Tuesday, May 17, 2022

የትግራይ ቦኮ ሓራም ተዋጊዎች በአማራ ተማሪዎች ስነልቦና ላይ ያደረሱት አሰዛኝ ድርጊት የቪዲዮ ማስረጃ ትርጉም ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 5/17/22

 

 

ትግራይ ቦኮ ሓራም ተዋጊዎች በአማራ ተማሪዎች ስነልቦና ላይ ያደረሱት አሰዛኝ ድርጊት

የቪዲዮ ማስረጃ

ትርጉም

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay)

5/17/22

ማስረጃው የተላለፈው ከእንግሊዝኛ ቅጂ ወደ ትግርኛ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የተላለፈ ነው። በዚህ ቪዲዮ የምትመለከቱት ጽሑፍ ፤ ትምህርት ጠል እና ዘረኛ የሆነው “የትግራይ ቦኮሓራም” በኦሮሙማው አብይ አሕመድ ትብብር ወደ  አማራ ክልሎች በመግባት የማስተማሪያ ዕቃዎችን  በመሰባበርና ህንጻውም የመዋጊያ ምሽግና የቆሰሉ የተዋጊዎቹ ሕክምና መስጪያ ጣቢያ አድርጎት ከመጠቀሙ ሌላ፤ ሰው የሚታረድበትና ፤ሬሳዎችም የሚከመሩበት ቦታ አድርጎታል።

ብርቱካን የተባለች አንዲት አማራ ተማሪ የደረባት የስነ ልቦና ስብራት እንዲህ ትገልጻለች፤

"ወንድሜ ከጓደኛው ጋር ሲጫወት በቦምብ ተገደለ። ብዙ መጥፎ ነገር አይቻለሁ። አካላታቸው ተቆራርጦ ሞተው እያለ በጥይት ሲደበደቡ አይቻለሁ።” ትላለች።

ወራሪው “የትግራይ ቦኮሓራም ተዋጊ” ግድግዳዎቹ ላይ፤ ጠረጴዛ ላይ ኮምፕዩተር ላይ በደም የተጨማለቀ ጽሑፍና እንዲሁም  አማራን የሚሳደቡ በርካታ ጸያፍ ዘረኛ ስድቦችን ጽፎ ትቷል።

ግድግዳው ላይ በትግርኛ ከተጻፉት ስድቦች አንዱ እንዲህ ይላል፡

“ኣድጊ ኣይመርሕ

ኣይረግሕ

እንተኾይኑ ዝርግሕ!”

 

ትርጉሙ ወደ አማርኛ፡

“አህያ መምራት አይችልም

መራገጥም አይችልም

ስለዚህ ሲቻል መዘረር ነው! (መግደል ነው!)

ይላል።

VOA Tigrigna ኣብ ክልል ትግራይ ብሰንኪ ዂናት 1 39 ሚልዮን ተማሃሮ

https://youtu.be/fA9KnlNUQrs


በዚህ ሁሉ “የወያኔ ቦኮሐራም ተዋጊዎች” አህያ እያሉ በሚሰድቡት የአማራ ታዳጊ ህጻናት ስነ ልቦና ውስጥ የማይጠፋ ጠባሳ ትተው ሄደዋል።

ቦኮሓራማዊው ወያነ ከቦታው ወደ ሗላ ፈርጥጦ ካፈገፈገ ወዲህ ‘ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን እንይቀጥሉ፤ ክፍላቸው በሰው ደም ተጨማልቆ በማየታቸውና የተቆለለው ክምር ሬሳ  በሕዝቡ ዕርዳታ ከክፍሉ ሲነሳ በማየታቸው፤ ተማሪዎቹ “አንማርም” ብለው በሓዘን እቤታቸው ብዙዎቹ ተቀምጠዋል። አስተማሪዎቹ እራሳቸው ሰለባዎች ቢሆኑም “ያንን ጠባሳ ችለው” ወደ ቤተሰብ ልመና በየቤቱ እየሄዱ በቂ ዝግጅት ባይኖርም ባለው ነገር እንዲማሩ እየለመኑ ነው።

 “ቦኮሓራማዊው የትግራይ ተዋጊ ሃይል” በፈጠረው ጦርነት ምክንያት ባጠቃላይ 1.39 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንዲፈናቀሉ ሆኗል። ይህ ወንጀል ወራሪው ጣሊያን ከሰራው ጋር ሲነጻጸር የትግራይ ሕዝብ ያሰማራቸው “ወራሪ የትግራይ ቦኮ ሓራም ተዋጊዎች” ያደረሱት ጥፋትና ጥላቻ አይበልጥም? አዎ ይበልጣል!!

ሰነዱን ተቀባበሉት!

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)