Monday, February 8, 2021

በግንዛቤ ግጭት ከራስ ጋር እየተጋጩ ያሉት የወያኔ ትግሬዎች የገቡበት ጣጣ! ጌታቸው ረዳ Ethio Semay 02/05/2021

 

በግንዛቤ ግጭት ከራስ ጋር እየተጋጩ ያሉት የወያኔ ትግሬዎች የገቡበት ጣጣ!

ጌታቸው ረዳ Ethio Semay

02/05/2021

የወያኔ ትግሬዎች ብየ ስል “ወያኔን የሚደግፉ ትግሬዎች ማለት ነው””

ወደ ርዕሴ ከመግባቴ በፊት ባለፈው ወር ስለ አክሱምና የታጠቁ ኤርትራኖች ጉዳይ በሚመለከት ሲወራ ዛሬ መረጃው እንዳገኘሁት “የታጠቁ ኤርትራኖች አክሱም ቤተክርስትያን በመግባት ግጭት እንደፈጠሩ እውን መሆኑን መረጃ አግኝቼአለሁ። ምንጮቼ እንደሚሉት መጀመሪያ 4 ታጣቂዎች መጡ፤ ምዕመናኑም ጫማችሁን ካላወለቃችሁ አትገቡም በሚል ግብግብ ተፈጠረ፡ ከዚያም 40 የሚሆኑ ታጣቂዎች ቤተክርስትያኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ ስለነበሩ እነሱም ወደ ግብግቡ በመግባት ግጭት ተፈጥሮ እንደነበር እና የተከሰተው ሁኔታ ግን በስፋት ከመግለጽ ተቆጥበዋል። በከተማውም ሰዎች በጥይት የተገደሉ እንዳሉም ሲነግሩኝ የግድያው ሁኔታም ዝርዝር ውስጥ ሊገቡ አልፈለጉም።

ምንጮቼ እንደነገሩኝ ነዋሪዎቹ ኤርትራዊያኖቹን ሲገልጽዋቸው እጅግ ሲበዛ “ዋይልድ” በሚል ቃል ነው የሚገለጽዋቸው~! ሌላ ቀርቶ ለምን ፍላጎት እንደፈለጉት ባይታወቅም “የእሳት መጫሪያ” ሳይቀር ወስደዋል” ሲሉ ከአገር ቤት መንጮቼ ነግረውኛል። ያም ሆነ ይህ አሁንም ገለልተኛ መርማሪ እስኪገባ ድረስ ሁኔታው “በክስተት” እናስቀመምጠው። አሳዛኝ ታሪክ ነው።

 

ወደ ርዕሴ ልግባ

ወደ ትንታኔየ ከመግባቴ በፊት አንድ ነገር ለመግለጽ የምፈልገው ሕዝብ ወይንም ትግሬዎች ብየ ስገልጽ ብዙ ሰዎች “ጠቅላላ ሕዝብ” የሚል የደነቆረ መረዳት በመያዝ “ጠቅላላ ሕዝብ” እንዴት ይጠቀማል/ይወቀሳል/ይወነጀላል……. ወዘተ እያሉ አተካራ ሲገቡ ስለማደምጥ ፤ በኔ ትንታኔ “ሕዝብ ስል ብዙውን ጊዜ የገጠሩን ገበሬ ሳይጨምር ከተሜው እና ምሁሩ በጅምላ እንዲሁም ውጭ አገር የሚኖሩ በጅምላ (99% አብዝሃው) መሆኑን እንድትገነዘቡልኝ ደጋግሜ ግንዛቤ ለማስያዝ እፈልጋለሁ። ነግር ግን “ጠቅላላ ሕዝብ” እንደ ሕዝብ በማንኛውም አገር ሃላፊነቱን ባለመወጣት የሚጠየቅበት ሁኔታ እንዳለም ላስጨብጣችሁ እወዳለሁ።

 ይህ ካልኩኝ ዘንድ ግንዛቤ የሚለው ቃል እኔ እንደገባኝ አንድን ነገር በቅጡም ይሁን በጎዶሎ መልኩ በጎጂም ይሁን በበጎ መልኩ የመረዳትን ሁኔታ የማሳያ ቅባሌ (ኮንሰፕት) ነው። በዚህ ትንታኔ መሰረት “ትግሬዎች” እያልኩ ወደ እምነትነው “ከራስ ጋር የገቡበት የግንዛቤ ግጭታቸው” ልግባ።፡

 

ትግሬዎች ለ27 አመት በደገፉት መንግሥታቸው በኩል የጦፈ ምቾት እና የበላይነት ማን አህሎኝነት በማስተጋባት በዘፈኖቻቸው እና በአካላዊ ስነ ምግባራቸውም ይሁን ላቅ ሲልም የራሳቸው መንግሥት ብለው በሚጠሩትና በሚደግፉት ሥርዓት እየኖሩም ቢሆን “ግልጽ በሆነ የሕግ ጥሰትና አድልዎ” በሺዎች ምናልባትም በሚሊዮን በሚገመቱ ብዙ ትግሬዎች በሕጋዊ መንገድ “እንደተበደሉ” በማስመሰል ወደ ውጭ አገር እንዲወጡ የመደረጉ አስገራሚ ድርጊት ወደ ከፍታዊ ምድራዊ ገነት ተሰቅለው እንደነበር የሚረሳ አይደለም።

 

 50 አመት እና ከዚያም 100 አመት እንገዛችሗለን ብለው በግሃድ ሲፎልሉ የነበረውን ማን አህሎኝነት ሳያስቡት ድንገት ከተሰቀሉበት ምድራዊ ከፍታ ወደ መሬት ሲፈርጡ የነበረው እንዳልነበረ ሆኖ ሲያዩት ራሳቸውን ባልጠበቁበት ዝቅታ አገኝተውታል። ውጭ አገር የሚኖሩ ትግሬዎች ዛሬ በየአለማቱ በባቡር ሀዲዶችና አውራ ጎዳናዎች ላይ ለተመልካች በሚገርም ትዕይንት ራሳቸውን በቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጥቁር ፕላስቲክ ተጠቅልለው አስፋልት ላይ በመንጋለል “በትግራይ ሕዝብ ሰቆቃ ስም” ሽፋን አድርገው “ድርጅታቸው በደረሰበት ሽንፈት ድንጋጤው ብርቱ ስለሀነ” አውነታው እያወቁም ቢሆን ‘ያንን ሽንፈት ላለመቀበል ሲሉ ሌት ተቀን ሲጮኹ’ እያየን ነው።

አንድ ነገር ልንገራችሁ፡

ዛሬ የወያኔ ምሁራን እና ጀሌዎቻቸው በየ አለማቱ እያሳዩት ያለውን ጩኸት ማለትም “የትግራይ ሕዝብ መራብ፤መፈናቀል፤ ግድያ………ወዘተ” እያሉ ያሉት የጩኸታቸው መነሻ ተከሰተም አልተከሰተም “ድርጅታቸው ከሥልጣን በመባረሩ ምክንያት አሁን እያደረጉት ያለውን ጩኸትና ውሸት ከማስተጋባት አይቆጠቡም ነበር። ምክንያቱም መነሻቸው የትግራይ ሕዝብ ተደበለ ሳይሆን መሪዎቻቸው ከሥልጣን ተባርረው በካቴና መታሰራቸውን የጩኸታቸው ዋናው መነሻ መሆኑን አትዘንጉ። ስለ ትግራይ ሪፑብሊክ መመስረት እቅድ በየ አለማቱ የሚገኙ ትግሬዎች በየአመቱ መቀሌ ውስጥ እየተሰበሰቡ የመገንል ጠበብት ነን የሚሉ ምሁራን የበደፉት እቅድ አዳራሽ ላይ ሲተላለፍ የነበረው ትምህርት እና ውሳኔ ከ7 አመት በፊት ሰፊ ጽሑፍ በድረገጾች ላይ ማቅረቤ ይታወሳል። ምናልባትም በቅርቡ ያንን እለጥፈዋለሁ። ወቅቱም “ኦሮሞ እና አማራ’ አካባቢ ሰፊ ተቃውሞ ሲቀሰቀስ በነበረበት ወቅት “ለድርጅታቸው አስጊ እንደሆነ አምነው ለግንጠላ መደራጀት አንዳለባቸው ያስታወቁበት ወቅት ነው።

ሁሉም እንደሚገምተው የሁኔታዎችን ድንገት መለዋወጥ በትግሬዎች ሕሊና የግንዛቤ ግጭት ታይቷል። በምሁራን እና ባልተማሩ ትግሬዎች ሕሊና ውስጥ ሁለት የሚቃረኑ እምነቶችን እና  እሴቶችን በመያዝ ከገጠማቸው ድንገተኛ ለውጥ ለማምለጥ ሞክረዋል። አንዱ መሸነፋቸውን አምነዋል፤ ሌላው ሽንፈታቸው መቀበል ግን ዳገት ሆኖባቸው ማምለጫ ሲፈልጉ ይታያሉ።

ለ47 አመት የተከተሉት የህወሓት የፋሺስቶች መርህ በድንገት መፈርከሱ በድርጅታቸው አሳድረውት የነበረው ዘላለማዊ “እምነት” ድንገት መፍረሱ ብቻ ሳይሆን፤ መሪዎቻቸውን የሚማርክ ምድራዊ ሃይል የለም ሲሉ የተመኩበት ምላሳቸው በሚገርም ባጭር ጊዜ  መሪዎቻቸው ከተሸሸጉበት ገደል በገመድና በቃሬዛ እየተጎተቱ በካቴና ታስረው በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት በቴ/ቪዥን መታየታቸው፡ በጣም፤በጣም፤እጅግ በጣም በሚባል ድንጋጤ ውስጥ ስለገቡ ሁለት አማራጮችን ይዘዋል

(1) ኢትዮጵያን እንደ አገራቸው ባለማየት ኢትዮጵያ መፍረስ ማየትና የዛሬዎቹ ዘመናዊ የሱዳን ድርቡሾችን መደገፍና አብሮ ኢትዮጵያን መውረር ለሽንፈታቸው አማራጭ አድርገውታል

(2)ትግራይን ከኢትዮጵያ መገንጠል (የቆየ መርህ እንደሆነ ብናውቅም) ። እነዚህ መስመሮች ሊከተሉ ያስቻላቸው ምክንያት የማይመች ስሜት ውስጥ መግባታቸው ማሳያ ነው።

 ማወቅ ያለብን አፍረውና ተሸማቅቀውም ቢሆንም ሰዎች በተፈጥሮ በአመለካከታቸው እና በአስተያየታቸው ውስጥ ያላሰቡት ቅራኔ ሲገጥማቸው ለየት ያለ ከቀገጠማቸው የሕሊና መጋጨት (ስቃይ) ለመሸሽ ሲሉ አስገራሚ ውሳኔ ውስጥ ይገባሉ። ለዚህ ነው ከላይ የጠቀስኩዋቸው ወጥነትን የመፈለግ አዝማሚያ እያየንባቸው ያለነው። በሚገርም ሁኔታ ሌለው ኢትዮጵያዊ ምሁርና ብዙውኑ ዜጋችን በወያኔ መገርሰስ ሲደሰት በተቃራኒው “በምሁራኑም ሆነ በተራው ትግሬ ግን የመረበሽ ስሜት እያየንባቸው ነው”። ኢትዮጵያዊያን እና በወያኔ ጀሌዎች መካካል እየታየ ያለው ይህ አለመመጣጠን ትግሬዎች የተከሰተባቸው የመረበሽ ስሜቶችን ለመቀነስ ይረዳናል በሚሉዋቸው ጎጂ በሆኑ የማምለጫ ሰላማዊ ሰልፎችንና አገራዊ ክሕደት እየተሳተፉ ነው ፡፡

አሁን እነዚህ ሰዎች ለማስረዳት አይቻልም። ክህደት ውስጥ ገብተዋል። ክስተቱ እውን መሆኑን አይተዋል፤ እንደገና እራሳቸውን ላለመቀበል የህሊና ተቃርኖ ውስጥ ገብተዋል። ውጥረታቸውን ለመቀነስ ትግሬዎች መሪዎቻቸውን የገረሰሰው ለውጥ በተለያዩ መንገዶች ለማቃለል ሞክረዋል። ለውጡ አይቀሬ ሆኖ ተከስቷል፡ ነገር ግን ከእምነታቸው ውጭ ማንም ይሁን ምንም ክህደት ውስጥ ስላሉ የኢትዮጵያን ሕልውና እና አዲስ ለውጥ ሊቀበሉ ዝግጁ አይደሉም።

መሪዎቻቸው ሲወስዱዋቸው የነበሩት የወንጀል ድርጊቶች ምክንያታዊ ለማድረግ በዓለም ውስጥ የውሸት ድምጽ በማስተጋባት ድርጅታቸው እና መሪዎቻቸው በሠሩት ነገር ላይ የማፈር ስሜት ሳያድርባቸው ወንጀላቸውን ለመደበቅ ሌት ተቀን አደባባይ ላይ እንደተበደሉ መስለው መታየት የክሕደታቸው ምልክት አንደኛው እና አይነተኛው ትዕይንት ነው። አሁንም እንደ ጥንቱ በትግራይ ሕዝብ ስም ሽፋን የድርጅታቸውን ከሥልጣን መወገድ እሮሮ ማስተጋባት!!!

ድርጅታቸውም ሆነ እራሳቸው ጀሌዎቹ ከዚህ በፊት ባደረጉት ነገር የጥፋተኝነት ስሜት ወይም መጸጸት ማድረግ “ተሸናፊነት” መስሎ ስለታያቸው ውስጣዊ ስቃይ ውስጥ በመግባት እኛን ለማሳየት የማይፈልጉት “ነገር ግን” በራስ ቅራኔ ውስጥ ገብተው ጭንቀትን ሓፍረትን ቁጭትንና ሐዘንና ልቅሶን የለት ተለት ውጥረት ውስጥ በመግባት በተስፋ ቆራጭነት ጎዳና እየተጓዙ ነው።

የወያኔ ትግሬዎች የተሸነፈው እምነታቸውን ወይም ባህሪያቸውን ድንጋጤአቸውን ከተቀረነው ለመደበቅ ሲሉ ከላይ የተጠቀሱ ችግሮችን ከውስጣቸው እየተጋፈጡ በትግራይ ሕዝብ ስም ሽፋን የፋሺስቶችን የነገድ ፖለቲካ እያስተጋቡ ናቸው። ይህ ሁሉ በየአደባባዩ መጮህ ጥፋተኝነት ስሜትን ለመቀነስ የሚያስተጋቡት ሽፋን ሁለት ጊዜ መሞት ነው፡፡

አመሰግናለሁ ፡

ጌታቸው ረዳ Ethio Semay