Tuesday, March 9, 2021

ትግራይ መከላከያ ሃይል ያሸንፋል! ትግራይ ታሸንፋለች!” የኢትዮ ሚዲያው የአብርሃ በላይ እና የወያነ የጋራ መፈክራቸው! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay) 3/9/2021

 

“የትግራይ መከላከያ ሃይል ያሸንፋል! ትግራይ ታሸንፋለች!” የኢትዮ ሚዲያው የአብርሃ በላይ እና የወያነ የጋራ መፈክራቸው!

ጌታቸው ረዳ

 (ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay)

3/9/2021



እዚህ ላይ የተለጠፈው ፎቶግራፍ የወያኔ ፋሺሰት ታጋዮች በኢትዮጵያ የመከላከያ ሃይሎች ላይ ከባድ መትረየስን አነጣጥሮ ሲተኩስ የሚያሳይ የወያኔዎች የወንጀል ፎቶግራፍ ነው።  የድምጽ ወያነ የሚጠቀምበት ፎቶግራፍ አብርሃ በላይ የፌስቡኩ የገጽታ ፎቶግራፍ ማድመቂያ አድርጎታል።

 ትግሬዎች የሚከተሉት የነገድ ፖለቲካ “ፋሺስቶች የሚያመልኩት ርዕዮት” ነው። አብዛኛዎቹ ትግሬዎች በፋሺሰት ርዕዮት በሚመራ ሕሊና የተቀረጹ የነገድ አክራሪዎች ናቸው ብየ ስል በምክንያት ነው። “ፋሽዝም በድርድር፤ በሰጥቶ-መቀበል የሚያምን የፓለቲካ ኃይል አይደለም። የፋሽስት ድርጅትም ሆነ መንግስት ዓለምን የሚያየው በአሸናፊና ተሸናፊ መድረክነት ነው። ፋሽስቶች ከተፎካካሪያቸው ጋር በመደራደር ሳይሆን ተፎካካሪያቸውን አታልለውም ሆነ አስፈራርተው በኃይል በማስገበርና በማጥፋት ያምናሉ።፡የፋሽስቶች ቋንቋ ኃይል ነው እንጂ ድርድር ወይም ሰጥቶ መቀበል አይደለም።” (አሰፋ ነጋሽ አምስተርዳም ሆላንድ (ዶ/ር)

ዶ/ር አሰፋ እንዳለው ወያኔ በሚከተለው ጸረ ኢትዮጵያነት የፋሺስዝም መርሆ የትግራይን ሕዝብ ሲረዳና መሰረተ ትምህርትና ሕክምና ሲገነባለት የነበረ ወልዶ ከብዶ ተሰባጥሮ ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ የትግራይን ሕዝብ ሰላምና ድምበርን በደሙ ሲያስከብርለት በኖሮው ምስኪኑ የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል ላይ “አታልሎና አስፈራርቶ” በተኛበትና በተዘናጋበት ሁኔታ ድንገተኛ ሃይል በመጠቀም አረመኔ ጭፍጨፋ አካሁዶበታል።

 

“የወያኔ ፋሽስቶች እንደ ፓለቲካዊ ጦር ምንጊዜም ወታደራዊ ዝግጅት አድርገው በተጠንቀቅ በመቆም የአብዮታችን ጠላቶች ናቸው የሚሏቸውን ወገኖች ለማጥፋት ይተጋሉ።” (ደ/ር አሰፋ ነጋሽ) በዚህም ምክንያት ምንጊዜም ወያኔዎች (ፋሺስቶች) በአይምሮአቸው በጠላት ተከበናል የሚል አስተሳሰብ ስለሚመላለስ ለጦርነት ዝግጁ ሆነው ይጠባበቁ ነበር።’ ዝግጁነታቸውም በተግባር አሳይተዋል።

የዛሬ አያድርገውና የትግራይ ተወላጆች ከማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ የበለጠ ከባድ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ከመሆናቸውም በላይ በትግራይ ውስጥ ከህጻናት እድሜ ክልል ጀምሮ ያሉ የትግራይ ተወላጆች ጠላቶቻቸውን እንዴት አድርገው እንዲሚያጠፉ በፕሮፓጋንዳ ብቻ ሳይሆን በወታደራዊ ስልጠና ጭምር እየተደራጁ ይገኙ ነበር (አሰፋ ነጋሽ ዶ/ር)።

 ዛሬ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ የትግራይ ማህበረሰብ በወታደራዊ አደረጃጀት የተዋቀረና ከትግራይ ክልል በታች ያሉትን የሌሎች የኢትዮጵያ ነገዶች ተወላጆች በተለይም አጎራባች የሆነውን የአማራ ክልል ህዝብ ለማጥፋት ሙሉ ዝግጅት አድርጎ ይጠባበቅ እንደነበር ሁላችሁም አትስቱትም። ትግሬ ኢትዮጵያን ለዘላለሙ ካልገዛት “ባፍንጫችን ትውጣ/ትፍረስ/ በማለት ሥልጣናችሁን አጋሩ ሲባሉ “ጥጋብ” መሸከም ስላቃታቸው ጦርንትን መርጠው አሁን ወዳለው ሁኔታ ገባን። ዛሬ በርካታ የትግራይ ምሁራን በነገድ ፍቅር ወድቀው የወያኔ መዝሙር መዘመር ዕለት ተለት ጸሎታቸው ሆኗል። ከነዚህ አንዱ አብርሃ በላይ ነው።

 

አብርሃ በላይ “የኢትዮ ሚዲያ” ድረገጽ አዘጋጅ ነው። ድረገጹ ጠንካራ ሙግት የያዙትን ኢትዮጵያዊያንን የሚሞግቱዋቸው ጽሑፎችን እንዳይለጠፉ በማገድ በሚገርም ሁኔታ ኦነጎችን እና እነ ወያኔዎችን እነ ስየ አበርሃን እነ ብርሃኑ ነጋን ሰፊውን መድረክ በመስጠት፤ የዚህ ድርጅት ብሔረሰብ ተወካዮች ነን እየሉ አዲስ የመገነጣጠል ፎርሙላ ለአገራችን ሲዘረጉ የነበሩት፤ ያለ ምንም መታከት ፕሮፓጋንዳቸውን ሲያሰራጩበት የነበረ ድረገጽ አዘጋጅ ነው። ዛሬ ድረገጹ ከተዘጋ ብዙ አመታት ወዲህ የወያኔ ወታደር እና መሪዎቻቸው ቅንቅን እንደበላው ግንድ ተደርምሰው ሲወድቁ፤ አብርሃ በላይ ዛሬ “ድመጺ ወያኔ” የሚያስተጋባውን “መፈክር” የፌስቡኩ መነሻ ፎቶግራፍ አድርጎ በመለጠፍ የወያኔዎችን ጎራ ተቀላቅሎ የወያኔን “ታላቁ አወዳደቅ” ለመሸፈን የወያኔን መፈክር እያስገባ ነው።

 

አብርሃ በላይ የሚከተለው መስመር ዋዣቂ በመሆኑ ካሁን በፊት በነቮምበር 17/2020 (በፈረንጅ) “ለአገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” በማለት የኢትዮጵያ ኮማንዶ ሰራዊት አባላትን ፎቶ እና እራሱም በወታደራዊ ዩኒፎርም በመልበስ አጋርነቱን አሳይቶ የፌስቡኩ የመነሻ ፎቶ አድርጎት ነበር።

ከዚያም “አብርሃ በላይ፤-

"የትግራይ ህዝብ ከውጭ ወራሪ ሲጠብቅ የኖረው የሰሜን ዕዝን ከጀርባው የወጋ የትግራይ ህዝብ ጠላት እንጂ ወዳጅ ሊሆን አይችልም። የትህነግ መሪዎች ለፈፀሙት ወንጀል ለፍርድ እስኪቀርቡ ድረስ እታገላቸዋለሁ። ድል ለጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል! ድል ለእምዬ ኢትዮጵያ ልጆች!" ሲል ጽፏል።

 

ከጥቂት ወራት በላ ደግሞ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን መቆሙን አቁሞ ከወያኔ ትግራይ ወታደሮች በመቆም የወየኔ መፈክር እያስተጋ ስታዩ የአብርሃ በላይ “ፖለቲካዊ ብስለት” ሳታውቁት ስታመሰግኑት የነበራችሁ አንባቢዎቹ የሚገለባበጥበት አቋሙ ታዝባችሁ ምንልባት ትግረሙ ይሆናል፡ እኛ ለምናውቀው ግን ብዙም አልተገረምንም።

 አብርሃ በላይ እንዲህ ተልፈስፍሶ በድምጺ ወያኔ መፈክርና ፎቶግራፍ ፕሮፓጋንዳ ፌስቡኩን ሲያቆነጃጅ፤ ሃሳቡን አልጥም ያላቸው አንባቢዎቹ “እንዴት እንዲህ ልትሆን ቻልክ?” ሲሉት የመለሰላቸውን መልስ እንዲህ ይላል፤-

 “ትግሬ መሆኔን ረስታችኋል?” በማለት በትግሬነቱ ማንነት የወያኔን ወታደር ለማሞካሸት እየዘመረ ያለው መዝሙር የትግራይ ሕዝብ በጦርነቱ ለምን ተጎዳ? የሚለው ሳይሆን፤ አብርሃ በላይ “ወያነ ለምን ለምን ሞተ!” መዝሙር እየዘመረ ነው    

 

በፌብሩዋሪ 26/2021 የአብርሃ በላይ መፈክር የተቃወመ ሰው ነው መሰለኝ አብርሃ ለዚያ ሰው እንዲህ ሲል መልስ ሲሰጥው አነበብኩኝ፦

 “የትናንቱን የማታስታውስ ዘገምተኛ፣ የነገውን አሻግሮ የማየት አቅም ከየት ይምጣ? አልፈርድብህም።” (አብርሃ በላይ) አለው።

 

እውን አብርሃ በላይ እራሱ የትናንቱን ማስታወስ የሚችል ሰው ነው?

 

አብርሃ በላይ በዲሰምበር 26/2020 “ትህነግ በመከላከያ ኃይላችን ተሸንፋ የት እንዳለች አይታወቅም።” ሲለን የነበረ ትናንት የተናገረውን በዝግምተኛ ትውስታው “ምክልኻል ትግራይ ይዕወት! ትግራይ ትስዕር!” (የትግራይ መከላከያ ሃይል ያሸንፋል! ትግራይ ታሸንፋለች) በማለት፤ አብርሃ በላይ “ትግሬ መሆኔን አትዘንጉ፤የምታውቁኝ በህወሃት ተቃዋሚነቴ ነው። የሳታችሁት ከትግራይ ህዝብ አብራክ የተገኘሁ መሆኔን ነው። ትግራይ ሲጨፈጨፍ፣ ዳር ቁሜ አላይም። ቢያንስ፣ በፅሁፍ አወግዛቸዋለሁ።” ይላል።

 

 ‘ኢትዮጵያ ወታደር ጨፍጫፊ ነው’ ካለ ትግሬ በመሆኔ ከወያኔ ጨፍጫፊ ጋር መቆሜ ትክክል ነው” በማለት በነ ደብረጽዮን የሚመራው የትግራይ መከላከያ ተብሎ የሚጠራው የፋሺሰት ተዋጊ ጦረኛን ሞራልና ፕሮፓጋንዳ በመካብ ላይ ድጋፍ መስጠት ምን እሚሉት ሞራል እንደሆነ ግራ የሚገባ ነው።

 

አብርሃ በላይ ስለ አክሱም እንዲህም ይላል፦

“ዛሬ ‘ሁማን ራይትስ ዎች’ በአክሱም በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኤርትራውያን ወታደሮች መጨፍጨፋቸው የዓለም መነጋገሪያ የሆነ ዘገባ ይዞ ወቷል። አክሱም የየት አገር ከተማ ነች እንዲህ መዓት የወረደባት? መቸም ኢትዮጵያ ውስጥ ብትሆን ኑሮ፣ ይኸኔ ብሄራዊ ሀዘን ይሆን ነበር። ግን ወፍም የለ። ዋ አክሱም! እንኳን ኢትዮጵያ ውስጥ ያልሆንሽ¡” (አብርሃ በላይ)

 

ለመሆኑ አብርሃ በላይ እየካበው ያለውን የትግራይ መከላከያ (ወያነ ወታደር) እና የወያኔ መሪዎች 27 አመት ሙሉ በአማራ ላይ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ሲያካሂዱ ባሕርዳር/ጎንደር/ደሴ/አዲስ አበባ እና በመላው አገሪቱ ከተሞች “ብሔራዊ ሓዘን” ተደርጎ ያውቃልን? አሁን ለአክሱም በተለየ ብሔራዊ ሓዘን ለምን አልተደረገም ብሎ የሚያላዝነው ማንን ከማን ጋር ለማነጻጸር ነው?

 

 አብርሃ ወደድክም ጠላህም አክሱም የኢትዮጵያ ነች። በነገራችን ላይ አክሱምም ሆነ ማንም ትግሬ “ኢትዮጵያ” ለመሆን የሚመርጠው፤ ለዓፋር፤ ወይንም ለአማራ፤ለኦሮሞ ምቾት ሲል ሳይሆን ለራሱ እንዲመቸው ሲል እንጂ ማንንም እንዲመቸው ብሎ አይደለም። የወያኔ ቅጥር ጋዜጠኛ ሆነህ አስመራ ድረስ ሄደስ ግንጣላቸውን ለመዘገብ ኤርትራ ሄደህ ነበር ፤ ከተደረገላችሁ የተራጩኋቸው መጠጥና ምግብ የግንጣለ ፈንጠዝያ ግብዣ በኋላ “ኤርትራ ተገንጥላ ምን ተገኘ? ንገሩን እንጂ! ~?  

ዛሬም ያው በትግራይ መከላከያ ድል “ሪፑብሊክ ትግራይ” ስታበስሩ እያመለክኸው ያለውን የፋሺስቱ የትግራይ መከላከያ ሃይላችሁን ከ1967 እስከ 2010 ዓ.ም በትግራይ ዘመዶቻችን ላይ የፈጸሙት ጭፍጨፋ እንደምታስታውስልንም ከወዲሁ እንማጸንሃለን። “ሓይሊ ምክልኻል ሰራዊት ትግራይ” እንደ ፎኒክስዋ ወፍ ከተቀበረበት አመድ ተነስቶ በድል ሲነሳ የትግራይ ፓስፖርትና ቪዛም እንደማትከለክለን ተስፋ እናደርጋለን!

 

የትግራይ ብሔረተኞች ጉድ በዚህ አላቆመም። በሚገርም ሁኔታ አብርሃ በዲሰምበር 21/2020 እንዲህ ብሎ የጻፈውን ላስነብባችሁ፦

“ቀደም ብዬ ‘ፖስት’ ያረኩት የ "ዘ ጋርድያን" ዘገባ ለትግራይ ህዝብ ተቆርቋሪ መስለው ህዝቡን መቀመቅ የከተቱት የትህነግ ካድሬዎች ይጨነቁበት። ይህ እንዳይመጣ ብዬ 27 አመት ሙሉ ጮህኩኝ። ሰሚ አልነበረም። እኔ የማርፍበት እንጂ መልሼ የምጨሁበት ጊዜ አይደለም። በዘገባው መነሳት ቅሬታ የተሰማችሁ ይቅርታ!”

 ሲል ለፌስቡክ አንባቢዎቹ አስነብቦዋቸው አነበብኩ።

 

 ዛሬ አብርሃ በማረፊያው ወቅት “ወያኔ ለምን ለምን ሞተ!” እያለ በመከላከያ ወታደሮቻችን ላይ አነጣጥረው እየተኮሱ ባሉት የወያኔ ፋሺሰት ወያኔዎች ተማምኖ “ትግራይ በትግራይ የመከላከያ ወታደሮች ትድናለች! ትግራይ ኢትዮጵያን ታሸንፋለች” እያለ የትግራይ መከላከያ ለሚላቸው ወግኗል።

ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ ኮማንዶ ሃይሎችን በማሞገስ ፎቶ የተነሳበትን ረስቶ ከመቅጽበት እንዲህ ሲል ያሾፍባቸዋል። ላስነብባችሁ፦

“ፌበሩዋሪ 28/ 2021 የሚገርም ነው! አዎ የሚገርም ነው! በሚል በድረገጹ የለጠፈውን የኢትዮጵያ ኮማንዶ ሃይሎችን ስያንኳስስ ላስነብባችሁ።

እንዲህ ይላል

====፦

“ትናንት በትግራይ ከአብይ ጎን ተሰልፈው "ሓይሊታት ምክልኻል ትግራይን" ለመደምሰስ ጦር መርተው ሲዋጉ ከነበሩ አንዱ መሪ ጋር በስልክ ተገናኝተን አውርተን ነበር።

"ጦርነቱ እንዴት እየሄደ ነው?" የኔ ጥያቄ ነበር። "ጦርነት? የምን ጦርነት!"

እንደዚያማ ከሆነ ያ ሁሉ ቁስለኛ ከየት መጣ?

እሱማ እዚህና እዚያ የደፈጣ ጥቃቶች ይጠፋሉ ብለህ ነው?

አልፎ፣ አልፎኮ ሓይሊታት ምክልኻል ትግራይ በብርጌድ ደረጃ፣ አልፎ ተርፎም ክፍለጦርን ደምስሰው የለም እንዴ?

"እኛን አይደፍሩንም"።

እናንተ ማናችሁ?

“ኮማንዶዎች ነን” ።

ማንን ነው ታድያ የሚደፍሩት?

ብዙ ነገር ያበላሸብን የሻቢያ ጦር እና የኛው መደበኛ ጦር ላይ ብዙ ጥቃት አድርሰውባቸዋል።

እኮ፣ እንደዛ ከሆነ የትግራይ ጦር ቢያንስ በብርጌድ ኃይል እየተንቀሳቀሰ ነው ማለት አይሆንም?

የለም! በብርጌድ ቀርቶ የሻለቃ ጦር የላቸውም። ግን 30 እና 50 ሆነው ከመቸ ተኩስ ከፍተው ብርጌዱን መተዉት እንደሚሄዱ የሚገርም ነው። ፍጥነታቸው ነው ሚስጥሩ። እንጂ፣ ጦር አሰልፈው እኛን ፊት ለፊት የገጠሙበት ጊዜ የለም።

ማለቂያስ አለው?

እሱ ፈጣሪ ነው የሚያውቀው።

የሚገርም ነው።

አዎ፣ የሚገርም ነው።” በማለት ኮማንዶዎቹን ያንኳስሳል።

አብርሃ በላይ በመቀጠል “"ሓይሊታት ምክልኻል ትግራይን" አዛዥ የሆነው የደብረጽዮን መፈክር በሚገርም ሁኔታ እንዲህ ሲል አብርሃ እያጋነነ ያስተጋባዋል፡

“ወደ ትግራይ መግባት ቀላል ሊሆን ይችላል። ግን መውጣት ይቻላል ወይ? ነው ጥያቄው። የገቡ መች ተመለሱ!!!” (አብርሃ በላይ)

ሲል ኢትዮጵያ ወታደሮች ትግራይ መቀበሪያቸው እንጂ ገብተው አይወጡባትም ሲል በወያኔነቱ ኮርቶ በትዕቢት ፈንድቋል።

እርግጣኛነቱም በፋሽስቶች መፈክር እንዲህ ሲል ገብተው እንደማይወጡ በፌበሩዋሪ 27/2021 አብርሃ እንዲህ ያረጋግጣል፡

“Tigrai is like the legendary Phoenix, the bird that they thought have burned and killed it. But it rose up from the ashes of fire with new life and vigor! That is Tigrai!  ትግራይ ትዕወት!

ወደ አማርኛ ልተርጉመላችሁ ፤እንዲህ ይላል፡

“አቃጥለን ገደለን ቀብረናታል ብለው እንዳሰቡት ከእሳት አመድ እንደተነሳቺው እንደ የአፈ-ታሪኳ “የፎኒክስ ወፍ” ሁሉ “ትግራዋይም” እንደ የፊኒክስዋ ወፍ ተቃጥሎም ተገድሎም ቢሆን ከእሳት አመድ በአዲስ ሕይወት እና በብርታት ይነሳል!  ድል የትግራይ ነው!” (አብርሃ በላይ)

በማለት ዓለም አቀፍ ፋሺስቶች የሚጠቅሱዋትና የሚወድዋትን ጥቅስ በመጥቀስ የወያኔ መከላከያ ሃይል “ሞብ” (የኢንተርሃሙዌው የወያኔ ሰራዊት) ፕሮፓጋንዳ ደጋፊ ሆኖ በግልጽ ተቀላቅሏል።

ለመሆኑ አፈታሪኳ የፎኒክስ ወፍ ማን ናት? ለሚለው በሌላ ቀን እመለስበታለሁ። ሆኖም ትግሬዎች በዚህ መፈክር የሚያብዱበት ምክንያት ስለ የትግራይ ፋሺስዝም ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ እንዳጠናው ፋሽዝምን ልዩ የሚያደርገው አክራሪ ብሄረተኛነት በሚፈጥረው ስሜት አንድን ምርጥ ህዝብ ወይም ጎሳ ተቀብሬ በውርደት ኖርኩበት ከሚለው የጭለማ ህይወት በትንሳኤ ሙታንነት አስነስቶ የክብር ማማ ላይ መልሼ አስቀምጥሃለሁ የሚል ተስፋ በመስጠት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሰፊ የሆነ ብሄረተኛ የፓለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ በማስገባት የተከታዮቹን ልብ ለመማረክ መቻሉ ነው። ይላል ደ/ር አሰፋ ነጋሽ።

 ለዚህ ነው አብርሃ በላይም ሆነ አጋሮቹ የትግራይ አክራሪ የነገድ አቀንቃኞች በትንሳኤ ሙታንነት የምትቀነቀነው የፊኒከስ ወፏ ምሳሌ እየጠቀሱ የወያኔ ትግራይ መከላከያ ሰራዊት ከተቀበረበት አመድ የጭለማ ህይወት በትንሳኤ ሙታንነት አስነስቶ በክብር ማማ ላይ ተመልሶ ያስቀምጠናል ወደ እሚል የፋሺስቶች መፈክር እያስተጋቡ የምናደምጣቸው።

እኔ ጨርሻለሁ፡ ሼር በማድረግ ጽሑፉን ማዳረስ የናንተው ድርሻ ነው።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

(ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay)