Tuesday, June 15, 2021

አማራ በተለይ የሸዋ ሕዝብ ሥልጣኑን እንዳንቀማው ዕሁድ ከቤተክርስትያን መልስ ወደ ጠንቋይ የሚሄድ ጸረ ትግሬ ሕዝብ ነው ይላል ትግሬው ዶ/ር ገላውዴዎስ አርአያ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

 

አማራ በተለይ የሸዋ ሕዝብ ሥልጣኑን እንዳንቀማው ዕሁድ ከቤተክርስትያን መልስ ወደ ጠንቋይ የሚሄድ ጸረ ትግሬ ሕዝብ ነው ይላል ትግሬው ዶ/ር ገላውዴዎስ አርአያ

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)



6/15/2021

አፍጥጦ የወጣው የገላውዴዎስ አርአያ ጸረ አማራ ጥላቻ በታሪክ እንዲመዘገብ ለአንድ የታወቀ ምሁር ወዳጄ ገላውዴዎስ በትግርኛ ያደረገው ቃለ መጠይቅ እንዲያደምጠው ጠይቄው ትግርኛ ሁለተኛ ቋንቋው ቢሆንም በሗላ ግን በትክክል ማድመጡ ይቸግረው ይሆን የሚል ጥርጣሬ ስላደረብኝ ወዳጄ የታሪክ ተመራማሪ ስለሆነ እግረመንገዱንም ለታሪክ ምርምር ይጠቅመጠው ይሆን በሚል እሳቤ ልተርጉመልህ ስለው “በደስታ” ስላለኝ፡ እኔም ይህ ሰፊ ቃለ መጠይቅ ለናንተም ጭምር አቅርቤዋለሁ።

 

 እርግጥ ብዙዎቻችሁ የፌስቡክ ጓደኞቼ ረዥም ጽሑፍ የማንበብ ልምዱ እንደሌላችሁ ባውቅም የብዙ አመት ተከታታይ ለሆኑት የኢትዮ ሰማይ ድረገጽ ተከታዮቼ ስላሉ ለነሱ የተለጠፈ ቢሆንም ሰነዱ ለናንተም ይጠቅም ይሆናል እና ከትግርኛ ወደ አማርኛ የተረገጎምኩትን አድካሚ ትርጉም ተጋበዙ። ብትቀባበሉትም ለታሪክ ጠቃሚ ነውና ሼር አድርጉት።

 

የህ ቃለመጠይቅ ያየሁት ዛሬ ጥዋት በድንገት ነበር። ሳደምጠው እጅግ አፈርኩኝ። ስለዚህም ልተረጉመው ወሰንኩ። ቃለ መጠይቁ ድንቁርና የተጫነው፤ በጥላቻ የተሞላ በቆሸሸ ሕሊና የተነገረ ስለሆነ ሳትበሳጩ በእርጋታ አንብቡትና የትግሬ ምሁራን ምን ያህል ያደፈ ሕሊና እንደተሸከሙ ለማወቅ ይረዳችሗል እነሆ።

 

በፈረንጆች ዘመን በ5/27/2021 “ትግራይ ትናንት፤ዛሬ እና ነገ” በሚል የኮሎመብያ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ እና ፖለቲካ ትምህርት ምሩቅ፤ “የሲቲ ዩኒቨርሲቲ ኒውዮርክ” ፕሮፌሰር የሆነው ኤርትራ ተወልዶ ያደገ “ትግራይ ከ9 ክፍል ተማሪ እያለሁ ጀምሮ ልቤ ውስጥ ተሸክሜ በእርስዋ ፍቅር ስቃጠል አድጌ ዛሬም አብራኝ ልቤ ውስጥ ተቀምጣለች” የሚለን ፋሺሰታዊ ብሔረተኛው ትግሬው ዶ/ር ገላውዴዎስ አርአያ “ትግራይ ሚዲያ ሃውስ” በሚባለው የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ ማዕከል ቃለመጥይቅ አድርጎ ነበር።

 

 ቃለ መጠይቁን ያቀረበው ትግሬው “ዳደ ደስታ” ይባላል።  ድሮ የ ቪ ኦ ኤ የትግርኛ ክፍል እና ካልተሳሳትኩም የጀርመን ድምጽም የነበረ ይመስለኛል ፤ በኋላ የወያኔዋ ሚሚ ስብሓቱ ‘ሚዲያ’ ባልደረባ ሆኖ አዲስ አባባ ውስጥ የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ሲሰራ የነበረ እርሱም በጥላቻ የታወረ እንደሆነ ዛሬ ከሚናገራቸው ቃሉ ለማረጋገጥ ችያለሁ።

 

መንትያ ለመንትያ የተገናኙበት ቃለ መጠይቅ “ጋዜጠኛ አቶ ዳደ ደስታ” አንዲህ ሲል ቃለ መጠይቁን ይጀምራል።

 

ጥያቄ፤---

 

ፕሮፌሰር ገላውዴዎስ አርአያ የዛሬ እንግዳችን ናቸው; ሑላችሁም ታውቀዋቸዋላችሁ። አንኳን ደህና መጡ። እንደ የታሪክ ምሁርነትዎ “ትግራይ ትናንት፤ዛሬ እና ነገ’ በሚለው ዝግጅት ላይ ያለዎትን አስተያየት ምን እንደሚመስል እንወያያለን። ከዚያ በፊት ግን አንድ መጥራት የሚገባው ነገር አለ። እርሱም ለአድማጮችዎ እንዲያብራሩልን የምፈልገው ነገር አለ።

 ባለፈው ሰሞን “መረጃ ቲ ቪ” ከሚባል “ዘመድኩን በቀለ” ከተባለው አዘጋጅ ጋር ያደረገለዎትን የአማርኛ ቃለ መጠይቅ ተቀብለው እንደነበርና እዛው ጋር አብረው የተጋበዙትም አቶ በረከትም ጭምር በትግራይ አድማጮች በኩል በናንተ ላይ ቅሬታ ተሰምቷል። ምክንያቱም አዘጋጁ እናንተን ያስተረናገደበት መንገድ ካሁን በፊት ጨዋነት ያልነበረው አቀራረብ በናንተው ለዘብ ብሎ አክብሮ አነጋግሮኣችሗል። ሰውየው የምናውቀው ጸረ ትግሬ እንደሆነ እና “አሁን ትግራይ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት ለኢትዮጵያ የችግሯ መፍትሔ ጥሩ አጋጣሚ ነው” ብሎ የሚናገር ሰው ነው። እና ሌላም ፤ሌላም የሚናገር በትግሬ ጥላቻነት የታወቀ ሰው ነው” ለዚህ ይሆናል ማሕበረሰባችን በእርስዎ ላይ ቅሬታውን ያሰማው። በዚህ በኩል የተሰማዎትን የግልዎን አመለካከት ይንገሩን እና ወደ ርዕሱ እንገባለን።

 

 መልስ-

ገላውዴዎስ አርአያ፡

እውነት ነው እኔም የሕዝቡ ቅሬታ ሰምቼዋለሁ። በዚህ ላይ ከሰብአዊነትና ከዕውቀት ትንሽ የወረዱ ሰዎች ሰድበውኛል። እነሱን ለማስረዳት ስንል  ከአቶ በረከት ጋር ሆነን “ሳይበር ፓወር ኦፍ ትግራይ” በሚባል ሚዲያ ማብራሪያ ሰጥተናል። አሁንም ተጨማሪ ትንሽ ምክር ቢጤ ልስጥ።

 

አንድ ሰው ባደረገው አንድ ጥፋት ምክንያት ያቺን እንደ ምክንያት ተይዞበት ያደረገው አስተዋጽኦ መደምሰስ የለበትም። ያቺ አንዲት ጥፋት መመዘኛ ልትሆን አይገባም። ካሁን በፊት ለትግራይ ሕዝብ ምን ዓይነት አስተዋጽኦ አድርጎ ነበር የሚል መመዘኛ ነው ሰው የሚመዘነው። ባሕላችን የዲሞክራሲ አሰራር ስላልተለመደ ሰውን ተሎ ማጥቃት እና የመሳደብ ባህል አለን።

 

እኔን ምን ነካህ? ብሎ የጠየቀኝ ሰው የለም። ያንን ከማድረግ ይልቅ ወደ ሚዲያ ሄዶ ስድብ ወደ ማውረድ ነብር የሮጡት። የሆኖ ሆነ ‘መረጃ ቲቪ’ ላይ የቀረብኩበት ምክንያት ከኛ ጋር ባይስማሙም አንዳንድ ነገር “ፕሮሞት” ለማድረግ (ቅሬታችንን ላማሳወቅ) ብለን ነው የሄድነው። ምክንያቱም በራሳችን ሚዲያ ብቻ ተወስነን መቅረት እርባናው ውሱን ነው። እዛው በራሳችን ብቻ መወሰን አይኖርብንም። አንዳንድ ጊዜ በጠላት ምሽግ እና ቀጣና ሄደህ በራሳቸው ምሽግ ውስጥ ገብተህ ጦርነት ማካሄድ ግዴታ ስለሚሆን፤ ከጠላቶችህም አንዳንድ ወቅትም ወደ ንግግርና ውይት ትገባለህ። እኔ እስከማውቀው ድረስ ወያኔ ከደርግ ጋር ሁለት ጊዜ አንዱ አክሱም ውስጥ አንዱ ደግሞ ሮም ጣሊያን አገር ውይይት አካሄደዋል። ከጠላት ጋር መነጋጋር የለብህም ማለት አይደለም።

 

 

የሆኖ ሆኖ እኔ ያላወቅኳት ነገር ነበረች። አስተናጋጁ ማንነቱን አላውቀውም። ውይይት ካደረግኩኝ በኋላ አንዳንድ ወንድሞቼ ደውለው “እንዴ ያ ሰውየ አታውቀውም እንዴ  የትግሬ ጠላት እኮ ነው” “ትግሬዎች ባሕል የላቸውም፤ታሪክ የላቸውም ብሎ እኮ ሰድቦናል” ብለው ነገሩኝ። እኔ ደግሞ ሰውየውን አላውቀውም “አንድ ጊዜ ብቻ ገንዘብ ሲሰበስብ” አይቸዋለሁ፤ በተረፈ አላውቀውም፤ ‘ለካ እንደዚያ ያለ ሰው ነው!?” “አላወቅኩትም ነበር” ብየ አልኳቸው።

 

የሚገርመው ከዚያ በፊት ሌላ አጋጣሚ ገጠመኝ ነበር። ኢትዮ 360 የተባለ ሚዲያ ስለ ወልቃይት ጉዳይ እንዳወያያቸው ደጋግመው ጠየቁኝ ። እኔ ደግሞ “ስንት ጊዜ ነው የምነጋገርበት፤ በጽሑፍ በግልጽ አጥርቼ ወልቃይት የትግራይ መሬት እንደሆነ ጽፌአለሁ። ታዲያ ይህንን እያወቃችሁ ምንድነው ከኔ የምትፈልጉት? ብየ ጠየቅኩዋቸው። ከአንድ “አቻምየለህ ታምሩ” ከሚባል “ትምክሕተኛ” ልያወያዩኝ ፈልገው ነበር እኔም አልወያይም አልኳቸው።

 

የትናንቱ የመረጃ ቲቪ “ዘመድ” ምናምን የተባለው (ዘመድኩን በቀለ) ትምክሕተኛ መሆኑን ባውቅ ኖሮ እሺ ብየ መስተንገዶውን አልቀበለውም ነበር። ባለማወቃችን ተቀበልነው። ስለዚህ በብዙ መልኩ እንደኔ ያሉ ብዙ አስተዋጽኦ ላደረግን ሰዎች፤ በተለይ እኔ ማንም ሰው ያላደረገው 9ኛ ክፍል እያለሁ “መሕበር ተጋሩ መንእሰይ አስመራ”  ኤርትራ ውስጥ “በአሥመራ የትግራይ ወጣቶች ” የሚል ማሕበር መስርቼ “ትግራይ” የሚል “ስሜት” “አንጎሌ” ውስጥ ከገባ 45 አመት” ሆኖኛል። በትግራይ ጉዳይ እቆረቆራለሁ፤ ያገባኛል ሕዝቤ ነው፤ አገሬ ነው። በሕይወት እስካለሁ ድረስ ለትግራይ እታገላለሁ።

 

ተሳዳቢዎቼ ይህንን የኔን ረዢም አስተዋጽኦየን መመለክት ነበረባቸው እንጂ ለምን ከጠላት ሚዲያ ዘንድ ሄደህ ተወያየህ ማለት ተገቢ አይደለም። ከኔ ጋር የቀረበው አቶ ይትባረክም “ባንዳ” ብለው ሰድበውታል። አቶ በረከት ስያትል አሜሪካ ውስጥ ከፍተኛ ምስጉን አስተዋጽኦ ያደረገ የታወቀ የትግራይ ታጋይ ነው።ባንዳ ማለት ነውር ነው። እኛ “ባንዳዎች አይደለንም “ትግራይ ግሎባል አድቮካሲ” ብለን እየተጋለን ያለን ሰዎች ነን። ስለ ጠየቀቅከኝ ስለ “መረጃ ቲ ቪ” ቃለ መጠይቅ ጉዳይ  የምለው ካለኝ ይኼው ነው።

 

(“ትግራይ ግሎባል አድቮካሲ” የሚባለው ውጭ አገር የሚኖሩ የተማሩ አክራሪ ትግሬዎች የሚበዙበት ቡድን በማስተባበር የመገንጠል ቀንቅስቃሴ ነጋሪት መቺ እና አፈቀላጤ የሆነው ይህ ድርጅት በሊቀመንበርነት የሚመራው ደግሞ ገላውዴዎስ አርአያ ነው።)


ጥያቄ፤-

እንዳልነው ለናንተ ይህ ስም እና ስድብ አይገባም። ምናልባት ሰዎቹ ያልተደሰቱበትን ያስቆጣቸው ነገር ሰውየው ስለ ኢትዮጵያ ግሎሪ “እያጎላ” ሲናገር ስለተደመጠ ይሆናል ትንሽ ሕዝባችን በናንተው ላይ የተንጫጫው። አሁን ወደ ዋናው ውይይት እንግባ።

ትግራይ ለኢትዮጵያ ያበረከተቺው አስተዋጽኦ ተቆጥረው የማያልቁ ብዙ አስተዋጽኦ አድርጋለች። ባንድ እኔ በተካፈልኩበት በአንድ ውይይት የሚገርም ጠቃሚ ነጥብ “ታደሰ መድሃንየ” የተናገረውን እዚህ ልጥቀስ እና እርስዎ አስተያየት ያክሉበት። እንዲህ ሲል ሰማሁት “በ1983 ዓ.ም ትግራይ አንድ እራስዋን የቻለች አገር ሊኖራት የሚገባ የንብረት፤ የጦር መሳሪያ እና መዋቅር ዘርግታ ነበር። ያንን ይዛ ወደ ኢትዮጵያ ገባች። ያንን ሁሉ ተቋማዊ ጉልበት ይዛ ለትግራይ ይሁነኝ ሳትል “ለኢትዮጵያ አበረከተቺው” ዛሬ “የትግራይ ሕዝብ መጨፍጨፊያ ሆኗል።” የዛች አገር ‘እስቴት አክተሮች’ ትግራይ መድከምዋን ባዩ ቁጥር ተደጋጋሚ ግፍ፤ወንጀል ሲፈጽሙባት ታይተዋል። እንዴት ነው፡ ምንድ ነው ይህ ተደጋጋሚ የታሪክ ጥቃት በትግራይ ላይ ሊደርስ የቻለው?

 

መልስ፦

ዶ/ር ገላውዴዎስ አርአያ፦

 በጣም ጥሩ ጥያቄ አንስተሃል። ዛሬ ትግራይን ለማጥፋት የታየው ጥቃት ከመቸውም የታሪክ ጊዜ ታይቶ አይታወቅም። ለታሪክ ጸሐፍትም ሳያስቸግር አይቀርም። ከዚያ በፊት ደርሷል፤ በመጠን ይለይ እንጂ ጥቃቱ ቀጣይ ነበር። የደርግን አይተናል፤ ሁላችን የታወቀ ነው። የሃይለስላሴም አይተናል፤ የትግራይ ሕዝብ መሬቱን እየተከፋፈለ እንዲደኸይ ሆን ተብሎ በሃይለስላሴ ሥርዓት ሕዝባችን ለስደት ተዳርጓል። ብዙውን ወደ ዓረብ አገር ሲሰደድ ከፊሉ እስከ አርሲ ጂማ…ድረስ ተሰድዶ ሲኖር ነበር።

ይህ ጥቃት እኔ ካሁን በፊት ለ “ፒ ኤች ዲ” ዲግሪዬ ዲዘርተሽን በሰራሁበት በዚህ ዲዘርተሽን ላይ የሸዋ ገዢዎች ከ1889 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁንዋ ድረስ የትግራይ ሕዝብ አስርበው ገዝተውታል። ፍላጎታቸወም ያ ነበር ብየ ጽፌአለሁ።” በ1980 ዲዘርተሽኔን ስሰራ ታሪክን ተመርኩዤ ነበር ያንን ያልኩት። በተለይ ሸዋ በትግራይ ሕዝብ ላይ ጥላቻቸው መረን የለቀቀ ነበር።

የአፄ ዮሐንስና የአፄ ምኒሊክ ግንኙነት ምን ይመስል እንደነበር እናውቀዋለን። ምኒሊክ ከጣሊያን ጋር አብሮ አንቶኖሊ የተባለው ጣሊያናዊ ጋር እየተገናኙ ዮሐንስን ለማጥፋት ምኒሊክ ብዙ ጥረዋል። ያኔ ትግሬዎች የበላይነት ነበራቸው። ትግሬዎች የሚጠቁበት ምክንያት ሁልጊዜ በፍትሕ እና እኩልነት ስለሚመሩ፤ ሉሁሉም ፍትሕ እና እኩልነት እንዲዳረስ የሚጥሩ ማሕብረሰቦች ናቸው። ስለሆነም ይጠቃሉ። ዮሐንስ ፍትሕ ለማስፈን በየቦታው “ሰሚ ፌደራሊዝም” ዓይነት ለአካባቢው ሹመኞች ሰጥተው ግብር ብቻ ክፈሉኝ የሚሉ የፍትሕ ሰው ነበሩ።

ስለዚህ ትግሬዎች በፍትሕ ስለሚመሩ ለጥቃት ይጋለጣሉ። ይህ የፍትሕ እና እኩልነት ማስተዳዳር ባሕላችን ነው። ለዚህ ነው የምንጠቃው።

 ሌላው ትግሬዎች ሥልጣን እስካሉ ድረስ እኛ ሥልጣን ላይ መቆየት አንችልም፤ የሚል ፍራቻ አላቸው። በተለይ እንዲህ የሚለው “አማራው ነው” ። ይህች ፍራቻቻው ትናንትም ነበረች፤ዛሬም በቅርቡ ባሕርዳር ውስጥ ደግመዋታል።

አማራዎች “ትግሬ ካልጠፋ እኛ በሥልጣን ላይ የመቆየት ቀጣይነት አይኖረንም፡” የድሮ ሥርዓታችን የቀሙን ትግሬዎች ናቸው” ይላሉ።

ደርግ በትግሬዎች ሲደመሰስ የአማራ ልዕልና ያኔ አቆመ። ከዚያ በፊት ግን ለ160 ወይንም 150 አመት አማርኛ ተናጋሪ ወይንም የአማራ ብሔር በሥልጣን ቆይቷል። ከትግሬዎች ሌላ ኦሮሞዎችን ድምጥማጣቸውን አጥፍተዋቸዋል። መሬታቸውን ነጥቀው ባርያ አድርገው ገዝተዋቸዋል።

“ትግሬዎች ወደ ሥልጣን ከተመለሱ እንጠፋለን እያሉ ያቺን የ150 አመት ሥልጣናቸው ለመንከባከብ ወደ ጠንቋይ ቤት ነው የሚሄዱት።” አማራዎች በተለይ የሸዋ ሕዝብ ዕሁድ፤ዕሁድ ቤተክርስትያን ይሂዱ እንጂ ከቤተክርስትያን መልስ ወዲያውኑ በቀጥታ ወደ ጠንቋይ ቤት ነው የሚሄደዱት። ጠንቋዮቹ ሥልጣናችሁ ታጣላችሁ ብለዋቸዋል መሰለኝ ፍራቻ አላቸው።”

ሰሞኑን ባሕርዳር ውስጥም የደገሙት ይህንን ፍራቻቸው ነው፡ የኛ ልዕልና የሚመለሰው ትግሬዎች ሲጠፉ ብቻ ነው ብለዋል” ።

ተመስገን ጥሩነህ የተባለ የአማራ ደንቆሮ “ትግሬዎቸ ከእስራል ነው የመጡት ጥንታዊ ኢትዮጵያዊያኖቹ እኛ ነን ሲል ተናግሯል። አየህ የአማራዎች ትምክሕት! አውቀወም ይሁን ሳያውቁት ድንገት ከልባቸው ውስጥ የደበቅዋትን ትምክሕት ሁሌም ድንገት ብቅ እያደረጉ ይናገሯታል።

 

የአማራዎች ፍላጎት “ኦሮሞዎችን ጨፍጭፈው፤ዓፋሮችን ጨፍጭፈው መግዛት ነው። ሁሉንም ጨፍጭፈው ምን ዓይነት ኢትዮጵያ ለመመስረት እንደፈለጉ ግራ የሚገባ ሁኔታ ነው”

እኛ ትግሬዎች የሓውልት ጥበብ ሥራ ጀምረን የአድባራት፤የማርያም ጽዮን፤የነጋሺ ቅርሶች ባለቤቶች የሆንን ሕዝብ ነን።  ሁሉም የሚገኙት ትግራይ ውስጥ ናቸው። አማራዎች ወደዱም ጠሉም ቅርሶቻችን በሙሉ ያሉት እኛ ጋር ነው ያለው። ሊነጥቁን ሊቀሙን አይቻላቸውም።ዕውቀቱም ንብረትነቱ የትግራይ ነው።

አማራዎች ፊደል የኛ ነው ይላሉ። አማርኛ ፊደል የሚባል የለም፤ የግዕዝ ፊደል እንጂ።ግዕዝ ፊደል የተፈጠረው ትግራይ ውስጥ ነው።  ዓለም የመሰከረው ሓውልት ያቆመ ሃብታም የታሪክ ባለቤት ትግራይ ብቻ ነው። አማራዎች እንደዚያ ዓይነት ታሪክ የላቸውም።

ዞሮ ዞሮ ትግሬዎች ካልጠፉ እኛ ሥልጣን ማግኘት አንችልም የሚለው ነው መነሻቸውም መድረሻቸውም።

 

ጥያቄ፡ጋዜጠኛ

ይህ ጥቃት እውን የሆነ “ኮንሲስተንሲ” ያለው ነገር ነው። ችግሩ የነሱ ችግሩ የነሱ ሳይሆን ችግሩ ከኛ ጋር ያለ አይመስለዎትም? እኛ ትግሬዎች ነገሮችን ተሎ እንረሳለን። እንጃጃላለን፤ እነሱ ግን “ኮንሲስተንስ ናቸው” የኛ ችግር አይመስለዎትም?

መልስ፦ ገላውዴዎስ አርአያ፦

ጥሩ ጥያቄ ነው ያነሳኸው አቶ ዳደ። በኛም በኩልም እኮ ድክምት የለም ማለት አይደለም። ወያኔ ደርግን ደምስሶ ሥልጣን ሲይዝ ምን የመሰለ “ብሪሊያንት” (የመጠቀ) ኮንስትትዩሽን (ሕገ መንግሥት) መስርተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ራሱን በራሱ እንዲተዳደር አድርጎ መብት አጎናጽፎት ነበር። በታሪክ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነው ያደረገው። ለትምክሕተኞቹ ግን አልተዋጠላቸውም፤ ምናቸውም አይደለም። ምክንያቱም “ሕገ መንግሥቱ፤ ቅልጥማችንን የሰበሩበት በዚህ ሕገመንግሥት ነው ይላሉ። መዘንጋት የሌለብን አሁን የአብይ አሕመድ አማካሪዎች በሙሉ ትንናት የደርግ አባሎች የነበሩ ናቸው። ቂማቸው እየተወጡ ነው!” ።

ችግሩ ግን ትግሬዎች ሥልጣን ከያዙ በኋላ ትግራይን ረስተው ባሕርዳርን አደመቁት፤ አዋሳን ናዝሬትን ሌሎችን መላውን አገሪቷን አደመቋት። ትግዎች ይህ ሁሉ መስዋዕት ከፍለው ትግራይን ወደ ኋላ አስቀርተው ረስዋት። እኔም ካሁን በፊት ወያኔዎችን በዚህ ጉዳይ በጽሑፍ ወቅሼአቸው ነበር። ሌላው ሲላማ ትግራይ ተረስታ ነበር። የሚገርም ነገር ነው። ይህ ስሕተት ነበር።

ምንም ቢደረግላቸው ከነዚህ ትምሕተኞች ጋር መስማማት መኖር አይቻልም። ፍጹም አስቸጋሪ ነው። አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ሲመጣ፤ ተሎ ብለው “የጨለማ ዘመን” ነበር ብለው በዕድገት የበለጸጉበትን ያደጉበትን ሕገመንግሥትና ሥርዓተ መንግሥት አወገዙት። አሁን በከፋ መልኩ የጨላማ ዘመን እንዲመጣ አደረጉ። አውነትም ትምክሕተኞች ናቸው።

ዓለም በሞላ እና ‘አይ. ኤፍ. ኤም” በትግሬዎች አገዛዝ 11 % ዕድገት እንዳመጣ ተመስክሮለታል። ያ የተመሰከረለት በተጨባጭ የታየው ዕድገት ለትግሬዎች “ክረዲት” ላለመስጠት ያቀዱት የትምክሕተኞች ባሕሪ ስለሆነ ነው።  ልማቱን እየተው ፤ትንንሽ ጉድለትዋን እያጎሉ ነው የሚናገሩት።ዕድገቱን ግን አይናገሩም። አሁን አገሪቷን ወደ ጭለማ ዘመን የከተትዋት እነዚህ ትምክሕተኞች ናቸው። እኛ ተጃጅለናል። አላወቅናቸውም። በተለይ አማርኛ ተናጋሪዎችን አማራዎች አላወቅናቸውም።

ያቺ ልዕልና በጣም ስለሚወድዋት ብቻ አይደለም፤በዚያ አልተወሰኑም። ቤንሻንጉል፤ መተከል፤ ዓፋር በኩል እስከ ወለጋም ድረስ የኛ ነው ይላሉ። አማራ እንዲህ የሚል መሪ ካገኘ ሁሉም የኔ ነው ባይ ነው። የሚፈልገው መሪ ብቻ ነው።

አማራዎች እንዲህ ያለ ትምክሕት ስላላቸው በሠላም የመኖር ባሕሪ የላቸውም። አሁን ትግሬዎችን አጥፍተናቸዋል፤ የሚሉት ኋላ ግን ያቺ አጥፍተናቸዋል የሚልዋት ነገር እነሱ ላይ በግልባጩ ይመጣል። ጤና ከሰጠን የምናየው ነገር ነው። የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው።

ሲል በጥላቻ፤በድንቁርና ያደፈ፤የተግማማው የዶ/ር ገላዲዎስ አርአያ የትግሬዎች የበላይነት የጀርመኖች የአርያን ዘር ዓይነት ፋሺስታዊ ልዕለ ሕሊና የተካሄደው ቃለ መጠይቅ በዚህ መልክ ነበር። ትግርኛ ለማታደምጡ ዜጎች ወይንም መጽሐፍ ለመጻፍ ወይንም የታሪክ ምርምር ለምታደርጉ በተለይ ደግሞ ‘የትግሬዎች ምሁራን ሕሊና ለማጥናት’ ይረዳችሁ ዘንድ ተርጉሜላችኋላሁ። በመቀባበል “ሼር” አድርጋችሁ ማሕበረሰባችሁን አስተምሩበት። ጠላት ምን እንደሚያስብ እና ምን እንደሚል ማሕበረሰባችሁ እንዲያውቅ ካላደረጋችሁ “በክርክር ዓለም ትደክመላችሁ፤ተጠቂዎችም ትሆናላችሁ” ።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay