Friday, November 17, 2023

የአማራ ሕዝባዊ ሃይል ፋኖ እና ቀዳማይ ወያኔ ያስተላለፉት አረመኔአዊ አዋጅ ተመሳሳይነት ጌታቸው ረዳ ( የ Ethiopian Semay ድረግጽና ፌስቡክ ዋና ድረግጽ አዘጋጅ)

 

የአማራ ሕዝባዊ ሃይል ፋኖ እና ቀዳማይ ወያኔ ያስተላለፉት አረመኔአዊ አዋጅ ተመሳሳይነት

ጌታቸው ረዳ

( የ Ethiopian Semay ድረግጽና ፌስቡክ ዋና ድረግጽ አዘጋጅ)

11/17/23

ብዙዎቻችሁ ለአመታት እንደተከታተላችሁኝ አማራው ምሁር እና አሁን የሚንጫጫው ወጣት ሳይነሳ ስለ አማራው ሕልውና እንዲነሳ ብዙ እንደጣርኩና አማራ ነን ከሚሉትም እንደተገለልኩና እንደተዘለፍኩ የምታውቁ ይመስለኛል። ዛሬ የአማራ ተጋድሎ የብረት ትግል ከተጀመረ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ብዕሬን ወደ ወቀሳ ሳሾል እያዘንኩ ነው። እነሆ ወደ ትችቴ ልግባ።

 አማራ ሕዝባዊ ሃይል ፋኖ እና ሌሎች በሌላ ስም የሚጠሩ ፋኖዎች ማን እንደሚመራቸውና ልዩነታቸው ስማቸውም በደምብ ጥናት አላደረግኩምና እባካችሁ ጠቁሙኝ። እኔ ግን የማውቀውና የገመትኩት “ፋኖ” የሚል አንድነት ያለው መጠሪያ መስሎኝ ነበር አሁን ግን ብዙ ቡድን እንዳለ ነው እየታዘብኩ ያለሁት፤ ሆኖም አንባቢዎች እንድትረዱኝ  በሃሳብ መስጫ ሳጥን ውስጥ ልዩነታቸውና መሪዎቻቸው ብታስረዱኝ እወደላሁ። ብዕሬን በማነሳበት በሚከተለው (አማሐራ ሕዝባዊ ፋኖ) በተባለው ድርጅት አርበኛ ፋኖ እስክንድር ነጋ እንደማይኖርበት ተስፋ አደርጋለሁ። ካለበትም ጠቁሙኝ።

ሰሞኑን በሕዳር 6/2016  ዓ.ም “አማራ ሕዝባዊ ሃይል ፋኖ” የሚል አንድ ጥሪ አስተላልፎ ነበር። ጥሪውም በዚህ በለጠፍኩት ቪዲዮ ታደምጡታላችሁ።ጥሪው አረመኔነትና ድንቁርና የተሞላበት እንዲሁም የሃይማኖት ዕምነቶችና የሰንበቴ፤ ዕድርና ማሕበረሰቦች ድርጅቱን በሚቃወሙ እና ቤተሰቦቻቸው ጭምር ምን ማድረግ እንደሌለባቸው በጥብቅ ያዛል።

ነገሮች ለማገናዘብ፤ የዚህ ድርጅት ጥሪ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ለማነጻጻር እንዲመቸን ሦሰት ድርጅቶች ማለትም በብረት ትግል ሲታገሉ ከነበሩት ከቀዳማይና ከዳግማይ ወያኔ የተላላፈ አዋጅ/ጥሪ/ እንዲሁም በሰላማዊ ትግል ሲታገል ከነበረው የ1997 ቱ የቅንጅት ሕዝባዊ ጥሪና ‘’አማራ ሕዝባዊ ሃይል ፋኖ’’ ከተባለው ጋር የተላለፉት ጥሪዎች ተመሳሳይነትን ልዩነታቸውን እንዲረዳን በየተራ እንመልከታቸው።

 መጀመሪያ በቅንጅት ጊዜ የነበረው ሕዝባዊ ጥሪ

ሕዝቡ ተቃውሞውን በሚከተሉት ሁኔታዎች እንዲገልጽ ጥሪ አድረጎ የነበረውን ከግርድፍ ትውስታዬ በግሌ የማስታውሰው ያስተላለፈው መግለጫ ጥቂቶቹ ላስነብባችሁ።

የቅንጅት መግለጫ በተቃዋሚዎቹ ላይ ያስተላለፈው የትግል ውሳኔ፡

<<እቤት በመቀመጥ (ወደ ስራ አለመሄድ/የቁጭ አድማ) ተቃውሞውን መግለጽ። 5 ቀን የሚቆይ የእቤት መቀመጥ አድማው የሚጀምረው ለእስላሞች ክብር እና ወንድማዊ ደስታ ለመካፈል ሲባል ሮሞዳን የተባለው እስላሞችን በዓል ካለፈ ነበር። 

በኢሕአዴግ ባለቤትነት የሚካሄዱ የንግድ ተቋማት አንደ አምባሰል፤ጉና፤ዲንሾ፤ዎንዶ፤ዳሸን ቢራ ፋቭሪካ እና ሜጋ የመሳሰሉት ሕዝቡ ግብይት እንዳያደርግ።  ከንግድ ድርጅቶቹ አልፎ በቁጥጥሩ ስር የሚገኙ የዜና ማሰራጫ ራዲዮኖች (ድምፂ ወያነ ትግራይ፤ ፋና፤ኢ FM 97.1  FM 96.3 የመሳሰሉ) እና እንዲሁም በጋዜጦቹ ላይ የንግድ ማስታወቂያ አለማድረግ፤ ስርዓቱ የሚያስተላልፋቸው ዜናዎች እና ቅስቀሳዎች እንዳያነብ እና እንዳያዳምጥ። በምትኩ የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮን እና ዶቸቬለ አንዲሁም ትንሳ ራዲዮ የመሳሰሉት ከውጭ የሚሰራጩ  የዜና አውታሮች ችን ማድመጥ።

ስርዓቱ የሃይል እርምጃ በወሰደ ቁጥር፤ በኢሕአዴግ አባላት እና እንዲሁም የተጭበረበረውን ምርጫ በግድ ተቀበሉ እያሉ ሰላማዊ የፖለቲካ ተቃወሚ አባሎችን እና በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉልበት በማሳየት፤ በመደብደብ፤ በማሳሰር፤በመግደል፤ በመሰለል፤በማስፈራራት ሕግን በመጣስ መብት የሚረግጡ የስርዓቱ ደጋፊዎች ሁሉ ሕብረተሰቡ እንዲያገላቸው።ቅንጅት ማንኛውም የቅንጅት አባልም ሆነ ደጋፊ ከላይ ከተጠቀሱ ምክንያቶች ውጭሃይማኖትን እና ጎሳንመሰረት ያደረገ ማሕበራዊ ማግለል እንዳይደረግ በጥብቅ አሳስቧል።>>  (ግርድፍ ይዘት ጌታቸው ረዳ EthiopIan Semay Editor) የሚል ነበር

እንግዲህ ከላይ እንደተጠቀሰው ቅንጅት <<ሰላማዊ የፖለቲካ ተቃወሚ አባሎችን እና በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉልበት በማሳየት፤ በመደብደብ፤ በማሳሰር፤በመግደል፤ በመሰለል፤በማስፈራራት ሕግን በመጣስ መብት የሚረግጡ የስርዓቱ ደጋፊዎች ሁሉ ሕብረተሰቡ እንዲያገላቸው።>> የሚል መግለጫ እንጂ ቅንጅትን በሚቃወሙ “ቤተሰቦች ላይ ጭምር” ማሕበራዊ ግለላ እንዲደረግላቸው ጥሪ አላቀረበም

በአንጻሩ << የአማራ ሕዝባዊ ሃይል ፋኖ>> የሚባለው ተዋጊ ሃይል  ያስተላለፈው ጥሪ ግን በሚቃወሙትና በሥርዓቱ ደጋፊዎች ብቻ ሳይሆን እርምጃዎች እንዲወሰድባቸው ያወጀው በቤተሰቦቻቸውም ጭምር ነው።

እንዲህ ይላል።

<< የአማራ ሕዝብ ሆይ ! አንተን በጠላትነት የፈረጁህ ሃይሎች ጥላሸት እንዲቀቡህ (ያደረጉት) ደማቅ ታሪክህ በትውልዱ መስዋዕትነት የመጨረሻው ትንቅንቅ እየተደረገ ይገኛል፡ ስለሆነም በውጭም በውስጥ አገርም ያላችሁ አማራ ወገናችን የሕልውና ተጋድሎ እስኪቋጭ ድረስ በቻልከው ሁሉ እንድትደግፍ የአማራ ሕዝባዊ ሃይል ፋኖ የሚከተለው ሕዝባዊና አማራዊ ጥሪ ያደርጋል፡……..”

ካለ በካስገረሙኝ ከጥሪዎቹን አንዳንዶቹን ልጥቀስ፡

1ኛ- በአሁኑ  ሰዓት ሠርግ ለማሠረግ ያሰባችሁ ፤ ተስካር ለማውጣት ያቀዳችሁ፤ክርስትና ለመደገስ የተዘጋጃችሁ ይህ የሕሊና ተጋድሎ እስከሚጠናቀቅ ድረስ እንድታራዝሙት ስንል አማራዊና ወገናዊ ጥሪ እናቀርባለን።

በ3ኛ- ደረጃ የጠቀሰው ሌላው ያስገረመኝ ጥሪው ደግሞእንዲህ ይላል፤

<<ለሥርዓቱ ያደሩ አማራ የሆኑ የሚሊሺያ የአድማ ብተና ቤተሰቦችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከዕድር ፤ከሰንበቴ ማሕበርና ከሌለቹ ማሕበራዊ ና ግብረገባዊ (“መስተጋብራዊ” ለማት ይመስለኛል አንባቢው “ግብረገባዊ” ሲል) ሥርዓቶች ባስቸኳይ እንዲገለሉ ስንል ጥሪ እናቀርባለን።>>  ይላል።

ሌላው ደግም 4ኛው እንዲህ ይላል፡-

<< የሚሊሽያና አድማ በታኝ እንዲሁም የመሳሰሉት እርምጃ ተወስዶባቸው ሞተው ሲገኙ ፍትሃት እና ልቅሶ እንዳይደረግላቸው” ጥሪ ያስተላልፋል።>> ሕዳር 6/2016 የአማራ ሕዝባዊ ሃይል ፋኖ።>>

እስኪ አንድ ባንድ እንመልከታቸው።

<<1ኛ- በአሁኑ  ሰዓት ሠርግ ለማሰረግ ያሰባችሁ ፤ ተስካር ለማውጣት ያቀዳችሁ፤ክርስትና ለመደገስ የተዘጋጃችሁ ይህ የሕሊና ተጋድሎ እስከሚጠናቀቅ ድረስ እንድታራዝሙት ስንል አማራዊና ወገናዊ ጥሪ እናቀርባለን።>>

ይህ አዋጅ ተመሳሳይነቱ በብላታ ሃይለማርያም ረዳ የተመራው ይትግሬው  የቀዳማይ ወያኔ ሳይሆን በመለስና ዜናዊ የተመራው ዳግማይ ወያነ ጥሪ በትግሉ ወቅት ማንኛውም ገበሬ ሰርግ እንዳያከናውን፤ክርስትና እንዳያስነሳ፤ ተስካር እንዳይዘክር ወዘተ ከሚለው ጋር  ይመሳሰላል።ከዛው ቃል በቃል የቀዳውም ይመስላል። ይገርማል!

እንዲህ ያለ ማሕበራዊና ሃይማኖታዊ ሕጎችን ባንድ ተዋጊ ሃይል ጥሪ ሲታገድ ይህንን ጥሪ ተላልፎ እምቢ ብሎ የተገኘ ሃይማኖተኛና ማሕበራዊ አከናዋኝ ቅጣት፤ እስራት፤ግድያ ውርሻ ፤መገለል  ወዘተ…….የመሳሰሉ ያልተጠቀሱ ዕርምጃዎች ሊፈጸምበት ይችል ይሆናል ማለት ነው። ይገርማል።

 ይህ ነው ትግል ማለት ?  ይህ ነው ሕዝባዊ እሴቶችና ሃይማኖቶችን ማክበር ወይስ ሃይማኖትና ማሕበረሰባዊ ዕሴቶችና ክንዋቤ ነፃነቶችን “በቁጥጥር ሥር ማድረግ”? ቀስ ብሎ ነገም እንደ ወያኔ መላውን አማራ ሲቆጣጠር ቤተክርስትያናትን እና መስጊዶችንም ጭምር በሥሩ እና ለራሱ ጠቀሜታ አዋጅ እያወጀ በሥሩ እንዲውሉ ማድረጉ አይቀሬ ነው ማለት ነው።

ወደ ቀዳማየው ወይኔ አዋጅ ድግሞ ልውሰዳችሁ፡

በቀዳማይ ወያኔ እንኳን መቃወም ቀርቶ በትግሉ ሕግ አምላክ ቁም ተብሎ ትግራይ ውስጥ አልቆምም ያለ የሚከተለው መገለል ጥሪ ተላልፎበት ነበር። ከመጽሐፌ ጥቂቱን ልጥቀስ፡

ድሮ በሃይለስለሴ ዘመን አንድ ሞገደኛም ሆነ አንድ ሰው ወደ ሕግ ለማቅረብ እንሂድ ስትለውበሃይለስላሴ በሕግ አምላክሲባል ነበር። የመሳፍንቶች እና የነገሥታት ዘሮች የሚበዙበት እና የሚወለዱበት አካባቢ አንደርታ አውራጃ በቀዳማይ ወያኔ ለንጉሥ ሃይለስላሴ አንገዛም በማለት “12 ገረብ” (አስራ ሁለት ጅረት/ድርጅቱን ተሰብስበው ባቋቋሙት ኣካባቢ የገጠር ማሕበሮች) በሚል ስም ጊዜያዊ የአማጽያን መንግሥት ሕዝባዊ ባይቶ/አሰምብሊ) መስርቶ በነበረበት ወቅት ደግሞዝባን ገረብ” (በገረብ ሕግ አምላክ) በማለት አንድ ሰው እንድትቆም ተማጽኖህ ካልቆምክ፤ ወይንም በገረብ ሕግ ዳጅነት ላለመዳኘት እምቢ ካለ የገረብ ሕግ ረግጦ እንደሄደ ተቆጥሮ የሚከተሉት በሕግ የጸደቀ የገረብ አዋጅ ይፈረድበታል።

(1)-የገረብ ሕግ ያላከበረ ታምሞ የአልጋ ቁራኛ በሆነበት ወቅት አግዚአብሔር ይማርህ ተብሎ በማንኛውም ጐብኚ እንዳይጎበኝ፤

(2)- በሃዘን ጊዜ ጥናቱን ይስጥህ ተብሎ አንዳይጠየቅ

(3)-ከሕዝብ እና ማሕበራዊ ግንኙነት እንዲገለል። የሚሉ ነበሩ።

ይህ የሚያመለክተው ባለጠመንጃዎች በሃሳብ ያልተስማማቸውን ሕብረተሰቡን በቁጥጥር አድርገው አዋጅ በማወጅ የሌላውን ነጻነት “ሰብአዊነትን” በሚጻረር መልኩ እንዴት እንደሚጋፉት ያሳያል። ፋኖ እያደረገ ያለውም በሚቃውሞዋቸው ቤተሰቦች ጭምር ጭካኔ አውጇል። የተቃዋሚያቸው አሞት  ሕክምና እንዳይደረግለትም ያካተተ ነው። የፋኖ ሙርከኛ ተዋጊዎች ግን ሆስፒታል ተኝተው ሲታከሙ ቆይተው ኦሮሙማው መንግሥት ወታደሮች እያወጡ ረሽነዋል። ይህንን ደግሞ ፋኖ ሲቃወመው ሰምተናል። ታዲያ ተቃዋሚያቸው ሲሞት ፍትሃትና ሕክምና እንዳይደረግለት ጥሪ ካደረጉ ከኦሮሙማው መንግሥት ጭካኔ በምን ይለያል? ባህልን እና ሃይማኖት ነክ ተያያዥ ነገሮችን መነካካት ለምን አስፈለገ? ኢህ ለጠላት ጥሩ የቅስቀሳ መሳርያ ማቀበል አይደለም ወይ?

በርካታ አመታት የታገልኩለት የአማራ ሕልውና ትግል ለመውቀስ ስገደድ እያዘንኩ ነው። ካሁኑኑ የኔን ምክር ሰምቶ እርማት ካላደረገ ትግሉ ወደ “የወያኔ ትግሬያዊ ባሕሪ” ሳይጓዝ አይቀርም የሚል ፍራቻ አድሮብኛል። እንዴት የሞተን ሬሳ አትቅበሩ ፍትሓት አታድርጉ ብሎ ጥሪ ያደርጋል፤ ቄሶችን ያስፈራራል? እንዳይቀበር ማለትስ ምን ማለት ነው?

ወደ ሌላው ጥሪው እንሻገር።  እንዲህይላል፡-                                                           

<<ለሥርዓቱ ያደሩ አማራ የሆኑ የሚሊሺያ የአድማ ብተና “ቤተሰቦችን” ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከዕድር ፤ከሰንበቴ ማሕበርና ከሌለቹ ማሕበራዊና ግብረገባዊ ሥርዓቶች ባስቸኳይ እንዲገለሉ ስንል ጥሪ እናቀርባለን።>

ከላይ የ1997 ቱ በእነ ሃይሉ ሻውል ፤ ልደቱና በእነ ብርቱካን ሲመራ የነበረው ከቅንጅት ላንድነትና ለዲሞክራሲ ድርጅት የተላለፈው ጥሪ እንዳስነበበኩዋች

ቅንጅት  <<የስርዓቱ ደጋፊዎች ሁሉ ሕብረተሰቡ እንዲያገላቸው።>> ሲል የአማራ ሕዝባዊ ሃይል ፋኖ የተባለው ደግሞ <<ለሥርዓቱ ያደሩ አማራ የሆኑ የሚሊሺያ የአድማ ብተና “ቤተሰቦችን” ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከዕድር ፤ከሰንበቴ ማሕበርና ከመሳሰሉ ማሕበራዊ ትስስርና መስተጋብሮች ባስቸኳይ እንዲገለሉ ስንል ጥሪ እናቀርባለን።>> ይላል።

ድርጅቱ ለመሆኑ የተማሩ ሰዎች አሉት? ምንም የፖለቲካ ሱታፌ በሌሉበት ምስኪን ህጻናት፤ሽማግሌዎች፤አካለስንኩላን፤ አቅም የሌላቸው ዕርጉዞች፤ ቤተሰቦቻቸው ጭምር ገበያና ሱቅ ሄደው እንኳ እህልና ሸቀጣሸቀጥ ገዝተው ልጆቻቸው እንዳይመግቡና እንዲከለከሉና አንዲገለሉ ከጎረቤቶች ጋር ቡና እንዳይጣጡ ለርሃብ ተጋልጠው እንዲሞቱ ውሳኔ አስተላልፏል።ይህ አረመኔነት ወይስ ነፃ አውጪነት?

አማራ በእንደዚህ አይነት ድንቁርና ነፃ መውጣት ይችላል? በፖለቲካ ንኪኪ የሌላቸው ቤሰተቦችን፤ እመጫቶችን፤ ዕርጉዞችን፤ህሙማንን ከማሕበራዊ እንቅስቃሴና ግብይት እንዲገለሉ ማድረግ አምሐራዊ ባሕል የተከተለ ነው? ስንሰማው የነበረው “አማሓራዊ ደግነትና ባሕል” ሲባል የነበረውስ ይህ ነው?

ትግሉን ላለማደናቀፍ በጣም ስጠነቀቅ ነበር የቆየሁ ፤ አሁን ግን ሳላስበው ወደ እዚህ አይነት ንዴት ሲጨምሩኝ ካሁኑ ጥንቃቄ ካላደረጉ ከነሱ በፊት እንደነበሩት ድርጅቶች እንዳንበረከኩኳቸው ሁሉ ለወደፊቱ ብዕሬ ወደ እነዚህ እንዳይዞር እየሰጋሁ ነኝ። ስለዚህ የብረት ትግል “ትዕግሥት፤ ጥንቃቄ፤ሰብአዊነትና ዕውቀት” ታጥቆ መጓዝን ስለሚጠይቅ እርማትና ጥንቃቄ እንድታደርጉ እጠቁማለሁ። የዚህ ድርጅት መሪዎች እነማን ይሆኑ? እስኪ አንባቢዎቼ ጠቁሙኝ። ይህ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምን ቢደረግለት ይድን ይሆን?

ጌታቸው ረዳ  (Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋ