ልደቱ አያሌው ክፍል 2
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
1-11-23
በክፍል 2 እንደገለጽኩት አቶ
ልደቱ ደደቢት ሚዲያ ከተባለ ወደ ትግራይ ይሰራጫል ከሚባልለት የወያኔ ፋሺዝም ፕሮፓጋንዳ የሚሰራጭበት የሳተላይት ጣቢያ ላይ ቀርቦ
ስለ የጊዜው ሁኔታ ለማብራራት በተጋበዘበት ባለፈው ሁለት ሳምንት አካባቢ ወያኔን እና ትግሬዎችን በሚመለከት አንዳንድ አስተያየቶችን
ሰንዝሯል። በዚህ ጉዳይ ስለ ትግሬዎች እና ወያኔ ግንኙነት የብራራውን እንመለካለን። በክፍል 3 ግን “ቄሎ” (ክሎ) በተባለ ባንድ
ኦነጋዊ ጡበት በሆነ በኦነግ አስተሳሰብ የፋፋ አንድ ምስኪን ወጣት በሚያዘጋጀው ሚዲያ ላይ ተጋብዞ ስለ አማራ ብሔረተኞች/አማራ
ኢሊቶች/ እና ቲ ፒ ኤል ኤፍ (ወያኔ) የትግሬዎች መንግሥት አይደለም በሚላቸው ላይ ያቀረበው ትችት በሌላ አጀንዳ ካልተጠመድኩ በክፍል 3 እንወያያለን።
የልደቱ ፖለቲካ እየሻከረብኝ ስለመጣ መበጠር አለበት ብየ የማምናቸው ለዛሬ በዚህ ክፍል 2 በደደቢት ሚዲያ ቀርቦ በተናገራቸው ሦስት
ነገሮች እንመለከታለን።
“የወያኔ መንግሥት በ27 አመት ውስጥ የትግሬዎች መንግሥት አልነበረም፡
(የሚለው በሌላ ጊዜ እምለስበታለሁ)
የትግራይ ማሕበረሰብ በወያነ ዘመን ከሌሎች በተሻለ አልተጠቀመም።
ወያኔ ሳይሆን ቲ ፒ ኤል ኤፍ ብየ ነው የምጠራው “
የሚሉ ንግግሮቹን እንመለከታለን።
በዚህ አባባሉ
ልጀምር።
ልደቱ እንዲህ ይላል፡-
<< ሃይሌ፤ ወያኔ
ስል ሰምተኸኝ ታውቃለህ? እኔ ቲ ፒ ኤል ኤፍን ወያኔ ብየ ጠርቻቸው አላውቀም። የምጠራቸው “ቲ ፒ ኤል ኤፍ” ብዬ ነው የምጠራቸው”
ሲል ወያኔ እና ‘ቲ ፒ ኤል ኤፍ’ ልዩነቱን ሳይገልጽ በደፈናው ቲ ፒ ኤል ኤፍ እና ወያኔ ማለት ልዩነት እንዳላቸው አድርጎ ለምን
አንደኛውን መጠሪያቸውን ካንደኛው የተወገዘ/ወይንም ጤነኛ መጠሪያ/ ወይንም አንዱ/ ካንዱ የተሻለ እንደሆነ ለመገለጽ ምክንያቱን
ባላወቅም ወያኔ ማለት ከላይ እንደምታዩት እራሱ ድረጅቱም ሆነ ድፍን የትግራይ ሕዝብ ድርጅቱን የሚጠራው “ወያኔ” እያለ ነው። “ቲ
ፒ ኤል ኤፍ” የሚለው የእንግሊዝኛው መጠሪያው ነው። ወያኔ ማለት “አብዮት/አመጽ/ ማለት ነው ብለው እራሳቸወም ሆኑ ሌሎች የትግራይ
ምሁራን ያብራሩታል። ልደቱ ለምን በተለየ እንደሚጠራው ሌላ ቀን ጠያቂ አግኝቶ ሲያብራራ የምነሰማው ይሆናል። የሚገረምው ግን በተደጋጋሚ
በቃለ መጠይቁ እዛው ሳይርቅ “ወያኔዎች” እየለ እራሱ በዛው መጠሪያ ሲጠራቸው ሰምቻለሁ።ሌላው የልደቱ ተደጋጋሚ ኣቋሚቹ የወያኔ
“ጥቂት” ደጋፊዎች እንጂ የትግራይ ሕዝብ አልተጠቀመም እያለ በዚያው ሚዲያም ሆነ በሌሎች ተደጋጋሚ አቋሙን ሲገልጽ ሰምቼዋለሁ።
ይህ እምነት የልደቱ ብቻ ሳይሆን በርካታ ሰዎች በዚህ መከራከሪያ ጸንተው ሲከራከሩ ሰምተናቸዋል። አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ የትግራይ
ልሂቃን ተጠቃሚ ሆነውም ሕዝባችን አልተጠቀመም እያሉ ሲከራከሩ መስማት “ስትረንጅ” (አስገራሚ ክስተት) ሆኖ እናገኘዋለን።
ይህ አባባላቸው የልደቱም ሆነ
የትግራይ ምሁራን መከራከሪያ አንድ ነው። እኔም ሆንኩ የኔን መሳይ መስመር የሚያራምዱ “የትግራይ ሕዝብ በመንግሥታቸው በትግራይ
መንግሥት ተጠቅመዋል” ብለን ስንል እነ ልደቱ እና መሰሎቹ ግን “የወያኔ
መንግሥት የትግራይ መንግሥት አይደለም” እያሉ ይከራከሩና ‘ትግሬዎች ተጠቅመዋል” በማለት የትግራይ ሕዝብ በተቀሩት ኢትዮጵያዊያን
ዓይን ቀውስጥ ገብተው ለግድያ እና ለብቀላ ምክንያት ሆነዋል (ወይንም ለወደፊቱ ይሆናሉ) እያሉ ሲዋሹ ለዘመናት የሰማነው የሽፋን
“ተንኮል” (በትግሬ ምሁራን)፤ ወይንም አጉል የፖለቲካ እወደድ ባይነት ወይንም የእይታ ዕጥረት (በነ ልደቱ ኣይነቶቹ) ሲሰበክ
የቆየ ነው።
እውነታው ግን የወያኔ መንግሥት 27 አመት ሲገዛ የትግሬዎች መንግሥት እንጂ የኢትዮጵያዊያን እንዳልነበረ ከተግባሩና ከባሕሪው መከራከር ይቻላል። የትግራይ ሕዝብም በድርጅት አጠራር “ውድባችን በመንግሥትነት ደግሞ “መንግሥታችን” እያለ ነው የጠራው። የትግራይ ሕዝብ በዚህ መንግሥት መጠቀማቸውም ደጋግሜ እኔም ሆንኩ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ፤ ክቡር አቶ ተክሌ የሻው እና እኔው እራሴ በተደጋጋሚ አንዳንዱም ከነዚህ ወዳጆቼ ሆኜ አንዳንድ ጽሑፎቼም በራሴ ያጠናሁዋቸው ሰነዶች በማስረጃ ሳቀርብ እንደነበር ታውቃላችሁ። እዚህ ፎቶ የቀረበው የሕክምና ሰንጠረዥ የትግራይና የሌሎች “ክልሎች” የሚያሳይ እንደ ናሙና ስትመለከቱ ትልቁ ስጋ የት እንደተመደበ ታያለችሁ። በዚህ ጽሁፍ ትግራይ በሕክምና ኢንዳስትሪ፤ንግድ፤ት/ቤት፤ማሰልጠኛ፤ ዩኒቨርሲቲ/ ሓኪሞች፤ ነርሶች፤ ምሁራን፤የመንገድ ሥራ፤የጭነት፤ የእንሹራንስ፤ የንግድ፤ የተማሪዎች፤ የእስኮላር ሺፕ ተጠቃሚነት፤ ኤምባሲ …ወዘተ… ትግራይ ከሌሎች ክልሎች በጠቀሜታ ልዩነት ለማሳይት በተለያዩ ጊዜያት የተለጠፉትን መመርመር ነው (በኔው ድረገጽ ማየት ትችላላችሁ) እዚህ እነዚህን ለማቅረብ ግን ሰፊ ዝርዘር እና ግራፎች/የጥናት ሰንጠረዥ ስዕሎች ስላሉት ፌስ ቡክ ገጽ ላይ ለማተም ኣያመቹም።
በዚህ ጥናት ያደረጉት ለምሳሌ
ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ (The Pillage of Ethiopia by Ethiopia by Eritreans and their Tigrean
Surrogates – Assefa Ngash, MD 1996) ወያኔ በወቅቱ የአገሪቱን ሃብት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት ረዲኤቶችና
(NGO) የገንዘብ ፍሰት ሕክምና ንግድ ቤቶችን ወታደራዊና የደህንነት
መዋቀሮችን እያፈራረሱ በትግሬዎች እየተተኩ በጠቅላላ
“Structural Adjustment Program “ በሚባለው ዘረኛ
እና የመበዝበዣ መርሃ ግብር የመሳሰሉ ንብረቶችና እርሻና የልማት ተቋማት/ዕቃዎች/ ወደ ትግራይ እየተጓዙ አገሪቷ እንዴት አራቁተው
ትግራይን በወላጅ አባቴ አገላለጽ “ቻይና” እንዳደረጉዋት በዛው በ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ መጽሐፍ ላይ ማየት ትችላላችሁ። መጽሐፉን
ለማግኘት “አማዞን የመጽሐፍ መሸጫ መደብር” የምታገኙት ይመስለኛል። ከዚያም ክቡር አቶ ተክሌ የሻው እና በኔው የቀረቡ ሰነዶች
በኔው ድረገጽም ሆነ በተለያዩ ድረገጾች የቀረቡ ስለሆኑ ማየት ጠቃሚ ነው። የቀረቡት ጥናቶች አንድም ሰው እስከዛሬው ድረስ በተጻራሪ
ማፍረስ አልቻለም። የምንሰማቸው ተቃውሞ ግን እንደ ልደቱ እና እንደ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም የመሳሰሉና ትግሬ ምሁራን ከአፍ
ተቃውሞ ያልተሻገረ ተቃውሞ ብቻ ስንሰማ ነበር ፤አሁንም ልደቱ ያ የተለመደው ማስረጃ የሌለው ተቃውሚ ነው እየተናገረ ያለው።
ለመሆኑ ወያኔ ለምን ተመሰረተ?
ትግራይ በአማራ ምክንያት ደህይታለችና ምጣኔ ሃብቷን ለማሳደግ አገር ለመመስረት ወዘተ..ወዘተ.. በሚል ነው። ይህንን እውን ለማድረግ
ደግሞ የትግራይ ተማሪዎች በረሃ ሄዱ። ደርግ ወደ ሥልጣን በመጣ በማግሥቱ 1967 ዓ.ም አስራ አንድ ሆነው የካቲት አስራ አንድ ደደቢት በረሃ ገቡ። ደደቢት የገቡበት ምክንያትም “ከላይ የተገለጸው መነሻ ያደረጉት እና ጨቋኟ የአማራ ብሔር” ብለው በጥላቻ የሚጠሩትን የአማራ ሕዝብን በመጥላት በማዳበልም የአማራ ውጤት ብለው የሚጠርዋትን አገር ኢትዮጵያንም ለማፈራረስ ከተመቸኝ በመንግሥትነት እስከወዲያኛው
እንገዛታለን ካልሆነም እንደምትፈርስ አድርገን እንሰራላታለን በማለት መጠሪያቸውም ተ.ሓ.ህ.ት (ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ
- የትግራይ ሕዝብ የአርነት ተጋድሎ) ብለው ሰየሙ። ቆየት ብለውም
ህ.ወ.ሓ.ት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) (በእሊዝኛው TPLF Tigaray People Liberation Front ብለው) እንደ ፖሊሳሪዮ እና ፓለስታይን
የመሳሰሉ የአርነት ታጋዮች ስማቸውን ሰየሙ። የጠመንጃቸው መነጽርና የፖለቲካ ቅስቀሳቸው ያነጠጠረው
አማራን ከሌሎች ብሔሮች ጋር ማጋጨት፣የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ከሌሎች እምነቶች ጋር በጠላትነት እንዲተያዩ ማድረግ፤እንዲፈናቀልና እንዲጨፈጨፍ ማድረግ ነበር። ተሳካላቸው።
አገር ለማፍረስ ከማንኛውም ጠላት ጋር ተሰልፈዋል። “እነመለስ ዜናዊ ፣ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሶማሌው ከዚያድ ባሬ ጎን ወግነዋል። ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከዩሐንስ አንገት ቆራጭ፣ ከሱዳን ጋር አብረዋል፣ተባብረዋል። አሁንም እየተባበሩ ነው። ከግብጽና ከሱዳን ጋር በደደቢት፤ በመቀሌና በተምቤን ዘመናቸው እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ላይ በአንድ ረድፍ በአንድ ዕዝ ሥር እየተመሙ ነው።’’ ይህንን ለመፈጸም የትግራይን ሕዝብ ከጎናቸው አሰልፈው ተባባሪ ማድረግ ነበርና በሚገርም ሁኔታ ለ47 አመት በላይ ሕዝቡ ተኮልኩሎ ከጎንም ከኋላም ከፊትም ሆኖ እየመገበም አየተዋጋም ፤እየተከላከለላቸውም ለመንግሥትነት አበቃቸው። መንግሥት ከሆኑ ወዲያም ተጠቃሚ ሆኖ አማራን እንደጠላት ማየቱን ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ሆነው አንደኛው መብረቅ አንደኛቸው ነጎድጓድ በሚል እየተዘፈነላቸው ኢትዮጵያን እና አማራን በጠላትነት አይን እንዲያዩትና በአሸናፊነት ስሜት ተከናንበው ቀጠሉበት። የአገሪቷን ሃብት ቦጠቦጡት ፤ ሥልጣንም የትግሬ ሆነ።
ነብሳቸው በአፀደ ገነት ያኑርልንና ከዚህ ዓለም የተለዩን ክቡር ሊቀ ሊቃውንቱ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ፕሮፌሰር መስፍን ኢትዮ-ሚዲያ ላይ አንድ ጽሑፍ ለጥፈው አይቼው ለፕሮፌሰር ጌታቸው ጠቆመኩዋቸውና ካነበቡት በኋላ የሚከተለውን ጽፈው መልስ እደሚሰጡ ነገሩኝ። እንዳሉትም በኔው ድረገጽ ተለጠፈ።
እንዲህ ይላል የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ጽሑፍ፡
ፕሮፈሰር መስፍን ወልደማርያም የትግራይ ሕዝብ በወያኔ አገዛዝ አለመጠቀሙን ለማሳየት ኢትዮሜዲያ ላይ አንድ ጽሑፍ አውጥቶ ነበር። ይህ የኔ ድርሰት የዚያ ተቃራኒው አስተያየት ስለሆነ መውጣት የሚገባው፥ እዚያው ኢትዮሜዲያ ላይ ነበር። ግን የኢትዮሜዲያ ባለቤት “በዚህ ድርሰትህ የትግራይን ሕዝብና ሕወሐት/ኢሕአዴግን አንድ አድርገሃቸዋል (“. . . TPLF a synonym with the Tigrai people.”) ብሎ ሊያወጣው አልፈቀደም። በእኔ አስተሳሰብ ይኸ ድርሰት ወያኔንና የትግራይን ሕዝብ አንድ አያደርግም።
ወደ ተነሣሁበት ልመለስና፥ እግር ኳስ ጨዋታ አጥብቄ እወዳለሁ። እንግሊዞች ፉትቦል፥ አሜሪካኖች ሶከር የሚሉትን ጨዋታ ማለቴ ነው። አሜሪካኖች ለምን ሶከር እንደሚሉት ምክንያቱን ለማወቅ አልሞከርኩም፥ አላሰብኩበትምም። በዚህ ጨዋታ ፍቅር የተነደፍኩት፥ በልኩ እንዳደርገውም ብዙ የተቀጣሁበት፥ ገና ፊደል ስቆጥር ነው። ለብዙ ነገሮች ያለኝ ፍቅር እየቀዘቀዘ፥ እየጠፋም ሲሄድ ለኳስ ጨዋታ ያለኝ ፍቅር ግን አሁንም ትኩስ ነው። ዛሬ መጫወት ባልችልም፥ ዋናዋናዎቹን የእንግሊዝና የእስፓንያ የጨዋታ ኅብረቶች (English Premier League and Liga BBVA) ጨዋታቸውን በቴሌቪዠን እከታተላለሁ። እንግሊዞች በጦርነት ጊዜ ለኳስ ጨዋታ ያህል ጦርነት ያቆሙ ነበር የሚሉት ተረት እውነትነት ቢኖረው አይገርመኝም። የወያኔ ባለጸጎችም የእንግሊዝ አገር የእሑድ ቅዳሜን ኳስ ጨዋታ ለማየት እንግሊዝ አገር ድረስ በረር ብለው የሚመጡትም የፍቅር ጉዳይ ሆኖባቸው ነው--እኛ በልጅነታችን አዲስ አበባ ካምፖሎጆ (“ካታንጋ” የሚባል ስም ከወጣለት ቦታ) ሄደን ተጋፍተን እንደምናየው ማለት ነው።
የመግቢያ ዋጋ መክፈል ከቻልኩ ጀምሮ “ከካታንጋ” ጋር ተለያይተናል። አሁን ከፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም፥ አንዳንዴም ከአቶ አርአያ አሰፋ ጋር፥ የሳምንቱ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ስቱዲዩም አዘውታሪ ሆኜ ነበር። እንዲያውም ለዚህ ጽሑፍ መንሥኤ የሆነኝ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም “የወያኔ ጥላቻ ፍሬ” በሚል ርእስ በቅርብ ጊዜ በኢትዮሜዲያ ያቀረበው አስተያየት ነው። መስፍን ጽሑፉን፥ “ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ . . . የትግራይ ሕዝብ መደህየቱ አልበቃ ብሎት ሲለምንም እየተሳቀቀ ነው” በማለት ይጀምራል። ጥቂት እልፍ ብሎ፥ “ትግሬነታቸው ብቻ እንዲህ የደላቸው በጣም፣ በጣም ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህ በወያኔ አገዛዝ ትግሬ ሁሉ ተጠቅሞአል ማለት ከጉልህ እውነት ጋር የሚጋጭ ስሕተት ነው” ይላል።
እንደ መስፍን “ንትርክ” ባልለውም እርግጥ በጉዳዩ ብዙ ቁም ነገር የሞላበት፥ ማስረጃ የቀረበበት ውይይት አንብቤያለሁ። ከሳሾቹ ብዙ ማስረጃ ስለሚደረድሩ፥ “በወያኔ አገዛዝ የትግራይ ሕዝብ አልተጠቀመም” የሚሉ የወያኔ ደጋፊዎች ብቻ መስለውኝ አላመንኳቸውም ነበር። የመስፍንን አቋም ስለማውቅ፥ ጽሑፉን ሳነበው ማሰብና “ተሳስቼ ይሆን እንዴ?” ማለት ጀመርኩ። የትግራይ ሕዝብ ሳይጠቀም ተጠቅሟል፥ እየተጠቀመ ሳለ አልተጠቀመም ማለት ከሁለቱ አንዱ ይቅርታ የሚያስጠይቅ ትልቅ ወንጀል ነው። በእኔ በኩል፥ ወያኔዎች ብዙ ሰው ደሙን አፍሶ የታገለለትን ዲሞክራሲን በማፈን የኢትዮጵያን ሕዝብ ስላሳቀቁት፥ በፍጹም ጥላቻ እጠላቸዋለሁ። ሆኖም የመስፍንን ድርሰት ሳነብ፥ ጥላቻዬ እውነቱን እንዳላይ ዓይኔን ጋርዶት ይሆን ብዬ፥ ቆም ብዬ መረጃዎቼንና አቋሜን መመርመር ጀመርኩ።
የወያኔ ተቃዋሚዎች ያቀረቧቸው መረጃዎች ያሳደሩብኝን እምነት በጀመርኩት የኳስ ጨዋታ ምሳሌነት ልግለጽ። ከፕሮፌሰር መስፍን ጋር ብዙ ጊዜ በሀገር ጉዳይ እንከራከር ነበር። እንደማስታውሰው፥ የተለያየ አስተያየት ይዘን ተነሥተን ውይይታችንን በተመሳሳይ አስተያየት ላይ እንጨርስ ነበር። አሁንም እንደግመው ይሆናል።
የክበብ ቡድኖች ኳስ ጨዋታ የወያኔን ፖለቲካ ለመረዳት አስተዋፅኦ አለው። የአንድ ቡድን አባላት፥ ሁሉም ከቡድኑ አባቶች ጀምሮ፥ በከፍተኛ ደረጃ ይግባባሉ። አይጥ (ጎል) የሚያገባው አንድ ተጫዋች ቢሆንም፥ ውጤቱ የሁሉም ጥረትና ተራድኦ አለበት። ጥቅሙም የሞላ ቡድኑ ስለሆነ፥ ደስታውም፣ ጭፈራውም፥ ሽለላውም አብሮ ነው። የቡድን አባቶችን የሚመርጡት አባላቱ ናቸው--በዘመድ ሳይሆን በችሎታው። ማንም ተጫዋች የራሱን ቡድን የሚጎዳ ጨዋታ አይጫወትም፤ ጥቅም ያስቀራል፥ መልቲነት ያለበት ተጫዋች ቢኖርባቸው ሥራው በግላጭ በአደባባይ ስለሚታይበት ወዲያው ይባረራል።
በግላጭ የሚያዩ የቡድኖች ደጋፊዎች ሁሉ ናቸው። እነሱም ጥቅመኞች ናቸው። በቡድኑ ጨዋታ የሚደሰቱት ወይም የሚያዝኑትና የሚቆጡት ስለዚህ ነው። መቸም ጥቅም በወርቅ ብቻ አይገመትም። እንዲያውም እኮ ወርቅ ለጥቅም መግዢያ እንጂ ራሱ ብቻውን ከጌጥነት ያለፈ፥ ብዙ ጥቅም የለውም።
የአንድ የኳስ ቡድን ጥቅመኞች ምን ያህል ብዙ እንደሆኑ እናስብ። ለምሳሌ፥ የእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ አባል ቡድኖች ደጋፊዎቻቸው፥ እንደ ወያኔ መኳንንት ኢንግላንግ ድረስ እየበረሩ ለማጨብጨብ የሚያስችል የተዘረፈ ወርቅ ባይኖራቸውም፥ ብዛታቸው እስከ ዓለም ዳርቻ ይደርሳል። እንግሊዝ አገር ለተደረገ ጨዋታ ዓለም ዳርቻ ያሉ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች እስከመፈናከት የሚደርሱበት አለ። ቡድኑ ደጋፊዎቹን እንዳያስቀይም ብዙ ይጠነቀቃል። ካስቀየመ፥ ደጋፊ ያጣል፤ ይወድቃልም።
ጥቅመኞቹ የጥቅም ደረጃቸው የተለያየ ነው። ለምሳሌ፥ ቡድኑ የክበብ ቡድን ከሆነ፥ የቡድኑ ባለቤት ገፈፉን ያነሣል። ተጫዋቾቹ ጥቅማቸውን የሚረከቡት የተገዙ ዕለት ነው። “የጨዋታ ቡድን ባለቤት አለው” ማለት፥ ባለቤቱ ከፈለገ፥ ምንጊዜም ይሸጠዋል፥ ይለውጠዋል ማለት ነው። ተጫዋቾቹም ከየቦታው ተገዝተው የተጠራቀሙ የመርሰነሪ (Mercenary)ብጤዎች ናቸው። ጀሌው ሕዝብ ግን አንድ ቡድን የሚደግፈው ቡድኑ ብሔራዊ ወይም የሱ ስለሆነ ሳይሆን፥ የሱ መሆኑን በጭፍን አምኖ ነው--በእምነት ብቻ። አለዚያማ፥ አዲስ አበባ ላይ ሆኖ ለሊቨርፑል ማጨብጨብ ትርጉም አይኖረውም።
እስቲ በዚህ አንጻር ወያኔዎችንና ደጋፊዎቻቸውን እንያቸው፤ ወያኔ እንደ አንድ የኳስ ቡድን ነው። እያንዳንዱ አባል የገንዘብ ጥቅመኛ ነው፤ ማስረጃዎቹ እንደሚያመለክቱት፥ ሁሉም አይበለጽጉ መበልጸግ በልጽገዋል። ራሱ ቡድኑም ቢሆን ለገንዘብ የተገዛ ነው ይባላል። በየደረጃው የሚጠቀሙ ጥቅመኛ ደጋፊዎች አሉት። “ገዢዎቹ የወንዛችን ሰዎች ናቸው” ማለቱ ብቻ የሚያረካቸው ሞኞችና አደገኛ ጥቅመኞች ጥቂት አይደሉም፤ ይኸም ጥቅም ነው ማለት ነው። ዋናው ጥቅም ግን የተመሠረተው በኢኮኖሚው ላይ ነው። የውስጥና የውጪ ዐዋቂዎች እንደሚነግሩን፥ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በወያኔ ደጋፊዎች እጅ ተይዟል። የመንግሥት ቁልፍ ሥራ የሚሰጠው ለትግራይ ተወላጆች ነው። አንድ ሰው ሥራ ሲጠይቅ የሥራ ማመልከቻ ይሰጠዋል። በማመልከቻው ላይ ችሎታውንና ዘር ማንዘሩን እንዲመዘግብ ይገደዳል፤ ማንነቱን ይናዘዛል። በዚህ ዘዴ ለአድልዎ ይጋለጣል።
መለስ ዜናዊ፥ “አይሁድ የአሜሪካን ኢኮኖሚ እንደያዙት የትግራይ ልጆችንም የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አሲዛቸዋለሁ” ብሎ የፎከረው በፉከራ አልቀረም። ኢኮኖሚውን በጠቅላላ የሚያንቀሳቅሱ የትግራይ ወጣቶች በጥድፊያ እየተዘጋጁ ነው። በመንግሥት ሀብት ወደ አሜሪካና ወደ አውሮፓ ስመ-ጥር ዩኒቨርሲቲዎች የሚላኩ ተማሪዎች የትግራይ ተወላጆች ናቸው። እነሱ እስኪደርሱ፥ አንዳንዱን ሥራ ሌሎች ይዘውት ብናይ ሌሎችም ተጠቅመዋል አንበል። ቦታ ጠባቂዎች ናቸው። የትግራይ መሬት ጠፍ ስለሆነ፥ በሰቲት ሁመራ፥ ወልቃይት ጸገዴ ትግራይ ሆነዋል። ከዚያ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ያልሆኑ ገበሬዎች ተባርረው የርሻ መሬታቸውን የትግራይ ተወላጆች ወርሰውታል። የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በመብራት እጥረት ምክንያት በጨለማ በዳበሳ ሲያመሹ፥ ትግራይ ውስጥ እንዲህ ያለ ችግር ከተወገደ፥ ዓመታት አልፈዋል። ይህ ሁሉ ሐሰት ከሆነ፥ አቋሜን እለውጣለሁ።
እውነት ከሆነ፥ ታዲያ እንዴት ነው፥ በወያኔ አገዛዝ የትግራይ ሕዝብ አልተጠቀመም ለማለት የሚቻለው? ምናልባት የዚህ ሀገራዊ ወንጀል ዜናው ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖሩት ታፍኖ፥ በውጪ አገር ለምንኖረው ብቻ ተከሥቶ ይሆን? ሁኔታው የጠበንጃ ጠባይ ተገላቢጦሽ ሆነብኝ። ጠበንጃ ድምፁን ማሰማት የሚጀምረው ተኳሹ ከቆመበት ቦታ ሆኖ፥ የሚመታው ርቆ ሄዶ ነው። የወያኔ አድላዊነት አዲስ ነገር አይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥ አልታፈነም። የወያኔ ጥረት፥ “ትግራይ እስክትለማ ኢትዮጵያ ትድማ” መሆኑ ውጪ ሀገር ለምንኖረው የደረሰን ኢትዮጵያ ውስጥ በሰፊው ተነግሮ ነው።
መቸም አንድን ሕዝብ በአንድ ትውልድ ከዳር እስከዳር ማበልጸግ አይቻልም። መስፍን “ትግሬዎች ሁሉ” እያለ “ሁሉ”ን የሚደጋግማት ስለዚህ ከሆነ፥ እንስማማለን። እንዲያውም፥ “ሁሉ” ከቁም ነገር አይቈጠርም፤ ለመወያያ ርእስነት ብቃት የለውም። ሁሉም ቀርቶ፥ ዘጠና በመቶው የትግራይ ሕዝብ እስኪያልፍለት ድረስ እንኳን ገና ብዙ ጊዜ ይፈጃል። ጅማሮው ግን ተጀምሮ እየገሠገሠ ነው። ፍሬ ማፍራትም ጅምሯል። እስከዚያ ብዙ ትግሬዎች እንደብዙ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ድኾች ሲለምኑ መታየታቸው አይቀርም። እትግራይ ውስጥ ቀርቶ፥ በብልጽግና በዓለም አንደኛውን ደረጃ በያዘችው አሜሪካን አገር እንኳን ለማኞች ሞልተዋል። ተአምራዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት ካልመጣ በያዝነው ሥርዓት፥ እስከተጓዝን ድረስ፥ ክርስቶስ፥ “ድኾች ሁል ጊዜም ከማህላችሁ ይኖራሉ” ያለው፥ የማይሻር ቃል ሆኖ ይኖራል።
“በወያኔ አገዛዝ የትግራይ ሕዝብ አልተጠቀመም” የሚል እምነት ያለው ሰው ማስረጃው የትግራይ ለማኞች በመንገድ ላይ ማየት ከሆነ፥ አንድ የትግሬ ለማኝ ከብዙ ኢትዮጵያውያን ለማኞች ማህል እስከተገኘ ድረስ፥ በእምነቱ ሊጸናበት ይችላል። ዋናው ቁም ነገር ግን እንዲህ ነው፤ የወያኔ አገዛዝ ለትግራይ ሕዝብ ያደላል ወይስ አያደላም። አያደላም ለማለት የዓይን ምስክሮችን መካድ፥ መለስ ዜናዊንም ውሸታም ማድረግ ይሆናል። “ለትግራይ ማዳላትስ አዳልተዋል፤ ግን ሕዝቡ አልተጠቀመም” ማለትም ይቻል ይሆናል። ግን እንዲህ ያለውን ተቃራኒ አስተሳሰብ ማስታረቅ ቀላል አይሆንም። እያዳሉለት ባይጠቀም፥ ወያኔዎችን ከማዳላት ወንጀል ነፃ አያወጣቸውም። ማዳላት አንዱን ጠቅሞ ሌላውን ጥቅም መንሳት ነው።
ማዳላት አደገኛ በሽታ ነው። ፍሬው ጥላቻ ነው። የተዳላበት ወገን ዳኛውንም የተዳላለትን ወገንንም አብሮ መጥላት፥ ከዚያም አልፎ ማቄምና ክፉ ነገር ማሰብን ያስከትላል። የትግራይ ሕዝብ አልተጠቀመም ማለት የትግራይን ሕዝብ አስጠልተውታል ማለት ከሆነ፥ እኔም እስማማለሁ። ጥያቄው ይኸ ከሆነ፥ በእንደዚህ ያለ ጊዜ፥ “ይህ ሁኔታ እኮ የወንድማማቾችን መተላለቅ ያስከትላል” ብሎ መሥጋትና በፍጥነት መፍትሔ መፈለግ የማንም ኢትዮጵያዊ ግዴታ መሆን አለበት። ለጥፋቱ ተጠያቂው የትግራይ ሕዝብ አይደለም። የትግራይ ሕዝብ፥ “እኛ የምንፈልገው ዕድላችን እንደጥንቱ ከሌላው ሕዝብ ጋር እኩል እንዲሆን ነው” ቢል የመሪዎቹን አርጩሜ አይችለውም። እስታሊን የሶቪየት ዩኒዮንን በቴክኖሎጂ ለማራመድ ያደረገውን እናውቃለን። ራሳቸው ትግሬዎቹም ወደመጀመሪያው ላይ ቀምሰውታል። (“ፋሺዝም በትግራይ” የሚለውን የጋዜጠኛ ሪፖርት እናስተውሳለን።) ስለዚህ ትኵረቱ መሆን ያለበት በደላቸውን እንዲያቆሙ ምክር በሚገባቸው በወያኔዎቹ ላይ ነው።
ወያኔዎችና ደጋፊዎቻቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላም እንዲኖር ከፈለጉ (ለመፈለጋቸው ምንም ምልክት አያሳዩንም)ዕርቅ ለማምጣት ዕድሉ ገና አላመለጠም። ብቻ የሚያሳዝነው፥ ኋላ ቀር ፖሊቲከኞች የሚነቁት ዕድሉ ካመለጠ በኋላ ነው። ቅዱስ ዳዊት፥ “ስሕተትን (በጊዜው) ማን ልብ ይላታል” ሲል ደምድሞታል።
ወደኳስ ጨዋታው ምሳሌ ልመለስና፥ የወያኔ ቡድን አንዳንድ ጊዜ በራሱ ጎል ላይ
አይጥ ያስቆጥራል። ባለቤቱን (ኢትዮጵያን) ስለከዳ፥ የባለቤቱን ጥቅም ያላንዳች ይሉኝታ ያዝረከርካል። አገሪቱን ወደብ-አልባ ማድረግ፥
መርከቦቿን መሸጨ፥ ጎሳዎችን ማጋጨት፥ አገር መከፋፈል፥ በኢትዮጵያ ሀብት የሌላ ሀገር ባንክ ማበልጸግ፥ ዓባይን ለመገደብ ካይሮ
ድረስ ሄዶ ማመልከቻ ማቅረብ ሁሉ በራስ ጎል ላይ ኳስ ማስገባት (አይጥ-በላ መሆን)፥ ነው።
ሲሉ ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃሳባቸውን ደምድመዋል።
በመቀጠል በራሴው መጽሐፍ እንደ ጥቅስ የጠቀስኩት አዲስ አበባ ደርሶ የመጣ አንድ ወዳጄ የላከለትን መልዕክት ወደ እኔ ያስተላለፈውን ልጥቀስና ወደ ሌላኛው ታዛቢ እገባለሁ።
የትግሬዎች ዘመናቸው የመሆኑ ምልክት ጥግ አልነበረውም። ሰማዩን ምድሩን የሚያነቃንቅ ጥጋባቸው በግልጽ ይታያል። ላስነብባችሁ፦ይህንንም በመጽሐፌ ጠቅሼዋለሁ።
<<…….እግዚአብሔር ይስጥልኝ ወንድሜ። ወደ ኢትዮጵያ ሄጄ ነበር የተወሰነ ወር ቆይቼ ነው የመጣሁት። የሰውን ፊት አይተው ይለያሉ፥ሊቃወመን ይችላል ብለው የሚያስቡትን ኤርፓርት ኢሚግሬሽን ቡት ውስጥ ከሚቀመጡት ዘረኛ ትግሬዎች ጀምሮ። በተለይ ቦሌ መድሐኒአለም ፊት ለፊት በኤድና ሞል ዝቅ ብሎ ብዙ ዘመናዊ ባለ 5 ኮከብ ሆቴሎች ተከፍተዋል ሁሉም የትግሬ ናቸው። ነጮቹ ‘ሆቴል ዲስትሪክት’ ይሉታል። የኛ ህዝብ መቀሌ እና አፓርታይድ ይለዋል ሰፈሩን። በተለይ “ቬኒሺያን” የሚባለው የትግሬ ሆቴል ገብተን 10 ዲቂቃ እንደተቀመጥን ካውንተሩ ላይ የሚቀመጠው እጅግ በጣም የጠገበ ሲራመድ መሬት የሚነቀንቅ ትግሬ የተቀመጥንበት ድረስ መጥቶ ያፈጣል። አስተያየቱ ሀሉ በጣም ነው የሚከብድው። ህዝቡ ኪሱ ውስጥ ያለውን ብር ቶሎ አራግፎ እንዲወጣ ነው የሚፈልጉት። ጥላቻቸው በግልፅ የሚታይ ነው። በዘረኝነት እና በጥላቻ ከተመረዘ ህዝብ ጋር መኖር በጣም ነው የሚከብደው። ህዝባችን በገዛ አገሩ ላይ እንዲሸማቀቅ እየተደረገ ነው። ባካባቢው ባሉት ሌሎች የትግሬ ሆቴሎች ውስጥም ተመሳሳይ ዘረኝነት ነው ያየሁት። “> ይላል ለዚህ ደራሲ የተላከለት ደብዳቤ (176)። ይላል።
እንዲሁም ኢትዮጵያ አዲስ
አባባ ውስጥ ኗሪ የሆነ ወዳጄ ትግሬዎች በመንግሥታቸው በኩል በስፋት የመጠቀማቸው ዕድል ሰፊነቱን በምሬት የጻፈውን ልኮልኝ በድረገጼ
ለጥፌው ነበር። ይህንንም ጠቃሚ ነውና አለፍ አለፍ ብየ ጽሑፉን እየቆረጥኩ ልጥቀስ፦
ታማኝ ከሦስት አመት በፊት
አንድ ግሩም ማስረጃ አቅርቦ ነበር፤ ያንን ስመለከት እነዚህ ሰዎች በመጨረሻው “ ‹ወጥ በወጥ› ያደርጉን ይሆን?” ብዬም
ተጨነቅሁ፡፡ ይህን የታማኝን ዝግጅት እነፕሮፌሰር መስፍንና መሰሎቹ በወያኔው መንግሥት የ“ትግሬ አልተጠቀመም”ና “ወያኔ
የትግራይን ሕዝብ አይወክልም” ዘፈን አቀንቃኞች እንዲመለከቱት በጣም ወደድኩ፡፡ ይመልከቱትና አንጎል ካላቸው እውነቱን
ከሀገራችን ጋዜጠኞች ብቻ ሣይሆን ከውጪዎቹ የሰብኣዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የበላይ ኃላፊዎች አንደበት ይረዱት፡፡
እውነት ብትመር ብትጎመዝዝም
ምርጫ በምናጣበት ወቅት ዶሮ ማታ ብለን መጨለጥ ይገባናል፡፡ እንዲህ ስናደርግ አንድም ከተጣባን ኮሶ እንሽራለን አሊያም ሌላ
አማራጭ እንፈልግና ከህመማችን እንፈወሳለን፤ እየተዝረጠረጥን መኖር ግን አይገባንም፡፡
አዲስ የቅኝ ግዛት ዓይነት
ነው የገጠመን፡፡ አዲስ የአፓርታይድ ዓይነት ነው የተጣለብን፡፡ የዚህ ጭራቃዊ ቅኝ አገዛዝና አፓርታይድ የመጨረሻ ውጤት
የሚሆነው የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እንጂ ከሦርያ የበለጠ ዕልቂት ነው፡፡ የናቁት … አስረግዞ 85 ሚሊዮን ሕዝብ እንዲህ
ካስደገደገን የተናቀው 85 ሚሊዮን ሕዝብ ከእንቅልፉ ሲነቃ ምን ሊያደርግ እንደሚችል ማሰቡ ይዘገንናል፡፡ ግን ግን ፈጣሪ
ከጎናችን አይለይ፡፡ የእስካሁኑ በቃችሁ ብሎ ለሌላ ውርጅብኝ አይዳርገን፡፡ ጸሎት መያዝ አሁን ነው፡፡ ከሆነ በኋላ መቆላጨት
ዋጋ የለውም፡፡ ….
ያለንበት አገዛዝ የትግሬ ቅኝ
ገዢ አገዛዝ ነው፡፡ ይህን ማስተባበል አንድም የሞትን ዕድሜ ወድዶ ማራዘም ነው፡፡ አንድም መዋሸት ነው፡፡ አንድም ጭልጥ ያለ
አድርባይነት ነው፡፡ ሀገሪቱ ከግርጌ እስከ ራስጌ በትግሬ ወያኔ ተቀፍድዳ ኤሎሄ እያለች ሳለ “ትግሬ እየገዛን አይደለም፤
ትግሬዎች አልተጠቀሙም” ብሎ መወሽከት ታሪክ ይቅር የማይለው የለየለት እብለት ነው፡፡ እንዲህ የሚሉ ወገኖች ግና በርግጥ
ዐይንና ጆሮ ይኖራቸው ይሆን? ለምን አዲስ አበባ አይመጡምና የመንግሥት ተብዬውን የወያኔ መናኸሪያ ጓዳ – ከተፈቀደላቸው –
አይጎበኙም? ታማኝ በየነ የሠራው የዳሰሳ ቅኝት ራሱም እንደጠቆመው አባይን በጭልፋ ዓይነት ነው፤ የትኛው የመንግሥት ቤት ነው
ከወያኔ ቀጥተኛ ቁጥጥር ነፃ የሆነና በሌሎች ኢትዮጵያውያን የሚተዳደር? ኢ-ትግራውያን ሠራተኞች የወያኔ ባርያና ሽቁጥቁጥ
ሎሌዎች አይደሉም እንዴ? በሁሉም መሥሪያ ቤት እንደልቡ የሚዘባነነው ማን ነው? ማነው አዛዥ ናዛዥ? ይህን የፈጠጠ እውነት
ማየት የማያስችል ምን ዓይነት ደምባራነት ነው? (በአንድ የመንግሥት – (“የመንግሥት” ስል እንዴት እንደሚቀፈኝ ብታዩ) –
የጦር ሆስፒታል አንድ ወቅት ስታከም እንደታዘብኩት ፈረቃቸው ደርሶ የተቀያየሩት ዘጠኙም የክፍሉ ሐኪሞችና ነርሶች ከጽዳቶቹ
ጭምር ትግሬዎች ናቸው(ግን ገራገርና ጥሩዎች ናቸው) – ይህ ምን ዓይነት አጋጣሚ ይሆን? ይህን የማፊያ ሥርዓት ላይገባው
የራስን ክብር አዋርዶ በውሸት ለማባበል መሞከር መናኛነት ይመስለኛል – ወይንም በአንዳች አእምሯዊ ግርዶሽ መሸፈን ነው፡፡
የንግዱንና ኢንዱስትሪውን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ወያኔ ትግሬ
ይዞት ለትግሬዎች እያዳላ ለሌላው ግን ግብርና ቀረጥ እንዲሁም የቤት ኪራይ እየቆለለ ከሥራም ከሀገራዊ የዜግነት መብትም ውጪ
ሲያደርግ እያየን ምኑ ላይ ነው ትግሬ አልተጠቀመም የምንለው? ምን ዓይነት አሽቃባጭነትስ ነው ገጥሞን ያለ ጎበዝ!)
ይልቁንስ በኔ በጠባቢቱ ዓለም
ትግሬዎችን በሁለት ከፍዬ እንደማያቸው ባጭሩ ልናገርና ላስረዳ፡፡ ትግሬ በአንድ ትልቅ ቅርጫትና በሌላ ትንሽዬ ዘምቢል በድምሩ
በሁለት ሊከፈል ይችላል፡፡ በትልቁ ቅርጫት ያለው ሕወሓትና ደጋፊዎቹ ናቸው፡፡ እነዚህ ብዙ ናቸው፡፡ ብዛታቸውም ከመቁጠር አቅም
በላይ ነው፡፡ በጥንጥዬ ዘምቢል ውስጥ የከተትኳቸው ትግሬዎች መጠናቸው በጣም ጥቂት ነው፡ ግፋ ቢል ከአንደኛ ክፍል የሒሣብ
መጽሐፍ የአራቱ መደቦች ክፍለ ትምህርት ውስጥ ሊካተት የሚችል መጠን ቢኖራቸው ነው – ማንም ሕጻን ሊደምር/ሊቀንስ የሚችለው
አነስተኛ አኃዝ ነው፡፡ እነዚህ ቢበዙልን የመከራ ደብዳቤያችን በቶሎ ይቀደድልን ነበር፡፡ የነዚህ ሚዛን ግን ገና በጣም
እንዳጋደለ ነው፡፡
ቀልድ አንቀልድም ብያለሁ፡፡
ብዙኃኑ የምላቸው ተጋሩ ወደዱም ጠሉም ሕወሓትና የህወሓት ናቸው፡፡ ይህን ስል የስንቶች ቅስም በሐዘን እንደሚሰበርብኝና
እንደሚያዝኑብኝም አውቃለሁ፡፡ ግን ምንም ማድረግ አልችልም፤ እግዚአብሔር ይመስገን አሁን በራሴም ላይ ከመፍረድ ወደኋላ
የማልልበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ – ተስፋ መቁረጥ ግን እንዳይመስላችሁ፡፡ (በነገራችን ላይ ከወያኔ የወጡና በአገዛዙ ብዙም
የማይደሰቱ በተራ ገቢና ከቀድሞ ድርጅታቸው ውጪ በአነስተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ትግሬ ጓደኞቼ በመለስ ሞት ጊዜ እንዴት እንደሆኑ
ታዝቤያለሁ – ቤታቸው በርሱ ፎቶ ተሞልቶና ማቅ በማቅ ሆነው ከርመዋል – ይህን እያወቅሁ ስለትግሬ ማንም ሊነግረኝ አይችልም፡፡
በቃ፡፡)
እናም አብዛኛው ትግሬ
ተጠቀመም አልተጠቀመም በፕሮፓጋንዳው ተሸንፎ ወያኔ ሆኗል ወይም መስሏል፡፡ ይህ አባባል ትግሬን ከሌላው ለመለየት ምናምን
እንደሚባለው ለመሆን አይደለም – እውነት ስለሆነ ነው፤ ደግሞም እኮ ዐማራና ትግሬ ሲለዩ ታየኝ፡፡ ወያኔዎችን ልፉ ቢላቸው
እንጂ የትኛቸው ነው ከየትኛቸው የሚለየው?… ለማንኛውም አምባሻ ሻጯ፣ ቁራሌው፣ መጥረጊያ አዟሪው፣ ወዘተ. እየተራበና
እየተጠማም ቢሆን ህወሓትን ከልቡ ይወዳል፡፡ (ለስለላ ሣይሆን ለእንጀራ ብለው በጠራራ ፀሐይ በየመንደሩ በእግራቸው የሚኳትኑትን
ማለቴ ነው) ዘር መጥፎ ነው፡፡ “ዘር ከልጓም ይስባል” ወይም “ትንሽ ሥጋ እንደመርፌ ትወጋ” የሚባለውም ለዚህ መሆን
አለበት፡፡
በአንጻራዊ አነጋገር ዐማራው ይሻል እንደሆነ እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁን
ሥልጣን የሚይዘው ግለሰብ የመጣበት ነገድ “የኔ ሰው ተሾመልኝ” በሚል መደሰቱ የሚቀር አይመስለኝም – ይህን ሁኔታ በአእምሮ
ዕድገት ምክንያት ንቀው ካልተውት በስተቀር ተፈጥሯዊም ይመስለኛል፡፡ የሆነ ሆኖ ይህ ብዙኃኑን ተጋሩ የዶልኩበት ቅርጫት ብዙ
ሕዝብ ያለበትና በትግሬ ሥልጣን ላይ መቀመጥ የማይከፋ ብቻ ሣይሆን የሚደሰት ነው፡፡ በኢኮኖሚ ያልተጠቀመም ቢያንስ በሥነ ልቦና
“እየተጠቀመ” ባዶ ሆዱን ተኮፍሶ ይውላል –…፡፡የሥነ ልቦና ነገር እጅግ አስቸጋሪ ነው አኅዋተይ፡፡ ሠለጠኑ የተባሉ የዓለም
ዜጎች ሣይቀሩ በደመነፍስ የሚዘፈቁበት መጥፎ አረንቋ ነው፡፡ አስታውሳለሁ – በ83 ዓ.ም ወያኔ አዲስ አበባ እንደገባ በወያኔ
ሬዲዮ የትግርኛ ፕሮግራም ስለትግራይ ሕዝብ በወያኔ ሥልጣን መያዝ ተጠቃሚነት የተጠየቀ አንድ ትግሬ ባለሥልጣን “የመጀመሪያው
ጠቀሜታ ሥነ ልቦናዊ ነው፡፡ ‹የኔ ሰው ሥልጣን ያዘልኝ› ብሎ ማሰቡ በራሱ ትልቅ ነገር ነው፡፡ ሁለተኛ ….” እያለ በኩራት
ይደሰኩር ነበር፡፡ እየተናገረኩት ያለሁት ጉዳይ እነሱ በተግባር ሲፈጽሙት የሚኮሩበትን፣ እኛ ግን ስንናገረው እንኳን በሀፍረት
የምንሸማቀቅበትን የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡ ሌላው የዚህ ተፃራሪ እውነት ደግሞ አንበርብር ሥልጣን ይዞ ጓንጉልና አበጋዝ
በርሀብ የሚገረፉ የመሆናቸውን ያህል ጎይቶም ሥልጣን ይዞ አብረኸትና ሀፍቶም በርሀብ ሳቢያ ከቀያቸው የመፈናቀላቸው አጋጣሚ
ሲጤን ሥልጣንና ነገድ ያላቸውን ልል ዝምድና አጉልቶ ማሳየቱ ነው፡፡ ሕይወት እንዲህ ናት – ዕንቆቅልሽ፡፡
የትግራይ ኤሊቶችም
እንደማንኛውም የትግራይ ሕዝብ ጤናማ ኅሊናን መሠረት ባደረገ ምርጫቸው ወይንም በይሉኝታና ለግል ጥቅም ሲሉ ከነዚህ ከሁለቱ
ጎራዎች አንዱን ወይ ሌላውን የሚቀላቀሉ ናቸው፡፡ ወደ ዘምቢሉ የሚገቡት ግን በጣት የሚቆጠሩ ናቸው ብዬ አምናለሁ፤ ብዙዎቹ
ይቺን “የዐማራ ጨቋኝ ብሔር” አይወዷትም – ከንቀታቸው ብዛት የተነሣ ደግሞ በአነስታይ ፆታ ነው የሚጠሯት – ግን ምን ዋጋ
አለው በነሱው ብሶ “በትግሬይቱ ጨቆንቲ ብሔር” ተክተዋት ዐረፉና እያሳቀቁ አሣቁን፡፡
ትምህርታቸው ከወረቀት ያላለፈ
የምሁር ማይሞች፣ በሰው ልጅ እኩልነት የማያምኑ የአእምሮ ጉንዲሾች፣ ዕይታቸው ከአላውኃ ወንዝ ጎጥ-ሰቀል አድማስ ያልዘለለ
የአእምሮ ስንኩላን የሆኑ የትግራይ ኤሊቶች ይህን በዘረኝነት ደዌ የተመታና ሀገርን የሚያወድም ወያኔ መደገፋቸውን ስናይ
ከዕውቀትና ከጥበብ ለሚመነጭ አስተዋይነት መገዛታቸውን ሣይሆን እንደውሻ ደምና አጥንት እያነፈነፉ ወደሚከረፋው የሆድ ውስጥ ዕቃ
ወደጨጓራና ጅብ አይበላሽ መውረዳቸውን እንገነዘባለን። ከዚህ አኳያ ብዙ ኅሊናቸው የታወረ ተጋሩ “ምሁራን” አሉ፡፡በዚህ የሰው
ልጆች ታላቅ የሥልጣኔ ዘመን እንዲህ ዓይነት “ሐጎስ ከአምባቸው ይበልጥብኛልና ከርሱ በፊት ያድርገኝ! በነስንሻው መቃብር ላይ
የሀፄ ዮሐንስ ሥርወ መንግሥት ያብባል!” የሚል መፈክር ያነገበ ደንቆሮ ምሁር ሲታይ በርግጥም የሰው ልጅ በተለይም
ኢትዮጵያውያን ምን እንደገጠማቸው ለማወቅ አዲስ ጥናት መደረግ ይኖርበታል ባይ ነኝ፡፡
ለማንኛውም ተቀበልነውም
አልተቀበልነውም ተጋሩ በሁለት መከፈላቸውንና ድንበሩም አንዳንዴ እጅግ ጠባብ መሆኑን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ አንድ የኤርትራ
ተወላጅና በደርግ ዘመን መጨረሻ አካባቢ በኤርትራ የወጣቶች ማኅበር ሊቀ መንበር የነበረ የዚያኔው ጠምበለል ሸበላ ወጣት አንድ
ቦታ ተገናኝተን ስናወራ “የሕወሓት ቫይረስ አደገኛ ነው፡፡ በማንኛውም ትግሬ ውስጥ የመገኘቱ ዕድል ደግሞ ከፍተኛ ስለሆነ
ተጠንቀቁ” ያለኝን መቼም ልረሣው አልፈልግም፡፡
ይህን አባባል የጣሱ ንጹሕ ኢትዮጵያውያን ትግሬዎችን እኔ የማውቃቸውን ብቻ
– ቁጠር ብባል የአንድ እጄን ጣቶች እንኳን በቅጡ የምጨርስ አይመስለኝም፡፡ የሚያስጨንቀኝ እንግዲህ ይህ ነው፤ ደግሞም ስንቶች
ምሁራን ተብዬዎች ወያኔን እየደገፉ ባሉበት ሁኔታ ተራው ማይም ዜጋ ከዚህ መርዘኛ አስተሳሰብ ነፃ እንዲሆን መጠበቅ
የተምኔታዊነት ምርኮኛ መሆን ይመስለኛል፡፡ እንቅልፍ የሚነሳኝ ታላቅ የዘመን ዕንቆቅልሽ ነው – ስታምነው የሚከዳህን ጠላት
ፈጣሪ ካልያዘልህና ካላሶበረልህ በተለይ በእንደኛ ዓይነቱ በመልክም በሰውነት ቅርጽም በቋንቋም በባህልም በሃይማኖትም …
በተመሳሰለ ማኅበረሰብ ውስጥ በሬን ካራጁ ለመለየት እጅግ በጣም ከባድ ነው፤ ይህም ችግራችን ይመስለኛል ጣራችንን ያበዛውና
የነፃነታችንን ዕለት ያዘገየው፡፡
እነሱ በደህናው ቀን ሁሉን
ነገር አሰናድተዋል፡፡ ይብላኝ ለኔ ቢጤው ከርታታ ዜጋ፡፡ እነሱ በኛ ስቃይ ይደሰታሉ፤ እኛ የነሱን ስቃይ እኛው ላይ ደርበን
ዕጥፍ ድርብ እንሰቃያለን፡፡ እነሱ ወደያዘጋጁት ጎሬ እየተወተፉ ለማምለጥ መሞከራቸው አይቀርም፡፡ ሞት ግን የትም ሀገሩ ነውና
ተደብቀው አያመልጡትም፡፡
ስሜት ብዙውን ጊዜ መጥፎ
ነው፡፡ በስሜት ያለቀን ነገር ኅሊናና ምክንያት በቀላሉ አሸንፈው አይመልሱትም፡፡ በስሜት ንግሥና ወቅት ቋንቋና አመክንዮ ዋጋ
የላቸውም፡፡ ወያኔዎችና ጭፍሮቻቸው ከምክንያትና ከሎጂክ ጋር ተቆራርጠው በስሜት ፈረስ መነዳት ከጀመሩ 40 ዓመታትን
ደፍነዋል፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ጀሌያቸው የነሱን ስብከትና የጥላቻ ፖለቲካ እየኮመኮመ እንደነሱው 40 ዓመታትን በመጓዙ ሠላሣ
ምክንያት እየደረደርክ “አብረን ነበርን፤ ወንድማማቾችን ነን…” ብትለው አይሰማህም፡፡ መስሚያው በወያኔ ጥጥ ተደፍኗል፤
“ተደጋግሞ የተነገ ውሸት ከእውነት ይቆጠራል” እንዲሉ በወያኔ የዘር ጥላቻ ቅስቀሳ አብዛኛው ትግሬ ሰክሯል ቢባል ማጋነን
አይደለም፡፡
ጥቂት የማይባል ትግሬ ደግሞ
በመሀል እየዋለለ ነው – እንኳን ትግሬውና ሆዳሙ ዐማራና የተጋቦት ትግሬው ሁሉ ከወያኔ ጋር አብሮ እያደሸደሸ በሚገኝበት
የነሆድ አምላኩ ዘመን የዐድዋውና የተምቤኑ “ንጡሕ” ትግሬ ለምን ወያኔ ይሆናል ብሎ መውቀሱም ፋይዳ የለውም – ፍርድ ከራስ
ነውና ገነት ዘውዴ ያልተጸየፈችውን ወያኔነት የሽሬው አይተ ገብሩ ተስፋጋብር አቅፎ ቢስመው አይፈረድበትም፤ “ልሃጫም ዐማራ”
እያለ ጌቶቹ በጋቱት ስድብ እመራዋለሁ የሚለውን ሕዝብ በስድብ የሚሞልጨው አለምነው መኮንን እያለ ኪሮስ አረጋዊን በወያኔነት
መጠርጠር ሞኝነት ነው፡፡
በሕወሓት ፕሮፓጋንዳ የተጠለፈው አብዛኛው ትግሬ በትምህርቱ የገፋ ባለመሆኑ
ሆዱ ከሞላና የሀብት ጥማቱ ከረካ ለሌላው ነገር ግድ ሊኖረው አይችልም፤ ስለመብት የሚታሰበው ደግሞ መብት ምን መሆኑን ሲያውቁ
እንጂ ከእረኝነትና ከተኩስ ወረዳ በቀጥታ ቤተ መንግሥት ለገባ ሰው የዜግነትም በለው ሰብኣዊ መብት ከቀልድ ፍጆታነት አያልፍም
– ለዚህም ነው እኮ ህገ መንግሥቱን ጠቅሰው መብታቸውን ሊያስከብሩ ለሚሞክሩ “የህግ” እሥረኞች “ለምትሉትን ህገ መንግሥት
ለእንትናችሁን ፅረጉበት፤ ከፎሎጋችሁም ቆቅላችሁ ብሉት…” እያሉ ያለሀፍረትና ያለአንዳች ይሉኝታ በማን አለብኝነት የሚናገሩት –
ከጥንቱ ጨዋ የትግራይ ሕዝብ እንዲህ ያሉ ማጋጣዎች መፍለቃቸው በውነቱ ሁል ጊዜ ይገርመኛል – ኣ! “ላም እሳት ወለደች…”
አሉ፡፡
እንደ ወያኔ ሥራ ከሆነ
እውነት ነው ይህ ዘመን በአፍራሽ ሁኔታ ከተለወጠ በትግራይ ወገኖቻችን ላይ ሊደርስ የሚችለው መከራና ስቃይ ሲያስቡት ከአሁኑ
በጣም አስጨናቂ ጊዜ እየመጣብን ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሀገረ እግዚአብሔር ናት መባሏ መጽናናትን ይሰጠን ይሆናል እንጂ አደጋው
ከሚታሰበው በላይ አስደንጋጭ ነው፡፡ የአበራሽን ጠባሳ ያዬ ደግሞ በእሳት ሊጫወት አይገባውም፡፡ የወያኔ ዐይንና ጆሮ ማታት ግን
መንስዔው ምን ይሆን? ምንድን ነው እንዲህ ያጀገናቸው ማለቴ ያደደባቸው?
ታዋቂና ተሰሚ የዐማራ ምሁራንንና የሀገር ሽማግሌዎችን ገድዬ ጨርሻለሁ ብሏል፡፡ የኢትዮጵያዊነት ምልክቶችን ሁሉ አንድባንድ ደምስሻለሁ ብሏል፡፡ በተቃውሞው ጎራ የሚገኙ ዐማሮችን ለቃቅሜ አይቀጡ ቅጣት በመስጠት – በስድብ፣ በግርፋት፣ በወፌላላ፣ በግብረ ሶዶም፣ በወሲብ ጥቃት፣ በጥፍር ንቅላትና በፈላ ዘይት ጥብሳት … ስብዕናቸውን በማዋረድ መቼም እንዳያንሠራሩ አድርጌያለሁ ብሏል፡፡ የዐማሮችን ቅስም ሰባብሬ ዳግመኛ ወደ ሥልጣን ዝር እንዳይሉ በአካልም በመንፈስም ኮድኩጃቸዋለሁ ብሏል፡፡ በአዲሲቷ ሕወሓት ሠራሽ ኢትዮጵያ ዐማራ ምንም ዓይነት ቦታ እንዳይኖረው በማድረግ በምትኩ ግን ሆድ አምላኩ የሆኑ ታዛዥ “ዐማሮችን” ሹሜ ከማካሂደው የዐማራን ዘር የማጽዳት ታሪካዊ ኃላፊነት የተረፉና ቀናቸውን የሚጠብቁ የዋሃን ዐማሮችን በዘዴ እስከጨርሳቸው አታልላለሁ ብሏል፡፡ … ብዙ ብሏል – ያላለው ነው የሌለው ይልቁንስ፡፡
ችግሩ ወያኔ ያደረሰውን ያህል
ጥፋትና ውድመት በተለይ በዐማራው ላይ ቢያድርስም ይህን “ጨርቅ” ሕዝብ ከምድረ ገጽ ማጥፋት አለመቻሉ ነው – አንዱን
ስትነቅለው ሌላ አራት አምስት ቦታ እንደሚበቅለው የፊት ላይ ኪንታሮት ሆነበት፡፡ ስለዚህም ወያኔም ሆነ ሀገሪቱ ሰላም
አላገኙም፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ደግሞ አንድን ሕዝብ ማጥፋት በፍጹም አይቻልም፡፡
ከሞት የተረፉ ዐማሮች ጊዜያቸው ሲደርስ ከያሉበት እየተጠራሩ መሰባሰባቸው ደግሞ አይቀርም፡፡ ሞትና የዘር ዕልቂት የታወጀባቸው ዐማሮች ከእንቅልፋቸው ነቅተው በቃን የሚሉበት ጊዜ መምጣቱ አይቀርም፡፡ አባታቸው፣ ልጃቸው፣ ወንድማቸው፣ እህታቸው፣ባላቸው፣ ሚስታቸው … የሞቱባቸው ጠንቀኛ ዐማሮች ከተኙበት ጠሊቅ እንቅልፍ ሲነቁና ካጠገባቸው የነበሩ ዘመዶቻቸውን ሲያጡ ለነፍሳቸው በመፍራት በሚችሉት መወራጨታቸው አይቀርም፡፡ “ደቂሰይ ነይረይ ተባራቢረይ” ከተዘፈነ በኋላ “ኢደይ ሰዲደ ኣሲረ ሰዓተይ” በሚለው ባህላዊ የትግርኛ ዘፈን ምትክ “ተኝቼ ነበር ነቃሁ፤ እጄን ሰድጄ ክላሼን ታጠቅሁ” የሚል የዐማርኛ ዘፈን መቀንቀኑ አይቀርም፡፡ …
ያኔ ነው ሰው የሚያስፈልገን፡፡ ያን አስጠሊታ የታሪክ ገጽታ ለመለወጥና ኃይላችንን ለመጠፋፋት ሣይሆን ለመልሶ ግንባታው ማዋል እንድንችል የሚያደርግ ጥበበኛ ሰው ነው ያኔ የሚያስፈልገን፡፡ ለዚያ ዓይነቱ መጥፎ አጋጣሚ የሚሆኑንን ሰዎች ከአሁኑ ማፈላለግ አለብን፡፡ “ሠርገኛ መጣ…” እንዳይሆንብን ሁላችን በተጠንቀቅ እንቁም፡፡
በትልቁ ቅርጫትና በትንሹ
ዘምቢል ውስጥ የሚገኙ ትግራውያን ወገኖቼም ቆም ብለው የሚያስቡበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ የጉሽ ጠላ ስካር መጥፎ ነው፡፡ ክፉኛ
ያነበርራል፡፡ አሁን በየቦታው በሥልጣን ኮርቻና በሀብት ማማ ላይ የምናያቸው ትግሬዎች ኅሊናቸውን ስተው ነፍልለዋል፤ ኢትዮጵያን
ብቻ ሣይሆን ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ሣይቀር እነሱ የፈጠሯቸው ያህል እየተሰማቸው በጣም ነሁልለው ይታያሉ – ቆሽተ ቀላል ሆኑና
ሊከሉት ይቻል ለነበረ ትዝብት ተጋለጡ፡፡
በዚህም ምክንያት ገለባነታቸው
ገሃድ ወጥቶ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ገመናቸው በአደባባይ ታዬ ፡፡ ፍትህና ርትዕ የነሱ ዕጣ ክፍል እንዳልሆነች ባለፉት 25
ዓመታት ውስጥ በሚያሳዝን ሁኔታ ለመላው ዓለም አሳዩ፤ ሌላው ሕዝብም ከነሱ ስህተት ትልቅ ዋጋ በመክፈል ጭምር ዘላለማዊ
ትምህርት ቀሰመ፡፡ …
ሱቅ ውስጥ እንደገባ ሕጻን
ሁሉንም ለኔ በሚል ፋሽን የሀገሪቱን አንጡራ ሀብት እስከነዘር ማንዘራቸው በመዥገራዊ መንቆር ቦጠቦጡት – ዕድሉን ያገኙና የተጠቀሙበት
ወያኔ ትግሬዎች፡፡ እንደነሱ የሚገርም ፍጡር በምድር ላይ ቢገኝ ለማነጻጸሪያት እንኳን በጠቀመን ነበር፡፡ መበዝበዛቸውና ሁሉንም
ነገር መቆጣጠራቸው ብቻ ቢበቃቸው መልካም በሆነ፡፡ ግን የማይነጋ እየመሰላቸው ሕዝብን በዘርና በሃይማት እየከፋፈሉ
ከማናቆራቸውና በጄኖሳይድ ከመጨፍጨፋቸው በተጓዳኝ በኢትዮጵያ ምሥጢራዊ ጓዳዎች ሁሉ ጥሬ እንትናቸውን እየከመሩ ሀገሪቱን ለከፋ
ዓለም አቀፋዊ ግማትና ክርፋት እየዳረጓት ይገኛሉ፡፡ ብላችን “ከመጠምጠም ማወቅ ይቅደም” ይል ነበር፡፡ እነሱ ግን ምንም
ሳያውቁና ለማወቅም ጥረት ሳያደርጉ በጀብደኝነትና በጉልበት በሚቆጣጠሯቸው የመንግሥት ሥራዎች ላይ በቀላሉ የማይፋቅ ታሪካዊ
ጠባሳ እያሳረፉ ናቸው – የሚኒስትር መሥሪያ ቤቶችን ወደ መቶ ሊያደርሷቸው እንደሆነም ካልተረጋገጡ ምንጮች እየሰማን ነው፡፡
ኢትዮጵያ በሁሉም ረገድ የምትገርም ሀገር እየሆነች ነው፡፡’’
አዲስ አባባ ውስጥ የታዘበውን
የትግሬዎች ተደላድሎ በሥራም፤ በንብረትም፤ በደህንነትም ፤ በስነሉቦናም ሰቀቀን ሳይኖራቸው ተመችቶአቸው የመኖራቸው ትዝብት
አይተናል። እነ ልደቱ አያሌው በዚህ ጉዳይ እንደገና ቢያጤኑት የተሻለ ነው እላለሁ።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ