በሙታን ላይ ቆመው የሚስቁ ተውኔተኞች!
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
12/26/22
ካሁን በፊት ይከሰታሉ ያልኳቸው ክስተቶች ሆኗል ከዚህ ወዲያ ሁለተኛው የሚመጣው ክስተት ይህ ልበልና ወደ ርዕሴ ልግባ!!!!
<< ወያኔና አብይ ጸረ አማራ ይቆማሉ፤ ኤርትራ ከወያኔ ትንኮሳ ለመዳን የአማራ አማጽያንን በማሰልጠን ጸረ ወያኔና ጸረ አብይ ጦርነት ይካሄዳል! >> * {ጌታቸው ረዳ}
ወንጀለኞቹ ወደ ትግራይ መቀሌ ከተማ ገብተው ናፍቆታቸውን እየተቃቀፉና እየተሳሳሙ በሙታን ላይ ቆመው የተሳለቁበትን ስዕለ ድምጽ (ቪዲዮ) መርቁልን ብለውናል።እኛም “ከሙታኖቹ ጋር ይቀላቅላችሁ!!” ብለናል። ቪዲዮውን ለማየት ወደ መጨረሻ ለጥፌዋለሁ ይህ ጽሑፍ አንብቡትና ተመለክቱት።
ትዝ ይላችሁ እንደሆነ ወንጀለኞቹ ተስማሙ በተባለበት በማግሰቱ ከማንም ጸሐፊና ፖለቲከኛ በፊት አስቀድሜ የጻፍኩት ጽሑፍ ነበር። ዛሬም ተልጠፎ ይገኛል፤ ያንን አንብቡት። እየሆነ ያለው ያ ነው።
አብይ አሕመድ የጎንደርና የወሎ መሬቶች ለትግሬዎች መልሶ ለማስረከብ ጸረ ፋኖ አፈና እንደሚያካሂድ ጽፌአለሁ።አሁን ያንን እውን ለማድረግ ከወያኔ ዱላ አስጥሉኝ ብሎ ፋኖዎቹነ ለምኖ በደማቸው ከተከላከሉለት በኋላ ዛሬ እነሱን ለማጥፋት ተነስቷል።
የ30 አመት ውትወታየ ዛሬም እነሆ ጥያቄው ፈጥጦ መጥቷል። የአማራ ወጣት በየፌስቡኩ ተወሽቆ “ዘራፍ ከማለት” ወደ አገሩ ዘልቆ ጫካ በመግባት የሽምቅ ተዋጊ ሃይል በማቋቋም የወንጀለኞቹ ስርዓት ቁም ስቅል ማሳየት መጀመር አለበት ስል ነበር። ዛሬም ከጓድ መንግሥቱ ንግግር ልዋስና << ወደ አገር ቤት ዘልቃችሁ እንደ ወያኔዎቹ ታጥቃችሁ ጫካ በመግባት መንግሥት ነኝ የሚለው ወሮበላ ቡድን ቁምስቅሉን ታሳዩታላችሁ ወይንስ የፌስቡክ ፉከራውን ትቀጥሉበታላችሀ? ብየ ልጠይቅ።
ብዙ የአማራ ወጣቶች ይችን ጥያቄ ስጠይቅ አይወድዋትም፡ ጽሑፎቼንም እነሱን የሚመለከት ስለሆነ ለበርካታ አንባቢ አያዳርሱትም፡ መልዕክቴን አይተው አንዳላዩ ያልፏታል።
እነኚህ ወጣቶች እና የወላጆቹን
ስቃይ ደንታ የማይሰጠው ንዑስ ከበርቴው “ምሁሩ ክፍል” ራስን ከማታለልና ከመደበቅ ልማድ ዛሬም መውጣት አልቻለም (ሂሱ ጥቂት አርበኞችን
አይጨምርም)።
በ17ኛው የፈረንጆች ክ/ዘመን የነበረ ጆርጅ ክሪስቶፍ ሊችተንበርግ የተባለው አውሮጳዊ ሊቅ << ዛሬ እውቀትን በየቦታው ለማዳረስ እየሞከርን ነው። ከዘመናት በኋላ ግን “የቀድሞ ድንቁርናችንን መልሶ ለማቋቋም” ዩኒቨርሲቲዎች እንደማይኖሩ ማን ያውቃል? >> ሲል አስገራሚ ትንቢቱን ገልጸ ነበር። እዚህ ላይ ልዩነቱ ዩኒቨርሲቲዎች አለመገንባታቸው ሳይሆን ዩኒቨርሲቲዎች በሺዎቹ ተመስርተውም ቢሆን ድንቁርና አለመዋጋታቸው ብቻ ሳይሆን ዩኒቨርሲቲዎች ድንቁርናን በመግንባት ላይ ናቸው። በዚህ ተጠያቂው ከላይ የጠቅስኳቸው “ንኡስ ከበርቴዎች” የሆኑት ውዳቂ ምሁራኖቻችን ናቸው።
ጠመንጃን ተገን አድርገው የመንግሥት ወንበር የተቆጣጠሩት ድንቁርናን በመገንባት
የአንድ ሚሊዮን ወጣት ህይወት በሁለት አመት ውስጥ አስጨርሰው በሙታኖች ሬሳ ቆመው እየተሳሳቁ የሚያሾፉ ወያኔዎችና የወያኔ አሽከሮች
የሆኑት “ውሾች” ከአዲስ አባባ በመብረር መቀሌ ገብተው አስረሽ ምቺው “ዊስኪ” ሲጨልጡ ብርጭቆ ለብርጭቆ እያጋጩ “ቪቫ ላሞርተ”
(ሞት ለዘላለም ኑር!!) እያሉ በሙታኖች ላይ ሲሳለቁ ውለዋል።
ዛሬስ ፋኖዎች ጠምንጃችሁ እንደተለመደው ልታስረክቡ ይሆን ወይስ እንደ ወላጆቻችሁ “ዱር ወገኔ” ብላችሁ አርበኝነታችሁን ለማሳየት እነዚህን ወንጀለኞች ቁም ስቅል ታሳዩ ይሆን?
የፋኖዎቹን እሮሮ እና የጋራ ስምምነትስ ያልጨመረው ሰላም ያመጣል ቢባል
እንኳ ወደ ትግራይ የሚያመሩ የጭነትና ተሽከርካሪ መኪኖች በፋኖና ዓፋር መንደሮች በሰላም ያልፉ ይሆን? በጊዜ የምናየው ይሆናል!
ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay
Ethiopian Semay
Criminals Praising Each other Meeting in Mekele መንግሥት ባለሥልጣናት ጉብኝት