓብዮት እንደ ማለት! አርስ በርስ መበላላት ፤መተላለቅ፡ የመቶ ዓመት ሥራ ቤት የመጠናቀቅ ሂደት እንደ ማለት! ማሰሪያው ኢትዮጵያዊ ሕሊና መሪ አክባሪ ነውና ያለ መሪ ራሱ በራሱ አነሳስቶ ለዓመጽ የመነሳት ልምድ እና ባሕል ስለሌለው የረጋ ወተት ሆኖ ለጊዜው መጠበቁ አይቀሬ አሳዛኙ መርዶአችን ነውና ለሃዘን እንቀመጥ! ስለሆነም ነው ብርቱካን መዲቅሳን ቀና ካለችበት ጎራ ተመልሳ እንዳታንሰራራ አደርጎ ከፖለቲካው ውጭ ነኝ በማለት የታምራት ላይኔን ዕጣ ፈንታ ገጥሟት እሷም “ጌታ እሱስ” ፍለጋ ቁልቢ ገብሪኤል መሄዷ አንዱ የአዲሱ ዓብዮት/የታሃድሶ ሕይወት መንገድ ፍለጋ ምልክት በዜና መበሰሩን ከልቦናችሁ በመያዝ፤ “ጌታ እየሱስ” ያበሰራችሁን ዜና ከልቦናችሁ ያሰድረው ያሳድርልን! አሜን! እንበል 12! አመሰግናለሁ። ደህና እንሰንብት! ጌታቸው ረዳ ኢትዩጵያን ሰማይ አዘጋጅ።www.ethiopiansemay.blogspot.commailto:getachre@aol.com%5C