Thursday, June 20, 2024

በአብይ አሕመድ ተበባሪነት በሂደት ላይ ያለው ትግራይን የመገንጠል ስልታዊ ስምምነትና የወንጀል ድርጊቶች ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 6/20/24

 አብይ አሕመድ ተበባሪነት በሂደት ላይ ያለው ትግራይን  የመገንጠል ስልታዊ ስምምነትና የወንጀል ድርጊቶች

ታቸው ረዳ Ethiopian Semay

6/20/24

ትግራይ ዛሬ ሕጋዊ የአገርነት ካባ ያልለበሰች  (a defunct secessionist state የሆነች) ግን ተገንጣይ ግዛትነትዋን ሕጋዊ ለማድረግ በደፈጣ እና በግሃድ እየሰራች ያለች አካባቢ ነች፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው ግን በአብይ አሕመድ እውቅና ነው፡፡

የኢትዮጵያ አካል ነች የሚያስብላት ምልክቶች ሁሉ ክምድርዋ አሰወግዳ የትግራይ ሪፑብሊክ የሚያስብላትን የራሰዋ ምልክቶችና ተቅዋሞች ተክታ እያየን ነው፡፡

ሕዝቡ በአካልም በሕሊናም ሁለት ጊዜ ተገንጥሏል፡፡ የገጠሩ 90% 1970-1983 (13 አመት) ከዚያም 1983 አገር ለመበዝበዝ መንገድ የከፈተላቸው ንግሥናቸው እውን ከሆነ ወዲህ አካላዊውን ግንጠላ በይደር አቆይተው “የሕሊና (አእምሮአዊ)” ግንጠላቸውን ግን እንደተጠበቀ ህያው በማድረግ ትግራይን አገር የሚያሰብላትን መዋቅሮችን ለ27 አመት በወኪልዋ በኩል ሰትገነባና ሰታግበሰበስ ቆይታ ንግሥናዋ ሲያበቃ፤ ወደ ሪፑበሊካዊነትዋ ምስረታ ለመግባት ጦርነት ከፈተችና ከሞላ ጎደል <<አካላዊና መንፈሳዊውን>> ሂደት በግምት ¾ኛውን የግንጠላውን ሂደት ሰታካሂድ የተቀረው መቶኛውንና ዋነኛውን የምጣ ክምችትዋ በጦርነት ሰለወደመባት፤ ያንን ለመገንባት <<ኢትዮጵያዊት መስላ> ከፖለቲካ አጋርዋ ከአብይ አሕመድ ጋር በመቀናጀት የገንዘብ ፤ የኔት፟፟ወርክ ፤ የአየር መንገድ ፤ የጭነትና የማመላለሻ መኪኖች፤ ነዳጅ ፤ የከፈተኛ ተቋማት ት/ቤቶች ሥራ ማሰክጃና የጤና አቅራቦት ፤ ፓስፖርትና ቪዛ .... የመሳሰሉ ያላቋረጠ ፍሰት እየሰጣት የገኛል፡፤

ድህነቱ ፤ ርሃቡ በሸታና እንዲሁም የከተማ ታጣቂ ዱርየዎች- ወንጀል በክፍለሃገሩ በመበራከቱ ጫና ቢኖሮውም፤ ያንን ለመወጣትም ከኤርትራኖቹ የተማሩት ጠባቂ የሌላት ወተትዋን እያለቡ ሰንደቃላማዋን ለማወለበለብ ከተጠየፉዋት ላሚትዋ ኢትዮጵያ የጠየቁትን እያገኙ ከጭም እንዲሁ በሚለገስላት እርዳታ ተጠቅማ በማጋገም ላይ ስትሆን አሁን የቀራት ወደብና የምርት ገበያ ግብይት የምትገበያይበት ከፖርት ሱዳን የንግድ ባለሃበቶችና የወደብ አስተዳደር ገዢዎችና የሱዳን መሪዎች በውስጥ ያደረገቺው የቆየ ውል በማስታወስ ወደ ውጭ የመውጫ በር የሚከፈተላትን መንገድ በማተኮር ላይ ነች፡፡

ይህንንም ለማሳካት ሥልጣን ላይ ሆና በነፍጥ የጠበቀቺው የወረረቺውን የጎንደር የወልቃይትና የወሎ የራያ መሬት እንደገና ለማግኘት በኦሮሙማው መሪ አብይ አሕመድ ፈቃጅነት ካልሆነም በነፈጥ ለመንጠቅ እየተንፏቀቀች ነው ፡፡

በርዕሰ ከተማችን አዲሰ አበባ ወሰጥ የሚኖሩ በሺዎቹ የሚቆጠሩ  የትግራይ ተወላጆች፤  ከባንዳዎቹ ኤርትራኖች የተማሩት ግንጠላውን እስኪያሳኩ ድረስ “ኢትዮጵያዊ መስሎ ኢትዮጵያን መበዝበዝ” <<አምሐራዊት” ፤ “የቆሰለች ጠላት” እና ‘’ፓየር”>> እያሉ በሚጠርዋት ኢትዮጵያ የምትሰጣቸውን ዕድል በመጠቀም እየበዘበዝዋት "ሃገርና" (አገራችን) ለሚልዋት ለምጻኢት አገራቸው ለሪፑብሊካዊት ትግራይ መከሰት በድብቅም በግሃድም እየሰሩ የገኛሉ፡፡

በዙ ማይም (በተለይ ኢትዮጵያዊው ምሁሩ ምሃይም) ይህንን ተንኮል አልገባውም፡፡እየሆነው ያለው እውነታ ብንነግረውም አይቀበለንም፡፡ ለምሳሌ ኤርትራኖች ኮሎኒ ከሚልዋት ምድር የኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ እየኖሩ “ኢትዮጵያውያን የተጨፈጨፉበትን ዓመት በኩራትና በከበሮ ሲጨፍሩ እያዩ፤ አንድም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ምሁርም ያልተማረም፤ ቅር ሳይለው ሳይቃወም አብሮ ሲጨፍርና የሚጨፍሩበት አዳራሽ ሲሰጣቸው ማየት እጅግ ያሳዘናልም ይገርማልም፡፡

ግንጠላ አቀንቃኝ ትግሬዎችም  አዲስ አበባ ውስጥም ሆነው መቀሌ  ሆነው ከነሱ ባልተናነሰ አገራችንን ሲዘልፉ እንሰማቸዋለን፡፡ ክነዚህ ሁለት ወገኖች በትግርኛ ቃለመጠየቅና ሕዝባዊ ስብሰባና በዘፈናቸው የሚሰነዘሩ መልዕክቶችና የሚውለበለቡ ምልክቶች ሕዝቡ ግንዛቤ እንዲኖሮው ተርጉመን ብናስነብበውም እንደ ትላንቱ ዛሬም “ወንድማማቾች ነን” የሚል የጠነዛው የፖለቲካ ማይምነታቸው እቦታው ላይ ስለሆነ “ምጽዋና ትግራይ የተሰውት የኢትዮጵያ ጀግኖች የሙታን አጥንት ቢጮህም ሰሚ አጥቶ እነሆ 33 አመት ሆኖታል፡፡

በጠቅላላ ኢትዮጵያ ጠንካራ አገር ውዳድ መሪ ስላጣች የሱማልያ አከራሪ ሰደተኞች፤ የደቡብ ሱዳን አከራሪዎች፤ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየዶለቱ ካሉ  ፖለቲካቸውን ሚያራመዱ ወያኔዎችና ኦነጎች፤  አረቦች፤ ተልእኮ ያላቸው ኤርትራኖች፤ የናይጀሪያ አጭበርባሪ ሌቦች ፤ የሃይማኖት አጭበረባሪ ወንጀለኞች ፤ ሰው አርደው ለስይጣን አመልኮ የሚሰው ኢሉሙናቲ አምላኪዎች ፤የውሻና ያህያ ሥጋ አርደው ሰውን የሚያሳስቱ አጭበረባሪዎች የሚርመጠመጡባት የሚያካሂዱባት የተኮላሸች አገር ሆናለች “አዲሰ አበባም እንዲሁ”፡፡ 

 ትኩረቴ የኔ ዘመዶች በሆኑት ትግሬዎች ላይ ነው፡፡ እያካሄዱት ያሉት ዋና ትኩረታቸው ብታምኑኝም ባታምኑኝም በመገንጠል ላይ ነው፡፡ መገንጠል ማለት “የፖለቲካ ፍቺ” ነው። (political divorce) ፤ ፍቺው ለማሳካት ግን ዘርፈው ያከማቹት ሃገራዊ ንብረትና ኢንዱስትሪ በጥጋባቸው ጦርነት ከፍተው  ሰለወደመባቸው አካላዊውና ፖለቲካዊ ግንጠላቸውን ወዲያወኑ ለመፈጸም አሰቸጋሪ ስለሆነባቸው  “አድብቶ መገንባትና መገንጠል” የኤርትራኖችን መንገድ በመከተል ላይ ናቸው፡፡ መሽሺያቸውም፤ ዱለታ የሚያካሂዱበትም ፤መበዝበዢያቸውም አዲስ አበባና መቀሌ አድርገዋል፡፡

ቅድመ ጦርነቱ በ27 አመት ሥልጣን ወስጥ እያሉ ቢፈልጉ ኖሮ ለምን ግንጠላ አያካሂዱም ነበር? የሚሉ ሞጓቾች ገጥመውኛል፡፡  ያን ያላደረጉበት መክንያት ለግንጠላ የሚያመች መሠረተ ድንጋይ ይጥሉ ስለነበር ነው፡፡ ለዚህም ማስረጃ ሥልጣን ከተነጠቁ ሥብሐት ነጋ እንደነገረን በየመንደራችን እንበታተናለን”  እንዳለው መሰሶ በማቆም ላይ ነበሩ፡የጦረነቱ ሽፋንም ያ ነበር፡፡

ትግራይ ሪፑበሊክን ለመመስረት ሲያደርጉ የነበሩዋቸው ግንባታዎች የሚከተሉት ነበሩ፡፡

ሥልጣን ላይ እንዳሉ አገር ለመመሥረት የሚያስችላቸው የልማት አውታሮች \ታሕታይና ልዕለ መዋቅሮች  በሰውም በተቁዋምም ግንባታው/ ምን የገነቡ እንደነበር ለማታወቁ አንባቢዎች ለግንዛቤ ቢረዳችሁ እነሆ ታደግ ከሚባለው የወዳጄ ከክቡር አቶ ተከሌ የሻው ከጦርነቱ (ከ10 አመት በፊት) (2003) (2011) የታተመ መጽሐፍ ዋቢ አድርጌ ላቅርብ፡፡ እየቆራረጠኩና እያሳጠርኩ እያከልኩበትም ሰለጠቀስኩ ስሕተቶች በሙሉ የኔ እንጂ የደራሲው አይደሉም፡፡ 

ልጠቅስና ለደምድም፡፡

‘’....የድርጅቱ ስም አለመለወጡ በራሱ የሚነግረን የመገንጠል ዓላማው ያለመተው ነው፡፡ ሰልሆነም የመገንጠል ዓላማ በሰከነ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ከስሙ ባሻገር የመገንጠል ዓላማው ቁሳዊና ሕሊናዊ መሰረቶችን በጣምራና በሰፋ መልኩ በሰከነ ሁኔታ እየተራመደ መሆኑ የሚያመላክቱ ጉልህ ማስረጃዎች አሉ፡፡

ለዚህም ወያኔ ትግራይ ወስጥ የመሰረታቸው ኢንዱስትሪዎች ማሕበራዊ አገልገለቶች፤መሰረተ ልማቶች፤ ለወደፊቱ ለምትገነጠለው ትግራይ እራስዋን ከመቻል አልፋ ቀሪዎቹን የኢትዮጵያ ክፍሎች ጥገኞች ለማድረግ በሚችል መልኩ መገንባታቸው ነው፡፡

 “ኤፈርት” እና “ትልማ” በተሰኙ ድርጀቶች ባለቤትነት ስም ወያ ክ76 በላይ የኢንዱስትሪ ፤የእርሻ፤ የማዓድን፤ ማከፋፈያ የግንባታ፤ የትራንስፖርት፤ የኅትመት ማሰታወቂያ... ወዘተ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ሕዝብ ሃብት እውቀትና ጉልበት ገንብቷል፡፡

“ልማት ቅድሚያ በጦርነት ለተጎዱ ክልሎች” የሚል አንቀጽ በሽግግር መንግሥቱ ቻርተር አሰገብቶከአመስት አመት በላይ የአገሪቱን በጀት ዐይን ባወጣና ማን አለበኝ በሚል መንፈስ ለትግራይ ሁሉ አቀፍ ልማት እንዲውል አድርል፡፡

ይህንን አሳዛኝ ድርጊት የታዘበ የብዕር ሰው በአዲሰ ዘመን ጋዜጣ “በአድማስ ባሻገር ዐምድ” የግጥሞቹ ስንኞች የመጀመሪያ ፊደሎች ቁልቁል ሲነበቡ፤ “ትግራይ እስክትለማ ሌላው አገር  ይድማ”  በማለት እውነቱን ከፍተኛ ጥበብ በተላበሰ አገላለጽ ለሕዝብ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ አዎ! ሌሎቹ እየደሙ ነው!! ማንም ኢትዮጵያዊ በቅጡ እንደሚያውቀው በ17 የአበዮት አመታት ጦርነት ያልተካሄደበት የኢትዮጵያ አካል የለም፡፡ የትግራይ ክልል ከሌሎች የሚለየው ቢኖር ጦርነቱ ከወያ ጋር ሰለነበር ወያ ብሶትን በማባባስ ደጋፊ ለማግኘት የመንግሥት ኢኮኖሚ ልማት ለማድቀቅና ለማዳከም ብሎም የውጭውን ዓለም ትኩረት ለመሳብ ሲል ድልድዮችን ፤ ትምሕርት ቤቶችን ሆስፒታሎችን ሆን ብሎ ማፈረስና ባንኮችን የሕዝባዊ ድርጅቶችን ንብረት መዝረፉ የታወቃል፡፡ 

ከዚህ ውጭ በመላ አገሪቱ በደቡብ ፤ በምሥራቅ ፤ ከሶማሊያ ፤ ከሲዳማ ነፃ አወጭ ፤ በወለጋ ፤ በመሃል አገር ከኢሕአፓ ፤ ከኢዲዩ ፤ በምዕራብ ፤ በጎጃም ... ወዘተ ቁሳዊና ልቦናዊ ጉዳት ያሰከተለ ጦርነት መካሄዱ የታወቃል፡፡ “ክርስቶስ ለስጋው አደላ” ሆነና ወያኔም ነፃ አወጣሃለሁ ላለው ወገኑ ብዙዎቹ ሆን ብሎ ራሱ ላወደመው ከልል፤ የልማቱን ቅድሚያ ለትግራይ ሰጠ፡፡

ግድቦች፤መንገዶች ታላላቅ የአይሮፕላን ማረፊያ ጣቢያዎችን ገንብቷል፤

(አንዱ የአከሱም አይሮፐላን ማረፊያ የሆነው እራሱ ወያኔ ጦርነቱን ካስጀመረ በላ ሆን ብሎ በግሪደር አፈራረሶ ወደ በረሃ ሲያፈገፍግ ፤ በዚሀ ወር ግን እንደገና ታድሶ ለሥራ መዘጋጀቱ ተደስታ የገለጠቺሊኝ እህቴ ስትነግረኝ (ደሰታዋ ቢገባኝና ተገቢ ቢሆንም መልስ ባልሰጣትም) ወያኔዎች ለመገንጠል ከሚዶሉቱባት በሃገሪቱ ገንዘብ የታደሰው ጣቢያ ነው፡፡ ጠያቂ የሌለው የወንጀላቸው ጥግ  ተመለክቱለኝ!!!)(በነገራችን ላይ ዛሬም አዲግራት ከተማ ስዩም መስፍን በሚል የሚጠራ አዲስ የአይሮፐላን ማረፊያ እየተሰራ ነው የባላል፡፡ ርሃብ አለ ይባላል፡ እየሰማን ያለነው ግን ለግንጠላው ቅድሚያ የሚሰጥ ግንባታ ይመስላል፡፡)

 በበዙ ወረዳዎች የወሊድ መታክሚያ ጣቢያዎች የከተማ ሆሰፒታሎች፤ የቴክኒክ ሞያ ማእከል ማሰለጠኛ፤ መቀሌ ከተማ ወሰጥ ከፍተኛ የሪፈራል ሆሰፒታል ወዘተ..።

ከዚህ ሁሉ በላይ  ለመጻኢት ሪፑበሊክ ትግራይ  የኢኮኖሚ መሰረት የጠነከረ እንዲሆን ከማድረግ በተጨማሪ ቀሪዎችን የኢትዮጵያ ከፍሎች ጥገኛ ለማድረግ የሚያስችልበት ታላላቅ ኤንዱስትሪዎች ገንብተዋል፡፡በአገሪቱ ወስጥ ተወጥነው በማደግ ላይ የነበሩትን የብረታብረት ኢንዱስትሪዎች የሚያጠፋና በብቸኝነት የብረታብረት ሥራ የሚሰራ “መስፍን ኢንጂነሪንግ” የተሰኘ  የብረታብረት ሥራ ይሰሩ የነበሩት ፋበሪካዎች ሁሉ ቅልሎ የሚሥራ በመሆኑ ቀደምቶቹ በፖለቲካ ጡንቻ ከሚታገዘው መስፍን ኢንጂነሪንግ ጋር መወዳደር ባለመቻላቸው ከገበያ ውጭ ሆነዋል፡፡

በወቱ ባገሪቱ ከፈተኛ ነው የሚባለው የግገል ጊቤ ይድሮ  ኤለክትሪክ ሃይል ግንባታ በማጓተት ትግራይ ወስጥ ለሚገነቡት ግንባታዎች በአስተማማኝና በብቸኝነት የይል ምንጭ ሊሆን የሚችልተኛ ይል የሚያመነጭ ይድሮ  ኤለክትሪክ ’ተከዜን በመገደብ ሰርቷል፡፡

በሁሉም የአገሪቱ ከፍሎች ሚዛናዊ  በሆነ መንገድ የተቋቋሙትን የጨርቃጨርቅ ፋበሪካዎችን (በባሕርዳር ፤ በአቃቂ ፤ በሞጆ ፤ በድሬዳዋ በአዋሳ  እና በኮምቦልቻ) በማቀጨጭ ከገበያ ፈጽሞ የሚያስወጣቸው “አልሜዳ” የተኘ ታላቅ የጨርቃጨርቅ ፋበሪካ ዓድዋ ውስጥ ተገንብቷል፡

ይህ ፋበሪካ ሌሎች ፋበሪካዎችን ከገበያ ውጭ በማስወጣቱ ተጨማሪ የአገሪቱ የመከላከያና የፖሊሰ ሠራዊት የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) የሚያመርትና የሚያከፋፍል በመሆኑ በቀጠተኛና በተዘዋዋሪ መንገድ የአገሪቱን በጀትና የሥራ ዕድል ለአንድ ክልል የሚያውል በመሆኑ በግልጽ ይታያል፡፡ ፋበሪካው ሌላ ሰራም አለው፡፡ በዚህ ፋበሪካ ከዓድዋ አወራጃ ተወላጅ ሴቶች በቀር የሌላ አወራጃ ተወላጆች ተቀጥረው ሊሰሩ አየፈቀድለትም፡፡ የወያኔ ዘረኛ ጎጠኛ ከሚያሰኘው ተገባርቱ መካከል አንዱ ይህ ነው፡፡

በአፈሪካ ከሚገኙት የሰሚንቶ ፋበሪካዎች በታላቅነቱም ሆነ በጥራት አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት የሙገር ሰሚንቶ ፋበሪካ ከገበያ ጭ ያደረገው ‘ሞሶቦ ስሚንቶ  ፋበሪካ የተሰኘ መቀሌ ላይ ተገንብቷል፡፡

26 ዓይነት መደሃኒቶችን የሚያመርት የመድሃኒት ፋብሪካ ዓዲግራት ውስጥ ተመሰርቷል፡፡ በትምሕርቱም ዘርፍ በርካታ አንደኛ  መለስተኛ ከፈተኛና 3 ያክል ዩኒቨርሲቲዎች ተከፈተዋል፡፡

ለምትገነጠለው የትግራይ ሪፑብሊክ የውጭ ግንኙነት ችግር እንዳይገጥማት ከጎንደር 5 ወረዳዎችና ከወሎ አንድ አወራጃ ወደ ትግራይ አካልሎ ከሱዳን ጋር ጉልህ የሚታይ ግንኙነትና ጉርብትና አለፎም አንዱን አንዱን መገባበዝና እና የሁመራና የገዳረፍ የግብይት የጸጥታ የጋራ ስብሰባ (ኮሚቲ መሰረተው) በማካሄድ  ፍቅር መስርተዋል (ሂደቱን ለማወቅ የ1968 ይህወሓትን መግለጫ ይመልከቱ ፤ ከዚያም ከገዳሪፍ ባለሥልጣናት ጋር ያደረጉዋቸው ስብሰባዎች አስታውሱ)፡፡

ዘመናዊ ኢንዳስትሪ እስትንፋሽ የሆነው የነዳጅ ዘይት አቅርቦት ችግር እንዳይገጠምውም የባቡር ሐዲድ ከሱዳን ወደ መቀሌ በመገንባት ላይ ያቀደውን ልብ ይለዋል፡፡

ዓዲግራት ላይ የነዳጅ ክምችት ማጠራቀሚያ “ዲፓ” ገንበቷል፡፡ (ታንከሩም ከጎንደር “ችቸላ” ተነቅሎ የተወሰደ ነው፡፡)

እነዚህና መሰል የወያ ድርጊቶች ተጠቃልለው ሲመዘኑ የወያ ፣መገንጠል ዓላማ በሰከነ መንገድ በጥበብ እየተራመደ እንደነበር መገንዘብ የሚገድ አይሆንም፡፡ የሕግ መንግሥቱ አንቀጽ (39) ንዑስ አንቀጽ (1) የተቀረጸው ለትግራይ ግንጠላ በተመቻቸ መንገድ መሆኑ የሚያሳይ እነሱም ዘወትር የሚጠቅሱት የግንጠላው ዓላማ ሕያውና ቀጣይነት እንዲኖሮው የሚማጐቱለት መሆኑን ነው፡፡

ከራሴም በመጨመር ያቀረበኩት የደራሲ አቶ ተከሌ የሻው ታደግ ከሚለው መጽሐፋቸው የተወሰደ፡፡

ይህ ነበረ በጦረነቱ ወቅት ወደመብን የሚሉት ለግንጠላ ሲዘጋጁበት የነበረው የኢኮኖሚ የጀረባ አጥንታቸው፡፡ ለዚህም ነው በድብቅና በገሃድ የወደመባቸው መልሰው ለመገንባት አሁንም እየተጡና ለግንጠላው የሚያመች ሕሊናዊና የግንጠላ ምልክቶች በፖለቲካውም ሆነ በሃይማኖት ትግራይ ምድር ወሰጥ ህያው ሆኖ እያየን ያለነው፡፡

በመጨረሻም

መገንጠሉስ ይሳካል ወይ? ለምትሉኝ፡ ማአከላዊውን በትረ መንግሥቱን የጨበጡት “መንትያ ጭንቅላቶች ባላቸው ዘንዶዎች” (Two headed Hydra ) እስከተመራ ድረስ ለግንጠላ ሂደት ሊመቻችላቸው የሚያስችል ‘አንዳንድ’ ሂደቶች ሊያሳኩ የችላሉ፡፡

ጌታቸው ረዳ