Saturday, August 26, 2023

ተራራ ሠራቂው የትግሬው ትውልድ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 8/26/23


ተራራ ሠራቂው የትግሬው ትውልድ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

8/26/23

 

ህ ትንታተኔ ወልቃይት የትግሬወ ነው ለሚለው ለኦሮሙማው አሽከር ለትግሬው አብርሃም በላይ እና ይህንን አቋም ለሚያራምዱ ትግሬዎች በሙሉ በምጽሓፌ የተቀነጨበ ዛሬም የምሰጠው መልስ ነው።

 

       ‘ወዲ ዐበይቲ’ አንዳንዴም ዘጽአት እያለ እራሱን በብዕኢር ስም የሚጠራው ትክክልኛው በሙያው ሐኪም የሆነው መጠሪያ ስሙ ጎይተኦም የተባለው “አማራ ከሚለማ የሲናይ በረሃ ቢለማ እምርጣለሁ” በማለቱ የሚታወቀው ጸረ አማራ የናዚ ወያኔ ትውልድና የመሳሰሉት ትግሬዎችና የነዚህ ፋሺሰቶች መምህር የሆነው ሟቹ መምህር ገብረኪዳን ደስታ  “አማራዎች ባህላችን ነጥቀው ወልቃይትና ራያ መሬታችንም ነጠቁን” የሚሉትን እሮሮ ማስተጋባታቸው ይታወቃል።

 

ይህ የሄጂመኒ” (የስልጠቃ) ወረራ እና ማስተጋባት ዛሬም እልባት ስላላገኘ ይህ ደራሲ በመጽሐፍ መልክም ሆነበድረገጾች በዚህ ጉዳይ ሲለው የነበረውረ ዛሬም  የጉዳዩ አሳሳቢነት በማየት የወያኔ ትግሬዎች የዝርፍያ ማሕደሮችን ለማሳይት ዛሬም እንሆ፡፡

 

 አማሮች ፤ጎንደሬዎች ይህንን ዘረፉን የሚለው እሮሮ ተመልሼ እነ አብርሃም በላይ የድሮ የወያኔ የስለላ ኢንጂኔር ሰራተኛ እና  እና መሰል ጎጠኞችን መልሼ ልጠይቅ?

 

‘የጎንደርን ወልቃይትንና የወሎን መሬት የመዝረፋችሁ ሳያንስ፤ ብላችሁ ብላችሁ ራስ ዳሽንም ሰረቃችሁ፡ ተራራም ይሰረቃል እንዴ? ብለው ጎንደሬዎች ቢጠይቁዋችሁ ምን መልስ አላችሁ?

 

ይህ ጥያቄ ያቀረበኩላችሁ እኔው ትግሬው ሳልሆን አማራው ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ነው፡ ክንፉን የጥቅሱ ጽሑፍ በመጽሐፌ ላሳትመው ብየ ጠይቄው በደስታ እንድጠቅሰው ስለፈቀደልኝ ያኔ ባሳተምኩት መጽሐፍ (የወያኔ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው?) በሚለው መጽሐፌ የታተመው ጥቅስ ። እንዲህ ይላል ክንፉ፦

 

<<ራስ ዳሸን ተራራ ከትግራይ “ክልል” ካርታ የመውጣቱ ‘አሲዮ ቤሌማ’ በብሄራዊ ቴሌቪዥን ሲናገር፤ “ደፍረውናል! ንቀውናል! ብታምኑም ባታምኑም በቁም ሞተናል!” የሚለው የኮሎኔል መንግስቱ ንግግር በጆሮዬ ላይ አቃጨለ። ድፍረቱ እና ንቀቱ እንዳለ ሆኖ፣ በቁም የሞቱት ግን እኛ ሳንሆን እነሱ መሆናቸውን የሚያበስር የዜና እወጃ ነበር።

ድምጽም በተደጋጋሚ ሰርቀዋል። ተራራ ተሰርቆ  ሲመለስ ግን የመጀመርያው ነው።

 

ከኢትዮጵያ አንደኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ በከፍታ 4ኛው ተራራ ነው ራስ ዳሸን። ከሰሜን ጎንደር ከበየዳ ወረዳ ተሰርቆ ለ25 አመታት ሙሉ ትግራይ ክልል ገብቶ ነበር። ወንጀሉ ወደ ትግራይ “ክልል” መግባቱ ብቻ አይደለም። አንድ ትውልድ እና በስነ-ምድር ሳይንስ በውሸት ታሪክ እንዲታነጽ መደረጉ እንጂ!>> ይላል ጋዜጠኛ  ክንፉ አሰፋ (ተራራም ይሰረቃል እንዴ? የራስ ደሸኑ ፖለቲካ September 18th, 2016 ምንጭ ክንፉ አሰፋ ድረገጽ EMF ኢትዮ ፎረም አዘጋጅ) (በራሴው መጽሐፍ ገጽ የታተመ -ጌታቸው ረዳ (89)

 

ይህ ሁሉ ስርቆት በትግሬዎች መንግሥት እየተፈጸም እየታወቀ ወልቃይትና ራያ አማራዎች ሰረቁን እያሉ ራስን እንደ ንጹህ ማቆነጃጅት የሚገርም ዘመን ነው። ሌላው ዝርፊያው ከተከናወነ በኋላ የሚሰረቅ ታጥቶ ተራራ ሲሰረቅ ማየት እውነትም  <<ተራራም ይሰረቃል እንዴ?”!>> የሚያሰኝ የሚገርም ጉድ ነው። ‘አላርፍ ያለች ጣት ……..ምን ዘንቁላ ትወጣለች” ነው የሚሉት የአማራ ምሳሌዎች!?

 

በ1998 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ትግራይ የተከለለ ራስ ዳሸን ተራራ በስህተት ነው ብሎ በ2009 መንግሥት ተብየው በቴ/ቪ ያቀረበው ሳይወድ እርማት ያደረገው “ተራራ ሠራቂ” የሌባ ዓይነደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ ይሉታል ይኼ ነው። የትግሬዎቹ መንግሥት  በተራራ ዘርፍያ ብቻ አላበቃም፤ፎቶግራፎቹ በመጽሐፌ የጣታሙ ምስሎች ናቸው።                                                         

ሌላው የመሬት/ የድምበር ዘረፋው/ (አነክሰሽን) ደግሞ እንደሚከተለው በስሕተት ነው እያለ ቅጥፈቱን ለማሳመር ይቅርታ ጠይቋል። የራስ ዳሸንን ተራራ ለ11 አመት ሙሉ በየትምህርት ቤቱ በእንግሊዝኛ መማርያ መጽሐፍ ውስጥ አትሞ ተማሪዎች የትግራይ ተራራማ መሬት መሆኑን ካስተማረ በኋላ ሲነቃበት <ስሕተቱ የማተሚያ ቤቶች ስሕተት ስለሆነ ይቅርታ እንጠይቃለን> ብሎ 11 አመት አላወቅኩም ነበር ሲል ወደ ‘አማራ ክልል’ ወደ ጎንደር ለባለቤቱ መልሰናል ብሎ ሲያበቃ፤ እንደገና ሌላ የቡንሻንጉልና አማራ መካበቢያውን ወደ ትግሬ ቀላቅሎ በአማራ መሬት በስጀርባው/በጓሮ በኩል እንደ እባብ ተጠምጥሞ አልፎ የአማራ ሕዝብ) ለብቻው ታጥሮ ወደ ሱዳን መንደርም እንዳይወጣ አጣብቆ በመከለል ከቤንሻንጉልም እንዳይገበያይ ‘እንዲነጠል” ያደረገው የትግራይ ወያኔ የመሬት ዘረፋ (አነክሰሽን) አከላለል ‘ካርታው’ በ ኢ ብ ሲ-ቴሌቪዥን የታየው በስሕተት ከኢንተርኔት የተወሰደ ካርታ ስለነበር  ይቅርታ ሲል ጠይቋል።

 

እንግዲህ ደጋግሞ በተለያየ ስርቆቱ ይቅርታ መጠየቁ የሕዝቡን ‘ቅንድብ’ ስለሚያቆም ፤ሐፍረቱን ለመሸፈንና ሌብነቱንም ሕጋዊ አድርጎ በሕዝብ ሕሊና ለማስረጽ 

 

ላቀደው ተንኮል ለመሸፈን እንዲያመቸው በማለት ብዙውን  የአገራችን ሕዝብ  በማያውቀውና በስፋት የማይገለገልበት <በፌስ ቡክ> ብቻ (ልብ በሉ! በቴ/ቪዥን አይደልም ይቅርታ የጠየቀው በፌስ ቡክ ቲ/ቪ ብቻ ነው ይቅርታ የጠየቀው።) ያስተላለፈው።

 

 ይቅርታው እንዲህ  ይላል።

 

<< ለክቡራን የኢቢሲ ተመልካቾቻችን በ18/12/2009 ዓ.ም በ ኤቢሲ የቀን ሰባት ሰዓት ዜና ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ ሽልማት መገኘቱን ተከትሎ በተሰራው ዜና ላይ ሰራውን ለማሳየት  ከኢንተርኔት የተወሰ የተሳሳተ ካርታ በዜናው ላይ የገባ ስለሆነ ለተፈጠረው ስህተት ኮርፖሬሽኑ ይቅርታ እየጠየቀ፤ ሌላ ምንም አይነት መነሻ የሌለው መሆኑን እንገልጻለን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን>> ይላል።>> (ታላቋ ትግራይን እንድለማመድ የተለቀቀው ካርታና የኢቢሲ ይቅርታ – ቬሮኒካ መላኩ (August 28, 2017 Ethioxplorer.com / Ethioforum.com) (91)  “ከኢንተርኔት የተወሰደ?” ይገባችኋል አነጋገሩ? መንግሥት ነኝ የሚል የአገሪቱን ትክክለኛ /ሕጋዊ የመሬት ነድፍ (ካርታ) ሳይኖሮው ከኢንርተርነት የተቀዳ ስሕተት ስለሆነ ብሎ ማለት ቀልድና ቅጥፈት ነው። ወያኔ ይቀልዳል! ኢንተርኔት ያለው ካርታ ማነው ያሰራጨውና የሰራው? “እራሱ “ወያኔ” ነው!

 

በመሰረቱ የሁለቱም ነጠቃ/ዝርፊያ/ይቅርታ ሲደረግ፤ 1ኛው በት/ቤት መማሪያ መጽሐፍ የሚያክል ትልቅ ጉዳይ፤ ለመጽሐፍት ጥራት የተቀጠሩ ምሁራን መርማሪዎች- ሳይጣራ፤ ሳይመለከቱት “ይለፍ” ተብሎ የታተመውን መጽሐፍ “አጣሪው’ ክፍል ስራው አልሰራም (የወያኔን ቃል “ስሕተት” የሚለው እንቀበለውና) ከፍተኛ “ስሕተት” ስለፈጸሙ ለግዴለሽነታቸው ከሥራቸው መባረር ነበረባቸው። አይደለም እንዴ? እርምጃ ከተወሰደባቸውም ለሕዝብ ወዲያውኑ ማሳወቅ ነበረበት። እይደለም እንዴ? ሌለው ወያኔ የሚለን “ማተሚያ ቤቱ ራስዳሽን ወደ ትግራይ የተካለለ አድርጎ አትሞታል በስሕተት” ይላል። ማተሚያ ቤቱ “ካርታ የማውጣትና መጽሐፉ ውስጥ የማስገባት፤የመደለዝ፤የማስወጣት፤የማረም፤የማስተካከል፤ መብት በየትኛው የሕዝብ ሥልጣን፤ ይሁንታ ወይንም  የፓርላማ ሕግ ስለተሰጠው ነው፤ይህ <ስሐተት> (የወያኔ ቃል) ወንጀል ለመፈጸም መብት የተሰጠው?

 

 ስሕተት ከሆነ ማተሚያ ቤቱ ወደ ሕዝብ ተጠርቶ በቴ/ቪዥንና ራዲዮ፤ ጋዜጣ ተጠይቆ  መልስ እንዲሰጥ ለምን አልተደረገም? ፍርድ ቤትስ ለምን ሄዶ ቅጣቱን እንዲያገኝ አልተደረገም? የአገሪቱ “ክልሎች” (አፓርተይድ ግዛቶችና ሰንደቃላማዎች) በሕግ ከጸደቀ ካርታ ዉጪ ያሰራጨ በሕግ እንደሚያስቀጣ በሕገ መንግሥት ተብየው ደንግጎ እያለ፤ በውስጡ የሚገኙ ዘርፎች በስሕተት ሰሩት ብሎ ከዋሸን ለምን አልተቀጡም? ወያኔ ሕዝብ አያውቅም እያለ በሕዝብ ሕሊና ይቀልዳል፤ያሾፋል። የጫካ ሕሊናው በከተማውም ውስጥ የሚሰራ እየመሰለው በለመደው በጫካ ባሕሪው አሁንም ማታለሉና ድንቁርናው ቀጥሎበታል። ሕጉ ለማን ነው የቆመው? ማተሚየ ቤቱና መንግሥት ሐላፊዎች ሥራቸውን በሚገባ ካልሰሩ  “በሕግ” ከመጠየቅ ነፃ ናቸው? ሕግ እያለ የሚያወራው ሕግ የት አለ? አማርኛ ቃል የታጣ ይመስል “ብሮድካስቲን ኮርፖሬሽን” እያለ የሚጠራው የወያኔ የዜና ማሰራጫ ማዕከል፤ በየድረገጹ እየለቀሙ  “ሕጋዊ ካርታ” አስመስለው ለሕዝብ ሲያቀርቡ ሥራቸውን ያልሰሩት የዜና ማዕከሎቹ (አርታኢዎቹ) ለምን አልተጠየቁም? ምንሰ እርምጃ ተወሰደ? አልተወሰደም፡ ምክንያቱም “ወያኔ” ሊያድረገው የፈለገው የራሱ “መመሪያ እና እምነትና ስርቆት” ስለሆነ።

 

 <<ይቅርታ> እና <ስሕተት> በሚሉ ቃላቶች ማላገጡን ቀልሎታልና የሌባ አይነደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ። የወያኔ ደጋፊዎችም የሚደግፉትን መንግሥት ተብየው፤ ሕግመንግሥት አያዩትም ፤ አያውቁትም ቢሆን ትግሬነታቸውና ድርጅታቸው ፍጹም ነው የሚል ምነት ስላላቸው እንደ ታቦት ያከብሩታል፤ ቢሳሳትም እያወቁም ቢሆን ተጨፍነው ይከራከሩለታል።

 

የሚቀርብባቸው ክስ ሁሉ፤ ሻዕቢያ የሰረው ካርታ ነው ሲሉ ጭፍን መለስ ሲዋሹ ተከታዮቹ ያምኑታል። <<ይህን ሐሰተኛ ካርታ የሰሩትና የተቀባበሉት ጽንፈኞች ናቸው ብለን እንወራረዳለን/እንሰደባለን።>> ሲሉ የሚወነጅሉንና እንወራረድ የሚሉንን ውርርዳቸውን በሚከተለው የወያኔ  ሕገ መንግሥታዊ ማስረጃ እንመልከት።  ታላቋ ትግራይን እንድንለማመድ የተለቀቀው ካርታና የኢቢሲ ይቅርታ – “ቬሮኒካ መላኩ” ወልቃይት.ካም welkait.com August 28, 2017) (92) <ለካርታው ይቅርታ ተጠየቀ! ሕገ መንግሥቱ እንዴት ይስተባበል?> (ሙሉቀን ተስፋው) (93) በሚል ካርታው በወያኔ ሕገ መንግሥታዊ አዋጅ የጸደቀ መሆኑን በማስረጃ እቅርቦታል እነሆ ፦


<<አሁን ጥያቄው የካርታውስ ጉዳይ በይስሙላ ይቅርታ ታለፈ! የተሰረቀው ተራራና የተሰረቀው ቤተ መቅደስም አፉ በሉን ተብሎ ተመለሠ፡፡ ይህ ሕገ መንግሥት ምን ዓይነት ማስተካከያ ሊደረግበት ነው? የሚለው ነው፡፡ ይህን  የቤንሻንጉል ክልል ሕገመንግሥት በፎቶው ላይ ይመለክቱ። ሕገመንግሥቱን ለማንበብ

እንዳይችግራችሁ እንዲህ ይነበባል፦

አንቀጽ 1

የክልሉ መንግስት ስያሜ ይህ ህግ መንግስት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዴሞክራሲያዊ አወቃቀርን ይደነግጋል። በዚህም መሠረት የሚቋቋመው መንግሥት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሚል ስም ይጠራል።

 

አንቀጽ 2

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ወሰን በምስራቅ--የኦሮሞ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፤ 

በምዕራብ -    ሱዳን በደቡብ -   ጋምቤላ ሕዝቦች ክልል በሰሜን -     የትግራይ ክልል

 

በሰሜን ምስረቅ -የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ያዋስናል። የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብሄራዊ መንግሥት

ሰንደቅ አርማ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልል የራሱ ሰንደቅ ዓላማና አርማ ይኖሮዋል።

(ሙሉቀን ተስፋው፡ የዘመኑ ዕልቂት ደራሲ፤ ጋዜጠኛ )

August 30, 2017 ETHIOEXPLORER.COM) (93)

(ምንጭ ይህ ደራሲ ፈልጎ ያገኘው የሚከተለው ምንጭም የላይኛውን ያረጋግጣል።)

<<የኢፌዲሪ ሕገ-መንግስትና የቤንሻንጉል-ጉሙዝ ሕዝቦች ታሪክና ተጠቃሚነት ለ9ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ለውይይት የቀረበ ህዳር 2007 ዓ.ም አሶሳ>> ይመልከቱ። የወያኔዎች ተንኮል መልሶ መላልሶ ልብ ያናድደናል! ወደ ሌላው የወያኔ ዘርፋያ እናምራ።   አማራዎቹ በሚከተለው ሰነድና ፎቶ እንዲህ ሲሉ ወያኔ ትግሬን  በስርቆት ይከስሳሉ-

 

(ከላይ ከምስሉ ጋር የምታዩት የጎንደሩ አንደኛዉ የጄኔረተር ክፍል ከ 24 አመት በፊት ተነቅሎ ወደ ትግራይ ተወስዶ ዉቆሮ አካባቢ ወደ አለችው የወረዳ ከተማ ሲራገፍ) ከአማራ አካባቢ

ወደ ትግራይ የወሰዳቸዉ ትልልቅ ጄኔረተሮችና ማሽነሪዎች የታወቁት

1.   የጎንደር ጄኔረተር፡

(ይህንን ጀኔሬተር በተመለከተ በክልሉ ም/ቤት ላይ እና በግልም ሀላፊዎችን በመጠየቅ ከፍተኛ ጥያቄ ያነሳ የነበረ ሰው በርካታ መረጃዎችን ይዘረዝራል)፤ ይህ ጄኔረተር ጎንደር ከተማዉንና የጎንደር ዙሪያ ያሉ ከተሞችን ያለምንም ችግር የ24 ሰአት የመብራት አገልግሎት ይሰጥ የነበረ አሁን ዉቅሮ አካባቢ ያለ። ጄኔረተሩ የነበረበት ሰፊ ቦታ አሁንም ድረስ አዉቶ ፓርኮ የሚባለዉ የከተማዉ እመብርት ላይ ታጥሮ ይገኛል።ጄኔረተሩን አናስወስድም ያሉ ሰወች በጥይት ተደብድበዉ ሞተዋል። 

2.  የባህርዳር ጄኔረተር፡

ይህ ጄኔረተር የባህርዳር ከተማን ሙሉ ለሙሉ የመብራት ሽፋን ይሰጥ የነበረ ሲሆን በጠመንጃ አፈሙዝ ነቅለዉ ወደ ትግራይ ወስደዉታል

3.  ፓዊ ጄኔረተር።

በድሮዉ ጎጃም ክፍለሀገር አሁን በቤንሻንጉል አካባቢ የሚገኝ ተልቅ የንግድ ከተማ ሲሆን የነበረዉን ጄኔረተር እንደዚሁ ህዝብ አስፈራርተዉ በጨለማ ወሰዱት

4. የመርሀ ቤቴ ጄኔረተር (ሰሜን ሸዋ)። ይህ አንድ ወረዳ ያበራ የነበር ጄኔረተር ሜንሽን ፎር ሜንሽን በተባለ የጀርመን ግብረ ሰናይ ድርጅት ከጀርመን ተገዝቶ ለአካባቢዉ ጥቅም ይሰጥ የነበረ ሲሆን። ህብረተሰቡ ሳያይ በሌሊት ነቃቅለዉ ወስዱት

5.                ግምጃ ቤት አካባቢ እንደዚሁ አንድ ወረዳ ያንቀሳቅስ የነበረ ጄኔረተር ተነቅሎ ወደ ትግራይ ተወስደ

6.               አዲስ አባባ እጅግ ዘመናዊና ትልቅ የዳቦ መጋገሪያ ማሽን ለአንድ ሚሊየን የአዲስ አባባ ህዝብ አገልግሎት ይሰጥ የነበር ማሽን ተነቅሎ ወደ መቀሌ ተወሰደ

7.                ደብረማርቆስ እንደዚሁ በአይነቱና በመጠኑ እጅግ ዘመናዊ የነበረ የድንጋይ መፍጫ ማሽን ተነቅሎ ወደ አዲግራት ተወሰደ የመሳሉ ጀኔረተሮች ወደ ትግራይ መወሰዳቸው  ‘ምጽአተ አማራ በሚለው መጽሐፍ ውስጥ በሰፊው ተዘግቧል። እላይ ካለው ጄኔረተር ፎቶ በተመለከተ አንድ ግጥም መገጠሙን ያሳያል። እንዲህ የሚል

<<አንዳንድ ብር አውጡ ፎቶ እንነሳ          እንደ ጄኔረተሩ ፋሲል ግንብ ሳይነሳ >>  (welkait.com የተለጠፈ ጽሑፍ የተገኘ) (94)

 

ሌላ ቀርቶ ላሊበላም በትግራይ ውስጥና የትግራይ ነው በማለት በቱሪዝም ሚኒሰትር ድረገጽ ማስታዊያና በ ቪዲዮ ማስታወቅያ አሳትሞታል። በዚህ ሌላ ቀን እምለስበታለሁ።

 

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ