መንግሥት አልባዋ ኢትዮጵያ የምትገኝበት
የታሪክ አጣብቂኝ!
ይነጋል በላቸው
Ethiopian Semay
6/29/22
ዛሬ ሰኔ 21 ቀን 2014ዓ.ም
ከምሣ በኋላ ቢሮ ገብቼ አንዳንድ ድረ ገፆችንና የዩቲብ ቻናሎችን እመለከት ያዝኩ፡፡ ንዴት ብስጭቴን እንደምንም ተቆጣጥሬ የተወሰኑትን
ዝግጅቶች ከያይነቱ ተከታተልኩ - እንደምንጊዜውም ሁሉ፡፡ አንደኛውን ግን መጨረስ አልቻልኩምና ስለመንግሥት አልባዋ ሀገራችን የአሁንና
የወደፊት ዕጣ ፋንታ የተሰማኝን ልጫጭር ብዬ ብዕሬን ከወረቀቱ አዋደድኩ፡፡
ያ ለዚህ ማስታወሻየ መነሻ የሆነኝ
ጉዳይ ከሀገር ምሥረታ አኳያ ከዳዴም ያላለፈችው የትናንቷ ደቡብ ሱዳንም ወግ ደርሷት ኢትዮጵያን ወርራ 170 ኪሎ ሜትሮችን በመዝለቅ
የወርቅ ማዕድናችንን ተቆጣጥራ ወርቃችንን በግላጭ እያፈሰች የመገኘቷን መርዶ የሰማሁበት ዝግጅት ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ብቻውን ኢትዮጵያ
መንግሥት እንደሌላት በግልጽ የሚናገር አስደንጋጭ ክስተት ነው፡፡
ወዲያውኑ “ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን
አይነቀንቁ” የሚለው ነባር ብሂል ታወሰኝ - የጄኔራል ጃጋማ ኬሎን ሀገር፣ የፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴን ምድር አንድ እዚህ
ግባ የማይባል የሽፍታ ቡድን ሲወርረውና ሲቆጣጠረው ምን ዓይነት የታሪክ ምፀት ላይ እንምንገኝ ታዬኝና ቁጭቱን አልችለው አልኩ፡፡
የሚገርመው ደግሞ የአካባቢው ባለሥልጣን ደቡብ ሱዳን ወርራን የወርቅ ማውጫ የማዕድን ሥፍራችንን መቆጣጠሯን ለመንግሥት ቢያሳውቅም
መልስ አለማግኘቱ ነው፡፡ ነገሩ በዚያም ብቻ አላበቃም፤ መንግሥት ተብዬው የአቢይ ጎራ የሚሰጠው ማስተባበያ ሁሉ አንድም እውነት
የሌለበት በውሸት የታጨቀ ዕብለት መሆኑም በግልጽ ታይቷል፡፡ የተወረረው አካባቢ የብልጽግና የወረዳ ኃላፊ በተደጋጋሚ ችግሩን ቢያሳውቅም
በርሱ ስም በፋና በወጣ ማስተባበያ ካለሰውዬው ዕውቅና ፎቶውን በመጠቀም ምንም የደረሰ ችግር እንደሌለና የሚባለው የደቡብ ሱዳን
ወረራ ሀሰት እንደሆነ ቅንጣት ሳያፍሩ መግለጻቸው ነው፡፡ ምን ጣለብን ጎበዝ!
እነዚህ ሰዎች ጥቂት ጊዜ ከቆዩ
ግዴላችሁም ለፊጂና ለሲንጋፖርም ከኢትዮጵያ መሬት እየጎመደሉ ኑና ውሰዱ ሳይሏቸው አይቀርም፡፡ ጠያቂ ጠፍቶ እንጂ እነማሊም እነጊኒ
ቢሳውም መውሰድ ይችሉ ነበር፡፡ ሶማሊያና ጂቡቲማ ተለምነው እምቢ ብለው ይሆናል እንጂ እስካሁን ድረስ አዋሽ አርባ ድረስ በመጡ
ነበር፡፡ እንዲያው ግን ፈጣሪን ምን ብንበድለው ይሆን ይህን የመሰለ በላዔሰብ ሰውዬ የላከብን? ኧረ እንጸልይ ምዕመናን!!
በነገራችን ላይ ሀገራችንን በአንክሮ
ለተመለከተ ኢትዮጵያ ለብቻዋ የታወጀ የ3ኛ ዓለም ጦርነትን እያስተናገደች ያለች ሀገር ትመስላለች፡፡ የማኅበራዊ ሣይንስ ምሁሮቿ
በሙሉ የሰውን ደም እየመረመሩ ነገድን ከነገድ በማበላለጥ “ይህኛው ደም ገዢ ሊሆን፣ ያኛው ነገድ ግን ተገዢ ሊሆን ይገባል፤ አለበለዚያ
አንክቶ አንክቶ መጨረስ ነው” በሚል ምርምር ተጠምደዋል፡፡ የጦር ምሁሮቿ በሙሉ ጦርነት በመንደፍና በማቀድ ላይ ናቸው፡፡ አብዛኞቹ
ገበሬዎቿም ዶማና ሞፈር ቀምበር ሰቅለው ወደጦር ዐውድማ እየተመሙ ናቸው - “ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ” በሚል መፈክር ታጅበው
ለዚያውም፡፡
ወጣቶች በሙሉ አንድም በልዩ ልዩ
ሱስና በመጠጥ ተጠምደው ጊዜያቸውን በወርቃማ የተዝናኖት ፕሮግራም እያሳለፉ ነው ወይንም የጦር ልምምድ እያደረጉና ያደረጉትም በተለይ
ኦሮሙማዎቹ የወገኖቻቸውን በተለይም የአማራውን አንገት ሕጻን ዐዋቂ ሳይሉ ባገኙበት ቦታ እያረዱ ነው - ለዚህም ግዳጃቸው እንደወሮታ
ተቆጥሮላቸው በአዲስ አበባ ማለቴ በፊንፊኔ የተገኘ ባዶ ቦታ ሁሉ እየታደላቸው - ከባለሦስት መኝታ ቤት ኮንዶሚኒየም ምርቃት ጋር
ነው ታዲያ - መምነሽነሻቸውን በስፋት ቀጥለዋል፡፡ የዚህ ሁሉ ድል ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ ልትኮራ ይገባታል፡፡ የእያንዳንዱ
ክልልና መስተዳድር ዋና ሥራ ልማትና እንደሚባለው ብልጽግና ሳይሆን የሌት ከቀን ስብሰባው አጀንዳ “እነእንትናን እንዴት እናጥፋ?
ሕዝቦቻችንን እርስ በርስ አቃርነን ስናበቃ እነሱን በማፋጀት ሥልጣናችንን እንዴት እናራዝም?” የሚል ነው - “ሀኪም ቤት፣ ትምህርት ቤት፣ መንገድ፣ ጤና ኬላ፣ ወዘተ.
ለሕዝባችን እንገንባለት” የሚል ወሬ ዕርም ነው፤ ከጦርነት የሚተርፍን በጀት ባለሥልጣኖቹ ይንደላቀቁበት እንጂ ሰፊው ሕዝብማ አየሩንና ፀሐይዋንም በነፃ በማግኘቱ ዕድለኛ ነው፡፡ ኢትዮጵያ እኮ መጠናት ያለባት
ልዩ ሀገር ናት፤ ሕዝቧም አብሮ ይጠና ታዲያ፡፡
ለሀገር የጦርነትና የርስ በርስ
ፍጂት ስኬት ሲባል የሚመለከተው የዘረኛው መንግሥት አካላት ሁሉ በመቶ ሽዎች የሚገመት ልዩ ኃይልና ሚሊሻ፣ መከላከያና ደኅንነት፣
ፌዴራልና ክልላዊ ፖሊስ፣ ኮማንዶና ሪፓብሊካን ጋርድ … እያሰለጠኑ
ማሰማራት ዓይነተኛው ተግባራቸው ሆኗል፡፡ ይህ ወርቃማ የጦርነት ዕድል እያለ ማን ወደ ምርት ይግባ? ይህን ሁሉ የሰው ኃይል ለልማት
አሰልጥኖ ወደግብርናውና ወደሜካናይዝድ እርሻው፣ ወደ ፋብሪካውና ኢንዱስትሪው ማን ያስገባው? ተመልከትልኝ - የኦሮሞ ልዩ ኃይልና
ሚሊሻ፣ የአቢይና ሽመልስ ሸኔ፣ የኦነግ ልዩ ኃይል፣ የትግራይ ልዩ ኃይል፣ የትግራይ መከላከያ፣ የአማራ ፋኖ፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣
የአማራ ሚሊሻ፣ የሶማሊያ ልዩ ኃይል፣ የቤንሻንጉል ልዩ ኃይል፣ የአፋር ልዩ ኃይል፣ የጋምቤላ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ፣ የደቡብ ልዩ
ኃይል፣ የቅምብቢት ታጣቂ፣ የሆሮጉድሩ ሸማቂ…. ፐፐፐፐፐፐ…. እንዴት ዕድለኞች ነን ግን!! “ሁሉ አረሰ ማን ይሸምት” አትልልኝም?
ሀገር የታጣቂዎች መፈንጫ፣ የአምራቾች
ማፈሪያና መሳቀቂያ ሆነች፤ ስም የሌለው ድድብና፤ ድንበር ያጣ ድንቁርና፡፡ ታዲያ ማን አምርቶልን ነው ለመዋጋትስ የሚሆን እህል
ውኃ የምናገኘው? እያስለቀሰች የምታስቅ ሀገር፡፡ ሁሉም ለውጊያ ከተሰለፈ ማን ይረስ? ማን እህል ያምርት? ይህን አስከፊ ምስል
የሚለውጥ አንድ ኔልሰን ማንዴላ እንዴት ይጥፋ? ይህን የተንሸዋረረ የዘርና የቋንቋ ምድራዊና ኃላፊ ጠፊ ልዩነት የሚያረግብና ወደልማት
የሚመልሰን አንድ ማኅተመ ጋንዲ እንዴት እንጣ? ከ120 ሚሊዮን ሕዝብ መካከል እነዚህን ዕብዶች በተገኘው መንገድ ሁሉ ታግሎ የሚጥል
መጥፋቱ በርግጥም ሀገራችን የመረረና የከረረ ዕርግማን ውስጥ እንዳለች መረዳት አይከብድም፡፡ መጥኔ ለወጣቶች - እኛስ መጓዛችን
ነው፡፡ ለማንም አይመከርም እንጂ መሄድ ደስ ሲል!! “ተኖረና ተሞተ!” ይሉ ነበር አሉ ባላምባራስ እርገጤ የድሃ ሰው ቀብር ላይ
ሲገኙ፡፡
የአቢይ ቡድን ገና ለገና ለቅዠት
ሀገር ለኦሮምያ ግዛት የሠሩ መስሏቸው ኢትዮጵያን ብቻ ሣይሆን ምሥራቅ አፍሪካን ባጠቃላይ ማተረማመሳቸው ገሃድ እየወጣ ነው፡፡ መጨረሻው
ለሁሉም አያምርም፡፡ ውኃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነውና የዚህ ጅምራቸው መጨረሻ በኢትዮጵያ ብቻ አይቆምም፡፡
አቢይ በርካታ የሀገር አመራር ሪከርዶችን
እያስመዘገበ መሆኑ ይነገርለታል፡፡ ይህችን ደቡብ ሱዳን ራሱ ጎትጉቶና ጎትቶ እንዳመጣት መረዳት አይከብድም፤ ዝም ብላ መቼም ይህን
ያህል አትዳፈርም፡፡ ይሄው ጉደኛ ሰውዬ ወደ ሥልጣን በወጣ ሰሞን ሰሜን ሱዳን ሰፊ የአማራ ግዛት እንድትወርና እንድትይዝ በውጤቱም
አማራን እንድትወጥርለት በምሥጢር ተስማምቶ የኢትዮጵያን መሬት በገዛ ፈቃዱ አስያዘ፡፡ ይህ ደግሞ የአንድ ሀገር መሪ የሌላ ሀገር
መሪን ለምኖ “ በሞቴ ግዛቴን ውሰድልኝ” በሚል ያልተለመደ ተማፅኖ አዲስ ሪከርድ አስመዘገበ፡፡ ቀጠለና ራሷን የቻለችን የቀድሞ
የኢትዮጵያ ግዛት ኤርትራን ወደ ትግራይ ገብታ አዳዲስ መሬቶችን እንድትወርና እንድትይዝ ተስማማ፡፡ ይህም ሁለተኛው የ“እባካችሁ
አገሬን እየቆረሳችሁ ውሰዱልኝ” ዓይነት ተጨማሪ ሪከርድ ነው፡፡ ሦስት አላችሁልኝ? ኧረ ጉዱ ብዙ ነው!!
በሀገር ውስጥ ያየን እንደሆነ የአማራን
ነባር ግዛቶች ወልቃይትንና ራያን ለትግራይ ለመስጠት ቀን ከሌት እየለፋ ነው፡፡ ምን ዓይነት ቀትረ ቀላል ሰውዬ እንደሆነ ሳስብ
ግርም ይለኛል፡፡ በተለይ በአማራ መሰቃየትና መሞት፣ መሰደድና መፈናቀል፣ መቸገርና መንገላታት ፈጽሞውን የሚረካ አልሆነም፡፡ አማራ
ለዚህ ሰውዬ እርካታ ሲል ምን ይሁንለት? የሚደንቀው ሚስቱና ልጆቹ ጥሎባቸው አማራ ናቸው አሉ፡፡
እንግዲህ ይህንና የመሳሰለውን ክስተት
ስንታዘብ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት መንግሥት እንደሌላት ለመረዳት ማንንም መጠየቅ አይገባንም፡፡ አሁን ሕዝቡ እየኖረ ያለው በኪነ
ጥበቡ ነው፡፡ ፈጥሮ የማይረሳው ጌታ እየጠበቀን እንጂ እንደኦሮሙማው የአራት ኪሎ መንግሥት ተብዬ ዘረኛ ስብስብ ቢሆን ኖሮ አንድም
ቀን ማደራችን ራሱ እንደህልም በተቆጠረ ነበር፡፡ መንግሥት ሲያምረን ይቀራል፡፡ የለንም ወንድማለም፡፡
ነገረ ሥራችን ሁሉ ዕብድ እንደያዛት
ብርሌ ወይንም ብርጭቆ ነው፡፡ “የዕብድ ቀን አይመሽም” ስለሚባል እስካሁን ቆየን እንጂ ከሞትን ሰነበትን፡፡ በሌላ ሥነ ቃላዊ አገላለጽ
ደግሞ “የዕብድ ቅል ማንጠልጠያው ክር” ይባላልና ዛሬ ማታ ወይንም ነገ ጧት ምን እንደምንሆን አናውቅምና ያን ማሰቡ ራሱ ጭንቅላትን ያዞራል፡፡ ስለሆነም ተሰሚነት ያላችሁ ከሁሉም ጎሣና ነገድ የምትገኙ
ትልልቅ ሰዎች እንቅልፍ ባይዛችሁ ጥሩ ነው፡፡ ዳኛ በሌለበት፣ ፖሊስ በሌለበት፣ ህግም ህግ አስፈጻሚም በተጓደሉበት፣ እንደልቡነት
በሰፈነበት፣ ጉልበተኞች በገነኑበት፣ ዘረኝነት በተንሰራፋበት፣ የማይም አገዛዝና የውሸት ዲግሪ ከግርጌ እስከራስጌ በነገሠበት፣ በአእምሮ
ሳይሆን በሆድ ማሰብ በተስፋፋበት፣ በእግር ተሄዶ ሳይሆን በእጅ ስንዘራ ብቻ የትኛውም ዓይነት ጉዳይ በሚፈጸምበት በዚህ የብላ ተባላ
ዘመን በደቂቃዎች ውስጥ ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ይከብዳል፡፡ በመሆኑም እውነተኛ ምሁራንና ለሀገርና ለወገን ተቆርቋሪ የሆናችሁ
ጤናማ ዜጎች በኅቡዕም ቢሆን እየተገናኛችሁ በመነጋገር ይህ አሁንም ቢሆን እንዳለ የማይቆጠረው የወሮበሎች መንግሥት በቅርብ ፍርክስክሱ
በሚወጣበት ጊዜ የሽግግር መንግሥት ሊመሠረት የሚችልበትን ብልሃት ከወዲሁ ቀይሱ - ግን የምትተማመኑ እንጂ አስመሳዮችንና ለጥቅምና
ለዘር ሐረግ የተንበረከኩትን እንዳታስጠጉ ተጠንቀቁ፡፡
እንዲህ ካልተደረገ ሶማሊያና ሦርያን
የመሆን ዕድላችን እጅግ ሰፊ ነው፡፡ አሁንም ራሱ ወደዚያ ሁኔታ ውስጥ የገባን ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም የአቢይ ወለፈንዴው መንግሥት
እንኳንስ ከአዲስ አበባ ውጪ አዲስ አበባ ውስጥም ምንም እየሠራ አይደለም፡፡ ከአዲስ አበባ አሥር ኪሎ ሜትርም ሳትወጣ ለምሣሌ አማርኛ
መናገርና የኢትዮጵያን ባንዲራ መያዝ አይፈቀድልህም፡፡ እንዲያ ብታደርግ እሥር ቤት ይወረውሩሃል፡፡ አላምነኝ ካልክ የኢትዮጵያን
ባንዲራ ወይንም አፄ ምኒልክ የተሳሉበትን
ቲ-ሸርት ለብሰህ ለገጣፎ ሂድ፡፡ ምድረ ቄሮ ፖሊስ ተሸክፎ ሰደቃህን ያወጡልሃል፡፡ ለበላይ አመለክታለሁ ብትል ደግሞ ይስቁብሃል፤
ለምን ብትል ጃዝ የሚባሉት ከላይ መሆኑን ያውቃሉና፡፡ የክልሉን እንተወውና ፌዴራል ተብዬውም፣ የአዲስ አበባ መስተዳድርም ምን አለፋህ
ሁሉም የሥልጣንና የኃላፊነት ቦታ በኦነግ/ኦህዲድ በመያዙ የትም ልሂድና ላመልክት ብትል “ሰባራ ዶሮ ሳትቀድምህ ሂድና አመልክት!”
ትባላለህ - ሊያውም በኦሮምኛ፡፡ ገባህ? ስለዚህ ዋናው አትቀደም ነውና ጊዜ እስኪያልፍ ጠንቀቅ በል፡፡
“ጉድ ነሽ ያንኮበር ቅጠል፤ የተሠራሽው ቂጥ ለማቃጠል” ያለው ሰውዬ
ወዶ አልነበረም - የደረሰ ደርሶበት እንጂ፡፡ ይብላኝልሽ አሁን ፀጥ ብለሽ እንቅልፍሽን የምትለጥጭ የአዲስ አበባና የትላልቅ ከተሞች
ነዋሪ ሁላ!! እማይደርስ መስሎሻል፡፡ የ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ኦሮሙማ በጭካኔውና በዐረመኔነቱ ዕጥፍ ድርብ ተሻሽሎ የቀደሙ አባቶቹን
ስህተትም አርሞ በአዲ ጎራዴ መጥቶብሻል፡፡ ዛሬ ተራው የአማራ ይሁን እንጂ ነገ ደግሞ የቀሪዎቹ ቤርቤረሰቦችና ሂዝቦች መሆኑ በጣም
ግልጥ ነው፡፡ ከሌሎቹ መጀመር ልፋትና ድካምን ስለሚያበረታበት ነው አያ ኦሮሙማ አማራ ላይ የጀመረው፤ እሱን ከጨረሰ ግን “ዕዳው
ገብስ ነው” ብሎ ያምናል፡፡ እንደነሱ እምነት ሌሎቹን በቀላሉ ያንበረክኳቸዋል - በቆንጨራ ወይንም በሞጋሣ፡፡
ምኞት አይከለከልም፤ በዚህ መንገድ ግን የትም አይደረስም፡፡ እናም
ኦሮሙማዎችዬ ማሰብ ጀምሩ፡፡ ማሰብ ከጀመራችሁ አሁን የተነጠቃችሁትን ሰው የመሆን ዕድል የሚከለክላችሁ የለም፡፡ ሁሉም ልብ ይበል!
ሳይወድ በግዱ ከአማራ ወላጆች በመፈጠሩ ብቻ የሦስት ቀን ዕድሜ ሕጻን ልጅ አንገት ከነእናቱ በሠይፍ መቁረጥ እንኳንስ
ደራሳውንና ዳዋሮውን፣ እንኳንስ ደቡቡንና ሰሜኑን፣ እንኳንስ ትግሬውንና ከምባታውን፣ እንኳንስ ጉራጌውንና በርታ - ሙርሲውን፣ ወገናችን
ነው የምትሉትን ዜጋ ሳይቀር ስሜት ያጨፈግጋልና ከገባችሁበት የጨቀዬ የአስተሳሰብ ዐውድ በቶሎ ውጡ - ለናንተው ነው፡፡ ነግ በኔ
የሚባል ብሂል ስላለ በአንዲት አስጠሊታ ኦፕሬሽናችሁ 120 ሚሊዮኑን ሕዝብ ነው ቋቅ እንዲላችሁ ያደረጋችሁትና ወደፊትም በዚሁ ከቀጠላችሁ
የምታደርጉት፡፡ ከገዳይ ይልቅ ሟች ረጂም ዕድሜ እንዳለው የምነግራችሁ በማያወላውል እርግጠኝነት ነው፡፡ የምትገድሏቸው ሰዎች የእናንተን
መቀበርያ ዘላለማዊ ጉድጓድ እንደቆፈሩ ካልገባችሁ እውነትም ከሰውነት ተራ የወጣችሁ ሰው መሳይ ዐውሬ ናችሁ፡፡ አቢይና ሽመልስ የእናንተን
ዘላለማዊ ሞት አይሞቱላችሁም - የነሱንም በቻሉት፡፡ አቢይና ሽመልስ የአጋንንት ልዑካን ናቸው - ይህንንም እነሱና ላኪያቸው ያውቃሉ፡፡
እናንተ ግን በበሬ ወለደ ፕሮፓጋንዳ ተጠምቃችሁና በጥቅም ታውራችሁ፣ ባለመማር የማይምነት ጥቁር መጋረጃም ተሸብባችሁ የነሱ ባርያ ሆናችኋል፡፡ እናም ልብ
በይ - ምድረ ሸኔ ቁንዳላ ፀጉርሽን እየፈተልሽ ሕጻንና አሮጊት መግደልን እንደጀብድ ቆጥረሽ
አሁን ብትሞላፈጪ የነገው ቀን ለእያንዳንድሽ ከተራው የቀኑ ጨለማም የበረታ ድቅድቅ ጽልመት ነው፡፡ ለነገሩ እኔን ምን አገባኝ!!
Ethiopian Semay