Sunday, September 15, 2019

በኢትዮ ሰማይ የተመረጡ የ2011 ዓ.ም አራት ምርጥ ኢትዮጵያውያን እና አንድ ምርጥ የአመቱ የዜና ማዕከል


በኢትዮ ሰማይ የተመረጡ የ2011 ዓ.ም አራት ምርጥ ኢትዮጵያውያን እና አንድ ምርጥ የአመቱ የዜና ማዕከል
ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
መስከረም 15/2012


Page views yesterday-826 on this commentary posted on Ethio Semay blog only. I thank you viewers for visiting. 

ባለፈው ሰሞን የ2011 ዓ.ም የተዋወቅናቸው አራት አዳዲስ ባንዳዎችን አይተን ነበር፤ ለማስታወስ ያህል እነሱም የአብይ አሕመድ ቱልቱላ ባንዳው ዲያቆን ዳኒኤል ክብረት፤ታማኝ በየነ፤ ፕሮፌሰር አል/አለማዮህ ማርያም፤ብርሃኑ ነጋ ነበሩ። ዛሬ የምንለከታቸው ግን የ2011 ምርጥ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ነው።  

እነኚህም የሚከተሉት ናቸው።

1ኛ-ቴድሮስ ጸጋዬ (ርዕዮት ሚዲያ ዋና አዘጋጅ)

2ኛ- አቻምየለህ ታምሩ የምጣኔ ሃበት ምሁር፤ የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር እና የታሪክ ተመራማሪ

3ኛ- ዶ/ር ኃይሌ ላሬቦ (የታሪክ ምሁር)

4ኛ- እስክንድር ነጋ (ጋዜጠኛ፤የሰብአዊ መብት ጠበቃ እና የአዲስ አባባ ስቪክ ማሕበር የባለአደራ ሊቀመንበር)

5ኛ- ተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

ሲሆኑ

በዜና እና በፖለቲካ ትንተና የሚዲያ ማዕከል በ2011 ዓ.ም ከማንኛቸውም በአገር ውስጥም ሆኑ በውጭ አገር የሚገኙ የዜና እና የፖለቲካ ትንታኔ የብዙዎቹን ቀልብ በመሳብ አሁን ያለው የሥርዐተ አልባው የኦሕዴዱ ኮሎኔል አብይ አሕመድ የሚመራው ፋሺስታዊ የመንጋው ሥርዓት ምንነቱን ተንትነው ለሕዝብ በማስረዳት ወደር የሌለው የጋዜጠኛነት እና የፖሊተካ ተንታኝነት ሙያ በብቃት የተዋጣላቸው የEthio 360 Media (ኢትዮ 360) አባላት ባለፈው አመት በ2011 ዓ.ም ባሳዩት የሚዲያ ተአማኝነት (ኢንተግሪቲ)  ቀዳሚ  ሆነው ተመርጠዋል።

ከላይ የተመረጡ ምርጥ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች እና የሰብኣዊ ተሟጋቾች፤ የፖለቲካ እና የታሪክ ተንታኞች “መደመር” ተብሎ በሚታወቀው የኢሊሙናቲው አብይ አሕመድ አጭበርባሪ ስልት በማጋለጥ የመደመር ምንነት እርቃኑን በማውጣት ተጋፍጠውታል። የአብይ አሕመድ የመደምር ፍልስፍና ኢትዮጵያ በእሳት እንድትጋይ በማድረጉ እነኚህ ምርጥ ዜጎች በዚህ ቁርጥ ቀን እና በዚህ አጭበርባሪ ቅጥረኛ ግለሰብ የሚመራ አደገኛ አስተዳዳር ዜጎች እራሳቸውን በፖለቲካ ንቃት አንዲያጎለብቱ በብቃት አስተምረዋል። በዚህ ግለሰብ አስተዳዳር በኢትዮጵያዊነት፤ በአማራነት እና በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እና በብሔራዊ ሉዓላዊነታችን ላይ እየደረሰ ያለው ውርድት ግምባር ቀደም ሆነው የፋሺሰቱን የአብይ አሕመድ ኦሮሞኣዊ አስተዳዳር በብቃት በመጋፈጥ ምርጥነታቸውን በማሳየት ኢትዮሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ እነኚህ የኢትዮ-360 የዜና ትንታኔ ማዕክል ባልደረቦች የአመቱ ምርጥ ዜጎች ብሎ ሰይሞአቸዋል።
ኢትዮጵያ ለዘልኣለም በልጆቿ ትግል ትኖራለች!

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ደርገጽ አዘጋጅ Ethio Semay) getachre@aol.com