Wednesday, January 16, 2019

ኢሳያስ ወያኔን ይመታልናል ስትሉ የነበራችሁ ነፈዝ ኢትዮጵያውያን ሁላ ይህ እፍ እፍ ፍቅር እዩ’ እና እርማችሁን አውጡ! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)


ኢሳያስ ወያኔን ይመታልናል ስትሉ የነበራችሁ ነፈዝ ኢትዮጵያውያን ሁላ ይህ እፍ እፍ ፍቅር እዩ’ እና እርማችሁን አውጡ!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
ትግራይ ትግርኚ ቀስ እያለች በእግሯ እየተራመደች እንደሆነ ለበርካታ አመታት ነግረናል። ትግሬ ለትግሬ አህያ ላህያ ቢራገጥ “ጥርስ አይሰበርም” ሲባል ሰምታችሁ አታውቁም? ከ20 አመት በፊት ሁለቱ ትግሬዎች ተሸክመውት የመጡ የበረሓ ጅኒ ውቃቤአቸው ተነስቶባቸው በባድሜ ሰበብ እርስበርሳቸው ሲራገጡ አንዳቸውም “አለቆች” ሳይጎዱ 
የሙሶሊኒ እና የሂትለር እፍ እፍ ፍቅር በተግባር ሲታይ
የተጎዳው ሳሩ (ሕዝቡ) ነበር። ወያኔ እና ሻዕቢያ ለ80ሺሕ በላይ ሕዝብ የሞት እና የስደት መዘዝ ሆነው ‘አንዳቸውም መሪዎች’ ተጠያቂ ሳይሆኑ እነሆ ከ20 አመት በላ ለብዙዎቻችን ግልጽ ባልሆነልን ግንኙነት መጨረሻ ደብረጽዮን እና ኢሳያስ ሻቢያ እና ወያኔ ‘እጅ ለእጅ’ ተያይዘው እርፍ አሉ!

ስትሉት የነበረውን የተሞኛችሁበት አባባላችሁ ላስታውሳችሁ። እንዲህ ነበር ስትሉ የነበረ፦ “አሁን ኢሳያስ ወያኔን በሰሜን በኩል መክቶ ይይዝል እና የወያኔ ወንጀለኞች በቀላሉ መቆጣጠር ይቻላል፥ወያኔ (ጌታቸው አሰፋ) በሁሉም በኩል ተከብ’ቧል የትግራይ ትግርኚ ሕልማቸውም ይቀጫል የወያኔ ግብኣተ መሬትም ተቃርቧል ፥…ወዘተ.ወተዘ.. ስትሉ የነበራችሁ ነፈዝ ኢትዮጵያውያን ሁላ ይህ የእፍ እፍ የፍቅር ፎቶ ስታዩ እርማችሁን አውጡ!!!ስሜታችሁ ተቆጣጠሩ እና በግድያ በዝርፍያ የተሰማሩ እጃቸው ላይ ደም የተቀቡ ፖለቲከኞችን እትመኑ ስንል አትሰሙንም!! አብይ አሕመድ ጥሩ ተናጋሪ ነው ፤በስሜት ብዙዎቻችሁን ያስመረቅናል ፤ግን ተግባር ላይ “ሙሾ ነው!’ እንዳሉት የጓድ ሊቀመንበር መንግሥቱ የማትረሳ አነጋገር!

      ኢትዮጵያውያን ምሁራንም ሆኑ ወጣቱ ትውልድ ያው ሁሉንም ከፍቶ መስጠት የለመደባቸው “ኮምፕሮማይዘሮች እና አኮመዲተርስ’ መሆናቸው ዓለም ያወቀው ባህርያቸው ስለሆነ ዛሬም ይህንን ሰንገልጽ “ታዲያ ምን አለበት? የምንፈልገው እኮ ይህንን ነው” እንደሚሉኝ መልሳቸው ገና አፋቸው ሳይከፈት አውቀዋለሁ።ስለሆነም ነው ተገንጣዩ እና ሽብርተኛው ጸረ አማራው ኦሮሚያ ነኝ የሚለን ኦነግ አዲስ አበባ ቁጭ ብሎ ወታደሮችን እና ምስኪን ኦሮሞዎችና ኢትዮጵያውያንን ሲገድል፤ሲዘርፍ ሲያፈናቅል፤ ዳውድ ኢብሳ ለፍርድ ይቅረብ፤ ዳውድ ኢብሳ ወደ አሥመራው ይባረር ብለው ሰላማዊ ሰልፍ የማያደርጉት አኮሞዲሰት ስለሆንን ነው። ምክንያቱም አብይ ፈቅዶላቸዋል እና እንደፈለጉት መሆን ይችላሉ፤ (ኦንሊ ኦን አብይ አሕመድ’ሰ ወርልድ!!!) ።

ኢትዮጵያውያን በባህሪያቸው (እኔን አይጨምርም) “ኣኮመዲተሮች እና ሰነፍ ኮምፕሮማይዘሮች” ናቸው። ጠላትን እና አራጃቸውን በማስተናገድ የታወቁ ራሳቸውን እና ሕዝባቸውን ለእርድ የሚያቀርቡ የጥንቶቹ አይሁዳውያን “አብርሃም እና ሳራዎች” ናቸው። (ይባስ ብሎ ዛሬማ ቀሳወስቱ እና ሼኮቹ ወደ መቀሌ ሄደው ወያኔ እና ብኣዴን ሊያስታርቁ ሄደዋል፤ የጉድ ጉድ ነው! ወደ ድሮአችሁ ተመለሱ እና ሕዝቡን ንደገና ፍጁት ብለው ቁጣቸውን እንዲያበርዱ እና እንደ ጥቱ እንዲሆኑ ነው ተልኡኮው!!)”” ኢትዮጵያውያን በእንደዚህ ያሉ የሃይማኖት ደላላዎች ‘መናፍሰት’ ሲመሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ “እየዘለሉ ኢሳያስን እያነቁ እንዴት ያቅፉ እና ያለቅሱ እንደነበር በቪዲዮ ኣይተናል አይደለም እንዴ?

ይህ ሰው አባታቸውን እናታቸውን በምጽዋ ባሕር ያረደ  ሬሳቸውን ያቀጣለ ፥ ንብረታቸው ዘርፎ “የጥርስ ወርቃቸው ሳይቀር አውልቆ ያባረራቸው ‘አረመኔ ናዚ” መሆኑን ቢነገራቸውም ኢትዮጵያውያን “አስተናጋጆች” ናቸው እና የፈሰሰው ደም ከመጤፍ ሳይቆጥሩት ኢሳያስ ወደ አዲስ አበባ እና ጎንደር ሲመጣ ለመታረድ እንዳማራት ሚዳቋ/ዶሮ ወንዱ ሴቱ ሙሁሩ ያሽካኩ ነበር። ኢትዮጵያውያኖቹ ይባስ ብለው የኢሳያስ ባንዴራ ምልክት ከፊታቸው ቀለም እየቀቡ የመስቀል ደመራን ሲያከብሩ ከናቴራቸው ሁሉ የሻዕቢያ ባንራ ያለው ቀለም ለብሰው እንደ እብድ ሲዘሉ ማየት ሆድ ቁርጠት ከማስነሳቱ አልፎ “ከብትነታቸው” በየትኛው ጠንቋይ ማስቆም እንደሚቻል ሲታሰብ እጅግ የሚያደክም መፍትሄ የታጣለት ጉደኛ ባሕሪ ነው።

ተቃዋሚ የሚባሉት ደደቦች እማ ይህንን የወያኔ እና የሻዕቢያ “እፍ እፍ ፍቅር” ሲመለከቱ በተለይ ግንቦት 7 የተባለው የኦነግ አጎብዳጅ እና የሻዕቢያ ቱልቱላ በደስታ እንደሚፈነድቅ አልጠራጠርም (ሰማያዊ የሚባለው ግም እዛው ደምሩት ያው ከግንቦት 7 ጋር የተደመረ ነውና)። ሌሎቹ (እነ በየነ ጴጥሮስ መረራ ወዘተ….እንደሌሉ ቁጠሩዋቸው፡ ያው የምናውቃቸው ፡”ኮመዲያኖች ናቸው”። የጊዜ ጉዳይ እንጂ ተቃዋሚው ከደብረጽየን ጋር እንደሚተቃቀፉ ጥርጥር የለኝም። አስመራ ግምጃ ቤቶች ውስጥ ታሽገው የነበሩት እነ ግንቦቴዎች እማ አለቃቸው ተቃቅፏል እና ለነሱ መተቃፉ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ያው የምናየው ይሆናል።

ተቃወሚ ተብየው አብይ እስከፈቀደ ድረስ “አይጎረብጣቸውም”። ከጥቂት ጊዜ በላ የደብረጽዮን እና የኢሳያስ መተቃቀፍ “አርኣያ ነው እና” በዘምባባ እና በጭብጫባ መቀበል አለብን ብሎ እንደሚሰብኩዋችሁ አልጠራጠርም። ሁሉም ስለ ማይጨበጠው “ፍቅርና መደመር” በሚባል ‘ኦፕየም’ ነፍዟልና እንከን የለውም። ሰላም እና እርቅ ሲባል ተቃዋሚው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ተገዢነታቸው ለሁለተኛ ጊዜ ለወያኔ እና ለሻዕቢያ የሚያረጋግጡ ናቸው ብየ ነበር ከሁን በፊት ዛሬም በአብይ አሕመድ ወይንም በቀሳውስት እና ሓጂዎቹ  ወኪልነት አደራዳሪነት እነሱም ከደብረጽዮን ጋር እንደሚደመሩ አያከራክርም። ይህንን አትጠራጠሩ! ኢሳያስም አስታረቂ ሊሆን ነው።

ሟቹ ወዳጄ እና መምህሬ ዶ/ር አለሜ እሸቴ The December 18-22 Addis Ababa  Peace & Reconciliation Conference በሚለው ሰፊ ሃተታቸው ውስጥ አንዲት ምዕራፍ የጻፉዋትን ይዤአት እንዲህ ብለው ጽፈው ነበር፦

Again They Tell us lies በሚለው ንኡስ ርዕስ እንዲህ ይላሉ፤-

“Once again, as usual, as we have been used for the last many years, they, those same organizations which never changes as if their existence depends on the non-existence of Ethiopia, as if they are commanded by the stirring of a pay-master, those same organization keep on telling us lies, keep on telling us , we Ethiopians, that they stand for Ethiopia unity while we know, we have known for years, that they have been dissolving Ethiopia, in collaboration with TPLF and EPLF, in the poison of the nihilist super-power imposed dogma of “self-determination up to secession”, to apply only to Ethiopia- stigmatized as on “empire state” made up of “colonies” and “oppressed tribes” or nations and nationalities.

Now while we know, and they know that they have sealed and signed the same nihilist dogma at the Paris Conference of March 11-13, the participants of the so called “peace and Reconciliation Conference” where they sat with such blood-stained ethno cleansers as the OLF of the Arba Gugu, Bedene, Assosa…massacres. OLF which keeps even now telling us that is has not moved an inch from its position of carving out the greater part of Ethiopia to form its Republic of Oromia,” with capital at Finfine-that is Addis Ababa…….”

እያሉ በተንተን ተቃወሚ ተብየው ፓሪስ ውስጥ ባሳለፈው አንቀጽ 6 (VI) ባሳለፈው ውሳኔ ማለትም “”The Conference reaffirms the right of people to self determination in accordance with the united nations Declaration of Human Rights of 1948” ይነበባል በማለት ወያኔ እና እነዚህ ተቃዋሚዎች “ሰልፍ አድምኒሰትረሽን” የሚሉት ትርጉም አንድ መሆኑ እና ተቃዋሚው ፍጹም አገር አቀፍ አጀንዳ እንደሌለው ያስታወሱበት ጽሑፍ ነበር።

ዛሬም በወያኔው ደብረጽዮን እና በኢሳያስ እንዲሁም በበቀለ ገርባ እና በኦነግ ፍልስፍና ተቃዋሚ ተብየው “መለሳለሱ” እንደማይቀርላቸው የቆየ ትዝታችን ትምህርት ነው። ስለዚህ የኢሳያስ አፈወርቂ እና የወያኔ ጥላቻ ለ27 አመት የዘለቀ ከልብ የመነጨ ጥላቻ ነበራቸው የምትሉ “ከብቶች” እባካችሁ ተሳስታችልና እርማችሁን አውጡ። ከወዲሁ አፓርታይዱ ወያኔን ከኢሳያስ እና አብይ ጋር አብረን በማበር ማስወገድ እንችላለን የምትሉ “የዋሆች” ያ “ደሊዥን” እንደማይቻል ከላይ በፎቶ እንዳያችሁት “እፍ እፍ ፍቅር” ትምህርት እንደምትቀስሙ ተስፋ አደርጋለሁ።

ዳዊት ወ/ጊዮጊስ እና ካሳ ከበደ እንዲሁም ንአምን ዘለቀ እና ብርሃኑ ነጋ ከነ አንዳርጋቸው ጋር ሆነው “ኢሳያስ አፈወርቂ” ለኢትዮጵያ በጎ አሳቢ ነው’ ሲሉዋችሁ የነበሩት የፖለቲካ ደላላዎቻችሁ ይኼው በተግባር “በጎ አሳቢነቱን” ከደመኛችሁ ወንጀለኞችን ከሸሸገው ከወያኔው ደብረጽን ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘው እንደሙሽራ ሲንሸራሸሩ ይኼው በጎ ምኞቱን ለኢትዮጵያ በገሃድ ፎቶግራፉ ላይ እየነገረን ነው!! ደላለቹ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ወንጀለኞችን ወደ እምትደብቅ ወደ ትግራይ ሄደው ያንን አፍ እፍ ፍቅራቸውን ልክ እነደ ኢሳያስ እንደማያሟሙቁላቸው በእርግጠኛነት ማስረገጥ አይቻልም።ምክንያቱም ሁሉም ኢትዮጵያን ተብየ ተቃዋሚዎች በተለያዩ ቡድኖች ሆነው ሲያበላሹ ሲያሳስቱ ሲያጋድሉ እና ሲገድሉ እንዲሁም ሲቦተልኩ የነበሩ ያንድ ስልቻ ዘመን ውጤቶች ናቸው።  

ስለዚህ ኢሳያስ ወያኔን ይመታልናል(ከወደ ሰሜን ወጥሮ ይይዝልናል) ስትሉ የነበራችሁ ነፈዝ ኢትዮጵያውያን ሁላ ይህ እፍ እፍ ፍቅር እዩ’ እና እርማችሁን አውጡ! የወያኔ ጀሌዎች እና ሻዕቢያ ጀሌዎች በተለይም የወያኔ ጀሌዎች (በተለይ የገዛ ተጋሩ ሃፍረተቢስ “እንደርታዎች”) መሪዎቻቸው ተቃቅፈው ስላዩዋቸ በየፓልቶኩ ምን እያሉ ይሳለቁባችሁ እንዳሉ ብትሰሙ መፈጠራችሁ ታቆሙ ነበር።
ጌታቸው ረዳ (ኢት ሰማይ)