Thursday, February 4, 2021

ኦሮሞዎቹ ያበረከቱልን አዲሱ ሂትለር እና የናዚ ሕዳሴ በኢትዮጵያ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 2/4/2021

 

ኦሮሞዎቹ ያበረከቱልን አዲሱ ሂትለር እና የናዚ ሕዳሴ በኢትዮጵያ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

2/4/2021


 

የትግራይ ወያኔ ቡድን ገበያ ቀንቶት ከትግራይ /ሃገር ከደደቢት በረሃ ገስግሶ ወደ መሃል አገር አዲስ አበባ በመግባት 1981 . ጀምሮ በረሃ ውስጥ ሲመራበት የነበረውንየብሔረተኛ-ፋሺዝምመመሪያውን እውን በማድረግ 17 አመት ትግራይን ቀጥቅጦ፤ 26 አመት ደግሞ ኢትዮጵያን ቀጥቅጥ አድርጎ ገርፎ፤ የነበረውን ሁሉ እንዳልነበረ አድርጎ አሁን ላለንበት ውርደትና ሓዘን ዳርጎናል

 በዚህኛው ብሔረተኛ ቡድን ትምህርት ሰልጥኖ በስለላ ሥራ ተመድቦ ሕዝባችንን ከትግሬ ብሔረተኛ ፋሺስታዊ ቡድን ጋር ወግኖ የወያኔኩሊበመሆን ሕዝባችን ለእስርና ለድብደባ ሲዳርግ ቆይቶ ከሁለት አመት በፊት ኦሮሞዎች ያበረከቱልንን ሥልጣን ዙፋን ላይ የወጣው ኮለኔል አብይ አሕመድ፤ የትግሬዎቹ ፋሺስት መሪ የነበረው የሟቹ የመለስ ዜናዊ ባህሪና የአመራር ስልት በማስቀጠል ባሰማራቸው የኦሮሙማ አጀንዳ ተከታይ ፖሊሶቹና የፍትሕ ሹሞኞቹ በኩልሆን ብሎየሚቃወሙትን ተቃዋሚ መሪዎችን እና ግለሰቦችን እንዲሁም ሰላማዊ ዜጎችን ለዳግም ድብደባ፤እስር እና በከፋ መልኩ ደግሞ አማራው ላይ የዘር ጭፍጨፋ እንዲካሄድ አድርጎ ኢትዮጵያ ወደ ከፋ ህይወት በመዳረግ አገሪቷ ገደል አፋፍ ላይ እየተንቀጠጠች ቆማለች።

 ምንም እንኳን ይህ ኮለኔል ዕልል ብሎ የተቀበለውን ሕዝብ ያስጨፈጨፈ፤ የካደ፤ በጣም ነውረኛ፤ ተንኮለኛ እና የከፋ ፋሺሰት መሆኑን ለሁለት አመት ሙሉ ያስፈፀማቸው ወንጀሎችን በሚመለከትአቤቱታና ጩኸትለዓለም ተቋማት (ከእስክንድር ነጋ ጋር ሆነው፤ እንደ እነ ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ፤ አገሬ አዲስ…. የመሳሰሉ ምሁራንና ጥቂት የሚዲያ ሰዎች  በማመልከት በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት ቢገልጹም  ዓለም ዝምታን መርቷል።

ኮለኔሉ ወደ ሥልጣን ከመጣ ወዲህ በፖሊስና በዳኝነት የተሾሙና የተሰለፉ አገልጋዮቹ ከእነዛኛዎቹ 26 አመት የትግሬጎስታፖፖሊሶች (ዳኞቹም የድሮዎቹ ናቸው) በከፋ መልኩ በእንሰሳነት ባሕሪ እየተመሩ ጭካኔ የተሞላበት ዘግናኝ ግፍ እየፈፀሙ ነው።

የሚገርመው ነገር፤ የኮለኔሉ ደጋፊዎች የሕግ የበላይነትን የሚጥስና የዘር ጭፍጫፋ በከፋ መልኩ እጅግ ለጀሮ የሚቀፉ ድርጊቶች መፈጸማቸው እያዩም ቢሆን ስሜት አልባ ሆነዋል።

ኩሊየምትለዋ የወዳጄ አምሳሉ ገብረኪዳን ቃል ልጠቀም እና ይህ የወያኔኩሊአምባገነን ነው ወይስ አይደለምየሚል ክርክር ሳይሆን (የዚህ ኮለኔል አመጣጥ ወደ መጀመሪያው ታሪክ ላስታውሳችሁ እና) ስለዚህ ግልብና አጭበርባሪ ሰው ኦሮሞ አባገዳዎች ምን እንዳሉ ላስታውሳችሁ።

እንዲህ ብለው ነበር፤-

አብይ አሕመድ ባይመረጥ ኖሮ ሁሉም ኦሮሞ በየቤቱ ጩቤ አዘጋጅቶ ሊወዳቅ ተዘጋጅቶ ነበር፤ አሁን ግን አብይን ወደ ሥልጣን ስለመጣኡፎይብለናልብለው የኦሮሞው አባገዳ መሪአቦ በየነ ሰንበቶየሚመራው የኦሮሞ ሽማግሌዎች ቡድንይግደላችሁ፤ያሰቃያችሁብለው መርቀው የሰጡንንየጂማው ኮለኔልየዓድዋውን ተጋዳላይ መለስ ዜናዊ የተካአዲሱ አዶልፍ ሂትለር ነው

ይህንን ለማረጋገጥ የኮለኔሉ ፖሊሶችና ዳኞቹ እንዲሁም የብልጽግና ሹሞች ተብለው አማራን በማሰቃየት ላይ ያሉት የአብይ ሹሞኞች ምን ሥራ ላይ እንደተሰማሩ በሦሰት አመት ውስጥ የፈጸምዋቸው ግፎችና በግልጽና በድብቅ ያስተጋባቸው “ኦሮሙማዊ” ንግግሮቹን በየሚዲያው የተለጠፉትን የተለያዩድምጾቹንአይታችሁ ፍረዱ።

የአሁኑን እና ያለፉትን የፖለቲካ ገጽታዎች ያለአንዳች ብልጭልጭ ማየት ለሚችሉ ሰዎች የማስጠንቀቂያ ምልክቶቹ ግልጽ ናቸው። ይህ “ወታደራዊ ፋሺሰት” የዜጎች መብት ለማፈን መለስ ዜናዊ መስርቶት የነበረው የስለላ /ቤት በሓላፊነት ተሰማርቶያገለገለውን የወያኔን መንግስት ከሰብአዊ መብት አፈና ጋር ያደረበት ፍቅር ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የተዋሃደው የአፈና ባህል ዛሬ ሊለቀው አልቻለም ፡፡

በእርግጥ አብይ አሕመድ የትግሬዎቹና የኤርትራ ናዚያዊያን ስርዓት በጣም አድናቆትና አክብሮት ስላለው (መቀሌና አስመራ ሄዶ የተናገራቸውን ንግግሮቹን አድምጡ) ሥልጣኑን ከተቆጣጠረ በኋላም ቢሆን የወያኔ ግልገል ፋሺስት ፖሊሶችን፤ የፍርድቤት ባለሥልጣኖችን፤ሚኒስትሮችን፤ አምባሳደሮችን፤ ሲቪልና የደህንነት ሠራተኞችን በድብቅና በግልጽ እንዲያገለግሉት በማድረግ በዙርያው አስሰልፎ የነበረውንፋሺስታዊ ፕሮቶኮሎቹንእንደመመሪያው አስቀጠሎአቸዋል።

በዚህ መልክ መጠነኛ የሚያጃጅሉየገጽታ ቅባትበማድረግ የተረከበውን የፋሺሰቶችን ሕግ እና ስርዓት ተቀብሎ የከፉ የመብት ረገጣዎች ተግባራዊ አደረገ።

አንድ የታሪክ ምሁር እንደገለጹት ሂትለር ተሸንፎ የጀርመን ጎስታፖና የናዚ ኤስ ኤስ የፖሊስ አባላት ወደ አሜሪካ እንዲገቡ ከተደረገ በሗላ 5 ዓመታት በኋላ የናዚ ፖሊሶች ኤፍ. . አይነት/ የምስክር ወረቀት ማረጋገጫ አግኝተዋልእንዳሉት ሁሉ በአብይ አሕመድ መንግሥት ሥር ያሉት የፍትህ መዋቅሮች እና ፖሊሶችም 26 አመት ሕዝብን በጥይት ሲደበድቡና ዜጎችን ሲያስለቅሱ የነበሩአረሜ ፖሊሶችና ዳኞችእንዲሁም ዘራፊዎች በከፋ መልኩ እኩይ ተግባራቸውን ያለምንም ተጠያቂነት እንዲቀጥሉበት ፈቅዶላቸዋል።

አሁንም ሥርዐቱ ውስጥ ያሉት እነዚህ የፍትህ አካላት ብዙዎቹ የአማራን ማሕበረሰብ ሲጨፈጭፉ የነበሩ ቢሆኑም፤ ከሥርዓቱየእልቂት ማሽንጋር ያላቸው ትስስር እንደማናውቃቸው ለማድረግ አዳዲስ ካባዎችን በመደረብ በብዙ ስልት ማንነታቸውን ለመደበቅና ለመቅረጽ ተሞክረዋል (አብይ አሕመድ የስለላ/የጠለፋ/ ሓለፊ ሆኖ ሲሰራበት በነበረበት ወቅት የተለቀቁ የተክለ ሰውነት ቀረጻ በሚዲያ የተለቀቁትን የማታለያ ቪዲዮዎችን አትርሱ) ፡፡

እንደምታውቁት በግልጽ የታወቁ የትግራይ የወያኔ ወንጀለኛ መሪዎችና ካድሬዎቻቸውን አንዳንዶቹን በዙርያው አማካሪ አድርጎ ሲሾም ሹመቱን አንቀበልም ብለው ወደ መቀሌ የመሸጉ እንደ እነ ስዩም መስፍን የመሳሰሉት ወንጀለኞችም በሰላም እንዲኖሩ ፈቅዶ

አብይ አሕመድም እንደልቡ ወደ መቀሌም ሆነ ወደ አክሱም ሁለቴና ሦስቴ ለመግባትና ለመውጣት ፈቃድ ተመቻችቶለት እንደነበር አስታውሱ። እባክህን እነዚህ “የጫካ ሰዎች” ስለሆኑ አንድ ነገር አድርግ ሲባል “ለአንድ እና ሁለት ሦሰት ሰው ስንል ጦርነት አንከፍትም” ሲል የነበረው “አብይ” የሥልጣን ጥመኛ ስለሆነሥልጣኔን አትንኩብኝ እኔም አልነካችሁምበሚል በፈጠረው የመለሳለስና ጓዳዊ የስልክ ልውውጥ እነሱም ሆነ እርሱ በሰላም እየኖሩ  እንደነበር ታስታውሳላችሁ።

ወያኔ በሰላም መኖር የማይችል፤  የወንጀለኞች ስብስብና የፋሺሰት ፍልስፍና የሚከተል ድርጅት ስለሆነ ጦርነት መክፈቱ የማይቀር እውነታ ነው ብየ ስጮህ (ይህ ደግሞ ለበርካታ አመታት እኔም ሆንኩ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ስንለው የነበረ አውነታ ነበር) ብዙዎቹ የአብይ ደጋፊዎች በኔ ላይ ያሾፉ ነበር። ደጋፊዎቹ ብቻ ሳይሆን የወያኔ ባህሪ የማያውቁ ኢትዮጵያዊያንም “ሰጥቶ መቀበል” ከተደረገ…ምናም እያሉ ወያኔ በሰላም ሥልጣን ይለቃል ሲሉ ነበር።

የሚገርመው ደግሞ ወያኔዎች ዛሬም የሥልጠን ተጋሪ ሆነው ፍልስፍናቸውና በረሃ ውስጥ የቀረጹት ሕገመንግሥታቸው ሥራ ላይ እየዋለ ነው።ለዚህም ነው አብይ አሕመድ ዛሬም በወየኔዎች መጽሐፍ እየተመራ ናዚያዊ ፖሊሶቹን በማሰማራት ዜጎችን በመደብደብ በመግደል እና በማሰርና የአማራ ሕዝብ በመጨፍጨፍ የናዚ ህዳሴ እያበሰረ ያለው።

አንድ የቀርብ ምሳሌ ልስጣችሁ - ፍርድቤት ያልቀረበ ወንጀል ያልፈጸመ፤ በወንጀል ያልተከሰሰና ያልተፈረደበትን እስክንድር ነጋን አብይ አሕመድ ቤታቸውን የፈረሰባቸውን ዜጎች ለምን ቃለ መጠይቅ አደረግክላቸው ብለው የአብይ አሕመድ ፖሊሶች (ኩሊዎች) አንድ ቀን አስረውት ከለቀቁት በሗላ፤ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የግል ሞባይል ቴሌፎኑን በእግዝቢት አስቀርተውየግል ምስጢሮችን በመበርብር ላይ እንደነበሩ ታስታውሳላችሁ። ያኔ እስክንደር ነጋም ስልኬን መልሱልኝ ብሎ ለዓለም እሪ እያለ ነበር። የሰብኣዊ መብት ጠበቆችም ሁኔታውን ኮንነውታል። የናዚ ህዳ አበሳሪው አብይ አሕመድ ግን ከጉዳይም አልቆጠረውም።

የናዚ ጎስታፖዎች የጀርመን ዜጎችን የስልክ እና የግል ደብዳቤዎቻቸውን መፈተሽና መሰለል መብት እንደነበራቸው ሁሉ፤ የአብይ አሕመድ የፍትሕ አካላት እና ፖሊሶች የሰላማዊ ሰው የግል ሞበይል ቴሎፎንም ሆነ ኢመይልና የደብዳቤ ማሕደሮችን የመፈተሽ የመንጠቅ እና የመሰባበር፤ የክርስትያን ማተብ የመበጠስ፤ ሰውን ያለ ሃጥያቱ መወንጀል፤ ሰንደቃላማችንን ጭቃ ላይ መጣልና በመቀስ መቀዳደድ አልፈው የዘር ማጽዳት እስከ ማከናውን መብት ተፈቅዶላቸዋል። ለዚህም ነውኦሮሞዎቹ ያበረከቱልን አዲሱ ሂትለር እና የናዚ ሕዳሴ በኢትዮጵያእናቶችና አረጋውያን በመራራ ዕንባ እያስለቀሰ ነው የምንለው።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (የኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) Ethiopian Semay