“አራጆች የሚል ቃል ባንጠቀም ጥሩ ነው” “እኔ ሰው ስለመታረዱ አላውቅም” የሕግ ምሁር መጎስ ተሾመ!
“አራጆችን አራጆች ካላልናቸው ምን እንበላቸው?
“ሃኪሞች እንበላቸው?” ጋዜጠኛ ተስፋየ ተሰማ
ትችት አቅራቢ
ጌታቸው ረዳ
(Ethiopian Semay) 8/3/23
ይህ ውይይት የተካሄደው በቴድሮስ ፀጋዬ አወያይነት በርዕዮት ሚዱያ ሲሆን ቴድሮስ ፀጋዬን ለሚዛናዊ አወያይነቱ
ሳላመሰግነው አላልፍም።
የሆነው እንዲህ ነው፤፡
“የሃሳብ ገበታ” የሚል የመወያያ መድረክ አዘጋጅ የሆነው የሕግ ምሁርና ተማሪ ሞገስ ተሾመ እና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ተሰማ በትናንት ዕለት፤ በርዕዮት ሚዲያ (ቴድሮስ ጸጋዬ) ቀርበው “አማራ የሕልውና አደጋ ተጋርጦበታል” በሚል ርዕስ ስለ አማራ ጉዳይ ውይይት አድርገዋል።
ረዢም ውይይት ካደረጉ በኋላ በውይይቱ መሃል “ጋዜጠኛ ተስፋዬ ተሰማ” እምባ እየተናነቀው ወለጋና የተለያዩ ቦታዎች ውስጥ አማራ በመሆናቸው ሳይሞቱ
በህይወት እያሉ “እንዲሰቃዩ” በሚል “እግር እና እጆቻቸው እየተቆረጡ” ተሰቅለው ከተሰቃዩ በሗላ ከዚያም ሲገደሉ ያዩ “ከግድያው
ያመለጡ አማራዎችን” አገር ቤት ሄዶ ቃለመጠይቅ አድርጎላቸው ከተመለሱ
ሁለት ሳምንት እንደሆነው እየገለጸ “ሆድ ብሶት” እምባ እየተናነቀው ስለ ሁኔታው ሲናገር ለነበረው “ጋዜጠኛ ተስፋዬ ተሰማን” ተወያዩ
አቶ መጎስ ተሾመ የሚከተለው አስደንጋጭ ንግግር ተናገረው፡-
<<ይህ “Appeal to pity” እያደረግክ ነው ያለኸው>> አለው።
“Appeal to pity” ማለት፡ ተከራካሪው ክርክሩን በሎጂክ(በተጨባጭ አመክንዮ) አስደግፎ ከመሞገት ይልቅ
በተመልካቾች ስሜት ውስጥ ሓዘን እንዲሰማቸው በማድረግ እንዲያዝኑልህ ድጋፍ በመፈለግ ስሜታቸውን በመስለብ ሞጓቹን ለማሸነፍ
መሞከር ማለት ነው።>>
በማስከተልም ሞገስ ተስፋየን እኔን በተመለካች ዘንድ “ለእርድ” አቅርበኸኛል፤ ማለትም “ጸረ እንዲህ ጸረ እንዲህ ነው እንዲሉኝ….” በማለት የተስፋየን እንባ አድማጭን በቀላሉ ስለሚስበው እኔን “ጥፋተኛ እና ለአማራ ስሜት እንደሌለኝ ለማድረግ መሞከር ነው” ሲል አወገዘው።
የሞገሰ አባባል ቢገባኝም “የመጎስ ተቃውሞ ፍጹም መባል ያልነበረበት፤ በሌላ መንገድ መግለጽ እንደነበረበት ብመኝም ፤
ጋዜጠኛው የሰነበተበትን እና ያደመጠውን የአማራዎችን አሰቃቂ እሮሮ (ሕሊናውን ትራማታይዝ እያደረገው) ድቅን እያለ ሲረብሸው ያለመረዳቱና
ነጥብ ለማስቆጠር እንደሆነ መተርጎሙ ይገርማል።
እንደውም እንደታዘብኩት ከሆነ ተስፋዬ ተጎሳቁሏል። የሳይኪያትሪስት ሐኪም በማያት “ከቱራማው” ለመራቅ እንዲረዳው ሕክምና ማድርግ አለበት የሚል ሃሳብ አለኝ። ሞገስ ይህንን እረዳዋለሁ ብሎ ቢልም “ልቅሶህ የአድማጭ ሐዘኔታ ፍለጋ ነው” በሚል “ቀፋፊ” ቃል መጠቀሙ አግባብ አይደለ።
ክርክራቸው እየተጋጋለ ሲሄድ ጋዜጠኛ ተስፋየ “አራጆቹ እያለ ሲናገር” ሞገስ << እኔ ሰው ለመታረዱ አላውቅም! እኔ አራጆች ብየ አልጠራቸውም፡ ያውም ማን እያረደ እንደሆነ በማናውቅበት ሁኔታ አራጆች የሚለው የአማርኛ ቋንቋ ባንጠቀም ጥሩ ነው>> (ሞገስ ተሾመ)
ጋዜጠኛ ተስፋየ ደግሞ “አራጆች ካላልናቸው ምን ብለን እንጥራቸው? ስም ስጣቸውና እንሰማው፡ ብሎ ሲጠይቀው ከመጎስ መልስ ሲያጣ <<አራጆችን “ሐኪሞች” እንበላቸው?>> ሲል ተስፋየ በድጋሚ መጎስን ቅርቃር ውስጥ አስገባው።
ውይይቱ “አማራ የሕልውና አደጋ ተጋርጦበታል” በሚለው ላይ ደግሞ “ጋዜጠኛ ተስፈየ ተሰማ እና የሕግ ባለሞያው ሞገስ ተሾመ” የሕልውና አደጋ መኖሩን ሁለቱም ቢስማሙም የሕልውና አደጋው ላይ ዝርዝር ሲገቡ ሞገስ ልዩነት አሳየ፤ እንዲህ ይላል በጥቅሉ
“ አዎ አማራ አደጋ ላይ ነው። ግን የሕልውና አደጋ አለው ስንል አጥቂዎቹ አማራን በሙሉ በያለበት እየሄዱ ያጠፉታል ማለት አይደለም። ያ ከሆነ አማራው ብቻው ሳይሆን የሚጠፋው “ምቹዋል መጠፋፋት” የጋራ መጠፋፋት ነው የሚሆነው፤ አንድ የተወሰነ ቦታ ብቻ ሊያጠቁት /ሊያጠፉት/ ይችሉ ይሆናል እንጂ ከምድረገጽ ሊጠፋ አይችልም..” ሲል
ጋዜጠኛ ተስፋዬ ደግሞ ወለጋም፤ አርሲም፤ ደብረዘይትም፤ ባሌም፤ ሐረርም……ወዘተ እየለ ይቀጥልና “አራጆቹ አቅም ካገኙ” አማራ አለበት በሚባልበት ምድር ሁሉ በመሄድ ያጠፉታል። “ሂትለር” እቅም ባከማቸ ወቅት እስከ አውስትርያ፤ ሆላንድ ፤ መላው ኣውሮጳ ወዘተ… ተሻግሮ “ይሁዲዎችን” ጭፍጭፏል። አማርም አራጆቹ አቅም ሲያገኙ ከምድረገጽ ከማጥፋት አይመለሱም። ስለዚህ የሕልውና አደጋው ከፍተኛ ነው።>> ስል መልስ ሰጠ።
መጎስ ደግሞ አማራውን ሲጨፈጨፍት መነሸውን ካላወቅን እና ካልነገሩን መላውን አማራ ያጠፋታል ማለት አንችልም። ይላል መጎስ። ተስፋዬ ደግሞ ምክንያታቸውን ለማወቅ ከነገሩኝ ምክንያት ሌላ ቁፋሮ ውስጥ አልገባም ፤ ምክንያታቸው “አማራ ነህ” ብለው ስለገደሉኝ “አማራ በመሆኔ ብቻ ስለገደሉኝ” ምክንያታቸው “ኣማራ በመሆኔ ነው”። ከዚህ ሌላ ምን ምክንያት እጠብቃለሁ።ይላል ጋዜጠኛ ተስፋዬ ተሰማ።
በማከታተል፤ አሁን ያለው መከላከያ የአገር መከላከያ ነው ወይስ የአንድ ነገድ መገልገያ ነው? የሚል ክርክር ገቡ። ሞገስ ደግሞ እንዲህ ይላል አጣቃላይ ማጠንጠኛው ንግግሩ << ፖለቲካው መካለከያውን ስላበላሸው እንጂ የኢትዮጵያ መከላከያ ነው።>> ሲል ጋዜጠኛ ተስፋዬ ደግሞ’ በጥቅሉ ሲገለጽ <<በኦሮሞ ጀኔራሎች እና አገር መሪዎች የሚታዘዝ ኦሮሙማ ለተባለው ሃይል አገልጋይ ነው እንጂ አገራዊ አይደለም። በተለይ ኦሮሞ ልዩ ሃይሉ አገር መከላከያው አገራዊ ቢሆን ኖሮ አማራን ባገኘው ዕደል ሁሉ በድሮን እና አይሮፕላን እየጨፈጨፈ፤ አራጆችን ብረት እያቀበለ እየተባበረ አይቶ አንዳላየ ከጸረ አማራዎች ጋር የቆመ እና በቀርቡም “የወንድ ብልት የቆረጠ”፤ ትግሬን የጨፈጨፈ አማራዎችን እየጨፈጨፈ ያለ የኦሮሙማ እንጂ ኢትዮጵያ መከላከያ ነው ማለት አልችልም። ሲል ተስፋዬ መጎስን ሞግቶታል።
ከዚህ በማያያዝ የ16 አመት ወጣት የሆነ ጎጃም ውስጥ መከላከያው ብልቱን ስለ ቆረጠው ወጣት ወላጅ እናቱ እንደተናገሩ አድመጠናል (ፋይሉን ሴቭ ባላደርገውም በጀሮየ ሲናገሩ ሰምቻለሁ)። ይህንን ተስፋየ በመናገሩ መጎስ በማስከተል <<፡“መከላከያ ብልት መቁረጡን ማስረጃ የለም”>> ሲል ሞገስ መልስ ሰጥቷል።
በሚገርም ሁኔታ ሞገስ <<“ማስረጃ የለም” ማለቱ ሳይበቃ “መከላከያ ብልት ይቆርጣል” ማለት አንድን ሕብረተሰብ ብልት ቆራጭ ነው ብሎ የማለት ያክል ነው። መጠንቀቅ አለብን።>> ሲል ሲመጻደቅ ሰማን። ብልት መቁረጥ ባሕል እንደነበረና እስካሁን ድረስም ብልታቸው እየተቆረጡ እንዳሉና ከዚያም አልፎ አማራዎች አየታረዱ ደማቸው እየተጠጣ ስጋቸው እየተበላ ዜናዎች እንደተዘገቡ አልሰማም ማለት ነው? ኦሮሞ ክልል ፕረዚዳንቱ “ሺመለስ አብዲሳ” እንኳ መስክራል፤”ሸኔ ዮሞተን የወንድ ሬሳ የሚደፍር ግብረ ሰዶማዊ ነው፤ የሰው ስጋ ይበላል” ሲል ተረናግሯል። ይህ ተደጋጋሞ እየተከሰተ ያለ ከስተት ካሁን በፊትም በኦሮሞ ማሕበረሰብ ባሕል ውስጥ ‘ብልት ቆረጣ’ የሚያኮራና ተቀባይነት “እንደነበረው” ሞገስ ተሾመ በዘው ማሕበረሰብ እንደማይታወቅ ለምን ሊክደን ፈለገ?
ጉምዝ ውስጥ “ሙርሌ” የተባሉት ነገዶች “ቀይ” ብለው የሚጠርዋቸው (አማራዎችን) እያረዱ እንደሚበሉና ባሕላቸው እንደሆነ እናውቃለን፡ አደለም እንዴ?
ያ እንዳይበቃው ሞገስ ተሾመ የሚከተሉት ነጥቦች ይዞ ሲከራከር ነበር፡
1) አምሓራን እየጨፈጨፈ ያለው ተጠያቂ ቡድን ማን መሆኑን እስካሁን ድረስ አይታወቅም” ሲል ሰምቼው ገረመኝ።
አምሐራን በፕሮግራም ነድፎ ስም አውጥቶውለት ጭፍጨፋ ሲያካሂዱ የነበሩት የፖለቲካ ቡድደኖች አንተ ባታውቃቸውም “አዎ!”
እኛ እናውቃቸዋለን።
አራጅ አለ፤ ታራጅ አለ። ከሳሽ አለ፤ተከሳሽ አለ። “ከሳሽ” የአምሐራ ሕዝብ ሲሆን ተከሳሽ ደግሞ የሚከተሉት ናቸው።
1)“በነ ሌንጮ እና ዳውድ እንዲሁም ጃል ማሮ እና አብይ አሕመድ እያገዙት የሚመሩት የረዢም ዕድሜ ያስቆጠረ የኦነግ
ቡድን” ፤
(2) “የህወሓት መሪዎች”
(3) አርቲፊሻል ወያኔዎች “የኦፒዲኦ መሪዎች”
(4) ዛሬ ሥልጣን ላይ ያለው “ስሙን የቀየረው የአኖሌው የጥላቻ ሃውልት መሰረተ ድንጋይ አኗሪ “አብይ አሕመድ”
የሚመራው የድሮው ኦፒዲኦ የዛሬው “ብልጽግና መንግሥት”
(5) ደቡብ ክልል ሲመራው የነበረው “የሺፈራው ሽጉጤ” ቡድንና ፖሊሶቹ።
(6)”ኽዋረጅ” የተባለ የጅማ ኦርቶዶክስ ቀሳወስትና ምዕመናን ሲያርድ የበረው እስላማዊ አክራሪ ሃይል፤
ከአንድ እስከ ስድስት ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ቡድኖችና ፓርቲዎች እንዲሁም ግለሰቦች ለአማራ ዘር ማጥፋት፤መፈናቀል፤ድህነት፤ ለበረንዳ አዳሪነት እና አማራዎች ለመታረዳቸው “ቀንደኛ ተጠያቂዎች” እነዚህ ናቸው።
በእነዚህ ድርጅቶች ውስጥ በስም የታወቁ (ሰለባዎች የሚጠቅሳቸው) የመንግሥት ወታደሮች (ፖሊሶችና ልዩ ሃይሎች)፤ ከንቲባዎች፤ ሚኒሰትሮች የፓርላማ አባሎች፤ የክልል መሪዎች እና ግለሰቦች ሲካተቱ፤ አብረውም በውጭ አገሮች የሚኖሩ ከአምሐራ እና ከክርስትያን ኦርቶዶከክስ ቤተ ጸሎት እንዲሁም የአምሓራዎች እስላም መስጊዶች እንዳትጋቡና እንዳትጸልዩ፤ እንዳትገበያዩ በማለት ከዘር አጽጂው ቡድን ጋር የተቀናጁ፤በስም የሚታወቁ የዜና ማዕከሎች ግለሰቦችና የፖለቲካ ተዋናዮች የተጠያቂዎች ናቸው። እያልን ሞገስን በእርግጠኛነት እሞግተዋለሁ።
እነዚህ በራሳቸው ፕሮግራምም ሆነ በሕዝባዊ ይፋ ቅስቀሳ አምሐራን ለማጥፋት ፕሮግራም ነድፈው አምሓራን ልዩ የመለያ ኮድ ስም ሰጥተው እየጨፈጨፉ (ሞገስ “ሸሽጉት” እያለን ያለው የጭፍጨፋ ቃል ልጠቀምና <<እያረዱ>>) ያሉ ቡድኖችና ግለሰቦች አይታወቁም ማለት “ፌዝ” ነው።
ለመሆኑ በአምሐራ ላይ የዘር ማጽዳት የመጀመሪያ ተሞክሮ የት እና መቸ ነበር?
ብዙ ሰዎች ሐረርጌ ውስጥ ነው ሲሉ እሰማለሁ። አይደለም።
አምሓራን በጅምላ መጨፍጨፍ የተጀመረው “አሶሳ”(በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ላይ የምትገኝ ከተማ) ውስጥ ነው።በፈረንጅ ዘመን
አቆጣጠር በጃኒዋሪ 1990 (1982 በራሳችን ዘመን) መኮነን በተባለ የኤርትራ ሕዝባዊ ግምባር (ሻዕቢያ) የኮማንዶ መሪ
በሚመራቸው ተዋጊዎችና ጥቂት የሱዳን መኮንኖች እንዲሁም የኦሮሞ ነፃነት (ኦነግ) ግምባር በመቀናጀት ከሱዳን ዘልቀው ወደ አሶሳ
በመግባት። የአማርኛ ተናጋሪዎችን ከከተማዋ ለማጽዳት በሚል ዝግጅት አምሐራዎችን ጨፈጨፉዋቸው።
ጭፍጨፋው የተካሄደው ሁለት ቦታ ላይ ነው። ታሪኩ እንደዚህ ነው። ጎጃም ሰፈር እየተባለ ሲጠራ የነበሩት ኗሪዎች ለስብሰባ ትፈለጋላችሁ ተብለው በተጋበዙበት አዳራሽ እንደገቡ መዝጊያው የኋሊት እንዲቆለፍባቸው ተደርጎ “ነዳጅ ተርክፍክፎ” ስፍር ቁጥር የሌላቸው አምሓራዎች በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ ተደርጓል። ሻዕቢያም ስለ ጥምር ዘመቻው በራዲዮኑ ተናገሮታል። የትግርኛ ዜናውም አለኝ።
ኪዚህ ባሻገር ኮለኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ስለ አሶሳው ጭፍጨፋ በወቅቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በቴ/ቪ የሚከተለውን ንግግር አድርገው ነበር፡ (የድምጽ ቅጁ እኔ ጋር ይገኛል)
ልጥቀስ፦
<<የተከፈተብንን ጦርነት እንዳለ ሆኖ፤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የኢትዮጵያን አንድነት ጸር የሆኑት ቡድኖች ከጎረቤት አገር አስታክክው በመግባት ከፍተኛ የውግያ ድጋፍ ተሰጥቶአቸው፤ በምዕራብ ኢትዮጵያ በኩል በተለይ አሶሳ ላይ አያሌ ንጹሃን ዜጎች በግፍ ተጨፍጭፈዋል።የሕዝብ የልማት አውታሮች የሆኑ የሐገር ንብረቶች ተዘርፈው ወደ ጎረቤት ሃገር ተወስደዋል።የተቀሩትም እንዲወድሙ፤ እንዲፈርሱና እንዲቃጠሉ ተደርገዋል። ከሁሉም፤ ከሁሉም የሚያሳዝነው ደግሞ ብዛታቸው ወደ 200 የሚሆኑ ሕሙማን ሳይቀሩ “የእገሌ ማሕበረሰብ አባላት ናቸው” በሚል ብቻ ተለይተው “ቤት ተዘግቶባቸው” በጥይት ተቆልተዋል ፤ በእሳት ጋይተዋል። በወቅቱም ተጨማሪ ጥቃት ላለመድረስ ሲባል ተገቢውን እርምጃ ተወስዷል። ይህንና በሌሎች ግምባሮች የከፈቱብንን ጦርነቶች በመቋቋም ላይ እያለን ‘ሻዕቢያ” ነኝ ባዩ ፤ ያለው የሌለው ሃይሉን በማሰባሰብ ፤ የሰሜኑን አገራችን ጎሮሮ የሆነው በምፅዋ በኩል በማስሰለፍ ሌላ የጥቃት በር ከፈቶብናል፡….>> (መንግሥቱ ኃይለማርያም)
ስለዚህም አማራን በማረድ ዝንተ ዕለት ሥራቸው ያደረጉ “አራጆች” በመጎስ ካላወቃቸው ማንነታቸውን መለየት አንችላልን፡ እናውቀዋቸዋለን።
እንዲህ ዓይነቱ እልቂት 1983 ወያኔ መንግሥትነቱን ከተቆጣጠረ በኋላም የጅምላ ጭፍጨፋው የተለመደ ሆነ። ወዲያውኑ የኢትዮጵያን ካርታ ቀይሮ ወደ 14 ብሔሮች፤ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በሚል 14 የውስጥ ድምበር ያላቸው “ጥቃቅን አገሮችን” መሠረተ። በቋንቋ "የተከለሉ በነዚህ ድንበሮች" ውስጥ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ አማራዎች ላይ በተጠቀሱት ቡድኖች መዋከብ ተጀመረ። ከዚያም በሺዎች የሚቆጠሩ አማርኛ ተናጋሪ እና ክርስቲያኖች ጅምላዊ መበራርና ጭፍጨፋ የዘወትር ትዕይንት ሆነ።
አድራጊዎችም በወያኔ አይዞህ ባይነት ያው ከአሶሳ ዕልቂት ጀምሮ ሲሳተፉ የነበሩት በእነ “ሌንጮ ለታ እና ዶ/ር ዲማ ነገዎ” የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግምባር መሪዎችና አባሎችና ደጋፊዎቻቸው ናቸው። ሰዎቹ ያኔ በዘመነ ወያኔ ጭፍጨፋ ሲፈጽሙ “ተቀምጠውበት በነበሩበት ፓርላማ” ዛሬም በሚገርም ክስተት ተመልሰው በዘመነ “አብይ አሕመድ ፓርላማ” አዳራሹን ተቆጣጥረውት የጭፍጨፋ ወንጀላቸውን እያካሄዱ ናቸው። እነ ገዱ አንዳርጋቸው፤ እነ ክርስትያን ታደለ እነ ዶ/ር ጫኔ እነ ቧ ያለው ወዘተ ንግግር ሲያደርጉ እየታፈኑና ሲያሾፉባቸው የምናያቸውና የምናደምጣቸው ያው የአራጁ ቡድን ተቧዳኝ አባልት ስለሆኑ እንኳን እኛ የፓርላማው አባል “ኦነጉ” ዶ/ር አንጋሳ ኢብራሂም” እንኳ ሳይሸማቀቅ <<እኔ ነገ ብሞት ይህችን ምስጢር ይዤ እንዳልሞት’ ሳልናገር ብሞት ስለሚቆጨን አራጁ ቡድን ምንግሥት እንደሆነና ሽመልስ አብዲሳም ግምባር ቀደም አሳራጅ እንደሆነ ነግሮናል። (ሻሸመኔ ከተማ አማራ እየተለየ ንብረቱ ሲቃጠል የከተማው ከንቲባ ለሺመልስ አብዲሳ ሥልክ ደውሎ ዕርዳታ ሲጠይቅ <<አያገባህም አርፈህ ተኛ>> እንዳለው መጎስ ተሾመ አልሰማሁም ሊል ነው? አራጆችና ተባባሪዎቻቸው እነማን መሆናቸው ብግልጽ ይታወቃሉ።
አብይ አሕመድም እኮ
ልክ እንደ ሞገስ ተሾመ “ሽብርተኞቹ እነማን መሆናቸውን በእርግጣኛነት እገሌ ነው ብሎ ለመለየት ያስቸግራል” ብሏል። አብይ
እንዲያ ሲል “እራሱ አብይ አሕመድ በምስጢር አሸባሪዎችን በልዩ ሃይሎቹ በኩል መሣርያ እያቀበለ በገንዘብም እንዲንበሻበሹበት
25 ባንኮችን በዓለም ታሪክ ተደርጎ የማያውቅ ፤ በአንድ ወር ውስጥ እንዲዘረፉ በማድረግ፤ በግብረ ሽበራው ሥራ እየተካፈለ
መሆኑን ስለሚያውቅ እኔ መሆኔን አለወቃችሁኝም”>>
ለማለት ነው፡ ‘አራጆቹ አይታወቁም’ ሲል የነገረን እንጂ ፤ ሰለባዎቹ ግን አራጆቻቻው እነማን መሆናቸው በየቃለ መጠይቃቸው
ብግልጽ ነግረውናል። ሰለባዎቹ የሚሉት እኛን ያረደንና ያፈናቀለን ንብረታችንን የዘረፈን “መከላከያው፤ ልዩ ሃይሉ፤ኦነግ ሸኔው
እና አገሬው” ነው ሲሉ በቃለ መጠይቅ ነግረውናል።
ከባሌ ከአባገዳዎች፤የሃይማኖት መሪዎች፤ከቄሮዎችና ከአገር ሽማግሌዎች የተላለፈው የሞት አዋጅ ታስታውሳላችሁ?
የአቋም መግለጫ የተባለ በገበያ የተነበበ “ነፍጠኛ እና ዶርዜ” ብለው በሚጠርዋቸው ዜጎች ላይ የታወጀው የጭፍጨፋና ንብረትን የመዝረፍ፤ወፍጮ እንዳያስፈጩ የሚያግድ የግድያ አዋጅ በቪዲዮ የተደገፈ፤ ምስላቸው የሚታይ ገበያ ላይ ወጥተው ሕዝብ ሰብስበው አዋጁን ሲያነብቡት እነማን እንዳወጁት “የሕግ አዋቂው” ሞገስ ባያውቀውም እኛ እናውቃቸዋለን። ይህ የባሌ የጭፍጨፋ አዋጅ የታወጀበትም ምክንያት ለዘነጋችሁ ሰዎች ላስታውሳችሁ
ጥቂት ልጥቀስ
እንዲህ ይላል፡
<<ዛሬ
ይህን ሰልፍና አዋጅ ያወጣነው ጅግናችን የቄሮ አባት የሆነው አቶ ጃዋር መሐመድ ላይ በጠላት የመገደል ሙከራ ስለተደረገበት
ደምፅ ሆነን ነው። ጃዋርን የሚቃወም መቸም ቢሆን የባሌ ሕዝብ ጠላት ነው።>>
የሚል ነበር የሞት አዋጁ የመነሻው ምክንያተቸው። ጃዋር በእርሱ ምክንያት ለታረደ ሕዝብ ይቅርታ ይጠይቅና ሓዘን ይሰማው እንደሆነ ሲጠየቅ” “እልጠይቅም” ነው ያለው። ስለዚህ እነ ማን መሆናቸውና በምን ምክንያት አማራውን እንደሚያርዱት መጎስ ባያውቅም “ነፍጠኛ” እያሉ የሚጠርዋቸው አማራዎችና “ዶርዜ” ብለው የሚጠርዋቸው ጋሞዎችም አራጆቻቸውና ለመታረዳቸውም ምክንያት “አማራ እና ጋሞዎች በመሆናቸው ብቻ” እንደታረዱ ያውቃሉ። ሌላ የሕግ ፍልስፍና መራቀቅ ውስጥ መግባት አያስፈልግም።
ኦሮሚያ ተብሎ ያልነበረ ካርታ ተቀይሶ አማራዎች ሲዋከቡ ወያኔ ከላይ ሆኖ አምስቱ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች OLF, Islamic
Oromiya Liberation Front (ILFO), Oromo People's Unity Organization (OPUO),
Oromo Abo Liberation00 Movement.
የዘር ማጽዳት እና ጥቃት በመፈጸም የቀን ተቀን ሥራቸው እንደነበርና ዛሬም እየቀጠለ መሆኑን አራጆች በመሪዎቻቸው
ስምና በድርጅታቸው መለያ ስም እነማን እንደሆኑ እናውቃቸዋለን።
ከላይ የተጠቀሱት ድርጅቶችና መሪዎች በፕሮግራማቸው ኢትዮጵያ “የአምሐራና የኦርቶዶክስ ስሪት” ነች ብለው ስለሚያምኑ፤ “አምሓራን
ማጥፋት” የሚል ንድፍ ነድፈው አምሐራን ቅኝ ገዚኛና “ነፍጠኛ” የሚል “ኮድ” መለያ በመስጠት በሐሰት ተንቀሰቅሰዋል። ስለዚህ
ሓላፊነት የሚወስዱ በስምና በድርጅታቸው የሚታወቁ ስለሆኑ ወንጀለኞችን እንደመደበቅ ተደርጎ እንዳይታይ ታሪክን ግራ ላለማጋባት
ጥንቃቄ እናድርግ።
ጌታቸው ረዳ