The single father with his baby on his lop seen is the victim of all the pictures of the elite seen above OLF,TPLF, ONLF all these are bandists and anti Ethiopia mercenaries. They should have been locked in prison for all their crime, thanks to USA and Europeans, they are sheltering these national criminals and humanright abusers!!
Posted on www.ethiopiansemay.blogspot.com ከአህመድ ይማም በቃ! የሚለው መፍክር የሰዉን ቀልብ ስቧል ቢባል ትክክል ነው። በበኩሌ ከበቃ በኋላ የሚፈለገውንም ያቀፈ መፍክር ቢኖር በተሻለ ነበር ባይ ነኝ። ዋናው ጉዳይ ይህ ባለመሆኑ ወደ ተነሳሁብት ርዕስ ልመለስ። ለወያኔ መንጋ በቃ ማለት ተገቢ ነው። ጊዜም አልፏል እንዲያውም። በንታገሳቸው፣ በመላ ወይስ ዱላ፣ የዴሞክራሲ በሩ ከፈት ብሏል፣ እና በሌሎችም ትግልን አዘናጊ አባባሎች የተከፈለው ዋጋ፣ በሀገርና በህዝብ ላይ የደረሰው ጉዳት ቀላል አይደለምና። የትላንት ስህተታችንን መርምረን ለዛሬ እምንማር ከሆነ። የትግል መፈክር ጉዳይ ሁሉን ዜጋ ይመለከታል፤ የትግልንም አቅጣጫ ሊወስን ይችላልና በጥያቄ መግባቱ ተገቢ ነው። መፈክራችን ለምን ተተቸ የምባል አይመስለኝም። ለሀገር አንድነት፣ ለህዝብ መብትና ህጋዊ የሥልጣን ባለቤትነቱ መረጋገጥ የምናደርገውን ትግል እስከአገዘ ድረስ። በአጭሩ የአንድነት ሃይሎች ይህን ትችቴን በቀና እንደሚያነቡልኝ ተስፋ አደርጋለሁ። በተቃራኒው ደግሞ ለሀገር መበታተን የቆሙ ሃይሎች፣ ወያኔንም ጨምሮ በበጎ እንደማያዩት ከወዲሁ እገነዘባለሁ። በቃ ለወያኔ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም በተለይ በሕዝብ ጎራ ውስጥ አለን ለሚሉም መባል ያለበት ነው የሚል ዕምነት አለኝ ። የ 1997ኡን የሕዝብ ድል የተቀማነው በግድያ ብቻ ሳይሆን በመሪዎችም ስህተትና ክህደትም ጭምር ነው። የሙት ከተማን አድማ ያከሸፉት የድርጅቶች መሪዎች ነን የሚሉ ናቸው። ልደቱ ክህደቱንም ይጠቅሷል። ለወያኔ ማስፈራሪያና ተንኮል ሰለባ እየሆኑ ያሳፈሩንም ሁሉ ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው። በሻዕቢያ ተገርተው፣ ለኦነግ መጫወቻ የሆኑትና ፋይዳ ቢስ የሆነ ኤ ኤፍ ዲ የሚባል ነገር መስርተው የነበሩትም ለሎች ናቸው። የድርጅት መሪን ወይም የትላንት ጓደኛቸውን ለወያኔ ከሰው የሚያሳስሩ የድርጅት መሪዎችም መጠቀስ ይችላሉ። ከወንበደው ወያኔ ጋር የስነስርዓት ስምምነት ያደረጉ፤ መሪያችን ባትፈታም ምርጫ እንገባለን ያሉ። በቃ በቃችሁ መባል የነበረባችውና ያለባችው ብዙዎች ናቸው። ላፈሰሱት ደም፤ ለፈጸሙት ክህደት ሕዝብን ይቅርታ ሳይጠይቁ የትግል መሪ ነን ያሉትና ለነዚህም ድጋፍ የሰጡ በቃ! በቃ! ሊያድነቁራቸው በተገባ ነበር። ግና አልሆነም። ከቅርብ ጊዘ ወዲግ ደግሞ "በዛ አበዛሀው!” መባል ያለበት ድርጅት ግንቦት 7 ና በተለይም መሪው ዶክተር ብርሃኑ ናቸው። በተሳሳተው ገንጣይና ተገንጣይን ማቀፍ በሚለው አጓጉል ፖለቲካቸው የተነሳ። ይህ ሀገርንም ትግልንም የሚጎዳ፤ ለነሻዕቢያ የሚጠቅም አቅዋም መሆኑ የሚያክራክር አይደለም። ከዚህ በፊት በህብረት ተጀምሮ ያኔ ቅንጅት በነበሩት የተፈጸመው ኤ ኤፍ ዲ የተባለ ጉድ፣ የኦነግን አጀንዳ ከግብ ሊያደርስ ታቅዶ የነበር ለመሆኑ ሳይውል ሳያድር ተጋልጧል። በስሙ እንኳን ኢትዮጵያ የሚል እንዳይገባ ተደርጎ ነበር። ከዚያ እስከዚህ የተከፋፈለው ኦነግ ተገንጥዬ ነጻ ኦሮሚያን እመሰርታለሁ ከማለት አንድ ቀንም ተቆጥቦ ኣያውቅም። ዓላማው የሚሞኝ ካገኘ ወያኔ እሱን እንደጋለበው፣ ሌሎችን ኢትዮጵያዊ ድርጅቶችን መጠቀሚያ ለማድረግ ነው። በ 1983 ወያኔ ለስልጣን ሲበቃ እነ ሌንጮ ለታ ከወያኔና ሻዕቢያ ጋር በማበር የወያኔን አስገንጣይ ፖለቲካ ያጀቡና በተጨማሪም በሽግግሩ ጉባኤ እነ ኢዴሐቅ እንዳይሳተፉ ሲደረግ የፈነደቁ ናቸው። የአንድነት ሃይሎችን ከመድረኩ አግለው፣ ሀገር በታኝ የሆነውን የወያኔ ፖሊሲ በህዝብ ላይ ተባብረው የጫኑ ናቸው። የትላንቱ ዛሬ የለም ብለው ሊረቱን የሚፈልጉት ደግሞ በርግጥም በኦነግ አቅዋም ለውጥ መደረጉን ወይም መምጣቱን ሊያሳምኑን ይገባል። በተጨባጭና ሳይንሳዊ መረጃ። ይህ መረጃ ግን የለም። ኦነግ ከሀበሻ ቅኝ አገዛዝ ስርዓት ተላቆ ነጻ ኦሮሚያን መመስረት የሚለውን/መሰረታዊና የቆየ አቅዋሙን አልቀየረም። እነ አሶሳና በደኖን በንጹህ አማሮች ደም ያቀላው ውጉዝ አቅዋም ማለት ነው። ኦነግ ግንቦት 7 ና ሌሎችንም ሊጠቀምባቸው ፈልጎ ኢትዮጵያዊ ቃና ያለው የሚመስል/ንግግርን ሊጀምር ቢችልም መሰረታዊ “ኦሮሞዎች ኢትዮጵያዊ አይደለንም” አቅዋሙን ለቅንጣትም አልቀየረም። በማስረጃነትም ድረገጹን ማየት ይበቃል። በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ዋና መስሪያ ቤቱ አስመራ የሆነው ቡድን ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያዊ ህብረት አካል ይሆን ዘንድ ተሞክሮ ከልቡ ፈቃደኛ ሆኖ አልተገኘም። ሞኝ ይመስል ነጋ ጠባ እንሞክረው እንለምነው ማለት ደግሞ ያስገምታል። ክብራችንን እንደ ኢትዮጵያዊ መጠበቅ ያስፈልጋል። ሻዕቢያ በበኩሉ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች በራሳችው አብረው እንዳይጠናከሩ የአቅሙን ሁሉ ሲስራ የቆይና አሁንም እየሰራ ያለ ነው። የአርበኞችን ግንባር ሲያዳክምና ሲያደናቅፍ መቆየቱን--በኣፈናና ግድያም-- በበቂ የተጋለጠ ነው። ኦነግንም ኦብነግንም የሚረዳና የሚያስታጥቅ ሻዕቢያ ነው። በዚያው ደረጃ ግን አማራ ተብሎ ታፔላ የተለጠፈብት አርበኞች ግንባርን ሲረዳ አልታየም -- ይባስ ብሎ መሪዎቹን ያስራል ይገድላል እንጂ! የኦነግ አቅዋም አለመቀየር ሀቅ ሲሆን/ የኦጋደኑ ግንባር ደግሞ ኢትዮጵያዊ ነህ መባልን ክትምክህትና ስድብ የሚቆጥር ነው። የነዚህ ድርጅቶች መሪዎች አመቺ ሁነታ ሲምጣ ራሳቸውን ለሹመት እያመቻቹ ዓላማ ያሉትን ዘንጋ ቢያደርጉም፣ ግባቸው በኢትዮጵያዊነት ደሞክራሲያዊ ህገር መመስረት አለመሆኑ ዓይኔን ገልጬ ልሞኝ ላላለ ሁሉ የሚታይ ነው። ከሻዕቢያ በተጨማሪ በተለይ አሜሪካና እንግሊዝ (እንዲሁም ተገንጣዮቹን ሁሉ ስትረዳ የቆየችው ኖርዌይ) የነገይቷን ኢትዮጵያን በተመለክተ የራሳቸው ዕቅድ ያላቸው ሲሆን ይህንንም ከግብ ለማድረስ ራሳቸውን ተቃዋሚ በሚሉትም እንደሚጠቀሙ የታወቀ ነው። በቅርቡ በወጣ ዊኪሊክስ የምስጢር የአሜሪካ መልዕክት ለምሳሌ የሶርያን ተቃዋሚ ድርጅቶች የሳተላይት ቴሌቭዥን (ከሎንዶን) ከ 5 ሚሊዮን ዶላር በላይ አውጥቶ ያቋቋመው ወይም የረዳው የአሜሪካ መንግስት መሆኑ ተጋልጧል። (ታዲያ ኤሳት የተባለው የቴሌቭዥ ጣቢያ በእኔና አንቺ መቶ ዶላር መዋጮ እየተካሄደ ነው? ቅቅቅቅ!) ለምን ብለው ነው ሀያላኖቹ የሚረዱ? ለሕዝብ አዝነው እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ነው። ከዚህም አንጻር አሜሪካ፤ እንግሊዝና ሌሎቹም ቢሆኑ በየታሪካችን ወሳኝ ወቅት ኢትዮጵያን ለማንበርከክ በሀገር በቀል ከሀዲዎች ሲጠቀሙ ቆይተዋል። ከጣሊያን ወረራ እንኳን ብንጀምር ምሳሌው ብዙ ነው። ወያኔና ሌሎች ተገንጣዮች ደግሞ በምዕራባውያን እየተረዱ ሀገራችንን መጉዳታቸውን ያየነው ነው። አሰብ ለኢትዮጵያ አትገባም የሚል የለየለት ከህዲን ቤተመንግስት የከተቱት እነ አሜሪካ እንግሊዝ ናቸው። በ 1997 መለስ ዜናዊን ከውድቀት ያዳኑት አሜሪካና እንግሊዝ ናቸው። ኦነግን እየረዱ ያቆዩት እነ እንግሊዝ፤ ጀርመን፤ ኖርዌይ ናቸው። የአረብ ሀገሮች ሚና ደግሞ ራሱን የቻለ ሰፊ ጉድ ነው። ወያኔ በሱዳን፤ ሶማሊያ፤ ሊቢያና ሳውዲ አረብያ ዕርዳታ መጠናከሩ ምስጢር አይደለም። ኢፒዲኤ ይባል ከነበረው የአሜሪካ ኮንትራ መሰል ስብስብ ውጪ ለማንኛውም ነጻ የኢትዮጵያ ድርጅቶች ግን አረቦቹም ሆኑ ሌሎቹም ሲረዱ አልታዩም። ይህን ዘፋኙ ስለሺ እንደሚለው ድንቆል ያደረግኩት የሩቅም የቅርብም ጠላቶቻችን ምን እንዳሴሩብን ማውቅ አስፈላጊ መሆኑን ለመጠቆም ነው። ምንም እንኳን አሜሪካ መለስ ዜናዊን ብትረዳም ነገ ሁኔታው ጠጥሮ ውድቀት ከመጣበት ከዛረው ተኪ ለማዘጋጀት መሯሯጧ የሚጠበቅ ነው። መንግስቱ ሀይለማርያም ሊወድቅ ሲል በተዘጋጀው የሎንዶን ጉባኤ አሜሪካም ብትሆን ኢደሀቅ በመታገዱ ተስማምታ ግን ኦነግን ጠርታለች። ለምን? ታሪክን መርሳት አይጠቅምም። ለኢትዮጵያ ያልቆሙትን ለሀገራችን የሚሟገቱ አስመስሎ መውሰድም በጣም ከባድና ጎጂ ስህተት ነው። አንዳንድ ዜጎች ስለ ባዕዳኑም ሆነ ስለ ኦነግ ተመሳሳይ ስህተትን እየፈጸሙ ነው። ኦነግ አለ፤ የሚጠፋ አይደለም ብ/ለው የሚናገሩም አሉ። ይሁን። ያለን ነገር ሁሉ ማቀፍ ግን ትክክል ነው ያለ ማነው? እነ ኦነግን ቀርቦ ማነጋግር ያስፈልጋል፤ የሚሉም አሉ – ደግ ነው እንበል። ንግግሩ ግን ኦነግን በያዘው የመገንጠል አባዜ ለማጅብ ሳይሆን አቅዋሙን ለማስቀየር መሆን አለበት። አቅዋሙን ካልቀየረ – የአቶ ዳውድ ኢብሳ ቡድን በነጻ ኦርሚያ ምስረታ ኣቅዋሙ እንደጸና ነው-- ኦነግን እሹሩሩው ብዙ ጥቅም የለውም። ከዚህ አንፃር በተለይ ዶክተር ብርሃኑ ላይ የሚሰነዘረው አግባብ ያለው ሂስ ከሌሎች ህልውናና ሚዛን--ክብደት ካላቸው ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ጋር በቅድሚያ ማበር ሲገባ ኦነግ ኦነግ ብለው መፈጠማችው ነው። በኣትላንታ በተጠራው ስብስባ የኦነግም ሆን የኦብነግ አንድም የአመራር ኣባል አለመገኝቱ በእኔ በኩል በንቀት የሚተረጎም ነው። ከሁሉም በላይ የሚገርምው ሌላ ጉዳይ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ከሚለው ከኦነግ ጋር ካልተባበርን የሚሉት ክፍሎች ለሌሎች ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ያላቸው አሉታዊ አመለካከት የከረረ መሆን ነው። ከዚህም የተነሳ ራሱ "በቃ!” መፈክር በግድ የሁሉም ካልሆነ በሚልም እየተደረገ ያለው ሁሉ በቃ ሊባለው ይገባል ። አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት ቅዱስ መጽሐፍ አጠበች እንደተባለው ሁሉ፣ የሌሎችን ትግል ፎቶ ኮፒ አድርገው በመራወጥ በትግሉ መድረክ ላይ ጮቤ ሊረግጡ የተነሱትን ደግም በኣስቸኳይ በቃ ማለቱ አስፈላጊ ነው። ትግል በአዳዲስና ትኩስ ሀይልና በሕዝብ ተሳትፎ መታደሱና መጠናከሩ የሚገባ ሲሆን በዚሁ ሽፋን ደግሞ በሬን፣ ወንድ ላም የሚሉ ኣላዋቂዎች በመድረኩ የበላይነትን ይዘው ነገር ዓለሙን ድብልቅልቅ አድርገው ለወያኔ ምቹ ሰልባ ሊያደርጉን መፍቀድ አይገባንም። በመድረክ ሆነው በያዙን ልቀቁን ስሜት ብልሽትሽትን እያምጡ ያሉት ክፍሎች፡ • የሀገራችውን የትግል ታሪክ ጠንቅቀው አያውቁም፤ • የሀገራችውን የፖለቲካ ሀይሎች/ይዘት በሚገባ አላጠኑም፤ • ከለልተኛ ናቸው-- የተወሰኑ ድርጅቶችን በጭፍኑ ይጠላሉ፤ • ወያኔን አያውቁትም፤ • አሜሪካ ሲታደጋቸው ይታያቸዋል፤ • ሀገር ወዳድ ሀይሎች እንዲያብሩ መገፋፋት ሳይሆን ክፍፍልን ማራገብ ይመርጣሉ፤ • እንዳመጣላቸው በስልክ፤ በኢሜይል፣ በእጅ ቴሌፎን መልዕክት እያስተላለፉ ሰዎችን ለአደጋ ያጋልጣሉ፤ • በህብረ ብሐር ድርጅቶች ላይ እየዘመቱ ከነ ኦነግ ጋር ትሥርን ይሰብካሉ፤ • እየታገሉ ያሉ ድርጅቶችንና ስብስቦችንም የእኛ አይደሉም በሚል ከሕዝብ ሊነጥሉ ይጥራሉ፣ • በውሽታቸውና በፖለቲካው መስክም መደዴ በመሆናቸው ተቃዋሚ ሀይሎችን ለወያኔ መሳለቂያ ያደርጋሉ፣ • ትግል ድርጅት አልባ ካልሆነ ብለው በመስብክ ትግልን አቅምና አቅጣጫም ሊያሳጡ ይጥራሉ። ውጤቱ? ኢምንት ናዳ። ባዶ። ቀፎ። ዜሮ። የጨረባ ተዝካር! ታዲያ በቃ ማለቱ ይነሰን? ሀገራችን ኢትዮጵያ ናት የሚሉ ሀይሎች ገና ሳይተባበሩና ሕዝብ ለትግል ተባብሮ ሳይነሳ ሀገራችን ኢትዮጵያ አይደለችም የሚሉትን በቅድሚያ እንቀፍ ብሎ መነሳት ኢትዮጵያን መጥቀም ነው ሻዕቢያን? ይህ አሳሳች መፈክር በቃ! ይብቃ! ትላንት በተለያዩ ምክንያቶች ኢትዮጵያዊው የአንድነት ወገን የሀገር አድን እና የዴሞክራሲ ትግሉን ባለማጠናከሩ ወያኔ ድሉን ቀምቶ እዚህ ደርሰናል። ዛሬ ደግሞ በ"ወያኔ ይውደቅ ብቻ" መፈክር እየተጃጃልን ሀገራችንና ህዝባችንን ለሌላ ዘረኛ ቡድን አሳልፈን መስጠት የለብንም። እባብ ሞኝን ሁለት ጊዜ ይነክሰዋል አሉ። መጀመሪያ ሳያየው፣ ሁለተኛ ደግሞ የነከሰውን እባብ ለማሳየት እጁን ሲዘረጋ። የነዶክተር ብርሃኑም ኦነግ ኦነግዬ ቅኝትም እንደዚያው ነው። የኢትዮጵያ አንድነት ደጋፊው ወገንን ትብብርና እንቅስቃሴ ለማጠናከር በመጣር ፈንታ፣ ሀገሪቱን ቅርጫ ለመጣል የሚጥሩትን ሃይሎች በጫንቃው ላይ በመጫን መናጆ ለማድረግ። ትላንት በደርግ ጊዜ እንደሆነው ዛሬም "ወያኔ ይውደቅ" በሚል ብቸኛ አደናባሪ መፈክር ግራ በማጋባት የሀገሩን ህልውና ዕጣ ፈንታ ለነ እንገንጠል ባዮቹ ቡድኖች አሳልፎ መስጠት። ይህንን በዝምታ ልናልፈው አይገባም። የሚሰሙ ከሆነ በቃችሁ ልንላቸው ይገባል። ብዙሃኑ የአንድነት ደጋፊ ወገኖች በየአካባቢያችን ተጠራርተን ህብረታችንን በማጠናከር እንቅስቃሴያችንን ማጎልበት፣ የትግላችንን ዋና ዓላማም የኢትዮጵያን አንድነትና የሕዝቧን የሥልጣን ባለቤትነት በማረጋገጡ ላይ ማድረግ አለብን። በተባበረ የሕዝብ አመጽ፣ አንድነቷ ተጠበቆ፣ የሕዝቧ ሰብዓዊ መብቶች የሚረጋገጡበት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማምጣት እንችል ዘንድ። በዚህ ተቃራኒ ሀገርን ለማፈራረስ ሌት ከቀን ለሚሰሩ ወያኔ፣ ኦነግ፣ ኦብነግም ሆነ ሌሎች ዘረኛ ቡድኖች መናጆ በመሆን፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የዕኩይ ተንኮላቸው አራማጆች እንዳንሆን ከትላንት መማር አለብን። ሰለኢትዮጵያ ቀና የሚያስብ ሁሉ ቸር ይግጠመው።